🙏ኦርቶዶክሳዊ ዝማሬ🙏


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Esoterics


ገና እንዘምራለን እንደ መላእክቱ
ብርሃንን ለብሰን ገና እንዘምራለን
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርሰቲያን አሰተምሮ ና ሰርአት የጠበቁ
✥👉መንፈሳዊ ትምህርቶች
✥👉መንፈሳዊ መዝሙሮች
✥👉መንፈሳዊ ንግሰ እናሳዉቃለን
✥👉መንፈሳዊ ምክር ነክ ፁሁፍ
✥👉መንፈሳዊ ታሪኮች
ለማስታወቂያ ሥራ👉 @mane_tekel21

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Esoterics
Statistics
Posts filter


🎙✞✝️ነይ ነይ እምዬ ማርያም✝️✞

ነይ ነይ እምዬ ማርያም
ነይ ነይ እምዬ ማርያም ነይ ነይ ቤዛዊት ዓለም

የአማኑኤል እናት የመድሃኒያለም
እኔ አንቺን አምኘ ምን ሆኘ /2/
አንቺን ያመነ መላው ዳነ /2/
እኔ አንቺን አምኜ ስሄድ
ምን ሊያደርግልኝ ዘመድ
እኔ አንቺን አምኘ ስጓዝ
ምን ሊያደርግልኝ ጉዝጓዝ
ስሟ ስንቅ ነው የእመቤቴ ስሟ ስንቅ ነው የእመቤቴ
አንድ እፍኝ ሽምብራ አልያዝኩም ከቤቴ
አንድ ጥርኝ ውሃ አልያዝኩም ከቤቴ
እመቤቴ ማርያም እመቤቴ ሆይ
አንቺን ያመነ ሰው ይኮነናል ወይ
ነይ ነይ እምዬ ማርያም


እረ እሰይ አማኑኤል
አማኑኤል አማኑኤል
እረ እሰይ እመቤቴ
እመቤቴ እመቤቴ
እሰይ ስለቴ ሰመረ እሰይ ስለቴ ሰመረ
ለኪዳነ ምሕረት ነግሬያት ነበረ
ወይን አበቀለ ደጅሽ
ኪዳነምሕረት ላሉሽ
ማር ይዘንባል ማር
ከእመቤቴ በር
ማር ይዘንባል ፈሰስ
ከእናቴ መቅደስ
ማር ይዘንባል ከእጅ
ከአዛኝቷ ደጅ
ማር ይዘንባል ጸዓዳ
ከአማላጄ ጓዳ
እኔስ ማርያምን እወዳታለሁ
እኔስ እናቴን እወዳታለሁ
እመቤቴ እላታለሁ
ያንድዬ እናት
አዛኝቴ
መጠጊያዬ
መመኪያዬ
አማላጄ
ያምላክ እናት
አስታዋሼ
የምወድሽ


🎙ዘማሪ ዲ/ን ሳምሶን ነጋሽ

#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ

@Orthodox_mezmur13
@Orthodox_mezmur13
         👆 ይ🀄️ላ🀄️ሉን   👆

🗓መዝሙር መጋበዝ ይቻላል👇 

መዝሙር ለመላክ👉@Zmarebcha


🗓ነገ ማለትም  ሚያዚያ ፳፩ ✝️እመቤታችን✝️ቅድስት✝️ድንግል✝️ማርያም ናት🌹


እንኳን አደረሳችሁ‼️

#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ

@Orthodox_mezmur13
@Orthodox_mezmur13
         👆 ይ🀄️ላ🀄️ሉን   👆

React ማድረግ እዳትረሱ ተወዳጆች👇


🎙✞ይህን ላደረገ✞
ይህን ላደረገ ሃሌሉያ በሉ 
እግዚአብሔር ታማኝ ነው ሁልጊዜ በቃሉ 
ሙሽራው ሙሽሪት እንኳን ደስ አላችሁ 
የያዕቆብ አምላክ ሞገስ ኾነላችሁ
 
ስንቱን ተራራ አልፈነዋል
በሰገነት ላይ አቁሞናል
እስቲ እንዘምር በደስታ
ሁሌ ታማኝ ነው የኛ ጌታ 
ከእኛ የሆነ ምንም የለም
ተመስገን ጌታ ለዘላለም 
ስራህ አበራ በምስጋና
በሙሽሮች ላይ እንደገና 
የማይሆን መስሎ የታየን
በእግዚአብሔር ኾኖ ስላየን 
እንደ አሳፍ ልጆች ተሰልፈን
ስሙን በቅኔ ለማመስገን 
የተባረከ በመዳፉ
ቅኔን ያፈሳል ሁሌ በአፉ 
ከመላእክት ጋር አንድ ኾነናል የእግዚአብሔር ሥራ መስጦናል 

ጋኑ ቢጎድል የወይን ጠጁ
ያስባል ጌታ ለወዳጁ 
መናኛው ይውጣ ከቤታችን
አዲስ እንጠጣ እርሱን ይዘን 
አቤንኤዘር ነው መዝሙራችን
እየረዳን ነው አምላካችን 
ፊታችን በራ በደስታ
ውበት ኾኖናል የእኛ ጌታ
ጋኑ ቢጎድል የወይን ጠጁ
ያስባል ጌታ ለወዳጁ 
መናኛው ይውጣ ከቤታችን
አዲስ እንጠጣ ጌታን ይዘን 
አቤንኤዘር ነው መዝሙራችን
እየረዳን ነው አምላካችን 
ፊታችን በራ በደስታ
ውበት ኾኖናል የእኛ ጌታ

🎙ሙሐዘ ስብሀት ዳግማዊ ደርቤ

#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ

@Orthodox_mezmur13
@Orthodox_mezmur13
         👆 ይ🀄️ላ🀄️ሉን   👆

🗓መዝሙር መጋበዝ ይቻላል👇 

መዝሙር ለመላክ👉@Zmarebcha


🎙✞ሙሽራዬ አበባዬ✞

ሙሽራዬ አበባዬ (2)
አበባ ነው አበባ የኛ ሙሽራ
አበባ የኛ ሙሽራ
አበባ ናት አበባ የኛ ሙሽራ
አበባ የኛ ሙሽራ

ከከመቼውም ይልቅ የኛ ሙሽራ አበባ የኛ ሙሽራ
አምረው አጊጠዋል     »   »   »
በነጩ ልብሳቸው      »   »   »
ፀአዳ መስለዋል       »   »  

Âť
ገብቷል ከቤታቸው     »   »   »
ከጣሪያቸው ስር         »   »   »
ደስታን ተጎናፅፈው      »   »   »
ታጥረዋል በፍቅር       »   »  

Âť
በድንግል ቃል ኪዳን    »   »   »
ሰምሯል እቅዳችኹ      »   »   »
የኛማ ሙሽሮች           »   »   »
እንኳን ደስ አላችኹ      »   »   »

ምስጢሩ እሱ ነው     »   »   »
እንዲህ ያማሩበት      »   »   »
በጾም በጸሎት ነው    »   »   »
ቀድመው በአብነት    »   »  

Âť
 
በእልልታ ታጅበው     »   »   »
በፍቅር ያዜማሉ        »   »   »
አምላክን በሀሴት      »   »   »
ያመሰግናሉ               »  
   

🎙ዘማሪ ዲ/ን ሳምሶን ነጋሽ

#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ

@Orthodox_mezmur13
@Orthodox_mezmur13
         👆 ይ🀄️ላ🀄️ሉን   👆

🗓መዝሙር መጋበዝ ይቻላል👇 

መዝሙር ለመላክ👉@Zmarebcha




Video is unavailable for watching
Show in Telegram
✝️ማርያም ✝️ማርያም ብዬ ስምሽን ልጥራው አይደክመኝም እኔ ብደጋግመው!!!

✝️ቤዛዊት አለም ድንግል ✝️ማርያም ደጓ አናቴ✝️


🎙✞ተነሳልን✞
     ተነሳልን/2/ ህዝቦች ደስ ይበለን
     ኃያል አምላክ ኃያል ጌታ ሞትን ረታልን
     ተነሳልን እልል እልል እንበል
ተነሳልን ወገናኙ ዘምሩ ተነሳልን ሞትን ለሻረልን
ተነሳልን በመስቀል ተሰቅሎ ተነሳልን ህይወቱን ለሰጠን
ተነሳልን ሰዎች ዝም አንበል ተነሳልን እናመሰግን በእውነት
ተነሳልን ከኃጢያት ላዳነን ተነሳልን ወረት ለሌለበት

    
ተነሳልን ጴጥሮስ ገሠገሠ ተነሳልን ከመቃብር ስፍራ
ተነሳልን ጌታ ግን ተነስቷ ተነሳልን የለም በዚያ ቦታ
ተነሳልን ሰዎች ደስ ይበለን ተነሳልን ሞትን ለረታልን
ተነሳልን በመስቀል ላይ ሆና ተነሳልን ከእስራት ለፈታን


ተነሳልን ሲያወሩ ስላንተ ተነሳልን እነቀልዮጳ
ተነሳልን ስለፍቅራቸውም ተነሳልን መሀላቸው ገባህ
ተነሳልን ማዕዱንም ባርከህ ተነሳልን ተገለፅክላቸው
ተነሳልን ሞትን የሚረታ ተነሳልን እንዳንተ ያለ ማነው
ህይወትን የሚሠጥ ተነሳልን እንዳንተ ያለ ማነው
ተአምርን የሚያደርግ
ተነሳልን እንዳንተ ያለ ማነውከሞት የሚያወጣን ተነሳልን እንዳንተ ያለ ማነው
🎙ሙሐዘ ስብሀት ዳግማዊ ደርቤ

@Orthodox_mezmur13
@Orthodox_mezmur13
         👆 ይ🀄️ላ🀄️ሉን   👆

🗓መዝሙር መጋበዝ ይቻላል 

መዝሙር ለመላክ👉@Zmarebcha


🎙✞ቃና ዘገሊላ✞
ቃና ዘገሊላ ቃና ዘገሊላ በዚያ በሠርግ ቤት
ተገኝተሻል ድንግል ከልጅሽ ጋራ
ተገኝተሃል ጌታ ከአናትህ ጋራ

አድምተኞች ሞልተው የተጋበዙት
ሲበሉ ሲጠጡ ወይኑ አልቆበት
ድንግል እናታችን ቤዛዊተ ዓለም
አንቺ ደረሽለት ሆንሽው አማላጅ
አንተ እያለህስ ማፈር የለባቸው
ሁሉ ይቻልሃል ወይኑን ሙላላችው
ማድጋው ባዶ ነው ብለሽ የተናገርሽ
ጌታን ያሳሰብሽው አመቤታችን ነሽ

የጌታ አምላከነት የተገለፀበት
ምንኛ ታደለ የእነ ዶኪማስ ቤት
ዛሬም ይኸው በዚህ በሠርገኞቹ ቤት
በረከት ፈሰሰ በአምላከ ቸርነት
ውኃው ተለውጦ የወይን ጠጅ ሲሆን
በቃና ገሊላ ሁላችን አየን
እግዚአብሔር ከኖረ በመካከላችን ሁሌ ይሰጠናል ይህን መሰል ወይን

ውኃው ተለውጦ የወይን ጠጅ ሲሆን
በቃና ገሊላ ሁላችን አየን
እግዚአብሔር ከኖረ በመካከላችን ሁሌ ይሰጠናል ይህን መሰል ወይን
🎙ቀሲስ ምንዳዬ ብራኑ

#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ

@Orthodox_mezmur13
@Orthodox_mezmur13
         👆 ይ🀄️ላ🀄️ሉን   👆

🗓መዝሙር መጋበዝ ይቻላል 

መዝሙር ለመላክ👉@Zmarebcha

New Ethiopian Orthodox Mezmur 2025


🎙✞ለክብርሽ✞

🎙ዘማሪ ዕዝራ ኃ/ሚካኤል

#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ

@Orthodox_mezmur13
@Orthodox_mezmur13
         👆 ይ🀄️ላ🀄️ሉን   👆

🗓መዝሙር መጋበዝ ይቻላል 

መዝሙር ለመላክ👉@Zmarebcha

New Ethiopian Orthodox Mezmur 2025


Forward from: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
ሰበር ዜና
ለፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ተሰጥቶ የነበረው
የዘገባ ፍቃድ ለጊዜው ታግዷል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥር የሚሰሩ ኦርቶዶክሳውያን የሚዲያ ተቋማት በአንድ ማዕከል  እንዲያገለግሉ፣ የመረጃ ፍሰቱ ወጥነት ያለውና ተቋማዊ መሆን ይችል ዘንድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የሁለት ቀናት ሥልጠና ተሰጥቶ የቤተ ክርስቲያን መሠረት እምነት፣ ሥርዓተ አምልኮና ትውፊት አክብረው በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ዘገባ ማከናወን የሚችሉበት ፈቃድ ከመምሪያው መሰጠቱ ይታወሳል።

ከእነዚህ የሚዲያ ተቋማት መካከልም የፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን አንዱ ሆኖ ዘገባዎችን ሲያሰራጭ ቆይቷል።

ሆኖም ግን በፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን በዕለተ ስቅለት "ቅድስት ድንግል ማርያም ቤዛዊተ ዓለም አትባልም።" በሚል ርእስ  የተላለፈው ትምህርትን ውዝግብ በማሰነሳቱና ቋሚ ሲኖዶስ በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ ለመስጠት ለረቡዕ ሚያዚያ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ የያዘ በመሆኑና ጉዳዩ በሚገባ ተጣርቶ ውሳኔ እስከሚሰጠው ድረስ ከመምሪያችን ለፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን የተሰጠው የዘገባ ፍቃድ ለጊዜው የታገደ መሆኑን እንገልጻለን።

                ሚያዚያ ፲፭ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም
                     አዲስ አበባ -ኢትዮጵያ

          የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
                      ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

#ድምፀ_ተዋህዶ
#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ


Forward from: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
በከመ ተብህለ" ሰናይ አርዝ ይፈሪ ሰናየ ፍሬ" ናሁሰ ፈረየት ጉባኤነ ሰናየ ፍሬ!
"መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራል" እንደተባለው  መልካሟ ግቢ ጉባኤያችንም መልካምን ፍሬ ማፍራቷን ቀጥላለች!
ጥዑም ዜማ: መዝገበ ርህራሄ
በዘማሪት ነፃነት ሲሳይ ፡የአንጋፋው ሀዋሳ ዩንቨርስቲ ግብርና ግቢ ጉባኤ አገልጋይ                                                                                                                                          
እሁድ ሚያዚያ 19 በ"ጊዜ" ሚዲያ ይለቀቃል።
ሁላችንም እናበረታታት🙏


Forward from: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
ቋሚ ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ቅድስት ድንግል ማርያምን በማስመልከት ባስተላለፉት ትምህርት ዙሪያ ተወያየ !

ቋሚ ሲኖዶስ ዛሬ ማለዳ ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ባሳለፍነው አርብ በስቅለት ዕለት በፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን በቅድስት ድንግል ማርያም ዙሪያ ያስተላለፉትን ትምህርት በተመለከተ ውይይት አድርጓል።

በብፁዕነታቸው  የተላለፈውን ትምህርት ዝርዝር ሁኔታን በመመርመርም ውሳኔ ለማስተላለፍ  ይቻል ዘንድ ሁሉም የቋሚ ሲኖዶስ አባላት በምልዓት በተገኙበት  ለአርብ ሚያዚያ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ ተይዞል።

በተያያዘ ዜና የሮም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ በሆኑት በፖፕ ፍራንሲስ ሥርዓተ ቀብር ላይ ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ ፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ቤተ ክርስቲያናችንን በመወከል እንዲገኙ ተወስኗል።

©የኢ/ኦ/ተ/ቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ
#ድምፀ_ተዋህዶ


ብፁዕ ኾይ፦
እመቤታችን 'እንደ ቃልህ ይሁንልኝ' ያለችው ቃሏ የእርስዎም ቤዛ ነው።

"ከእናንተ መኖር ይልቅ የክርስቶስ ትንሣኤ ብዙ ማስረጃ አለው"
ክርስቶስ አልተነሣም ላሉ ሰዎች አንድ ሊቅ የተናገረው ቃል ነው።
የእመቤታችን ቤዛነትም እንዲሁ ነው። ከአቡኑ ማብራሪያና ዕውቀት ይልቅ  ብዙ ማስረጃ አለው።ሌላውን ብዙ ጥቅስ ትተን
"ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ፤
እንደቃልህ ይሁንልኝ" ያለችው ቃል ብቻ በቂያችን ነው። የመጣው ለዐለም ኹሉ ቢኾንም የተወለደው ከእርሷ ነውና። 'ይሁንልኝ' ያለችው መልሷ የእርስዎም የእኛም ቤዛ ነው። ህየንተ (ምትክ) ማለት ነው።
ደግሞስ የድንግል ማርያም ቤዛነት ምኑ ይገርማል?
"ይኽ መስቀል ቤዛችን ነው" እያለ ቅዱስ ያሬድ ለመስቀሉ ዘምሮ የለምን?
"መስቀልከ ዕፀ ተነብዮ መስቀልከ ለሰይጣን ሞዖ ዝንቱ መስቀል ቤዛነ።"
አኹን ቅዱስ ያሬድ ዕንጨቱን ቤዛ በማለት አምላክ አደረገ ብለን እናርመው?በፍጹም!
እንኳን እሱ፥ እኛ ስለ እመቤታችንም ኾነ ስለመስቀሉ ይኽን ስንል የፈጣሪን ቤዛነት ከፍጡራን ለይተን ዐውዱን ጠብቀን ነው።

ተሳስቻለሁ ይቅርታ ማለት ጴጥሮሳዊነት ነውና ቃልዎን እንደሚያርሙ ተስፋ አደርጋለኹ።

ሊቀ ሊቃውንት ስሙር አላምረው

#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ


Forward from: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
ብፁዕ አባታችን። ድንግል ማርያም ቤዛዊት አትባልም ብለው ድምዳሜ ሰጥተው ሲያስተምሩ ሰማሁ። ነገር ግን ሙሉ በሙሉ አይባልም ብለን ከምንደመድም እንዲህ ብንል አይሻልምን?

🥀እናታችን ድንግል ማርያምን ቤዛዊተ ኩሉ ዓለም እንላታለን። ክርስቶስን ቤዛችን ስንለው በመስቀል ተሰቅሎ እኛን ስላዳነን ነው። ድንግል ማርያምን ቤዛዊት ስንላት ግን ቤዛኩሉ ክርስቶስን ስለወለደችልን ነው። ከእርሷ ተወልዶ ዓለምን አድኗልና ነው። ምክንያተ ድኂን ስለሆነች ነው። ልጇ የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ ብሎ እንዳስተማረን እሱን ብርሃን እርሷን ደግሞ የብርሃን እናት እንላታለን። ልጇ አምላክ ስለሆነ እርሷ እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ ትባላለች። አምላክን የወለደች የአምላክ እናት ማለት ነው። ቤዛዊት ናት ስንል በጸጋ እንደሆነ ልብ እናድርግ። ምናልባት በባሕርይው ቤዛ ሆኖ ያዳነን ክርስቶስ ብቻ ነው ለማለት ፈልገው ከሆነ መልካም ነው።

🥀ንስጥሮስን ክርስቶስ ላይ ያለው የምንታዌ (Dualism) እይታ ድንግል ማርያምን ወላዲተ ሰብእ ከማለት አደረሰው። ድንግል ማርያም የወለደችው ሰው የሆነ አምላክን አምላክ የሆነ ሰውን ነው እንጂ ዕሩቅ ብእሲ (ሰው ብቻን) አልወለደችም። ነገረ ክርስቶስን ከድንግል ማርያም በበለጠ የሚያውቀው ፍጡር የለም ። እርሷ ልጇን ይዛ ከሀገር ሀገር ተንከራታለች። በመስቀልም ጊዜ ከጽንዐ ፍቅሯ የተነሳ ከመስቀሉ ሥር አልቅሳለች። ድንግል ማርያምን እናከብራታለን፣ እናመሰግናታለን፣ እንሰግድላታለን። ነገር ግን ለእርሷ የምናቀርበው ስግደት እና ምስጋና የአክብሮት ስግደትና ምስጋና ነው እንጂ እንደ አምላክ የአምልኮ ስግደት አይደለም።  

🥀ድንግል ማርያም ዓለም ጣዖትን በማምለክ ጨለማ ውስጥ ሳለ ብርሃንን የወለደችልን እናታችን ናት። ድንግል ማርያም ዓለም ለሰይጣን በመገዛት ባርነት ውስጥ ሳለ በመስቀል ተሰቅሎ የእኛን ሞት ሞቶ ነጻነት የሚያጎናጽፍ ጌታን ወለደችልን። ዓለም ተርቦ ነበር። እሷ ግን የሕይወት እንጀራን ወለደችልን። ድንግል ማርያም የትሕትና እናት ናት። ምሥጢራዊም ናት።ማርያም ግን ይህንን ሁሉ በልቧ ትጠብቀው ነበር ተብሏል። እውነትን ይዛ ሳለ በሐሰተኞች ወደ ግብጽ እንድትሰደድ ሆነች።

የቤዛነትን ትርጉም ንገረን ላላችሁኝ እነሆ

ቤዛነት ምንድን ነው?

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሰው ልጆች በሰው ልጆች ምትክ ያደረገው ሥራ ቤዛነት ይባላል። ቤዛ በአገባቡ "ስለ" ነው። ምሥጢሩ ምትክነትን፣ መቤዠትን ይገልጻል። ቤዛ "ቤዘወ-አዳነ" ከሚለው ግሥ ሲወጣ መድኃኒት ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። በሁለቱም ለክርስቶስ ቢነገር ያስኬዳል። መድኃኒታችንም ነውና። ቤዛ-ስለ በሚለው አገባብ ከተተረጎመ ስለእኛ በመስቀል ተሰቅሎ ማዳኑን ይነግረናል። ክርስቶስ ያደረገው ሥራ ሁሉ ስለእኛ ነው። በትርጓሜ በሐተታ በእንቲኣነ (ስለእኛ) እየተባለ የሚገለጸው እንደ ኃጥኣን ስቶ፣ እንደ ሰማዕታት ዕሴትን ሽቶ ያደረገው አለመሆኑን ለመግለጽ ነው።

ይህ ክርስቶስ ያደረገው የቤዛነት ሥራ የባሕርይ ሥራ ነው። ቅዱሳን ደግሞ አምላካቸው ክርስቶስን መስለው ስለሌላው ሰው ብለው የሚቀበሉት መከራ ቤዛነት ነው። ግን የጸጋ ቤዛነት ነው። "ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም" የሚለው ቃል ሰዎችም በአቅማቸው አንዱ ለአንዱ ቤዛ መሆን እንዲችሉ የተነገረም ጭምር ነው። ግእዙ "አልቦ ዘየዐቢ ወይኄይስ እምዝ ፍቅር ከመ ብእሲ ዘይሜጡ ነፍሶ ቤዛ ነፍሰ ቢጹ" ይለዋል (ዮሐ.15፥13)። ቅዱሳን ክርስቶስን አብነት አድርገው ስለሌሎች ሰዎች ሲጸልዩ፣ ሲጾሙ፣ ሲሞቱ አይተናል። ጌታም የእነርሱን ፍቅር አይቶ ኃጥኣንን ሲምር በብዛት ተጽፏል።

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ሐዲስ ኪዳን ላይ ስንገባ በሰፊው እንመለከተዋለን።

©በትረ ማርያም አበባው

#ድምፀ_ተዋህዶ


☞ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን!
☜ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን!
☞ አሰሮ ለሰይጣን!
☜ አግዐዞ ለአዳም!
☞ ሰላም!
☜ እምይእዜሰ!
☞ ኮነ!
☜ ፍስሐ ወሰላም!

[ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፣  በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ፣ ሰይጣንን አሠረው፣ አዳምን ነጻ አወጣው ፣ ሰላም፣ ከዛሬ ጀምሮ ፣ ይሁን ፣ ሰላም]

እንኩዋን ለብርሃነ ትንሣኤ በሰላም አደረሳችሁ! መልካም በዓል


✞ ትንሣኤከ ለእለ አመነ

ትንሣኤከ ለእለ አመነ
ብርሃነ ከፈኑ ዲቤነ /2/

      
የትንሣኤው በኩር የሰው ልጆች ሕይወት
ኢየሱስ ክርስቶስ ተነስቷል በእውነት
በዝግ መቃብር ውስጥ ተነሳ ሳይከፍተው
አዳምንም ከሞት ከሲኦል አወጣው

በትንሣኤው ተነስተን ዘመርን
የምህረቱን ዓመታት መቁጠር ጀመርን/2/

አዝ__

የሲኦል መውጊያዋ ፍላጻው ተነስቷል
የኛ መድኃኔዓለም ሞትን ድል አድርጓል
የእዳ ደብዳቤ በሲኦል ያለውን
ደምስሶት ተነሳ አውጥቶ ነፍሳቱን

በትንሣኤው ተነስተን ዘመርን
የምህረቱን ዓመታት መቁጠር ጀመርን/2/


አዝ__

ማርያም መግደላዊት የጠራሽ በስምሽ
በዓይንሽ ያየሽውን ሐዋርያት ይስሙሽ
መላእክቱም አሉ ተነስቷል ተነስቷል
የነገራችሁን እዩት ተፈፅሟል

በትንሣኤው ተነስተን ዘመርን
የምህረቱን ዓመታት መቁጠር ጀመርን/2/

አዝ__

የሞት ኃይሉ ታየ ሲዋረድ በጌታ
በድንግል ማርያም ልጅ በፍጥረት አለኝታ
እናቱ እናቴ እመቤቴ ወልዳው
በትንሣኤው ደሞ ሰላሜን አገኘው

በትንሣኤው ተነስተን ዘመርን
የምህረቱን ዓመታት መቁጠር ጀመርን/2/


አዝ__

ለትንሣኤው ልጆች ለምናምን ለእኛ
ብርሃንን ላክልን ላይጨልም ዳግመኛ
እንዘምር ለክብሩ ከበሮ ይመታ
ተነስቷል ኢየሱስ እንዳይቆም እልልታ

በትንሣኤው ተነስተን ዘመርን
የምህረቱን ዓመታት መቁጠር ጀመርን/2/


                   ዘማሪ
       በሱፍቃድ አንዳርጋቸው

✝️ከወደዱት✝️ለወዳጆ ሼር ያድርጉት↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨

      👍    🔄      🙅‍♂️         ✍️  
      ˡᶦᵏᵉ   ˢʰᵃʳᵉ   ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ


✞ እሰይ እሰይ የምሥራች ✞

እሰይ እሰይ የምሥራች ደስ ይበለን
ሞትን አሸንፎ ተነሳልን
በሞቱ የእኛን ሞት አጠፋልን

ሲኦል ባዶ ሆነ ዘንዶው ድል ተመታ
ሞትን በሞት ሽሮ የትንሳኤው ጌታ
እንባችን ታበሰ አገኘን ነጻነት
ከሲኦል እስራት ወጣን ከባርነት
አዝ••••••••••••••••••••••••••••••••
ቁልፎቿ ሲወድቁ የሲኦል መዝጊያዋ
ከዙፋኑ ሲወርድ ዲያቢሎስ ጌታዋ
አርነት ስንወጣ በጌታ ትንሳኤ
በእልልታ ደመቀ የሰማይ ጉባኤ
አዝ••••••••••••••••••••••••••••••••
የሞታችን መውጊያ ተሰበረ ቀስቱ
ጥልም በመስቀሉ ፈረሰ በሞቱ
የትንሳኤው ብርሃን ወጣ በላያችን
አምላክ መድኃኔዓለም ሲነሳ ጌታችን
አዝ••••••••••••••••••••••••••••••••
እንደ ህልም  አለፈ የኲነኔው ዘመን
ዲያብሎስን አስሮ አሳየን ብርሃን
ሞትና መከራ ከእኛ ተወግዷል
መቅበዝበዙ ቀርቶ ክብርን አግኝተናል

             መዝሙር
       ዘማሪ ፍቃዱ አማረ

✝️ከወደዱት✝️ለወዳጆ ሼር ያድርጉት↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨

      👍    🔄      🙅‍♂️         ✍️  
      ˡᶦᵏᵉ   ˢʰᵃʳᵉ   ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ


Forward from: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
የማርያም ለቅሶ

ልጄ ወዳጄ ሆይ ለእኔ ወዮታ አለብኝ ... በጦር ሲወጉህና ሲገድሉህ ዓይኖቼ ከምያዩ ይልቅ ልጄ ወዳጄ ሆይ ነፍሴን ከስጋዬ ትለያት ዘንድ እማልድሃለሁ።

ልጄ ወዳጄ ሆይ ይህ በራስህ የተቀዳጀኸው የእሾህ አክሊል ምነው እኔ በተቀዳጀሁትና የመከራህ ተሳታፊ በሆንኩ።

ልጄ ወዳጄ ሆይ አንተን በእሱ ላይ በሰቀሉበት መስቀልህ በሰላም እሰናበትሃለሁ።

ልጄ ወዳጄ ሆይ አይሁድ መራቃቸውን በተፉበት ብርሃንንም በተሞላ ፊትህ እሰናበትሃለሁ: ንጉስ ሆይ በሁለት ወንበዴዎች መካከል እርቃኑን ለቆመው አካልህ እጅ እየነሳሁ እሰናበትሃለሁ።

ልጄ ወዳጄ ሆይ እጣ በተጣጣሉበት ክብር ልብስህ እጅ እየነሳሁ እሰናበትሃለሁ።
ልጄ ወዳጄ ሆይ አክሊለ ሶክክን ለተቀዳጀ እራስህ ሰላም እያልኩና እጅ እየነሳሁ እሰናበትሃለሁ።

ምንጭ ግብረ ሕማማት

#ድምፀ_ተዋህዶ
#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ




✞ ንሴብሆ ✞

ንሴብሆ /2/ለእግዚአብሔር /2/ 
ስቡሐ ዘተሰብሐ /4 
እናመስግነው/2/ እግዚአብሔርን/2/ 
ምስጉን ነው የተመሰገነ /4/ 
       አዝ-----
ባህሩን ተሻግረን ወንዙ ደረቅ ሆነ
በጠላታችን ላይ ድሉ የኛ ሆነ
ከባርነት ቀንበር ፍፁም ነፃ ወጣን
ሕይወት የሚሰጥ መና ነው ምግባችን
       አዝ-----
አስፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር
ሁሉንም አለፍነው አምላካችን ይክበር
ጉልበታችን ቢዝል መከራ ቢበዛ
ኃይላችን ጌታ ነው የዓለሙ ቤዛ
       አዝ-----
ከአለት ላይ ውሃ ፈልን ጠጣን
ይህን ታላቅ ጌታ ኑ እናመስግን
ሰዎች ደስ ይበለን ሕይወታችን ድኗል
ሰይጣን ጠላታችን አፍሮ ተመልሷል
       አዝ-----
አስፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር
ሁሉንም አለፍነው አምላካችን ይክበር
ጉልበታችን ቢዝል ፈተና ቢበዛ
ኃይላችን ጌታ ነው የዓለሙ ቤዛ

✝️ከወደዱት✝️ለወዳጆ ሼር ያድርጉት↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨

      👍    🔄      🙅‍♂️         ✍️  
      ˡᶦᵏᵉ   ˢʰᵃʳᵉ   ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ

20 last posts shown.

54 809

subscribers
Channel statistics
Popular in the channel

ቅዱሳኑን ያዳነ ቅዱስ መልአክ እኛንም ያድነን ዘንድ እንደ አባቶቻችን "አድኅነኒ ዘአድኃንኮሙ በአክናፊከ ምንትው:: አመ ውስተ እሳት ተወድዩ ሠለስቱ እደው...
✞ ቸር_አገልጋይ_ማነው ቸር አገልጋይ ማነው ለንጉስ የታመነ መክሊቱን ያልቀበረ አትርፎ የከበረ ባለ አምስቱ መክሊት መልካም ያደረገው በመውጣት በመውረ...
✞ በመከራ ጽና ✞ በመከራ ጽና በመከራ ጽና በፈተና ጽና ለጊዜው ነው እንጂ ሁሉም ያልፋልና /፪/               አዝ ======== ኢዮብ ተጨ...
የምስራች ከሀገር ውጪ ለምትኖሩ! የግእዝ (የአብነት) ትምህርት በስልኮ መጣሎት። ማንኛውም ምዕመን ውዳሴ ማርያምና መዝሙረ ዳዊትን መጸለይ እንደሚገባው ...
✝☦️  ✝️ 🙏🙏🙏ተመስገን🙏🙏🙏 ስለ እኔ ስትል ከዚያ ከዙፋን የወረድክ         እየሱስ ክርስቶስ ሆይ             ✝️ተመስገን✝️ ስለበደሌ በ...