Forward from: ዋቄ ገጽ
ይህን ሰሞን ስለ ዓለማወ ዘፈንና ሙዚቃ የሚወዛገዱ መምህራኖችን ተመልክቻለሁ።
እኔ የቀኖና ሊቅ አይደለሁም። ነገር ግን በሃይማኖት የማስብ ስለሚመስለኝ አስተያየት መስጠት አስፈላጊ መስሎ ታየኝ።
ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ሃይማኖትን ሕይወቱ ስላደረገ ሰውና ማኅበረሰብ ስንነጋገር የሰሞኑን ፖለቲካና ከመንፈሳዊ ዓላማ ውጭ የሆኑ ድብቅ ፍላጎታችን በተቻለ መጠን ያልተቀላቀለበት ትምህርት መስጠት ምእመናንን በማሳሳት ምክንያት ከበጎቹ ጌታ ከእየሱስ ክርስቶስ ቅጣት ያድናል።
ቤተ ክርስቲያን ከሁሉ በላይ የቅዳሴ የጸሎት ዜማን እስከነ ዓላማውና መንፈሳዊ ግቡ፥ ከእነ ጥልቅ ምሥጢሩ ተረድተን እንድናዜም ትፈልጋለች። ታስተምራለች፥ በተግባርና በህይወት ታሳያለች። በሂደቱ ሁሉ ህሊናችን፥ ዓይነ ልቦናችን እና መላው ተስፋችን ሁሉ ሰመያዊ ማንነታችንን አንጾ በመገኘት ላይ ታተኩራለች። ልጆቿም እንዲሁ በግልና በጋራ ድምፍ አውጥተው ወይንም በአርምሞ ሲያዜሙና ሲናገሩ ቅዳሱው ባመለከታቸው መሠረት ነፍሳቸውን ወደ ሰማዩ አባታቸው እንድታተኩር አድርገው ፈጣሪያቸውንና መድኀኒታቸውንን ክፍ ክፍ ማድረግና ማመስገን እንዲሆን እንደምታስተምር የቅዱሳን ሕይወት ሁሉ ይጠቁማል።
ቤተ ክርስቲያን በግልጽና በአትቃላይ ዓለማዊ/ሥዝም ዘፈንን ኣታወግዝም። በመጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠን ምልክት በጥንቃቄ መመልከት ያስፈልጋል፦
ሮሜ 13፡13-14 “በቀን እንደምንመላለስ በአግባብ እንመላለስ። በጭፈራና በስካር አይሁን፤ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፤ በክርክርና በቅናትም አይሁን። ይልቁንም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም ይፈጽም ዘንድ ለሥጋ በዐሳባችሁ አትመቻቹለት። “
1 ጴጥሮስ 4:3 “አሕዛብ ፈቅደው እንደሚያደርጉት በመዳራት፣ በሥጋዊ ምኞት፣ በስካር፣ በጭፈራ፣ ያለ ልክ በመጠጣት፣ በአስጸያፊ የጣዖት አምልኮ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል። “
ገላትያ 5:16-25፤ ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ። 17፤ ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ይመኛልና፥ እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ፤ ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም። 18፤ በመንፈስ ብትመሩ ግን ከሕግ በታች አይደላችሁም። 19፤ የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት፥ ርኵሰት፥ 20፤ መዳራት፥ ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥ 21፤ መለያየት፥ መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም። 22፤ የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፣ 23፤ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው። እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም። 24፤ የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ። 25፤ በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ።
የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክትና የቤተ ክርስቲያናችን የምንመለከተው ተግባራዊ ሕይወት የሚናበቡና የሚተረጓጞሙ መስለው ይታያሉ። የጠቀስናቸው ጥቅሶች በአንድ መሥመር ቢጠቃለሉ ገላ 5፥25 ይሆናሉ። እርሱም “በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ፨“ የሚለው ይሆናል።
እንግዲ ቤተ ክርስቲያን ልጆቿ በመንፈስ የመኖር አቅም እንዲያዳብሩ፥ ጎጂውንና ጠቃሚውን በራሳቸው እየለዩ አምላካቸውን እንዲያስደስቱ፥ የመንፈስ ቅዱስ ማኅደርበነታቸውን በሕይወት እንዲቀምሱ ታበረታታለች።
እንደ ኣይሁንና እንደ እስላም ወይንም እንደ ሌሎች ሰው ሠራሽ እምነቶችና ድርጅቶች ንካ-ኣትንካ፥ ቁም-ተቀመጥ እያለች በትምቀት በክርስቶስ ሞትና ትንሳዔ በጥምቀት ተካፍለው ዓለምን ሊዋጁ በውትድርና የተሠማሩ ልጆቿን በመንፈሳዊ ተጋድሎ ውስት አልፈው እንዲኣድጉላት “በመንፈስ ኑሩ!” ብላ የገዳማውያንን ሕይወት እንደ ምሳሌ በተግባር እያሳየች በጎቿን ትመግባለች።
እንግዲህ ዘፈን ይፈቀዳል ወይስ አይፈቀድም የሚለውን እሰታ ገባ ለሊቃውንት ጉባኤ ብያኔ ትቼ እኔ የበለጠ እስክማርና እስክረዳ አሁን እንደምረዳው ከሆነ ዘፈንን በሚመለከት የሚከተሉትን ነጥቦች ልብ እንድንል ትፈልጋለች፦
1. የዘፈኑ ዓላማ ይዘት፦ ክርስቲያኖች ዘፈን ሲሰሙ (ሲዘፍኑ አላልኩም) የዘፈኑን ዓላማና ይዘትን በሚመለከት በክርስቲያናዊ መንፈሳዊ ሚዛን ሊለኩ ይገባል። ይዘቱ ከመንፈሳዊ ዓላማ የሚያዘናጋ፥ ሥጋዊ ስሜት የሚቀሰቅስ፥ አሉታዊ ጠባይ እንድንለማመድ ምክንያት የሚሆን እና መንፈሳዊ ተመስጦን በሚያዳክም መንገድ በአእምሮ ምስለ-ዘማን (ፖርኖገራፊክ ምስሎች) የሚያትም እንዳይሆን አትብቃ እንደምታስጠነቅቅ ከአባቶቻችን ትንቃቄ እንማራለን።
2. በነፍስ ላይ የሚኣሳድረው ተጽእኖ፦ ከኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ተግባራዊ ሕይወት እንደምንረዳው ቅዳሴውና ማኅሌቱ ከይዘቱና አካል እንቅስቃሴ፥ ዝውውርና ሂደት ሁሉ የክርስቲያኖችን ነፍስ (ካህን በዓብይ ዜማ “ልባችሁን ወደ እግዚአብሔር ከፍ አድርጉ” ሲል ምእመናን ደግሞ “ብግዚአብሔር ዘንድ አለን/ነን” ማለታቸው የማዜማችንን ዓላማ ያመለክታል። ዜማ/ሙዚቃ በነፍስ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ እንደሚኣሳድር ከቤተ ክርስቲያን የበለጠ የሚረዳ ያለ አይመስለኝም። የቅዱስ ያሬድ ክግዚአብሔር የአገልግሎት፥ የውዳሴና የቅዳሴ ዜማ መቸሩ ይህንነኑ ተጽእኖ ያመለክታል። ከዚህ ተነስታ ቤተ ክርስቲያን ልጆቿ ዓለማዊ ዜማና ዘፈንን ከእግዚአብሔር ጋር ከሚኖረን የቀና ግኑኝነትና ከመንፈሳዊ እድገታችን አንጻር እንድንመረምር ታስተምረናለች።
3. አቅመ-ማንጸር፦ ምእመናን ሙዚቃ ወይንም ዘፈን ለማዳመጥ የትኛው ለነፍስ የሚጠቅም ወይንም እንደሚጎዳ የማንጸር አቅም እንዲያዳብሩ ታበረታታለች እንጂ እንደዚህ እንደ ኣሁኑ ትውልድ በጭፍን መንጋነት ብዙኃን የወደዱትን መከተል፥ ዘመኑ ያገለለውን መጥላት፥ ማስታወቂያ ያገነነውን በጭፍን መጋትን እንድንጸየፍ ታሳየናለች። ማንጸሪያችን ዘፈኑ ከክርስትና እሤት፥ ዓላማና የመኖር ትርጉም ጋር ያለውን ግኑኝነት በመመዝን መሆን አለበት። ጥያቄውም ዘፈኑ ወደ እግዚአብሔር ፍቅርና ምስጋና የሚመራ ነው ወይስ ለመንሳዊነት እንቅፋት ነው? በሚል ማንጸር ያሻል።
4. ከመምህረ ንስሐ መመሪያ መቀበል፦ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ልጆቿ በተለያዩ መንፈሳዊ አቅም፥ በተለያዩ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ስለሚኖሩ አንድ አስገዳጅ ሕግና መመሪያ የሰጠቸን ኤእመስለኝም። በዚህ ምትክ ክርስቲያኖች በሚኣደርጉት ብቻ ሳይሆን በሚኣስቡትና ባቀዱት ጉዳይ ከንስሐ አባቶቻቸው ከካህን ጋር በመምከር ለነፍሳቸው የሚበጀውን መመሪያ መቀበል አንደሚገባቸው እንደምታስተምር ቤሌሎች የትዳርና የግል ሁኔታዎች ውስጥ ሁላችንም እናውቀዋለን። ለክርስቲያን “መዝናኛ” በሚል ዓለማዊ ስሜት ቀስቃሽ፥ ርኩሰትና ኃጢአትን የሚኣበረታታ የዘመኑን ዘፈን ከክርስትና መንፈሳዊ ሕይወት ጋር ፈጽሞ የማይስማማ በመሆኑ ከንስሐ አባት ጋር መምከርን ታዛለች።
ሲጠቃለል ኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስቲያን ዘፈንን ሁሉ ስታወግዝ አልመለከትም። ግልጽ ሆኖ የሚታየኝ ምእመናን ሙዚቃን/ዘፈንን በሚመለከት የመጀመሪያ ጥያቄያቸው “የምሰማው ወይንም የምዘፍነው ዘፈን ለመንፈሳዊ ሕይወቴ እድገትና ከእግዚአብሔር ጋር ያለኝን ግኑኝነት ያሳድግልኛል ወይስ መንፈሳዊ ሕይወቴን ይጎዳል?” ብሎ በመጠየቅ፥ እንዲሁም ከመምህረ ንስሐ ጋር በመምከር መበየን ይኖርባቸዋል።