2. ጳውሎስ የኤፌሶን አማኞች እንደ የክርስቶስ አካል ክፍሎች እንዴት ሊመላለሱ እንደሚገባቸው ያስተምራል (ኤፌ. 4-6)። እግዚአብሔር የባረካቸው ሰዎች እንደ እግዚአብሔር ልጆች መኖር ይጠበቅባቸዋል። እኛ የአንድ አካል ወይም የአንድ ቤተስብ አባላት ስለሆንን፥ በፍቅርና በአንድነት ልንኖር ይገባል። እግዚአብሔር የአካሉን ክፍል በመንፈሳዊ ብስለት ለመገንባት ሲል ለመሪዎች ስጦታዎችን ይሰጣል። አማኞች ሰማያዊ አባታችንን የሚመስል የተቀደሰ ሕይወት መምራት ይኖርብናል። በዚህ ቤተሰብ ውስጥ በፍቅር፥ በሥርዓት፥ በአንድነትና በመቻቻል ልንኖር ይገባል። የክርስቶስንና የቤተ ክርስቲያንን ምሳሌ በመከተል ሚስቶች ለባሎቻቸው ሊገዙ፥ ባሎች ደግሞ ሚስቶቻቸውን ሊወዷቸው ይገባል። በሥራ ቦታ በሠራተኞች (ባሮችን) እና በቀጣሪዎች (ጌቶች) መካከል መከባበር ሊኖር ይገባል። በመንፈሳዊ ውጊያችን ደግሞ ክርስቶስ የሰጠንን የጦር መሣሪያ በመጠቀም ነቅተን ራሳችንን ልንጠብቅ ይገባል።
የኤፌሶን መልእክት አስተዋጽኦ
1. ጳውሎስ ለኤፌሶን ክርስቲያኖች፥ አማኞች በክርስቶስ ማን እንደሆኑና ቤተ ክርስቲያን ምን እንደሆነች ያስተምራል (ኤፌ. 1-3)፡፡
ሀ. መግቢያ (ኤፌ. 1፡1-2)
ለ. የእግዚአብሔር ልጆች መንፈሳዊ በረከቶች (ኤፌ. 1፡3-14)
ሐ. ጳውሎስ አማኞች እንደ እግዚአብሔር ልጆች ያላቸውን መንፈሳዊ ስፍራ እንዲረዱ ይጸልያል (ኤፌ. 1፡15-23)።
መ. ሙት የነበሩ የእግዚአብሔር ጠላቶች በጸጋው ሕያዋን ሆነው ድነዋል (ኤፌ. 2፡1-10)
ሠ. ሁሉም አማኞች ሰብአዊ ክፍፍሎች በማይታሰቡባት አንዲት ቤተ ክርስቲያን ተጠልለዋል (ኤፌ. 2፡11-22)
ረ. ጳውሎስ ስለ ክርስቶስና ቤተ ክርስቲያን የሚናገረውንና የእግዚአብሔር ምሥጢር የሆነውን ወንጌል ለማወጅ የተመረጠ አገልጋይ ነው (ኤፌ. 3፡1-13)
ሰ. ጳውሎስ አማኞች የክርስቶስንና ከእርሱ ጋር ያላቸውን ግንኙነትና ታላቅነት ይረዱ ዘንድ እግዚአብሔር ጉልበት እንዲሰጣቸው ይጸልያል (ኤፌ. 3፡14-21)።
2. ጳውሎስ የኤፌሶን አማኞች ለወንጌሉ እንደሚገባ ይመላለሱ ዘንድ ያደፋፍራቸዋል (ኤፌ. 4-6)።
ሀ. ለወንጌሉ እንደሚገባ መመላለስ ማለት እንደ አማኞች አንድነትን መፍጠርና እርስ በርሳችን መዋደድ ነው (ኤፌ. 4፡1-6)
ለ. እግዚአብሔር የአካሉ ክፍሎች እርስ በርሳቸው እንዲረዳዱና በብስለት እንዲያድጉ የተለያዩ ስጦታዎችን ሰጥቷቸዋል (ኤፌ. 4፡7-16)።
ሐ. እግዚአብሔር ልጆቹ በቅድስና በመመላለስ እርሱን እንዲመስሉ ይፈልጋል (ኤፌ. 4፡17-5፡20)
መ. እግዚአብሔር የቤተሰብ አባላቱ እርስ በርሳቸው እንዴት መዛመድ እንዳለባቸው አብራርቷል (ኤፌ. 5፡21–6፡9)።
ሠ. እግዚአብሔር ልጆቹ ራሳቸውን ከሰይጣን ጥቃቶች እንዲጠብቁና የድል ነሺነትን ሕይወት እንዲመሩ መንፈሳዊ የጦር ዕቃዎችን ሰጥቷቸዋል (ኤፌ. 6፡10-20)
ረ. የመጨረሻ ሰላምታ (ኤፌ. 6፡21-24)
(ማብራሪያው የተወሰደው በ ኤስ.አይ.ኤም ከታተመውና የአዲስ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣ ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡ እግዚአብሔር አገልግሎታቸውን ይባርክ፡፡)