Posts filter


ንጹህ ፍቅር

“የትእዛዝ ፍጻሜ ግን ከንጹሕ ልብና ከበጎ ሕሊና ግብዝነትም ከሌለበት እምነት የሚወጣ ፍቅር ነው” (1ጢሞ. 1፡5)፡፡

ንጹህ ፍቅር አንድን ነገር ስናደርግ ካለን የመነሻ አሳብና እንዲሁም ከምናደርገው ተግባር አንጻር የሚታይ ጉዳይ ነው፡፡ ስለዚህ፣ ንጹህ ፍቅር በአንድ ጎኑ አንድን ነገር ስናደርግ ያደረግንበት ምክንያት ንጹህ የመሆኑ ጉዳይ ይነካል፡- “ፍቅር በባልንጀራው ላይ ክፉ አያደርግም፤ስለዚህ ፍቅር የሕግ መፈጸሚያ ነው” (ሮሜ 13:10)፡፡

በሌላ ጎኑ ደግሞ ምንም እንኳን በውስጣችን ፍቅር እንዳለ ብንናገርና መነሻ ሃሳባችን ንጹህ ቢሆንም ንጹህ ፍቅር በመልካም ተግባር ይገለጣል፡- “ልጆች ሆይ፤ በተግባርና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት ብቻ አንዋደድ” (1ዮሐ. 3:18)፡፡

የግሪኩን ጽሑፍ በሚገባ የሚገነዘቡ የስነ-መለኮት አስተማሪዎች የተለያዩ የፍቅር ገጽታዎች እንዳሉ ያስተምሩናል፡፡

1) ስቶርጌ (Storge) - የቤተሰብ ፍቅር ነው፡፡ ለምሳሌ፣ ወላጆች ለቤተሰባቸው ያላቸውን ፍቅር ያሳያል፡፡

2) ኢሮስ (Eros) - በተለያዩ ጾታ መካከል ያለ ፍቅር ነው፡፡ በሰው ላይ ከምናየው ውብ ነገር ከመነሳት የሚኖረንን ፍቅር ያሳያል፡፡

3) ፊሊዮ (Philio) - የጓደኝነት ፍቅር ነው፡፡ ሰውን በፍጹም ጓደኝነት ስንወደው የሚኖረንን ፍቅር ያሳያል፡፡

4) አጋፔ (Agape) - ሰውን ካለምንም ቅድመ ሁኔታ የምንወድበት ፍቅር ነው፡፡ እግዚአብሔር እኛንና ዓለምን የወደደበትን ፍቅር ያሳያል፡፡ እኛም እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ የተባልንበት ፍቅር ነው፡፡

ቃሉ፣ “የገዛ ሥጋውን የሚጠላ ማንም የለም” (ኤፌ. 5፡2) ስለሚል አንድ ሰው ለራሱ የሚኖረውን ፍቅር አልፈን ስንሄድ፣ ሶስት አይነት የአጋፔ የፍቅር መገለጫዎችን እንደመለከታለን፡፡

1. እግዚአብሔርን መውደድ

“ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ” (ማቴ. 22፡37)፡፡

ቃሉ ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር በምንም የእንካ-በእንካ ላይ ያልተመሰረተና ንጹህ እንዲሆን ይመክረናል፡፡ ጌታን ለመውደድ ምንም ሌላ ምክንያት አያስፈልገንም፤ “እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን” (1ዮሐ. 4፡19)፡፡

2. ባልንጀራን መውደድ

“ባልንጀራህን … ውደድ” (ማቴ. 22፡39)፡፡

ለእግዚአብሔር ያን ንጹህ ፍቅር የሚታወቀው አጠገባችን ላለው ወገናችን በምናሳየው ፍቅር ነው፡፡ “ማንም፣ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን መውደድ አይችልምና” (1ዮሐ. 4፡20)፡፡

3. ጠላትን መውደድ

“ጠላቶቻችሁንውደዱ” (ማቴ. 5፡44)፡፡

“የእግዚአብሔር ጠላቶች ሳለን በልጁ ሞት ከእርሱ ጋር ከታረቅን” (ሮሜ 5፡10) እና በንጹህ ፍቅር ከተወደድን እኛም ይህንን ፈለግ በመከተል ጠላቶቻችንን በይቅርታ በመቀበል ልንወድ እንደሚገባን ክርስቶስ ምሳሌን ትቶልን አልፏል፡፡

የሚቀጥለው ትምህርት፡ “ንጹህ አምልኮ”


ንጹህ ፍቅር


ምን ይሆናል ለጸጋው ታልፎ የተሰጠ
መንገድ ጎዳናውን ለእግዚአብሔር ይኸውልህ ያለ
ያየህለት እንጂ የሚያልፍ የሚያገድመው አያገኘው
ቃሉ እንዳለ እንደተጻፈለት ነው የሚኖረው✨🤍


"…ወተት''- ቅቤ ከሚሆንበት 'ጉዞው' ይልቅ፤
''ቅቤ'' - ወተት እንደነበር 'ማስታወሱ' አድካሚና ረብየለሽ ይሆናል፤

ወተት ቅቤ እንደሚወጣው ማወቅ ግን
ዕውቀትም ፣ ተስፋም ፣ ዕምነትም እውነትም ነው !!!"




የትኩረት ጉልበት!

•  ችግሩ እያለ፣ ትኩረታችንን ትክክለኛውን መፍትሄ መፈለግ ላይ ስናደርግ . . .

•  ፍርሃቱ እያለ፣ ትኩረታችንን በጥንቃቄ ወደ ፊት በመራመድ አልፎ መሄድ ላይ ስናደርግ . . .

•  የሰዎች ክፋት እያለ፣ ትኩረታችንን ስናስባቸው የሚያበረታቱን ጨዋ ወዳጆቻችን ላይ ስደርግ . . .

•  የተለወጠብን ሰው እያለ፣ ትኩረታችንን አብሮነቱ የማይለዋወጠው ሰው ላይ ስናደርግ . . .

•  ያልተሳካው ነገር እያለ፣ ትኩረታችንን የተሳካው ላይ እና ወደ ፊትም ሰርተን የምናሳካው ነገር ላይ ስደርግ . . .

•  ስህተትና ስህተቱ ያስከተለው ጉዳት እያለ፣ ትኩረታችንን ከስህተቱ ያገኘነው የእድሜ ልክ ትምህርት ላይ ስናደርግ . . .

•  በምርጫ ግራ መጋባቱ እያለ፣ ትኩረታችንን ምንም ምርጫ የሌለው ኑሮ ከሚኖሩ ሰዎች የመሻላችን ሁኔታ ላይ ስናደርግ . . .

ኃይላችንን እቆጥባለን፣ ነገን ለመጋፈጥ ጉልበት እናገኛለን፣ በሆነ ባልሆነው ግራ አንጋባም፣ ከልክ ካለፈ የሃሳብ ግልቢያ (overthinking) ረገብ እንላለን፡፡

የትኩረት ለውጥ እናድርግ!

      @revealjesus


Enjoy our content? Advertise on this channel and reach a highly engaged audience! 👉🏻

It's easy with Telega.io. As the leading platform for native ads and integrations on Telegram, it provides user-friendly and efficient tools for quick and automated ad launches.

⚡️ Place your ad here in three simple steps:

1 Sign up

2 Top up the balance in a convenient way

3 Create your advertising post

If your ad aligns with our content, we’ll gladly publish it.

Start your promotion journey now!


በበዝቶ ካለው ጩኸት ሸተተኝ ሰላሙ
ከጨለማው መሀል ታየኝ ወጋገኑ
ከድፍርሱ መሀል ኩልል ያለነገር
ይታየኝ ጀመረ በቃልህ ስታመን
      የሀሳብህ ጥልቀት ባይገባኝ ድምድሙ
      ጅማሬ ላይ ቆሜ ቢበዛ ለምኑ
      የፍርስራሽ ክምር ግራ ቢያሳስበኝ
     ማዶን አሻግሬ ለማየት ሲያቅተኝ
      ጎራ ስል ወደቃልህ ነገረኝ ነገሩን
      የዛሬው ትርምስ ነገ ላይ ማማሩን
      ለአይን የሚመች ነገር ባያዩ ዓይኖቼ
      ግን በስራ ላይ ነህ ልቀመጥ ረግቼ (2x)
      የለም ከሰው ሰፈር የፍቃድህ ምክር
      ፍጥረትን ሰብስበህ አትቆም ለድርድር
      ለዝብርቅርቁ ቅርፅ መልክ ላጣው ውበት  
     ሰተት ብሎ ይገባል አሜን ባለአንደበት
ዝምታ መልስ ሆነኝ  አሀሀሀ (2x)
እየሰራ እንደሆነ ዘፍጥረት ነገረኝ

@revealjesus




እኔ አለኝ እልልታ// ዘማሪ አቤኔዘር ለገሰ እና ዳግም በላቸው// ine alegn ililita Singer Abenezer Legese & Dagim Belachew

@revealjesus


Forward from: መዝሙር (MEZMUR) E4J
ዝማሬ በዘማሪት ማዕረግ

@e4jesus

https://t.me/e4jsong
@e4jsong

ኢትዮጵያን ለኢየሱስ


Mesay Birhanu @ Kingdom Sound Worship Night 2025 ' Anten Bicha Sasib ' Original Song By Dagmawi Tilahun

@revealjesus


ሰሞኑን “ሰማያዊ አመለካከት” በተሰኘው ርእስ ስር የተማርናቸውን አምስት ክፍሎች ተግባራዊ ለማድረግ እንዲመቻችሁ የሚከተሉትን የግል ጥሞና ጥያቄዎችን ትቼላችኋለሁ፡፡

1. ሰማያዊ የአስተሳሰብ ዘይቤን ከማዳበር አንጻር በሕይወቴ ምን ለውጥ ለማምጣት አሰብኩ?

2. ሰማያዊ የንግግር ዘይቤን ከማዳበር አንጻር በሕይወቴ ምን ለውጥ ለማምጣት አሰብኩ?

3. ሰማያዊ የሕይወት ዘይቤን ከማዳበር አንጻር በሕይወቴ ምን ለውጥ ለማምጣት አሰብኩ?

4. ሰማያዊ የውጊያ ዘይቤን ከማዳበር አንጻር በሕይወቴ ምን ለውጥ ለማምጣት አሰብኩ?

5. ሰማያዊ የጥበብ ዘይቤን ከማዳበር አንጻር በሕይወቴ ምን ለውጥ ለማምጣት አሰብኩ?


የግል ሕልማችሁ ጉዳይ

(“የተደራጀ ሕይወት” ከተሰኘው ሰሞኑን ከታተመው አዲስ የዶ/ር ኢዮብ መጽሐፍ የተወሰደ)

የተደራጀ ሕይወት ከመኖር አንጻር ሕልማችን ላይ የመስራታችንን አስፈላጊነት ትኩረት ሰጥተን እንመለከታለን፡፡ በቅድሚያ ግን “የግል ሕልም” ስንል ትርጉሙ ምን ማለት እንደሆነ በመስማማት እንጀምር፡፡

“የግል ሕልም ማለት በተለያዩ የግል ሕይወታችን ዘርፎች ስኬታማ እና ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ለመኖር የሚያስችሉንን መርሆች በመከተል የልህቀት ከፍታ ውስጥ የሚከቱንን ሁኔታዎች መገንባት ማለት ነው፡፡”

በዚህ ትርጉም መሰረት በሕልም ላይ ስለመስራት ማሰብ ማለት የራስን ሕይወት መገንባትና ማሻሻል ማለት ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ፣ ራእይ የሰውን ሕይወት የመገንባትን፣ የማሳደግንና የመለወጥን ሁኔታ ሲነካ፣ ሕልም ደግሞ የራስን ሕይወት የመገንባትን፣ የማሳደግንና የመለወጥን ሁኔታ ይነካል፡፡

ይህ ሕልም ብለን የምንጠራው ጉዳይ የራሳችንን ሁለንተናዊ ሕይወት ከማሳደግ ጋር የሚገናኝ ልምምድ ሲሆን፣ ሁኔታው እንዲሁ በሃሳባችን የፈጠርነውን ነገር ሁሉ እንደሚሆን በጭፍንነት የማሰብ ጉዳይ ሳይሆን ተግባራዊ ሂደትን ተከትሎ ስኬታማ ሕይወት ውስጥ የመግባት ጉዳይ ነው፡፡

ሕልሞቻችን ቅዠት ሆነው እንዳይቀሩ መውሰድ ከሚገቡን ወሳኝ እርምጃዎች መካከል የሚከተሉትን ቀላል መርሆች ማስታወስና መለማመድ ይጠቅናል፡፡

1.  አልመው - እያንዳንዱ ታላቅ ስኬት የሚጀምረው በአንድ ሰው አእምሮ ውስጥ ሲፈጠር ነው።

2.  እመነው - ሕልም ጋር የሚደረሰው ያለምነውን ሕልም ልንደርስበት እንደምንችል በማመን ነው፡፡

3.  እየው - ሕልማችንን በገሃዱ አለም ከማየታችን በፊት በአይነ-ህሊናችን ማየት አስፈላጊ ነው፡፡

4.  አጋራው - ሕልማችንን በውስጣችን አምቀን ከምንይዝ ይልቅ ለተገቢ ሰዎች ማጋራት ወደ ስኬት ያስጠጋናል፡፡

5.  አቅደው - ያለምነውና አምነን በውስጠ-ህሊናችን ያየነውን ሕልም በእቅድ ደረጃ ማውረድ አለብን፡፡

6.  ስራው - ሕልማችንን ካመንነውና ካቀድነው በኋላ ወደ እንቅስቃሴ መግባት ይኖረብናል፡፡

7.  አጣጥመው - በሕልም ተጀምሮ ጠንክሮ በመስራት እጃችን የገባውን ውጤት ማጣጣምና መደሰት ያስፈልጋል፡፡

መጽሐፉን በቅናሽ ለማግኘት በ 0947930369


      @revealjesus




👉ዛሬ ስለአንድ ነገር አፅንኦት ሰተን እንመለከታለን። እሱም ስለ መንፈሳዊ ልባችን ነው ሁላችንም ልቦናችንን ልንመዝን አስፈላጊ ነው ምክንያቱም ክርስቶስ በምሳሌው ይነግረናል ልብ ምን ያህል ለ መንፈሳዊ እድገትን እና ፍሬ ለማፍራት መሰረት እንደ ሆነ።

👉ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ከመፅሀፍ ቅዱሳችን (ሉቃስ 8፥4-15) ይህ ክፍል የሚያወራው የዘሪውን ምሳሌ ነው። ምሳሌውም 2 ነገሮች ላይ ትኩረት አድርጔል እስቲ እንመልከት።

📌1ኛ= ዘር ሲል  የሚወክለው የእግዚአብሔርን ቃል ነው( ሉቃስ 8፥11) ልንመለከት እንችላለን ይህ ዘር አንድ ሆኖ ሳለ ካረፈበት መሬት የተነሳ ግን የተለያየ ፍሬ ሲያፈራ እንመልከት።
📌2ኛ መሬት (ዘሩ የወደቀበት ስፍራ) እሱ የልባችን ምሳሌ ነው ።


(ዕብራውያን 1፥1-2) ላይ ሲናገር ይህ የእግዚአብሔር ቃል በተለያየ ሁኔታ ለአባቶች ፤ እንዲሁም አሁን በአዲስ ኪዳን በልጁ በክርስቶስ ለእኛ ተናገረን እንደሚል ቃሉ ከመነገር ካልተከለከለ እንዴት ልባችንን ከቃሉ ጋር አስማምተን ፍሬ እናፈራ ይሆን?
በዚህ ምሳሌ ላይ 4 አይነት ስፍራዎችን እናያለን።
👉1ኛ "መንገድ ዳር "ተብሎ የተገለፀ የልብ አይነት ያላቸው ሰዎች በ (ሉቃስ8፥12)እንደተገለፀው ቃሉን የሚሰሙ ነገር ግን አምነው እንዳይድኑ ድያብሎስ ቃሉን ከልባቸው የሚወስድባቸው።
👉2ኛ "አለታማ"ቃሉን የሚሰሙ ነገር ግን በፈተና ወቅት የሚክዱ ናቸው።
👉3ኛ "በእሾህ መካከል ያለ መሬት"ቃሉን የሚሰሙ ነገር ግን ምቾት እና የለተለት ሩጫ እንዳያፈሩ ያነቃቸው ናቸው።
👉4ኛ"መልካም መሬት" ቃሉን በመልካም እና በበጐ ልብ ቃሉን የሚሰሙ ብቻ ሳይሆን ፀንተው የሚጠብቁ ናቸው። በመሆኑም መቶ እጥፍ ያፈራሉ።ስለዚህ ሁላችንም እራሳችንን እንጠይቅ የእኛ ልብ የቱን ይመስል ይሆን?


👉በስተመጨረሻም ስለ መንፈሳዊ ፍሬ እና ስለ ልባችንን ስናስብ ምን ላይ እናተኩር ለሚለው የሚከተለው እንይ።
📌1ኛ የእግዚአብሔርን ቃል በማወቃችን (በመስማታችንና በማንበባችን) ብቻ አንደገፍ ምክንያቱም ባየነው ምሳሌ ላይ ሁሉም የሚሰሙ ስለነበሩ በመስማት ላይ እምነትን እና ከራስ ጋር ማዋሀድን(ማሰላሰልን) ይጠይቃል።
📌2ኛ(ያዕቆብ 1፥12) በፈተና የሚፀና ሰው የተባረከ ነው ። እንደሚል ምን ያህል ከመከራችን በላይ ቃሉን እናምናለን እንደገፈዋለን? ፅናት ታማኝነት ስለሆነ አጥብቀን ልንይዘው ይገባል።
📌3ኛ መልካም ልብ፣ በጐ ህሊና ሊኖረን ይገባል።ለበለጠ( 1ጢሞ1፥19) እንመልከት።
📌4ኛ በምቾትና በድሎት ማነቆ ስር እንዳንሆን ልንጠነቀቅ ይገባናል ለስጋችን እንደምንጨነቅ እንደዚያው ለመንፈሳዊ ህይወታችን ልንጨነቅ ይገባናል በመጠን መኖርን እራሳችንን እናስለምድ።እንግዳ ነንና!




Video is unavailable for watching
Show in Telegram


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


ሰማያዊ የሕይወት ዘይቤ

“ከእንግዲህ ወዲህ በሥጋ ልትኖሩ በቀረላችሁ ዘመን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ እንደ ሰው ምኞት እንዳትኖሩ” (1ጴጥ. 4፡1)፡፡

እስከዛሬ የኖርነውን ሕይወት መለስ ብለን ስንመለከት ምናልባት እንደቃሉ ያልሆኑ ልምምዶቻችን እናስታውስ ይሆናል፡፡ ያለፈው ልምምዳችን ያም ሆነ ይህ፣ በቀረልን ዘመን የሰውን ምኞት ተወት በማድረግ እንደ ጌታ ፈቃድ የምንኖርበት የሕይወት ዘይቤ እንድንይዝ ቃሉ ያበረታታናል፡፡ እንደ ቃሉ ስናስብና እንደ ቃሉ ስንናገር እንደቃሉ ወደሆነ የሕይወት ዘይቤ አንድ እርምጃ እንደተጠጋን ማስታወስ አለብን፡፡ ለዚህ አይቱ ሰማያዊ የሕይወት ዘይቤ ምሳ የሚሆኑን ብዙ ምስክሮች አሉን፡፡

“ኖኅ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር አደረገ” (ዘፍ. 6:9)፣ “ሄኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔርጋር አደረገ” (ዘፍ. 5:22)፡፡ ኢያሱም ቢሆን፣ “በምትሄድበትም ሁሉ እንዲሳካልህ፣ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል” (ኢያ. 1፡7) የሚለውን ቃል ሰምቶ ልቡን ያበረታ ሰው ነበር፡፡

እነዚህና ሌሎች እንደመና የከበቡን ምስክሮች የተውልንን ፈለግ በመከተል ሰማያዊውን የሕይወት ዘይቤ ለማዳበር ዋነኛው ጉዳይ ምርጫ ይባላል፡፡ የትኛውን የሕይወት ዘይቤ እንመርጣለን? የሚከተሉትን ምርጫዎቻችንን እንመልከት፡፡

1. እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የመመላለስ ምርጫ

“በመንፈስ ተመላለሱ” (ገላ. 5፡16)፡፡

ሐዋርያው ጳውሎስ ይህን ቃል የተናገረበት አውድ የስጋን ስራ የመፈጸምንና እኛ የምንፈልገውን ሳይሆን ጌታ የሚፈልገውን ነገር የማድረግን እውታ ያካተተ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ በትእዛዝ መልክ ተቀምጦ ለእኛ ምርጫ የተተወ እንደሆነ ቃሉ ይጠቁመናል፡፡ እርስ በርስ የሚቀዋወሙትን የመንፈስና የስጋ አሳብ በመለየት ለመንፈስ አሳብ መወገን በመንፈስ እንድንመላለስ በርን ይከፍትልናል፡፡

2. እንደ ሰው ልማድ የመመላለስ ምርጫ

“ቅናትና ክርክር ስለሚገኝባችሁ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደላችሁምን? እንደ ሰው ልማድስ አትመላለሱምን?” (1ቆሮ. 3፡3)፡፡

ዙሪያችንን እንመለክተው፡፡ በስራና በማሕበራዊ መስኮቻችን የሚገኙ የዚህ አለም ሰዎች ያላቸውን የሕይወት ዘይቤ እናጢነው፡፡ የቅንአቱ፣ የክርክሩ፣ የዘረኝነቱ፣ የክፋቱ … ዘይቤ ከእኛ የተሰወረ አይደለም፡፡ ቃሉ በግለጽ የሚያስተምረን እንደነሱ እንዳንመላለስ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን በእኛም ሳይቀር እነዚህ የሰው ልማዶች ብቅ ሲሉ እናያቸዋለን፡፡ ዛሬ ግን በመንፈስ የመመላለስን ምርጫ መውሰድ እንችላለን፡፡

3. እንደ ጠላት ፈቃድ የመመላለስምርጫ

“በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው” (ኤፌ. 2:1)፡፡

ሐዋርያው ጳውሎስ ከላይ በተጠቀሰው ሃሳብ ላይ ራሱን በመጨመርና እርሱም የዚያ አይነት ሕይወት ተሳታፊ መሆኑን ካመነ በኋላ “ነገርግንበምሕረቱባለጠጋየሆነእግዚአብሔር … በክርስቶስሕያዋንአደረገን” በማለት በጸጋው ጉልበት አዲስ የሕይወት ዘይቤን መምረጡን ይጠቁመናል፡፡ እዚህም ጋር ምርጫው የእኛ ነው፡፡ ክፉው ሹክ እንዳይለንና ወደ ክፉ እንዳይመራን የመንፈስን መንገድ የመምረጥ ጸጋው ተሰጥቶናል፡፡

የሚቀጥለው ትምህርት፡ “ሰማያዊ የውጊያ ዘይቤ”

Dr. Eyob

20 last posts shown.