ሳሙኤል አለሙ-Samuel alemu


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ሌላ መገኛዬ...
facebook.com/samialemu

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


ልፃፍሽ ወይ ግጥም?

አንቺ ውብ በራሪ፡
አንቺ ትንግርት ሀሳብ
አፈር ላይ በልቤ፡ ወድቄ ከምሳብ
ከኔ ዘንድ የመጣሽ
አንች ሀሳብ ምረጪ፡
ምንድን ይሁን እጣሽ?

ንገሪኝ...ልፃፍሽ?
ልግለጥሽ በግጥም?
ወይ ልቤ ደብቄሽ፡ ውበትሽን ላጣጥም?
ወይስ እንዳላየ፡ ልተውሽ በእንጥልጥል?
ከኔ የላቀ ሊቅ፡ ዐይኖቹን እስኪጥል
ያ'ፈር ላይ ኑሮዬን፡ አርፌ ልቀጥል?

አንቺ ውብ በራሪ
ክንፋም ተወርዋሪ
ሀሳብ ተናገሪ
ምን ላርግሽ? ወስኚ
መልክሽን ገጥሜው የኔ ብትሰኚ
የብርሃን ክንፍሽ፡ በቃል ይታሰራል
ልትሆኝ የነበረ፡
እጣ ፈንታሽ ሁሉ፡ ግጥም ሆኖ ይቀራል

ረቂቅ ነውና፡ የሀሳብ ፍጥረቱ
ፊደል ሲወስነው፡ በጠባብ ደረቱ
ውብ ቢሆን መናኛ፡ ድንቅም ቢሆን ከንቱ
እንዳከሳሰቱ፡ የሚያሳሳ የታል?
ያሰቡት ድንቅ ሁሉ፡ ሲፅፉት ይሞታል።

አንች ሀሳብ ያሰብኩሽ
ንገሪኝ ምን ላርግሽ?
ላኑርሽ? ሳልገጥም?
ታምርሽን በልቤ ፡ሰውሬ ላጣጥም
አውጥቼ አውርጄ፡ ላስብ ላብሰልስልሽ
በህልም በሰመመን፡ በምናብ ላድንቅሽ
ዝም ብዬ ላልቅስሽ? ዝም ብዬ ልሳቅሽ?
የሌቴን መከራ ፡ የቀኔን አበሳ
አስታወሼሽ ልርሳ?
አልል ልቤ ሳሳ
ስኖር የኖርኩብሽ፡ ስሞት ብትሞቺሳ?

አንች ሀሳብ ያሰብኩሽ
ንገሪኝ ልተውሽ? ጉጉቴን ገትቼ
ውበት ትንግርትሽን፡ ለሚገባው ትቼ
ስትበሪ አቅርቅሬ፡ ትቢያውን ቃርሜ
ሚስጥርሽን ባዕድ፡ ውበትሽን እርሜ
ላድርግ ልፀየፈው?
የሆንሽውን ሁሉ፡ የሆነ እስኪፅፈው
አንች ሀሳብ ክንፍሽን፡ ተስቤ ልለፈው... ?

ንገሪኝ? ሀሳቤ
ከግጥም ከልቤ
ወይ ደሞ ከመተው
ከየቱ ስልቻ፡ እጣሽን ልክተተው?
የት ላርግሽ ንገሪኝ፡ እኔ ልክ አላውቅም
መጠየቅ ብቻ ነው፡ የፀሐፊ አቅም።

#rediet_assefa

@Samuelalemuu


የገጠር ትልቅ ድስት ይባላል ሰታቴ!

(በእውቀቱ ስዩም)

ያኔ የዩንቨርስቲ ተማሪ እያለን አንድ ክልስ ጓደኛ ነበረን፤ ቶማስ ይባላል፤ አባቱ ጣልያን ሲሆን እናቱ ደግሞ ኢትዮጵያዊት ናት፤ ጠጉሩ የበቆሎ እሸት መነሳነስ ይመስላል፤ በክልስነቱ የሚሰነዘርበት አሉታዊ አስተያየት ምቾት አይሰጠውም ነበር፤አንድ ቀን፥ የአድዋ በአልን ለማክበር በተዘጋጀ ተውኔት ላይ እንደ ጀኔራል ባልዴሴራ ሆኖ እንዲጫወት ሲጠየቅ በጣም ተናደደ “ ሲጀመር የምታስቡትን ያክል ፈረንጅ አልመስልም! ብመስል እንኳ፥ ያንን በስባሳ ጄኔራል ሆኘ አልጫወትም! ከፈለጋችሁ ያጤ ምኒልክ አማካሪ የነበረውን ስዊዘርላንዳዊ ኢልግን ሆኘ መተወን እችላለሁ” ብሎ መለሰ:
:
ተውኔቱን የጻፈው እና ምኒልክን እና ባልቻን ደርቦ የሚጫወተው ተኮላ ግን ገገመ፤

“ እሺ ጄኔራል ባልዴሴራን ሆኖ መተወን ከደበረህ የጣልያኑን ንጉስ ኡምበርቶን ሆነህ ተጫወትልን ”

ቶማስ ንዴቱን መቆጣጠር አልቻለም ፤

“ እናትህን ንጉስ ኡምበርቶ ይርዳልህ! ሲጀመር አንተ የኡጋንዳውን ፕሬዚዳንት ኢዲ አሚንን ዳዳን እንጂ ምኒልክን አትመስልም! እኔ ንጉስ ኡምበርቶን ሆኘ የምተውነው አንተ የንጉሱን ዙፋን ሆነህ ከተጫወትክ ነው” በማለት አንባረቀ ፤


ቶማስ ብዙ ጊዜ ከጣልያን ጋር ግኑኝነት ያላቸውን ቃሎችን ላለመጠቀም ይጠነቀቃል፤ ለምሳሌ ማኪያቶ ላለማለት፥ ካፌ ገብቶ “እስቲ የቡና እና የወተት ብርዝ አምጡልኝ “ ብሎ ያዝዛል፤ “ጓንት” የሚለውን ቃል አይጠቀምም፤ “የእጅ ፓንት “ የሚለውን ቃል ይመርጣል፤

በግጥም ምሽት ላይ የሚያቀርባቸው ግጥሞች ባብዛኛው ለኢትዮጵያዊነቱ አጽንኦት የሚሰጡ ነበሩ፤

‘የገጠር ትልቅ ድስት ይባላል “ሰታቴ”
ጥርጥር የለኝም በኢትዮጵያዊነቴ”

የሚለው ስንኙ አይረሳኝም፤

የሆነ ጊዜ ላይ ሰይጣን ልጁን ሲድር ፥ ለሰርጉ ድምቀት ግቢያችን ውስጥ የብሄር ግጭት አስነሳ! የተወሰኑ ተማሪዎች በሁለት ብሄሮች ተቧድነው መሸካሸክ ጀመሩ፤ የዚህች ወግ ጸሀፊን ጨምሮ ብዙ ተማሪዎች ዶርማቸውን ቆልፈው መሸጉ፤ አመሻሽ ላይ ቶማስ ግጭቱ በርዷል ብሎ በመገት ወደ ካፌ እየተራመደ እያለ ፌሮና ድንጋይ የታጠቁ ጥቂት ተማሪዎች ወደሱ ሲሮጡ ተመለከተ፤ ባልበላ ጉልበቱ ትንሽ እንደሮጠ ስቴድየሙ አካባቢ ደረሱበት፤

ቶማስ እጁን ወገቡ ላይ አድርጎ ባጭር ባጭሩ እየተነፈሰ እንዲህ አለ፤

“ ወንድሞቼ ! እኔ ብሄር የለኝም ! እልል ያልሁ ጣልያን ነኝ ! እኔን በመደብደብ ኢትዮጵያን ከአውሮፓ ህብረት ጋር ደም እንዳታቃቧት"


@Samuelalemuu


እንኳን ለአድዋ የድል በአል በሰላም አደረሳቹ🇪🇹🔥💪

@Samuelalemuu


እዚህ ባልሆን
በዚህ ሰአት
ምናልባትም እንዲህ ባልሆን፣
ልሆን የምችለው
እሆነው የነበር የሆነ ሰው ይኖር ይሆን?

ትልቅ ምናልባት ነው
ማለቴ ምናልባት
መለኪያ ባልጨብጥ
አረቂ ባልጠጣ መለኪያውን ባልሰብር፣
የሆነች ቆንጆ ጋር
ጭማቂ እየጠጣሁ
እጇን እየዳበስኩ
አይንአይኗን እያየሁ ሊሆን ይችል ነበር።

ትልቅ ምናልባት ነው
ግን ከዚህ የሚሻል የሆነ 'እኔ' አይጠፋም፣
የሰውን ማንነት 'መሆኑ' አይገልፀውም።

ትልቅ ምናልባት ነው፣
ምናልባት ምናልባት
ሌላ ነበርሽ አሁን
የሆነ ቀን ለታ አንችን ባትሆኚ፣
የዛኑ ቀን ወጥተሽ እኔን ባታገኚ፣
ከህይወት ታሪክሽ ይቺ ቅንጣት ብትቀር፣
የያዝሽው ሲጃራ እጣን ይሆን ነበር፣

ትልቅ ምናልባት ነው...

[ FB; vector de morta ]



@Samuelalemu


ልብ ያልላልኩት )

አረግሽኝ እንጂ
የከውኑ የአለሙ አዲስ እንግዳ
ጀባሽኝ እንጂ
ሩጬ ማልሸሸው ማኣት ዱብዳ

አፍዝዞ ያደናገረኝ
አክላቁን ውሉን የሳትኩት
ድሮንስ ይሄን አልነበር
ደግሜ ደግሜ የኖርኩት

ሁሉንም አውቃቸዋለሁ
አኳኳን አከራረመሙን
ሰው ከሰው ይሰማል እንጂ
መለያ መጠሪያ ስሙን

መራቅሽ ያንሰፈሰፈኝ
ናፍቆትሽ ያንገበገበኝ
የማጀት የእልፍኜን ዝቆ
ለራቤ እስኪመግበኝ

አላውቅም የራሴ እንደሆን
ይህ ሁሉ የኔ እንደነበር
በልክሽ አቁሜ ስኖር
በሩሄ በጅስሜ ማገር

ቃላባይ ልብሽን አይቶ
መሄድሽ ጠልቆ ነገርኝ
ለነገ መንገድ ሚሆን
ብዙ ስንቅ እንደነበረኝ

[ አዲብ ]



@Samuelalemuu


ጀምበር ገባች ፥ መሸ
ያጸዳሁት ቤቴም ፥ መልሶ ቆሸሸ
አልጠፋም መብራቱ
አልተበላም 'ራቱ
አሁንም ክፍት ነው በርና መስኮቱ ።
ለቁር ተጋለጠ ፥ ጓዳዬ እንደ ውጪው
መቼ ነው የምትመጪው ?

መጽሐፍ ገለጥኩና መልሼ ዘጋሁት
ልጽፍ አሰብኩና ብዕሬን ወረወርኩት
መቆም መንጎራደድ
መቆም መንጎራደድ
መቆዘም መተከዝ ፥ በሐሳብ መሰደድ
ደርሶ ብንን ብንን
ደሞ ቁጭ ብድግ
ካንቺ ውጭ አላውቅም ምን እንደምፈልግ ።

ምኞት ነው ያለኝ  ፥ ዝም ብሎ ምኞት
ወይ የማያኖር ፥ ወይ የማያስሞት

ትመጫለሽ እያልኩ በጉጉት ከምኖር
ምናለ በሞትኩኝ ለአንድ ለስድስት ወር ።

By Hab Hd

@Samuelalemuu


.            ተንበርክኮ መድረስ
           ተጎንብሶ መንገስ
        አቀርቅሮ  ሹመት
   አሽቀንጥሮ ድሎት
                 ጸሎት

እስኪበሩ ማንከስ
   እስኪስቁ ማልቀስ
      እስኪይዙ ማጣት
           እስኪረቱ ችሎት
                             ጸሎት

By Rediet Aseffa


@Samuelalemuu



ስለሚገባው ፣ ሰው የማይገባው
በጽሑፍ አልቅስ ፣ ሆዱን አባባው።
“ንገረኝ” ሳይል የሰበረህን
“የት ጋ ነው?” ሳይል ስብራትህን
ያንተ ወጌሻ ፣ ስለሚያክምህ …
ግጥም ጻፍለት
ሥዕል ሳልለት ፣ ጸሎት ሲደክምህ🖤

[ Henok B ]


@Samuelalemuu


'የአባቴን ባድማ ፈሪ ገብቶ አረሰው
የጀግናውን ሽመል ሞኝ ተንተራሰው፣
እንዲያ እንዲያ ቢሆን ነው ሀገር የሚያለቅሰው።'
ትለኛለህ ምነው ?!
ልጅህ ደርሶ ሳለ አባባ የሚልህ
ልጅህ ደርሶ ሳለ ጀግናዬ የሚልህ
አንተም ወደ ትላንት ነገር ማንጠልጠልህ።

ያው እንደምታየው አሁን አንተና እኔ
አልፈጠረብንም አንዳች ሀሞት ወኔ!
የተረፈን አቅም የያዝነው ቁምነገር ፣
"ወዴት ልትሄድ ነው?!" ማለት ነው ይች አገር ።

[ አስካል ]


@Samuelalemuu


ይኸው ደሞ ክረምት ሆነ
ትዝታ ከደጅ አደረ፤
የአምናን መዝሙር
በአሁን አቅም
በክራሩ ደረደረ።

ናፈቀ አዲስ መስከረም፤
ተመኘ ፍካት ልጅነት፤
በመጸው ልብ በፅጌ ወር፤
የዐደይ እንቁ መሸመት።

ቢጫ ዕንቁ፣
የማር ሰፈፍ፣
ህቱም ጸጋ፤

የአበባ ልብ፣
ምዑዝ ጠረን፣
ነይ በዝናም፤
ነይ ክረምቱን፤
ስለ ወቅትሽ፤
ስለ ወቅቴ ፤
በሙላህ ሆነን
እናውጋ።

ነይ ሐምሌን ክረሚ፤
ነይ ጳጉሜን ታገሺ፤
የመጠበቅ ልክ፤
የመክረምን አቅም፤
ከዘመን ተዋሺ።

የወንዙን ሙላት ዕይ፤
ማለፊያ ፍለጋ የከፋፈተውን
የአፈር ገላ ለይ።

ቅመሺው አየሩን፤
ቀዝቃዛውን ንፋስ፤
ቀላል እንዳይመስልሽ፤
ይሔንን ቁር አልፎ
መስከረም ዜማሽን
ካንቺ ጋ መደነስ።

( ወቅትሽ ላይ መነስነስ....!)
ኹለን ወር አውቃለኹ፤
አንቺ አታውቂም እንጂ፤
ነይ እስኪ ነሐሴ
የደረሰ ተስፋ
የጨለመን ሌሊት፤
ከትዝታ ጋራ
ማሳለፍ ልመጂ።

የአፈር ቀለም ይንካሽ፤
ሰው ሰው
ይሽሽተት ገላሽ፤
ከ ዓመት እስከ ዓመት
እንዳትሰወሪ ...
ግጥም እፅፋለኹ
ቃሌ ነው መታያሽ።

ወንዙን ተከትለሽ
ሂጂ ከባህሩ፤
ያስቀመጥኩት ዕንባ፤
ከዚያ ነው መገኛው
በቀደመ ክብሩ።

ዕንባ ክብር አለው፤
አለው ቅድስና ፤
ይሄንም ቅመሺ
እንደኔ ኹኚና።

ሰው መሆን ቻይበት፤
ታናሽ የመሰለሽ
ይሔ ቤተ አምልኮ፤
መለኮት አለበት።

ማን እንደሆንሽ ዕይ፤
ቃልን ተሸከሚ፤
በእኔ እድሜ ቁመት
ክረምቱን አዝግሚ ።

ነይ ወንጌል ድገሚ፤
ነይ ሃሌ ዘምሪ፤
ቤተ ውበትሽን፤
በጉባኤ ምሪ፤
ነይ ፅጌን ሞሽሪ።

ነይ ከኔ ክረሚ ፤
ነይ ከኔ ክረሚ
ቁሩን አሳልፉሽ
መፀው ላይ አዝግሚ።


[ መንበረ ማርያም ሃይሉ ]


@Samuelalemuu


ከስጋ ጎደልኩ - ነፍሴ በለጠኝ
አቅል ከቀልቤ ከ'ጄ አመለጠኝ
ገና ሳስብህ አቁነጠነጠኝ ።
-
አንዳች ውብ ብርሀን በላዬ አረፈ
ልቤ እንደ ቡራቅ ተወነጨፈ ።
በፍቅርህ ልስከር
ልዙር ልሽከርከር
ሰማዩን ምድሩን ላስስ ልቃኘው
የትም ነውና የምትገኘው !

[ ሃብታሙ ሃደራ ]


@Samuelalemuu


〽️

ትደንሳለች ዛፍ ሥር
ንፉሱ ዳንሷን ያፈጥናል
«መገፋት» እዛ ቦታ ለይ
እንዴት አባቱ ውብሆኗል።
.
እጅ የለው ገሃድ የወጣ
አይታይ በአካል ሲመጣ
ሲነካት እጁን ታውቃለች
ሲደርሳት ትደንሳለች
ደ...ስ..ታ ...እዛ ነው ያለች ።
.
ነፋስ ጋር ጨዋታ ደራ
ዳሌዋ ቀሚሷን ፈራ
ተነሳ ጨርቋ ወደላይ
እሷ ግን አልገደዳትም
አእምሮ ደስታን ባየበት
እብድ ነው...እብድ ነው የትም ።
.
ወገቧን ሰፈረው ነፋስ
ለክቶ ቁጥሯን ገመተ
ከንፈሯን ሳይታይ ስሞ
ሳይገዛ ፍቅር ሸመተ
ደስ ሲል.. መዞሩ ጣማት
(እንደዛ ...እንደዛ መቅረት አማራት ።
.
ስጋዋ ከክር ቀጠነ
ለነፍሷ ትንሽ ወገነ
ሐሳቧ ባንድ ላይ ሾረ
አያውቀው ሳህን አንስቶ
አያውቀው ደስታ ሰፈረ
እፍ አለች ...እፍ እንደ ቅጠል
ዞረችው የመሬትን ገጽ
አርያም ደረሰ ልቧ
ሳትበር ከላይ ቤት መድረስ
ይህ ነበር...ይህ ነበር ግቧ ።
.
እዛው ናት እጇን ዘርግታ
ምድር ላይ በሐሳብ ጠፍታ
ቀሚሷ ቬሎን አስንቆ
ተልቆ
ጭኗ ላይ ያለው ንቅሳት
በጣቱ ሲቀሰቅሳት
ቀጥ አለች ፥ተወችው ዳንሷን
መለስ አረገች ቀሚሷን ።
.
ቁጭ አለች ከዛፉ ግርጌ
አሰበች ስለመዞሯ
ገረማት የነፋስ ልፋት...
(ሲያዞራት እሱም መዞሩ
አሁን ነው የገባት ነገሩ።)

[ ድረስ ጋሹ ]

@Samuelalemuu


እዚህ..
ከራስ ቅሌ ጣሪያ ሥር...
እንደሚፈርስ ትልቅ መንደር ፥ ቡልዶዘር እንደዋለበት፥
ወይ ደሞ:
እንደ ሰፊ ድግስ ቤት ፥ ንጉስ ልጁን የዳረበት፥
እዚህ...
የልቤን ዳስ የሞላውን፥
እስክስታና እዬዬውን፥
ፍርስርሱን ድርምስምሱን፥
ጩኸትና ትርምሱን፥

ለመድሁና፡

ሲንኮሻኮሽ አሸልቤ ፥
ተስማምቼ ከቱማታው ፥ ተላምጄ ከድለቃው፥
ዝም! ሲል ነው የምባትት ፥ ፀጥ! ሲል ነው የምነቃው።

#ሚካኤል_ምናሴ

@Samuelalemuu


ከዚህ ወድያ አልወድሽም
(በእውቀቱ ስዩም)

ከዚህ ወድያ አልወድሽም
የለም እወድሻለው ገና
ማፍቀር አጭር ቢሆንም
መርሳት ረጅም ነውና።

 
@Samuelalemuu


ቃላት እንደ መደርደር፤
ተረክ እንደ መሰደር፤
ቀላል አይምሰልሽ፣
ደህና ውሎ ማደር!
.
ዝም እንደማለት. . .
ከምናብ ብቻ እንደ መዶለት፣
በፈሪ ልብ እንደማፈግፈግ፣
ከሞቀ መዳፍ እንደ መለፈግ፣
መዳከር፣መመንመን፣
መከስመን፣መጠውለግ፣
ቀላል አይምሰልሽ. . .
የነፍስን ቦታ በአንድ ዕድሜ መፈለግ!
.
ይኼን ስልሽ. . .
ብረት አልምሰልሽ፣
የማልዝግ፣የማልሰበር፣
የማልነ'ካ፣የማልቆፈር፣
ሰማይ አልምሰልሽ!
ዐውቃለሁ...እመስላለሁ፣
እወድቃለሁ፣እጎዳለሁ፣
እኔም ይከፋኛል፣
መቼም ሰው አይደለሁ?


[ ፈይሠል_አሚን ]


@Samuelalemuu


የሽምብራ እሸት እየጠረጠሩ
አብሮ ወፍ ጥበቃ ማማ ላይ ተሰቅሎ
ካፊያውን በገሳ በአንድ ተጠልሎ
እሳት አቀጣጥሎ፣ በቆሎ ጠባብሶ፣
አየሁ አላየሁም፣ ሰማሁ አልሰማሁም …
በላልቶ አፍ አብሶ፣
ለስልሶ አስፈትሎ፣ የናት ኩታ ለብሶ
ላዋቂ ተልኮ ለልጅ ተጎናብሶ…
ደስ ይላል መስከረም!!!
ባንድ አብሮ ለመክረም…
ደስ ይላል መስከረም!!

ለቅኔ ዘረፋው… ጠፈፍ ሲል ፈፋው
የቆሎ ተማሪ..ያ ተመራማሪ፣
የወላዲት አምላክ የድንግል አዝማሪ፣
ያ ደበሎ ለባሽ… በእግዚትነ ማርያም
እባካችሁ ልባሽ፣ እባካችሁ ቁራሽ፡፡
እያለ ሲለምን ከጥንቅሹ ቅንጥሽ ማሩቴ ባይሰጠው..
አይቀር መደንገጡ አራሽ አባ ወራሽ አገር ያሰለጠው..! …የማይለወጠው!!
በዓይኑ እየመዘነ በልቡ የማይመርጠው፡፡
ገሩ ባላገሩ፣ ያ ባለሞፈሩ፣
ያ ባለዘገሩ፣
በሞቴ ነው ቋንቋው፣ ስሞት ነው ነገሩ!! "
ደስ ይላል መስከረም


[ ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ ]


@Samuelalemuu


ኑሮ ሲጥለን - ገጥሞን እጅ በ'ጅ
አሜንታ ላይቀል - ለምንታም ላይበጅ
ሕይወት እንደ ሰው - መች ትታማለች
ሥጋ ደህና አይደል - ነፍስም ታማለች

ሞት ቆሞ በሩቅ - ሲል እንቁልልጭ
ኩታ ደርቦ - የሚያብለጨልጭ
አዘጋኝ ጠፍቶ - እፍኝ ጠመዡን
ማልቀስ ተረፈን - እያስጎመዡን

ግን ማልቀስ ከንቱ..
እምባውን ይዞ - ስንቱ አነጅቧል?
ይህ ግጥም እንኳ - በእምባ ታጅቧል
ግን መች ተውቧል?

መቼ ተውቧል - የኑሮ ማጀት
በቃ እጣችን ነው - ሕመም ማቆንጀት?
ሳይነጉ መምሸት - ሳያድጉ ማርጀት?
በዘበት ማለፍ - እንደዳከሩ
ክረምቱስ አልፏል - የታል መከሩ?

ባከነች ነፍሴ
ዘጋኝ በዛባት ባይኖሯት እፊያ
ምን አደከማት? - ኩርፊያና ልፊያ!
ነፍሴን ሸክፏት - አካሌን ቋጥሩት
ንብረቱን ይውሰድ - እግዜርን ጥሩት
እግዜርን ጥሩት - እንድታገለው
ነገን ና በሉት - ይምጣ እንድገለው
በቃ አይግደደኝ - ስለሕልሞቼ
ሊገሉን ሲሹ - ላሸንፍ ሞቼ!

ሁሉንም ወድዶ
ሁሉንም አጥቶ
እንዴት ይኮናል?!
እንዲህ ላለው ጣር - እግዜር ልኮናል!
እግዜር ልኮናል - ኩታ እንባ አልብሶ
ሞት ምን ቢከፋ
ያስለቅሰናል ከሕይወት ብሶ?

ብቻ ደክሞናል!
ብቻ አሞናል!
ባንቀምሰው እንኳን - መሞት ጥሞናል!


[ ዮናታን ጌታቸው ]


@Samuelalemuu


የታለሽ ?
የቱጋ ?
ስፈልግሽ ነጋ።

ወዴት ነሽ?
ከምን ስር?
ዘላለም አልማስር።

ወዴት ነሽ?
ንገሪኝ!
እንዳታሳድሪኝ።
...
ታውቂዋለሽ ቤቴን
ጨለማው
ገደሉን
እሾሁን .. ክለሉን፤
..
ሲመሽ ያስተጋባል
ሸለቆ ና ጫካው ፤
አትጃጃይ አሁን
ሳሚኝና ልንካው።

#mikiyas_feyisa

@Samuelalemuu


ሌሎችም ውስጥ...
(ሳሙኤል አለሙ)

መች ኑር ብለሽኝ...
አልኖርም አልኩ፤
መች ሙት ብለሽኝ...
አልሞትም አልኩ፤
በክቡራን'ና ክቡራት
አልታይሽም እየተቀደምኩ።


እንደው...
ታክቶሽ እንጂ ለምስጋናው
ዝለሽ እንጂ ለፍለጋው፤
አታጭኝም ነበር...
ሌሎችም ውስጥ እየተጠጋጋው።


@Samuelalemuu


መንቃት መረገም ነው
(በእውቀቱ ስዩም)

ሰማሽኝ ወይ እቱ!
ለንጀራው ለርስቱ
ፍጥረት ሲተባበር፥
አፍርሼው ተኛሁኝ ፤የቀን ሌቱን ድንበር
ህልም የሚሸጥ ቢሆን ፥ ከብሬልሽ ነበር::


እንዴት እንደዛልሁኝ ፥
በኑሮ እንደታከትሁ
በቅርበት ያላየች ፥
ጸሀይ ያለ ልምዷ ፥ ለመጥለቅ ዘገየች ፥

ልቤን ለንቅልፍ ሰጠሁ
ዓይኔን ለሰመመን
መንቃት መረገም ነው ፤በዚህ በኛ ዘመን ::


@Samuelalemuu

20 last posts shown.