Forward from: ስሜትን በግጥም
በጨዋታቸው መሀል...ሀኑኔ...ወዬ...ብር ባይኖረኝም ታገቢኛለሽ?...ሳቋ ደበዘዘ፤አንገቷን ደፋች። ለጥያቄው ዝምታዋ መልስ ሆነ ግና ዝምታዋ ብዙ ያወራል። ሀሳቡ ተደበላለቀበት፤ ተነስቶ መንገዱን ጀመረ። አልጠራችውም። ቆይ አንዴ ላስረዳህ አላለችውም። የምታስረዳው ነገር እንዳልሆነ ታውቃለችና። ሊወቅሳት አልፈለገም ቤተሰቧ ጋር የምታገኘውን ምቾት እሱ ሊሰጣት አይቻለውምና። ከእናንተ ውስጥ ምቾቱን ለፍቅር ሲል የሰዋ እስቲ ይውቀሳት። ፍቅር የተራበ ሆድን አይሞላም የታረዘ ገላን አያለብስም የተጠማ ጉሮሮን አያርስም። ፍቅር መንፈስ ነው። የማይታይ የማይዳሰስ የማይጨበጥ በምናብ ያለ የሀሴት ምንጭ የመኖር ሚስጥር የተግባቦት ቀመር የመፈላለግ ጥልቀት። እሷ ንግስት ንብ ፈላጊዋ ብዙ በመልክ ብትሻ በስነምግባር ቢያሰኛት ሀብትማ የግሏ እሱ እሱ ግን ተራ ሰራተኛ መኖሩ የማንም ብስራት ያልሆነ ቢሞት ሞቱ የማንም ሀዘን የማይሆን ታዲያ ስለምን እሱ የመጀመሪያ ምርጫዋ ሊሆን ይቻለዋል። በእርግጥ ማንም እንደሱ አይሆንላትም እሱም እንደ ማንም አይሆንላትም። መንገዱን ቀጠለ በጨለማው ሰፈር በጣም በሚያስፈራው። ፀሀይ ከጠለቀች ማንም ዝር ከማይልበት፤ እሱም ከዚ በፊት ያልደፈረው ነገር ግን ዛሬ ምንም ሆነበት። ለካስ የሰው ልጅ ፍረሀት ውስጡ የሚጫረው ተስፋ ሲኖረው ነው፤ የሚወደው ነገር ህይወቱ ውስጥ ሲያገኝ ግና እሱ ያንን ተነጥቋል። ጨለማው ለሱ ምንም ሆኗል። መኖሬ ትርጉም ይሰጣታል ያላት ለፍጡራን ቀሎ ለእሷ የከበደ ማንነቱ ወድሟል። ታዲያ ስለምን መኖሩን ይኑረው? ፍርሀትንስ ይፍራው? ልቡ ለጨለመ የመንገድ ብርሀን ምኑም ነው። የልቤ ብርሀን...እኔነቴን አለመለመችልኝ ያላት...እሷ...ዝም አለች.....
ከበትር የላቀ የማይቀል ከቃል
ለካ ለተረዳው ዝምታም ይሰብራል.... መንገዱን ቋጨው የጨለማውን....ወደ ሌላ ጨለማ....
ቆመሽ እንዳትቀሪ ቆሞ መቅረት ለኔ
ላንቺ ጀምበር ወጥታ ምሽት ይሁን ቀኔ
የሰርግሽ 'ለት ጥሪኝ ተረረም ተረረም
ባላገባሽ እንኳን ላጨብጭብ ግዴለም።
✍ ተፃፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ
ከበትር የላቀ የማይቀል ከቃል
ለካ ለተረዳው ዝምታም ይሰብራል.... መንገዱን ቋጨው የጨለማውን....ወደ ሌላ ጨለማ....
ቆመሽ እንዳትቀሪ ቆሞ መቅረት ለኔ
ላንቺ ጀምበር ወጥታ ምሽት ይሁን ቀኔ
የሰርግሽ 'ለት ጥሪኝ ተረረም ተረረም
ባላገባሽ እንኳን ላጨብጭብ ግዴለም።
✍ ተፃፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ