የሰለፍያ ደዕዋ በቻግኒالدعوة السلفية فى مدينة الشاغنى


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ወደ ቻናሉ👇 ለመቀላቀል 👇ከፈለጉ👇
t.me/selefiyadawabechagni
አስተያየታችሁን 👇ወይም 👇እርማታችሁን👇
t.me/selefiyadawabechagnibot
ይፃፉልን። ይላኩልን።

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


Forward from: Abdul Halim Al Letemiy
ዱኒያ ፈታኝ ናት!

ታላቁ ታቢዒይ ሐሰን አል-በስሪ እንዲህ ይላሉ።


❝ በአሏህ እምላለሁኝ በኒ ኢስራዒሎች ዱኒያ'ን በመውደዳቸው የተነሳ አር-ረሕማን'ን ያመልኩ ከነበረ ቡኃላ ጣዖት ( ወይፈን) አምልከዋል።❞

📚 አዝ-ዙሕድ ሊብኒ አቢ ዱኒያ


t.me/Abdul_halim_ibnu_shayk
t.me/Abdul_halim_ibnu_shayk


Forward from: Abdul Halim Al Letemiy
ሙስሊሞች ሆይ አብሽሩ !
-------------------------------------

ሙስሊሞች ሆይ አብሽሩ! በርዚህ (በረመዷን) ወር ስምንቱም የጀነት በሮች ለናንተ ሲባል ተከፍተዋል። በሙዕሚኖችም ልብ (የረመዷን) ትሩፋቶች ተበትነዋል። የጀሒም በሮች በሙሉ ለናንተ ሲባል ተዘግተዋል። ለእናንተ ሲባል የኢብሊስና የዘሮቹ እግር ተጠፍሮዋል። በርዚህ ወር ከኢብሊስ በቀል ይወሰዳል ። ወንጀለኞችም ከእርሱ እስር ምንም ፋና ሳይተው ይመለጣሉ። በምሽጉ አስገብቶ ስሜቶችን የቀለባቸው ጫጩቶቹ ነበሩ ዛሬ (ረመዷን) ላይ እነዚያን ምሽጎች (መኖሪያዎች) ትተዋቸዋል። የምሽጉን ምሶሶዎችን በተውበትና በኢስቲግፋር መዶሻ ያፈራርሳሉ። ከእስር ቤቱ (አምልጠው) ወደ ኢማንና ተቅዋ ምሽግ ሸሽተዋል። ከእሳትም ቅጣት ድነዋል። (የሸይጧንን) ወገብ በተውሒዷ ቃል (ላ ኢላሀ ኢለሏህ) ሰብረውት አሁን ላይ የስብራቱን ሕመም እያሰሞተ ነው። በሁሉም የፈድል(የኸይራት) አዝመራዎች ያዝናል። በርዚህ ወር (ረመዷን) ግና የሚወርደውን የእዝነት እና የወንጀል መማር ሲመለከት ዋ! ጥፋቴ በማለት ይጣራል። የአር-ረሕማን ሰራዊት ረታ። የሸይጧን ሰራዊት ተረታ። (ለሸይጧን) በኩፋሮች ላይ እንጂ የቀረው ምንም አይነት ስልጣን የለም። የስሜት አገዛዝ ወደቀ። ሱልጣኔቱም ለተቅዋ አገዛዝ ሆነ "አስተውሉም የአእምሮ ባለቤቶች ሆይ!"❞

📚ኢብኑ ረጀብ | ለጣኢፉል መዓሪፍ (325)


🗓 IBNU SHAYKH | ሸዕባን 26/1446

t.me/Abdul_halim_ibnu_shayk
t.me/Abdul_halim_ibnu_shayk
t.me/Abdul_halim_ibnu_shayk


Forward from: Bahiru Teka
✅ የእህታችን መዲና ሞት አሳዛኝ የሚያደርገው ምንድነው ?

ክፍል ሁለት

እህታችን መዲና ህመሟ ወደ ሞት የተሳፈረችበት መጓጓዣ መሆኑን ስታውቅ ከልጆቿ ጋር የነበራትን ሁኔታ ቀየረች ። የመጀመሪያው ጠዋት ወጥቶ ወደ ተቀጠረበት ሱቅ ስለሚሄድ እቤት ብዙ አይገኝም ። ሁለቱ ልጆቿ አንዱ ወንድሞችን አስቸግሬ የአመት እንዲከፈልለት አድርጌ ሁለተኛውን ደግሞ ት/ቤቱን ስላለው ሁኔታ አስረድቼ እንዲቀበሉት አድርጌ እየተማሩ ነው ።
እነዚህ ልጆች ከእናታቸው ውጪ የሚያውቁት የለም ከት/ ቤት ሲመጡና በእረፍት ቀን ካጠገቧ ዞር አይሉዩም ።
እሷ አልጋ ላይ እነርሱ መሬት ላይ ሆነው ይተያያሉ ። እናት ለልጆቹ ተንሰፈሰፈ ሲባል የሷ አቻ የለውም ። የሆነ ሳአት ወጥተው ከተጫወቱ ይታጠቡ ልብስ ይቀየርላቸው ትላለች ። ቢያንስ በቀን ሁለቴ ታጥበው ልብስ ይቀየርላቸዋል ። በሳምንት ሁለቴ ገላቸው ይታጠባል ። ምግባቸው እሷ ሳታየው አይቀርብላቸውም ። የመጨረሻውዎቹ ሁለት ወሮች አካባቢ በልጆቿ ላይ ሁኔታዋን ቀየረች ።
ይህ የሆነው በሞት እንደምትለያቸው ስታውቅ ነበር ። አጠገቧ እንዳይቀመጡ ማድረግ ጀመረች ። ፊት ነሳቻቸው ታመናጭቃቸዋለች ። ይህን የምታደርገው ውስጧ እየተሰቃየ ስለያቸው እንዳይጎዱ ይጥሉኝ በሚል አሳዛኝ ውሳኔ ነው ። ምክንያቱ በማይገባቸውና በማያውቁት ሁኔታ የእናታቸው ሁኔታ የተቀየረባቸው ህፃናቱ ግን መሄጃ የላቸውምና ወደርሷው ነው የሚመለሱት ። ትስቅልን ይሆናል ታቅፈን ይሆናል በሚል ያዩዋታል ይቀርቡዋታል ይጠጉዋታል ። ሁኔታዋ ከእለት እለት እየተባባሰ ሁለመናዋ እየከዳት መጣ ። አይኗን መክፈት ያቅታት ጀመር ምላሷ በምትፈልገው መልኩ ማዘዝ አቃታት ። አጠገቧ ላሉ እህቶች እያቃሰተችና በተራ ተራ ፊደሎችን በትግል እያወጣች ለልጆቼ እናታችሁ አላህ ወስዷታል በሉዋቸው አለቻቸው ። መጨረሻ ላይ አላህ ሆይ ልጆቼን አደራ ብላ ከአላህ በኋላ የልጆቼን አደራ እኔን ለማዳን ለተሯሯጡ እህቶቼና ወንድሞቼ ሰጥቻለሁ ብላ በዱንያ ላይ ላታያቸው ትታቸው ወደ ማይቀረው አገር አኼራ ሄደች ።

ክፍል አንድን ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/bahruteka/5731

https://t.me/bahruteka


Forward from: Bahiru Teka
🔷 የእህታች መዲና ሞት አሳዛኝ የሚያደርገው ምንድነው ?
ክፍል አንድ

እህታችን መዲና ደምሴ ለሞቷ ሰበብ የሆነው የጡት ካንሰር እንደነበር እናውቃለን ። አላህ በሰው ልጆች ላይ የፃፈው ሞት ቅሮት የለውም ። ሳአቱን ጠብቆ ይመጣል ሰበብን ከሰበቡ ባለቤት ጋር እንዲገናኝ ያደረገው አላህ ለማንኛውም ሰው ሞት ሰበብ አድርጎለታል ። የእህታችንም ከዚህ የተለየ አልነበረም ።
ይሁን እንጂ ከሞት ሰበቦች ውስጥ አንዱ ህመም ነው ። የህመሙ አይነት በጣም ቢለያይም ሰዎች በተለያየ መልኩ ህመምተኛውን ከህመሙ እንዲድን ሰበብ ያደርሳሉ ። በሰበቡ እንዲድን አላህ የፈቀደው ይድናል ። አላህ በሰበቡ እንዲድን ያልፈቀደለትና ያ ህመም ለመሞቱ ሰበብ የሚሆነው በዛው ወደ አኼራ ይሄዳል ። ነገር ግን ሰበብ በማድረሱ ቤተሰብና ዘመድ ሰበብ አድርሰናል የአላህ ውሳኔ ነውና ምንም ማድረግ አንችልም ብሎ ይፅናናል ።
በጣም በሚገርም መልኩ ብዙ ቤተሰቦች ከቤተሰባቸው ሞት ይልቅ ሰበብ ባለማድረሳቸው ሁሌም ፀፀት ሆኖባቸው ይኖራሉ ።
ወደ እህታችን መዲና ስንመለስ በሽታዋ ካንሰር መሆኑ ከታወቀ በኋላ የሚቻለው ሁሉ ሰበብ ለማድረስ ሁሉም ተረባርቧል ። ቅስም የሚሰብረውና ውስጥን የሚያደማው ግን እህታችን የጡቷ ህመም ሲጀምራት ለመታየት ሐኪም ቤት ለመሄድ አቅም ማጣቷ ነው ።
እራሳቸውም ከህይወት ጋር ትግል ውስጥ ካሉት ወንድሞቿ አንዱን ጡቴን እያመመኝ ነው ሐኪም ቤት ለመታየት ትንሽ ሳንቲም ፈልግልኝ ብትለውም ወንድሟ ሊያገኝላት ባለመቻሉ ሳትታይ ትቀራለች ። የጡቷ ህመም ግን ስር እየሰደደ አቅሙን እያዳበረ ነበር ። አደጋው እያወቀችውና እየፈራችውም ግን ለማን ትንገር እህቶቿን ማስቸገር አልፈለገችም ከህመሟ ጋር ግብግብ ቀጥላ ቀናቶች ለሳምንታት ሳምንታት ለወራቶች ቦታ እየለቀቁ ህመሟ ከአቅሟ በላይ ሲሆን ለአንድ እህቷ ትናገራለች ። እህት ደንግጣና ፈርታ ወደ ሀኪም ቤት ይዛት ትሄዳለች ስትመረመር የፈራችው አልቀረም በጣም ዘገያችሁ ወደ ካንሰርነት ተቀይራል ተባሉ ። የዚህን ጊዜ ነበር ጉዳዩ ወደኛ የደረሰው እንደምታውቁት ብዙ እህትና ወንድሞች ርብርብ አድርገው የሚቻለው ሁሉ ህክምና ተደርጎላት ነበር ። መጀመሪያ ሐኪም ቤት ለመሄድ 500 ብር ያጣችው እህታችንን ህይወት ለመታደግ እስከ 800, 000 ወጥቷል ።
እህታችን መዲና አላህ በጀነት የምታርፍ ያድርጋት እንጂ ህይወቷ በፈተና የተሞላ ነበር ። ባለትዳርና የሶስት ልጆች እናት የነበረችው መዲና የትዳር አጓርዋ የሳንቲም ድህነት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ነገር ነበር ማለት ይቻላል ። ብዙ ወንድሞች የተለያየ ከሸክም እስከ ሊስትሮ ከዘበኝነት እስከ ፅዳት ሰራተኝነት አነስተኛ ስራ እየሰሩ ቤተሰባቸውን ያስተዳድራሉ ። ይህ የሀላፊነት መሰማት ውጤት ነው ሀላፊነት የማይሰማው የሆነ አካል ችግር ሲመጣ ጥሎ ይጠፋል ። የመዲናም ባለቤት ከእነዚህ አንዱ ነበር ። በካንሰር ተይዛ ከካንሰሩ በላይ የልጆቿ ረሃብ በሽታ ሆኖ የሚያሰቃያትን ባለቤቱን ለመርዳት ከመጣር ይልቅ ጥሎ መሸሽ ነበር የመረጠው ። እናቱ ኬሞ ስትጀምር የሰውነቷ ፀጉር ሲረግፍ ያየው የመጀመሪያ ልጇ የ9 ጠኛ ክፍል ትምህርቱን ትቶ የእናቱን ሸክም ለመቀነስና ለማሳከም ሲል ሰው ቤት ተቀጠረ ። ‼
ይሁን እንጂ ይህ ውሳኔ በእናቱ ላይ ሌላ ሸክምና ህመም የሚጨምር ነበር ። ልጇ ከእድሜው በላይ ጫና ውስጥ ገብቶ ትምህርቱን ማቋረጡ ሌላ ህመም ሆነባት ። ህመሟ በወንድሞችና እህቶች እርዳታ ህክምና ጀምራ በተለይ ከውጭ ሀገር ይምጣ የተባለው መርፌ ከጀመረች በኋላ ተስፋ ሰጪ ሁኔታ ላይ የነበረ ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ ግን ሁኔታው አስከፊ መሆን ጀመረ ። ሁለቱ ልጆቿ እድሜያቸው ገና ሲሆን ሶስተኛው አምስት አመቱ አካባቢ ነው ። እነርሱን እያየች ስታለቅሰ አጠገቧ እየተቀመጠ ጡትሽ ስለተቆረጠ ነው ወይ የምታለቅሺው አይዞሽ ይበቅላል ይላታል ። የእነዚህ ልጆቿ ሁኔታ ፊት ለፊቷ እያዘገመ እየመጣ ካለው ሞት የበለጠ እንደውጋት ቀስፎ እየያዛት በአካልና የውስጥ ህመም ውስጥ ሆነች ። ከቀናት በፊት ባለቤቴ ልትጠይቃት ሄዳ ሳለች በእንባዋ ትራሷ ርሶ አየች ምን ብላ ልታፅናናት እንደምትችል ግራ ገብቷት እያለ ትንሹ ልጇ እናቴ አትሙችብኝ ብሎ ያቅፋታል ። ከብዙ መረባበሽ በኋላ አላህዬ ያንተን ውሰኔ እቀበላለሁ ግን ለእነዚህ ልጄቼ ብኖር ደስ ይለኝ ነበር ብላ የበለጠ ተረብሻ ባለቤቴም የሚያፅናናት ሲያስፈልጋት ትታ ወጣች ።

https://t.me/bahruteka


Forward from: Bahiru Teka
🔷  የረመዳን ወር መግባቱ የሚታወቀው በጨረቃ ነው ።

   እስልምና የየአንዳንዱ ዒባዳ መመሪያ መለያ ያደረገለት ሲሆን ማንም በመሻርና በማፅደቅ እጁን ማስገባት የማይችልበት ከየትኛውም እምነት ለየት የሚያደርገው በመሎኮታዊ ድንጋጌዎች የተገደበ ነው ::
   ከእነዚህ መመሪያዎች አንዱ የረመዳን ወር መግባትና መውጣት ( ማለቅ ) የሚታወቀው በጨረቃ መታየት መሆኑ ነው ::
    አላህ በተከበረው ቃሉ ይህን አስመልክቶ እንዲህ ይላል :–

" فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ الشَّهْرَ فَلْيَصُمْهُ ……"
                   البقرة  ( 185)
" ከእናንተም ወሩን ያገኘ ሰው ይጹመው "፡፡

    የረመዳን ወር መግባቱ የሚታወቀው ጨረቃ በመታየቱ መሆኑን የአላህ መልእክተኛ መናገራቸውን አስመልክቶ ዐብዱላሂ ኢብኑ ዑመር የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል ይላል : –

    وعن ابن عمر – رضي الله عنهما – قال:  أن رسول الله – صلى الله عليه وسلم – قال
" إذا رأيتموه ( هلال رمضان )  فصوموا،  وإذا رأيتموه ( هلال شوال ) فأفطروا،  فإن غم عليكم فاقدروا له "

          أخرجه الإمام البخاري 
  
      " ( የረመዳን ወር ጨረቃን ) ባያችሁት ጊዜ ፁሙ,  ( የሸዋልን ወር ጨረቃ ) ባያችሁት ጊዜ አፍጥሩ,  ከተሸፈነባችሁ ወስኑለት ( የሻዕባንን ወር 30 ቀን ሙሉ) "

     የረመዳን ወር መግባቱ አንድ ታማኝ የሆነ ሰው ጨረቃን አይቻለሁ ብሎ ከመሰከረ ረመዳን የሚያዝ ይሆናል ።
     ይህም የአላህ መልእክተኛ - ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም - አብዱላሂ ኢብኑ ዑመር  - ረዲየላሁ ዐንሁማ - ጨረቃ ማየቱንን ነግሯዋቸው ፆም እንዲያዝ ማዘዛቸው የሚያመላክት ሲሆን  በሌላም ጊዜ አንድ የገጠር ሰው ማየቱን ነግሯቸው አዘዋል ::
    ማለቁ ደግሞ ሁለት ሰው መመስከር አለበት የአላህ መልእክተኛ ሁለት ሰው ከመሰከረ ፁሙ አፍጥሩም ብለዋል መግባቱ ከዚህ የወጣው ቅድም ባልነው የኢብኑ ዑመርና የገጠሩ ሰው ምስክርነት ነው ። በመሆኑም ሙስሊሞች ፆማቸውን የሚዙትም ሆነ የሚፈቱት ጨረቃ ሲታይ ነው ::
   ምናልባት ደመና ሆኖ ጨረቃ ማየት ካልተቻለ ሻዕባንን 30 ቀን መሙላት እና ረመዳን አንድ ብሎ መጀመር ነው :: ሌላው አንድ ሀገር ላይ ጨረቃ ከታየ ሌላው ሀገር መፆም ግድ ይለዋል ወይ ? የሚለው ነው ።
   ለዚህ ከዑለሞች የተሰጠው መልስ ሀገሮቹ የተቀራረቡና የጨረቃ መውጫቸው ተመሳሳይ ከሆነ አንድ ላይ መፆም አለባቸው የተራራቁና የጨረቃ መውጫቸው ( መጣሊዓቸው ) የማይገናኙ ሀገሮች የራሳቸውን እይታ ይከተላሉ የሚል ነው ::
       በአንድ ሀገር ጨረቃ ከታየ የጨረቃ መውጫ መስመራቸው የተቀራረበና አንድ የሆኑ ሀገሮች መፆም ይኖርባቸዋል ። ከላይ እንዳልነው የረመዳን ወር ጨረቃ መግባቱ አንድ ታማኝ ( ዐድል) የሆነ ሰው ከተናገረ የሚመለከታቸው አካላት ምስክርነቱን ተቀብለው ፆም እንዲጀመር ማድረግ ይኖርባቸዋል ። ይህ ብይን ዐድል በሚለው መስፈርት እንጂ ከዚህ አገር ከሆነ በሚል ስላልሆነ የጨረቃ መውጫ መስመራቸው በሚገናኙ ሀገራት ውስጥ የትም ቢታይ ሊሰራበት ይገባል ።
     ጨረቃ ያየ ሰው ምስክርነቱ ተቀባይነት ባያገኝ ምን ያደርጋል በሚለው ነጥብ ዑለሞች የተለያየ እይታ አላቸው ።

አንደኛ – ብቻውንም ቢሆን መፆም አለበት ሸዋልም ካየ ከጀማዓ እንዳይለይ በድብቅ ማፍጠር አለበት ።
      ይህ የኢማሙ ሻፍዕይና የኢብኑ ሐዝም እይታ ሲሆን ኢማሙ አሕመድም ቀውል አላቸው ።

ሁለተኛ – ረመዳንን ይፁም ማፍጠሩ ግን ከሰዎች ጋር መሆን አለበት ።
      የአቡ ሐኒፋና ኢማሙ ማሊክ እይታ ሲሆን ኢማሙ አሕመድም ቀውል አላቸው ።

ሶስተኛ – በእይታው መስራት የለበትም ። ከሰዎች ጋር ፆሞ ከሰዎች ጋር ማፍጠር አለበት ።
    አንደኛው የኢማሙ አሕመድ ቀውል ሲሆን ሸይኹል ኢስላም ይህን መርጧል ።

http://t.me/bahruteka


Forward from: Abu abdurahman
نعوذ بالله من سوء الأخلاق


Forward from: Abu abdurahman
فضيلة الشيخ! ما نصيحتك لمن هم على أبواب التخرج من الجامعة؟

نصيحتي لهم: أولًا: أن يشكروا الله عز وجل، أن أوصلهم إلى هذا المستوى.
ثانيًا: أن يجتهدوا في نشر العلم الذي ألهمهم الله إياه في كل مناسبة.
ثالثًا: أن يكونوا قدوة في الأخلاق ومعاملة الناس لأن بعض طلاب العلم الآن أجفى من الأعراب، لا عنده بشاشة ولا تسليم ولا تواضع، بل بعض الناس كلما ازداد علمًا يزداد كبرًا والعياذ بالله، والعالم حقًا هو الذي إذا ازداد علمًا ازداد تواضعًا

https://t.me/abuabdurahmen


Forward from: قناة الشيخ الدكتور حسين بن محمد
‏صورة من حسين عبد الله


Forward from: قناة الشيخ الدكتور حسين بن محمد
‏صورة من حسين عبد الله


Forward from: Muhammed Mekonn
የኛን ምን ልትል ነው ⁉️

.የምንተኛበት አልጋ ኪስራና ቀይሰር ከሸለሉበት ዙፋናቸው በላይ ምቾት አለው።

. መጓጓዣችን እነዚያ አምባገነኖች ከፎከሩባቸው ፈረሶችና ግመሎች በመቶዎች እጥፍ የተሻሉና ምቾት ያላቸው ናቸው።

. የባንክ አካውንታችን የሚስጥር ቁጡር ብዙዎቹ ይሸከሙት የነበረውን የቃሩንን የካዝና መክፈቻ የሚያስንቅ ስራ የቀለለበትና አስተማማኝ ነው።

. ከእኛ ውስጥ አንድ ልብስ ብቻ ያለው ሰው ቢፈለግ በተአምር አይገኝም። ከሰሓቦች ውስጥ ግና ... "ለሁላችሁ ሁለት ልብስ ኣለችሁ እንዴ?" በማለት ነበር መልዕክተኛውﷺ የጠየቁት።


" ሰይፋቸው በትኬሻቸው አዝለው፤ በአንድ ጨርቅ ተጠቅልለው ፤ ጥቂት ቴምሮችን በልተው ውኃ እየጠጡ ፤ በአሏህ መንገድ ይታገሉ በነበሩት ላይ ነው "ስለድሎታችሁ ትጠየቃላቹ" የሚለው አንቀጽ የወረደው። እኛ ጋር ካለው ሲነጻጸር የጀነት ሪዝቃችንን እየበላ ነው የሚመስለው።


Forward from: Abu abdurahman
~ በሚዲያ ወይስ በቤት

በቤቱ ውስጥ ሚስቱ የትዳርን ጠዓም አጥታ እየኖረች በየሚዲያው እየወጡ ስለ ሁብ (ፍቅር) የሚሰብኩ ሰዎች ጉራ በጣም ይገርመኛል !

ውጭ ላይ የምንዘረውን ሁብ (ፍቅር) እቤታችን ውስጥ መኖር ብንችል እርግጠኛ ነኝ ምርጦቹ ነን ።

https://t.me/abuabdurahmen


Forward from: Abu abdurahman
**

~ ሰዎችን በገንዘቡ እና በምግቡ ባያግዝ በፊቱ ፈገግታ እና በመልካም ስነምግባሩ ያግዛቸው !

ኢብራሂም ኢብኑ አድሀም ረሂመሁሏህ እንዲህ ይላል -:

( من لم يواس الناس بماله وطعامه وشرابه فليواسهم ببسط الوجه والخلق الحسن )

ሰዎችን በገንዘቡ እና በምግቡ በመጠጡ ባያግዝ በፊቱ ፈገግታ እና በመልካም ስነምግባሩ ያግዛቸው ።

____
ሂልየቱ አል አውሊያዕ ❪٤٨٩/٨❫

አልሃፊዝ ኢብን ረጀብ ረሂመሁሏህ እንዲህ ይላል ፦

( وربما كان معاملة الناس بالقول الحسن أحب إليهم من إطعام الطعام والإحسان بإعطاء المال ، كما قال لقمان لابنه : يا بني لتكن كلمتك طيبة ووجهك منبسطاً ، تكن أحب إلى الناس ممن يعطيهم الذهب والفضة )

"አንዳንዴ ሰዎችን በመልካም ንግግር መኗኗር ወደነሱ ምግብን ከመስጠት እና ገንዘብን ከመስጠት በላይ ይወደዳል ሉቅማን አልሀኪም ለልጁ እንዳለው _ልጄ ሆይ ንግግርህ ቆንጆ ይሁን ፊትህ ፈገግ ይበል ወደ ሰዎች ብርና ወርቅ ከሚሰጣቸው አካሎች በላይ የተወደድክ ትሆናልህ "
__
ጅሙዑረሳዒል ❪١٠٠/١❫

- والمرء بالأخلاق يسمو ذكره *.وبها يفضل في الورى ويوقر .

👉በመልካም ስነምግባር ዙሪያ አውርቶ ከማለፍ ብዙዎቻችን የተፈተንበት ነገር ነው አሏህ ለመልካሙ ስነምግባር ይግጠመን ።

join #telegram ቻናል
https://t.me/abuabdurahmen
https://t.me/abuabdurahmen


Forward from: Bahiru Teka
የማይታመን የሰለፍያ ማእበል

ክፍል ሁለት

ምስራቅ ሐረርጌ የፈነዳው የሰለፍያ ምንጭ በአላህ ፈቃድ ለብዙዎች ሂዳያ ሰበብ ሳይሆን አይቀርም ። በሚገርም መልኩ በምስራቁ ክፍል ለተፈጠረው አስገራሚ ክስተት ፈር ቀዳጁ ታላቁ ሸይኽ ሸይኽ አሕመድ ወተሬ ናቸው ። ስለ ሰለፍያ ተጠይቀው ሲመልሱ የሰለፎችን መንገድ መከተል ትክክለኛ እስልምናን መከተል ነው ። ሰለፍይ ነኝ ማለትና ወደ ሰለፍያ ራስን ማስጠጋት ቢዳዓ አይደለም ። ይላሉ ኦሮምኛ የምትሰሙ በሚቀጥለው ሊን ገብታችሁ ንግግራቸውን አዳምጡ : –
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://drive.google.com/file/d/1919_wod5cov7M0GszgR0_8egghV2T6Dw/view?usp=drivesdk

ሌላኛው የሸይኻቸውን ፈለግ በመከተል የኢኽዋንን ማንነት በመግለፅ የሰለፍያ ዳዕዋ ሐቅ መሆኑና ሰለፍዮችም ሐቅ ላይ መሆናቸውን ሰለፍዮችን የሚጠሉት የሐሰኑል በና ፣ የሰይድ ቁጥብና የቀርዳዊ ተከታይ ኢኽዋኖች ናቸው ካሉ በኋላ እኛ ከሰላሳ በላይ የዑለማእ ምክር ቤት አባላት አሉን የመጅሊሱን ምክር ቤት አንፈልግም የሚሉት ሸይኽ ጀማል ዐብዱላሂ ሐሰን የ4ተኛ መስጂድ ኢማምና ኸጢብ እንዲሁም አስተማሪ ናቸው ። በሚቀጥሉት ሊንኮች ገብታችሁ አዳምጡዋቸው :–
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️

https://drive.google.com/file/d/193IF9URvl7izrNqiWz5jChAWA-HtHFHn/view?usp=drivesdk

https://drive.google.com/file/d/1C6TzzVn-q5XEK0ZcBwYcEkUBf91zBJWK/view?usp=drivesdk

ሌላኛው ደግሞ ሸይኽ ሙሐመድ አሕመድ ጭሮ ይባላሉ ። እሳቸውም እኔ መሻኢኾቹ የተናገሩትን እንጂ አዲስ ነገር የለኝም ። ዛሬ ሐቁ በዑለሞች ተነገረ ሰማችሁ ። ታዲያ የሰማችሁትን ሐቅ አትከተሉም ወይ ሲሉ ህዝቡ እንከተላለን ብሎ ይመልሳል በሚቀጥለው ሊንክ ገብታችሁ ስሙት : –
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://drive.google.com/file/d/198Hz_SI8SgKQcEYJ6QnN8SoK0ldNpbbt/view?usp=drivesdk

አራተኛው ከሸይኽ አሕመድ ወተሬ ተማሪዮች ዋነኛው የሆነው ሸይኽ ኢልያስ ሲሆን ባለፈው በመጅሊሶች ድንፋታ ብዙ ማስፈራሪያ ከደረሰባቸው ውስጥ የነበረ ነው ። ዛሬ ሰለፍያን የምትጠሉ በቁጭታችሁ ሙቱ በማለት የሰለፍያ ዳዕዋ ባንዲራ ከፍ ብሎ እየተውለበለበ መሆኑን እያበሰረ ነው ።
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️

https://drive.google.com/file/d/199Oo4H4FlarJTY0skObcB8fQH-VyHPfI/view?usp=drivesdk

https://t.me/bahruteka


Forward from: Bahiru Teka
✅ ኢብኑል ቀይም የተባለው ታላቁ ዓሊም – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላል : –

" ፆም አላህን ለሚፈሩ ሉጋም ነው ። ( ፍላጎትን) ለሚዋጉ ጋሻ ነው ። ለደጋጎችናወደ አላህ ለቀረቡት ( የእርካታ) እንቅስቃሴ ነው ። እሱ ከሌላው ስራ በተለየ ለአላህ ነው ። "

https://t.me/bahruteka


Forward from: Bahiru Teka
✅ የማይታመን የሰለፍያ ማእበል
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯

🔎 ክፍል አንድ

👉 ሐቅ የተዳፈነ እሳት ነው ንፋስ አግኝቶ የተቀጣጠለ ቀን ባጠለልን ወሬ ነጋሪ እንዳይኖር አድሮጎ ይፈጀዋል። ባጢል የፈለገ ቢገን ገናናነቱ ሐቅ እስኪደርስበት ነው። ሲደርስበት የገባበት ይጠፋል አንገቱን ይደፋል የውርደት ካባ ይከናነባል

የሱፍይ የኢኽዋንና ሙመዪዓ ጥምር የባጢል ሀይል እያቅራራና እየፎከረ በኢኽዋን መሪነት ሐቅን ለመቅበርና የሐቅ ባልተቤቶችን ለማንበርከክ መንግስት ነን እኛ ያልፈቀድንለት መኖር አይችልም እስከማለት ደርሶ በቀረርቶና ሽለላ እንደ እንቦሳ በማናለብኝነት ሲፈነጥዝ ብዙዎችን አስፈርቶ ነበር።

➩ በተቃራኒው የሐቅ ሰዎች እንደ ብረት ሙሶሶ ረግጠው ቆሞው ከቁርኣንና ሐዲስ መርህ ያፈነገጡ ሸሪዓ ደንጋጊዎች ነን የሚሉ የመጅሊስ አመራሮች አይወክሉንም ያሉት ሰለፍዮች ዛሬ ተአምር እያዩ ነው። እናንተ የተቋም መሪ እንጂ የሀገር መሪ አይደላችሁም። መመሪያችሁም የተቋም መመሪያ እንጂ የሀገሪቱ ዜጎች የሚተዳደሩበት መመሪያ አይደለም። እንደ ሀገር ሁሉንም የሚመለከት የዜጎችን የእምነት ነፃነት ያወጀ ህገመንግስት አለ በመሆኑም መብታችን ሊከበር ይገባል። በናንተ የጭቆናና የአምባገነን መመሪያ አንተዳደርም ብለው በመፅናት ከዳር እስከዳር ሲታገሉ የሐቅ ብርሃን አድማሱን እያሰፋ ደቡብ፣ ምእራብ፣ ሰሜን ላይ ጮራውን እየፈነጠቀ የነበረው ሰለፍያ ምስራቁን ክፍል በማይታመን ሁኔታ ባጢልን እያናወጠውና እያሳደደው ነው።

➜ የፌዴራሉ መጅሊስ መሪ ፕሬዝዳንት ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ከወራት በፊት ምስራቅ ሐረርጌ አመራሮቹን አስከትሎ በመሄድ ሁሉም ዑለሞችና ኢማሞች እንዲሁም ኡስታዞች በግድ እንዲገኙ በማድረግ እኛ ያልፈቀድንለት አይኖርም። ዝም ስንል የተኛን መሰላችሁ እንደ ውሀ ነን ውሀ ዝም ብሎ የተነሳ ቀን ይበላል። እኛም ዝም ስንል ያላወቅን እንዳይመስላችሁ እናጠፋችኋለን። ኬት የመጣ ሰለፍይ ነው? ሰለፍይ አይደለም ሰለኽይ ነው። እያለ እያላገጠና እያሸማቀቀ ፎክሮ ከተመለሰ ከጥቂት ወራት በኋላ ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆኖ የማይታመን ክስተት ተከሰተ። ዝም ብለው የነበሩት ዑለሞች በቃ አሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ሐቅ መሰከሩ። ኢኽዋኖቹ የዘመናችን ቡኻሪይ ሲሉዋቸው የነበሩት የእድሜ ባለፀጋው አንጋፋው ሸይኽ አሕመድ ወተሬ ሰለፍያ ሐቅ ነው አሉ።
አላሁ አክበር !!!
አላሁ አክበር !!!
አላሁ አክበር !!!


♻️ ሸይኽ አሕመድን የማያውቅ ምስራቅ ሐረርጌያዊ የለም። በዙህዳቸውና በዒልማቸው የሚታወቁት የእድሜ ባለፀጋው ሸይኽ አሕመድ ኢኽዋኖች ጃኬታቸውን የሚሰቅሉባቸው የኛ የሚሏቸው ነበሩ

🔎 እኚሁ ታላቅ ዓሊም ከሳቸው ስር የወጡ በርካታ ዑለሞችንና መሻኢኾን ይዘው ኢኽዋንን በቃ አሉት። እኛ ሰለፍዮች ነን የመጅሊስ አመራሮች አይወክሉንም ዑለሞች አሉን መመሪያችን ቁርኣንና ሐዲስ በሶሓቦች ግንዛቤ ነው። የናንተን የሰው ሰራሽ መመሪያ አንፈልግም በቃን አሉ። ኢኽዋንና ግብረ አበሮቹ ምድር ዞረባቸው። ስልጣንም ገንዘብም ምንም ማድረግ እንደማይችል አምነው ለመቀበል ተገደዱ። በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል መንገድ በሚያጨናንቁ የሰለፍዮች ፕሮግራሞች ናላቸው የዞረው የመጅሊስ አመራዞች ምስራቅ ሐረርጌ ላይ በተፈጠረው ነገር እግራቸው ራሳቸውን መሸከም ያቃተው ይመስላል። በአላህ ፈቃድ የመሻኢኾቹን የአቋም መግለጫ በሚቀጥለው ክፍል የማቀርብላችሁ ይሆናል። ሁላችሁም ለእነዚህ መሻኢኾች ረዥም እድሜ ከመልካም ፍፃሜ ጋር ለምኑላቸው እላለሁ።

https://t.me/bahruteka


Forward from: Abu abdurahman
▪️فليقل خيرا او ليصمت

قال رَسُولُ اللّٰه ﷺ:

من كان يؤمن بالله واليوم الآخر فليقل خيرًا أو ليصمت

📚رواه البخاري (٦٤٧٥)، ومسلم (٤٧)

وعن جابر بن سمرة رضي الله عنه
ان رَسُولُ اللّٰه ﷺ

كان طويلَ الصمتِ ، قليلَ الضَّحِكِ .

📚صحيح الجامع (٤٨٢٢)


Forward from: Muhammed Mekonn
ሰዎቹ ለይቶላቸዋል።
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
ሲፈልጉ በአንድ መድረክ ለሙሐደራ ገጭ ይላሉ ሲፈልጉ ተቋሞቻቸውን ይጎበኛሉ።

✅ ከላይ እንደምትመለከቱት ነሲሃዎች አፍሪካ ቲቪን ጎብኝተዋል። ሙመይዓዎች እና ኢኽዋኖች ፍቅራቸውን እያጣጣሙ ነው። እነሱ አምነውበት ትክክለኛ ነው ብለው በመሞገት እየሰሩ ነው። ለመስለሃ ነው እያለ ኡዙር ፍለጋ የሚኳትነው ሰው በጣም ይገርማል።

➘➘➘➘➘
«የሰለፍያ ደዕዋ አንዱ መታወቂያ ተመይዩዝ ነው፣ የዐቂዳ ልዩነት ካላቸው አፍራሽ ሃይሎች ጋር አለመጋፋት። እራስን ችሎ መቆም። መለየት። ዐቂደቱል በራእ ከካፊር ጋር ብቻ አይደለም፣ በኢስላም ስም ከሚንቀሳቀሱ የጥመት አንጃዎችም ጭምር እንጂ።

ባይሆን ሚዛን ትጠብቃለህ። ማለትም ከነሱ አንፃር የሚኖርህ አቋም ባለባቸው ጥፋት ልክ ይሆናል ማለት ነው። እንጂ ሚዛን ትጠብቃለህ ማለት ትላንት ከነበረህ አቋም ትንሸራተታለህ፣ ትላንት ስታወግዛቸው የነበሩ አካላትን ከጥፋታቸው ሳይመለሱ ታደንቃለህ ማለት አይደለም። ሚዛን ትጠብቃለህ ማለት መሰረታዊ የአህሉ ሱንና አቋሞችን ለድርድር ታቀርባለህ ማለት አይደለም።»
➶ እያሉ ሲፅፉ የነበሩት የአሁኖቹ እንባ ጠባቂዎች የት ሄዱ!?

«ተመይዩዝ ተራው ሙስሊም ዘንድ በአህሉ ሱንና እና በቢድዐ አንጃዎች መካከል ያለው ልዩነት በግልፅ እንዲታይ ያደርጋል። አብሮ መጓዝ ሲኖር ግን የአቋም ልዩነቶችንም፣ ጤነኛና በሽተኛ አካሎችንም መለየት አይቻልም። ይሄ ከባድ አደጋ ነው።»
➶ ሲል የነበረው ኢብኑ ሙነወር ምን ዋጠው?

«ለምሳሌ ከኢኽዋኖች ጋር ብትሰለፍ ሙስሊሙን በጅምላ የሚያከፍረው፣ ሶሐባ የሚያብጠለጥለው፣ የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን የሚያስተባብለውን ሰይድ ቁጥብ ሲያወድሱ ያንተም አቋም ተደርጎ እንዲታሰብ ያደርጋል።»
➶ ይህንን ሐቅ ምን አደረጉት?

🏝
https://t.me/AbuImranAselefy/9938


Forward from: Muhammed Mekonn
.
አዲስ ልዩ የኮርስ ፕርግራም
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯👌


🏝 በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ሰለፍዮች ጀመዓ የተዘጋጀ የኮርስ ፕሮግራም ሲሆን በአሏህ ፍቃድ ዛሬ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ ባለው ወቅት የሚጀመር ይሆናል ባልነው መሰረት አሁን ተጀምሯል።

🔍 عنوان : "مجمل أحكام الصيام"

🔎 ርዕስ፦ «ጥቅል የፆም ፍርዶች»



        ጀ
                  መ
                              ረ



🏝   ➘➴➘    ✅ ⬇️⬇️⬇️⬇️
https://t.me/WRU_Selefy_Students?videochat=45f7f93f0d7f8efdae

የኪታቡን pdf ለሚፈልግ
https://t.me/WRU_Selefy_Students/22149


Forward from: አቡ ያሲር ዩሱፍ አስሰለፊይ
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
📍ሐቅ አሸናፊ ነው

🎙ኡስታዝ ባህሩ ተካ
(አቡ ዑበይዳህ) ሐፊዘሁላህ

🔸 ውዱ ኡስታዝ በጣፋጭ አንደበት ምርጥ ምክር። አላህ የሐቅ ባለቤትና ለሐቅ ተከራካሪ ጠበቃ ያድርገን። ሁላችንንም በሐቅ ላይ ያፅናን።
📌 ተጨማሪ ትምህርቶችን ለማግኘት👇
https://t.me/ensenoanasmesjid/11481
https://t.me/YusufAsselafy
https://t.me/YusufAsselafy


Forward from: Abu abdurahman
መጥፎ ግምት እናሰድርበት ነበር

عن ابن عمر رضي الله عنهما أنه قال:

”كنا إذا فقدنا الرجل في الفجر والعشاء أسأنا به الظن“.

« አንድን ሰውዬ በፈጅር ወይም በዒሻዕ ሰላት ስናጣው መጥፎ ግምትን እናሳድርበት ነበር »

📓 التمهيد لابن عبد البر (19/4)

https://t.me/abuabdurahmen

20 last posts shown.