☦🎤ለቀዳስያን እና ለቆራቢያን 🎤☦
ነገ ጠዋት ቢያንስ እስከ 3 ሰዓት ድረስ1 መመገብ
👉 መመገብ ማለት ሥጋ ወተት እንቁላል .... ወዘተ ሳይሆን የጾም ምግቦችን መመገብ!
ለምን ቢሉ ጾም ነውና!👉 ከባህርያችን ጋር የሚስማሙ ምግቦችን መመገብ ! ይህም ማለት የማይስማማን ምግብ ካለ አለመመገብ በተለይ ጨጓራ የሚያመው ሰው ጥንቃቄ ያረግ ዘንድ ይገባል!
ለምን ቢሉ ጾም ከተጀመረ በኋላ የማስመለስ 🤮የማቅለሽለሽ🤢 የህመም ስሜት እንዳይፈጠር ! 2 መታጠብ
👉 ንጽሕናን መጠበቅ ተገቢ ነው እና ሰውነታችንን መታጠብ አለብን!
እየጾምን ብንታጠብ ምን ችግር አለው?
በአፌ እስከ አልገባ ድረስ የሚሉ አሉ ! ግን ይሄ ፍጹም ስህተት ነው! ሰውነታችን
ክፍት ነው ስለዚህ ከመታጠብ ልንቆጠብ ይገባል!
🚨
ማስጠንቀቂያ ለዲያቆናት 🚨
ቀዳስያን 18 ሰዓት መጾም እንዳለባቸው ተነጋግረናል! ተረኞች የሆናችሁ ግዴታ መጾም አለባችሁ! ያልሆናችሁም ብትጾሙ እና ብትቆርቡ እጅጉን ይመከራል! ልብ በሉ ያልጾማችሁ ዲያቆናት ምን አልባት ድምጻዊ ተብላችሁ ወይም ጎበዝ ቀዳሽ ተብላችሁ ድንገት ቅዳሴ ግቡ ልትባሉ ትችላላችሁ! አልጾምኩም ብትሉ እንኳን ምን ችግር አለው ምናምን ሊሏችሁ ይችላሉ ! ወይም ከብጹዓን ጳጳሳት ጋር የምትግባቡ ከሆነ ድንገት ግቡ ልትባሉ ትችላላችሁ! ሼም ይዟችሁ እንዳትገቡ! አደራ ! አደራ! አደራ! እንደዚህ አይነት ነገር የሚያሳስባችሁ ከሆነ ነገ ጹሙ! ካልሆነ ግን አደራ እንዳትገቡ! አጉል ተርዕዮ 📸 (ልታይ ልታይ) ፈልጋችሁ! እሳት ውስጥ እንዳትገቡ አደራ አደራ አደራ!
💧🌹✅
መልካም በዓል ✅🌹💧
ይቆየን!
@Bkudeaconሃሳብ አስተያየት ጥያቄ👇
@Bkudeaconbot