ይሉኝታ ባይኖረህ ህይወትህን እንዴት ትኖራት ነበር?
“Care about what other people think and you will always be their prisoner.” – Lao Tzu
ሌሎች ስለኔ ምን ያስባሉ እያልክ የምትጨነቅ ከሆነ ያለምንም ጥያቄ እስረኛ ነህ። የአይምሮ ባርነት በባለቤቱ ካልሆነ በቀር በማንም ነጻ አውጪ ነኝ ባይ ነጻ የማይወጣ ከባድ ባርነት ነው። እርግጥ ነው ፈጽሞ ስለሰው ሳይጨነቁ መኖር እጅግ የሚከብድ ነገር ነው። ነገር ግን የባርነቱን ጥብቀት ግን መለወጥ ይቻላል። ሰዎች እንደመሆናችን መጠን በሌሎች ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘትና ለመወደድ ስንል ብዙሃኑ የሚወዱትን ነገር እናደርጋለን። የነፍሳችንን ጩኸት አፍነን፤ የሌሎችን ምርጫ እውን ለማድረግ እንጥራለን። በዚህ ማህል የራሳችንን ደስታ መስዋት እናደርጋለን።
ሰዎች ስለኛ ያላቸውን አመለካከት ለማስተካከል ያልሆንነውን እየሆንን፤ የማንፈልገውን እያደርግን ህይወታችንን በይሉኝታ የታጠረች ጠባብ መንገድ እናደርጋታለን። እውነት ግን ስለሌሎች ግድ ባይኖረን ህይወታችን ምን አይነት መልክ ይይዝ ነበር? ደስታችን እስከየት ይደርስ ነበር? ነጻነታችን ምን ያህል ጥልቅ ይሆን ነበር? ከምንም በላይ ምን ያህል የህይወት ልምድ ይኖረን ይሆን። ስህተትን እና ውድቀትን የምንሸሸው እኮ እራሳችንን ፈርተን አይደለም። ሌሎች በውድቀታችንና በስህተታችን የሚኖራቸውን አስተያየት በመፍራት እንጂ። እኛ ብቻ የምናውቀው ስህተት እና ውድቀትማ ምን ያስፈራናል? ነገር ግን ሌሎች ምን ይሉኛል በማለት ውድቀትን እና ስህተትን እየሸሸን አዲስ ነገር ከማየት ተቆጥበናል።
የሚከተሉት ነጥቦች ከይሉኝታ ተላቀን የነጻነት ኑሮን እንድንኖር የሚረዱ ነጥቦች ናቸው።
ሁሉንም ማስደሰት አይቻልም- መቼም አንድ ሰውን ብቻ አውቀን ህይወታችንን አንገፋም። በተለያዩ የህይወት አጋጣሚዎች ብዙ ሰዎችን እናገኛለን። ሁሉም ታዲያ ህይወትን የሚያዩበት የተለያየ የህይወት መነጽር አላቸው። ሁሉም አንተን ሲመለከቱ በግላቸው የህይወት መነጽር ነው። አንተ ላይ እንከን የሚሉትም ሆነ የሚያደንቁልህ ነገር ከራሳቸው እምነት፤ እውቀትና የኑሮ ልምድ በመነሳት ነው። እናም ኑሮዋቸውን እንደሚያዩበት መነጽር በተገቢ ሁኔታ እንድትታያቸው ይፈልጋሉ። ለሁሉም ሰው መልካም ሆኖ መታየት ከባድ ነው፤ በአጭሩ ሁሉንም ማስደሰት አይቻልም። ስለዚህ የራስህን ኑሮ ኑር፤ የምታደርገው ነገር አንተን እስካስደሰተህ ድረስና የህሊና ሰላም እስከሰጠህ ድረስ ትክክል ነው።ይሉኝታ ከአላማህ ያደናቅፍሃል-እውነት አላማ ካለህ በእርግጠኝነት የአላማህ እንቅፋት የሚሆኑ ሰዎችን መራቅህ አይቀርም። ምናልባት የቅርብ ጓደኞችህ ወይም የቤተሰብ አባል ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ሰዎች የአላማ እንቅፋት የሚሆኑት ሆን ብለው አይደለም። እኛ የምናየውን ነገር ማየት ስለትሳናቸው ብቻ ነው። በእኛ መነጽር ሳሩ ስለታየን ወደፊት እንጋልባለን፤ እነሱ ግን ሳሩ ስለማይታያቸው ሊያስቆሙን ይጥራሉ። አንዳንዴ አላማችን የእውነት ከሆነ ሌሎች ስለኛ ምን ይላሉ ሳንል ወደፊት መገስገሱ ያዋጣናል።
ስህተት እና ትክክለኛነት በእያንዳንዱ ሰው ዘንድ የተለያየ ትርጉም አላቸው-በጥንታውያን ግሪኮች ታሪክ ሶቅራጠስ አስተሳሰቡ በዘመኑ ከበሩ ሰዎች የላቀ ስለነበር፤ እውቀቱ እንደስህተት ተቆጥሮ ለሞት በቃ። የሶቅራጠስ አስተሳሰብ ስህተት ሆኖ ሳይሆን፤ በዘመኑ የነበሩ ሰዎች መረዳት ስላቃታቸው ብቻ አወገዙት። ይኸው የሶቅራጠስ አስተሳሰብ ዘመን ተሻግሮ እኛም ጋር ደርሷል። ስለዚህ ሌሎች ሰዎች ለምን አመለካከቴን እና አስተሳሰቤን አልተቀበሉትም ብለህ አትጨነቅ፤ ምክንያቱም ሁሉም እውነትን የሚመዝነው ባለው የአይምሮ ስፋት እና ጥበት መጠን ነው።
በመጨረሻ ሰዎች እንደምንታስበው ስለአንተ አያስቡም- እውነት ነው! ለምሳሌ ያልታጠበና የተጨማደደ ሸሚዝ ለብሰህ ወደቢሮ ሄድክ እንበል። ሰዎች በተንሾካሾኩ እና በተሳሳቁ ቁጥር ባንተ ሸሚዝ የሚሳለቁ ይመስልህና ቀኑን ሙሉ ስትጨነቅ ትውላለህ።በመንገድ ስታልፍ ሌሎች “ቆሻሻ” የሚል ቃል ሲናገሩ ከሰማህ ስላንተ የሸሚዝ ቆሻሻ የሚያወሩ ይመስልሃል። ይህ “ሌሎች ስለኔ ምን ይላሉ” የሚለው ጥያቄ እያሯሯጠህ ቀንህን የፈተና ያደርገዋል። እውነታው ግን ምናልባት ሰዎቹ ምን አይነት ሸሚዝ እንደለበስክ ላያስተውሉ ይችላሉ።
ደግሞም ያንተ ህይወት ያንተ ብቻ ናት በአንተ ደግነት ሌላው አይጸድቅም ባንተ ሃጥያት ሌላው አይኮነንም
@sewmehoneth