“ ድግግሞሹ ቀንሷል፤ እንደድሮው አይደለም። ግን የነበረውን ጥንቃቄ አጠናክሮ መቀጠል ነው ” - አታላይ አየለ (ፕ/ር)
ከዚህ ቀደም ካጋጠሙ ክስተቶች አንጻር በከፍተኛ ሬክተር ስኬል የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ከመተሃራ በቅርበት ላይ አርብ ሌሊቱን ተከስቶ ነበር።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ አርብ ሌሊት መተሃራ አካባቢ 6.0 ሬክተር ስኬል የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን በተመለከተ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉን ተመራማሪ ጠይቋል።
በዩኒቨርሲቲው የመሬት መንቀጥበጥ ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ አታላይ አየለ (ፕ/ር)፣ በሰጡት ምላሽ፣ “ አዎ። ልክ ነው ተፈጥሯል። ሌሊት 5 ሰዓት ከ28 ደቂቃ ገደማ ከምሽቱ ” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
“ ነገር ግን ሰው አልሰማውም እንደድሮው ” ሲሉ አክለው፣ “ እንደዚያ የሆነበት ምክንያት ደግሞ ከመሬት ወለል በታች ጥልቅ ስለሆነ ነው እንጂ እንደዛ ባይሆን ኑሮ በጣም ብዙ ጉድ ይሆን ነበር ” ብለዋል።
የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 6.0 የተመዘገበ ነው መባሉ ልክ ነው ? ስልን ላቀረብንላቸው ጥያቄ፣ “ እውነት ነው ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ይህ የሚያመላክተው ስኬሉ እየጨመረ እንደመጣ ነው፤ ሰሞኑን ትንሽ ቆም ሲል ጠፋ የሚል ተስፋ ተሰንቆ ነበር፤ አሁንም እንቅስቃሴው አለ ማለት ነው ? የሚል ተጨማሪ ጥያቄም ለተመራማሪው አቆርበናል።
“ እንደዛ ሆነ ማለት ይቀንሳል ማለት አይደለም። እየቀጠለ ነው ያለው ነገርየው። ሙሉ ለሙሉ ቆመ፣ ሞተ ለማለት አያስደፍርም። እንቅስቃሴው እንዳለ ነው ” ብለዋል።
“ ከመስከረም ጀምሮ እስካሁን አቅም በፈቀደ ሁሉም ሰው ጥንቃቄ እንዲያደርግ ለማድረግ እየተሞከረ ነው። አሁንም ያው ከመሬት ወለል በታች ጥልቅ መሆኑ ነው የበጀን ” ሲሉ ተናግረዋል።