🇦🇿 የኮፕ29 ጉባኤ ደሃ ሀገራት የዓለም ሙቀት መጨመርን መከላከል የሚያሰችላቸውን የ300 ቢልዮን ዶላር ዓመታዊ ፋይናንስ አፀደቀ
200 የሚደርሱ ሀገራት፤ ደሃ ሀገራት የዓለም ሙቀት መጨመርን መከላከል እንዲችሉ በዓመት 300 ቢልዮን ዶላር መመደበቻውን፤ በአዘርባጃን ዋና ከተማ ባኩ የተዘጋጀው የ2024ቱ የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ኮንፈረንስ (COP-29) ሊቀመንበር ሙክታር ባባዬቭ በጉባኤው የመጨረሻ ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።
📄 አዲሱ የአየር ንብረት ለውጥ የጋራ ፋይናንስ መጠን፤ የዓለም ሙቀት መጨመርን በቅድመ-ኢንዱስትሪ ደረጃ 1.5 ዲግሪ ሴልሺየስ ለመገደብ የሚደረገውን ጥረት ይደግፋል። በተጨማሪም፤ ከፍተኛ ብክለት ያካሄዱ የበለጸጉ ሀገራት፤ የደሃ ሀገራትን ወጪ እንዲሸፍኑ በስምምነቱ እንደተካተተ ተገልጿል።
አዲሱ የአየር ንብረት ለውጥ የጋራ ፋይናንስ መጠን፤ ያደጉ ሀገራት ለታዳጊ ሀገራት በዓመት 100 ቢልዮን ዶላር ለማቅረብ በ2009 ገብተውት የነበረውን ቃል ይተካል።
"የባኩ ፋይናንስ ግብ ልንደርስ የምንችለው የተሻለ ስምምነትን ይወክላል፤ ለጋሽ ሀገራት ላይ በተቻለ መጠን ጫና አሳድረናል። ዓለም አቀፍ የፋይናንስ አርክቴክቸርን ቀይረናል እንዲሁም 1.5 ዲግሪ ሴልሺየስን ለማሳካት ትልቅ እርምጃ ወስደናል። የሚቀጥሉት ዓመታት ቀላል አይሆኑም። ሳይንስ የሚያሳየው ፈተናዎቹ እየጨመሩ እንደሚመጡ ነው። አብረን የመስራት አቅማችን ይፈተናል። የባኩ ስኬት የሚመጣውን ፈተና እንድንቋቋም ያስችለናል" ሲሉ ባባዬቭ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ
📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡-
👉 APK ፋይል ሊንክ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉@sputnik_ethiopia