ቢያስፈራም(ሱመያ ሱልጣን)
ፋጢማ ቢንት አል ኸጧብ እስልምናን ከነባሏ ስትቀበል የሚደርስባት ስቃይ አልተረሳትም ። ከ ሁሉም ከ ሁሉም ደግሞ ከ ዑመር
የዚያ የ አሸራ ሙበሸራ፣ የዛ ጀግና ደረቱ ለ ኢስላም ለመወጋትን የማያመነታው ባሏ፣ ዑመር ላይ ሲሆን እንኳን ለሚስቱ ሊመክት የራሱን አንገት ከዑመር መዳፎች ማስጣሉን ይጠራጠራል። ለምን? ዑመር ነዋ! ሃቢቡና ዲነል ኢስላምን በሱ ወይ በ አባ ጀህል ይነስር ዘንድ ዱዓ ያደረጉ እና በ ዑመር የጸደቀላቸው!!
እናናናና... ሚስጥራቸው ተደብቆ ሊቆይ አልተቻለውም። ሰማላቸውና ከኋላው የቁርአን ንባብ ድምጽ የሚሰማበትን የቤታቸው በር እስኪያቃስት ድረስ ደብድቦ አስከፈተ። አይኑ እያየ እህቱ "ላት" እና "ዑዛን'' ትታ አላህን ልታመልክ?! እኮ የ ዑመር ሩህ ከ ጀሰዱ ሳትለቅ? እንዴት ተደርጎ?! ይህ ለመቀበል የሚከብድ የርሱ ቁስል ነበር።
ከዛስ ባሏን ከመሬቱ አንጥፎ፣ እርሷን ከ አፍንጫዋ አንስሮ ፣"ዘራፍ" አለ!
አልበቃውም! "ስታነበንቡ የነበረውን አምጪ!" ሲላት ያው ንዴቱ ጣራ እንደነካ ነበር። ከዛስ? አፍንጫዋን ደም ያለበሰው የወንድሟ ጡጫ ከሚያሳምማት በላይ በሺርክ የተጨማለቀ እጁ ቁርኣንን ነክቶ ሊያረክስባት መሆኑ ከበደባት እና "አይሆንም!" አለችው። የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም አይደል! ያ ሸይጧን እሱን ሲያይ መንገድ የሚቀይረውን ዑመርን "ያለ ውዱዕ አላስነካህም!" አለችው። "ታጠብ!'' ማለቷ እኮ አልነበረም ችግሩ። " ንጹህ አይደለህም!" መባሉ ነው እንጂ። እናማ እስቲ "እኔን አፏን ሞልታ ቀና ብላ ልትናገረኝ የ ልብ ልብ የሰጣትን ጉድማ ላንብበው።" አለ። ልቡ በ ኢማን ሊሞላ የ ሱራ ጧሃ 1ገጽን ንባብ ያህል ጊዜ አልወሰደበትም። ከዛስ? እሳቸውን ሊገድል የዛተባቸው ነብይ "ዑመርን የጠላ እኔን ጠላ! እሱን የወደደ እኔን ወደደ" ብለው መሰከሩለት።
እና ለማለት የፈለግኩት በ ፋጢማ ቤት ከተፈጠረ የ ደቂቃዎች ትርምስ በላይ "የሰማ ቀን ይገድለናል" የሚል የከረመ ሰቀቀን ነበረበት። እናና አንዳንድ ውሳኔዎች መጀመሪያቸው ፍርሃት፣ መሃላቸው ሰቀቀን መጨረሻቸው ስቃይ ሊኖረው ይችላል። ግን እሱ! እሱ ውሳኔ የህይወትን ሙሉ ይዘት በሰኪና ይተካዋል። ለዛም ይመስለኛል "እናንተ ብቻ ለመቀየር ወስኑ እንጂ እኔ ከናንተ(በሚደርስባችሁ ነገሮች ከምትታገሱት)ጋር ነኝ ብሎ { إِنَّ ٱللَّهَ مَعَ ٱلصَّـٰبِرِینَ } ታጋሾችን የሚያበሽረው።
ከዛስ?{ إِنَّ مَعَ ٱلۡعُسۡرِ یُسۡرࣰا }"ከችግርም ጋር በርግጥ ምቾት አለ" ብሎ ያበረታው። { إِنَّ ٱللَّهَ لَا یُخۡلِفُ ٱلۡمِیعَادَ }አላህ እኮ በርግጥ ቃሉን በጭራሽ አያብልም/አያፈርስም" ብሎ ስለ ቀጣዩ ምቾታችሁ ያረጋገጠው።
እናማ ለውጥ ቢያስፈራም የማንሸሽበት፣ ለውጣችን ኢስቲቃማ ያለው የሚሆንበት ረመዷን ይሁንልን!
@sumeyasu@sumeyaabot