አምስቱ የአማራ ግዛቶች፤
አንድም አምስትም፡
አምስትም አንድም
አማራ በመካከለኛው ዘመን የነበረው ይዞታ በአሁኑ ሰአት የለም፡፡ ቀደም ብሎ
እንደተጠቀሰው አማራው በኦሮሞ ተጨፍጭፎ፣ የተረፈውም ህዝብ ማንነቱ ተለውጦ
አማራ-ኦሮሞ ሆኖ ይገኛል፡፡ አማራው በታሪክ የኖረበትም ምድር ተኮርምሞ ተኮርምሞ
የፍየል ግንባር የምታክል መሬት ቀርታዋለች፡፡ እሷንም ለመሰልቀጥ የትግሬና የኦሮሞ አውዳሚ ብሄረተኞች ሲያፋሽጉ ይውላሉ፣ ያድራሉ፡፡ ከዚህች ከቀረችውም ምን ያህል
እንደሚቦጭቁ የየራሳቸውን ካርታ ሲስሉ ያድራሉ፡፡ በዚህ ፈተና ውስጥ ሆኖም እንግዲህ
አማራ አንድነቱን ጠብቆ ይገኛል፡፡ እስካሁን ባየነው ሀተታ መሰረትም አንድ ህዝብነቱን
በዘመናት ወጀብ ሁሉ ይዞ ይገኛል፡፡ ይህ ህዝብ በአራት ከፍላተ ሀገራት ገቢራዊ-መሬታዊ
ግዛቶች (Actual territory) እና በአምስተኛ ሀሳባዊ-ታሪካዊ ግዛት (Potential and
imaginary territories) ውስጥ ይገኛል፡፡ አምስተኛው ሀሳባዊ ግዛት ማለትም
ኢትዮጵያ ውስጥ የአማራው ነባር ይዞታዎች በነበሩት፤ ነገር ግን አሁን በተወረሩት
መሬቶች ተበታትኖ እና በመላው ዓለም ተበትኖ የሚኖረውን ህዝብ ያጠቃልላል፡፡ አማራ
በአራት ገቢራዊ ግዛቶች እና በአምስተኛው ሀሳባዊ ግዛት ተበትኖ ቢኖርም ቅሉ አስደናቂ
አንድነት ያለው ህዝብ ነው፡፡ ለዚህም ነው አማራ አምስትም አንድም፡ አንድ አምስትም
ነው ለማለት የቻልነው፡፡ ይህንን አረዳድ ይዘን እስኪ የአማራውን ውስጣዊ አንድነት
ምንጭ እያጣቀስን እንመልከት፡፡
የአቢሲኒያ ቤት አሰራር በጣም ቀላል እና በሁሉም መደቦች እኩል የሆኑ
ናቸው፤ ወደ ሰሜን በድንጋይ፡ በሸዋ ደግሞ በእንጨት ከመሰራታቸው በቀር 368 በሚለው
የቡላቶቪች ምልክታ የአማራን ውስጣዊ ብሄራዊ አንድነት እንመለከታለን፡፡ በሰሜን
አማራ አካባቢ ውድሞ፣ ደርብና ምድር ወይም በዘመኑ አጠራር underground,
ground and upstairs (towers) የተባሉ የቤት አሰራር ክፍሎች ነበሩ፡፡ ይሄ አይነት
አሰራር ድንጋይ እንደልብ በሚገኝባቸው አካባቢዎች ይዘወተር የነበረ ነው፡፡ ይህ ህዝብ
በዚህ በቤት አሰራር ብቻ ሳይሆን በሁለንተናዊ አኗኗሩ ረገድ አንድ ወጥ ማንነት ያለው
ህዝብ ነው፡፡
አማራ ከጥንት ከሞላ ጎደል ከበባዊ በሆነ ምድር የሚኖር ህዝብ ነበር፡፡
በኋለኛው ዘመናት በወራሪነት የገቡ ህዝቦች መሬቱን ሳይወስዱበት የነበረው መሬታዊ
ቅርጽ ከበባዊ (Compact) ነበር፡፡ ዳር ዳር አካባቢ ከሚገኙ ቆላማ የአየር ንብረቶቹ
በቀር የምድር ገነት የሚባል አይነት ቦታ ላይ ሰፍሮ የኖረና የሚኖር ህዝብ ነው፡፡ በድሮው
ጊዜ በተለያዩ ምክንያቶች ከቦታ ቦታ ሲዘዋወር የኖረ ከብሄርነት አልፎ ዘመድ የሆነ ህዝብ
ነው፡፡ ዘመድ እስከ ሰባት ቤት በሚለው ብሂል የሚሰላው አይነት፡፡ አሁን በአራት
ትላልቅ ግዛቶች ማለትም በጎንደር፤ በሸዋ፣ በሳይንትና በጎጃም፤ እንዲሁም በአምስተኛው
ሀሳባዊ ግዛት ከመወሰኑ በፊት ብዛት ባላቸው ግዛቶች እና ንኡሳን ግዛቶች ይኖር ነበር፡፡
ከአንዱ አካባቢ ወደ ሌላው በተደረገው ያልቁዋረጠ የህዝብ ዝውውር የተነሳ አማራ
በጠቅላላው ዝምድናው ወደ ቤተሰብነት ያደገ ብሄር ነው፡፡ ለምሳሌ የአማራ ሳይንት
ሰዎች ገዥዎች ቢሆኑ ወታደርና መኳንንት በሞላው ወደ ሌሎች አካባቢዎች ይላካል፡፡
የሌላው አካባቢም ወታደርና መኳንንት በሹመትና በግዞት ወደ ተለያዩ አካባቢዎች
ይላካል፡፡ የአማራ ሳይንት መኳንንትም አስተዳደራቸውን ለማደላደል ሲሉ ከመላው
አማራ አካባቢዎች ጋር መንግስታዊ ጋብቻ ያደርጋሉ፡፡ የጎዝመን (ጎዛመን) እና የጎንጅ
አካባቢ ገዥዎች በሚሆኑበትም ጊዜ እንደዛው ያደርጋሉ፡፡ የጌራ ምድር እና ተጉለት ገዥዎች በሚነሱበት ጊዜም እንደዛው ያደርጋሉ፡፡ የደምቢያና ስሜን ገዥዎች በሚነሱበት
ጊዜም ያንኑ ያደርጋሉ፡፡ ባጭሩ የአማራ የህዝብ ለህዝብ ትስስር እንደሸረሪት ድር
የተሳሰረ፤ እንደሸማኔ ዝሀና ፈትል የተዳወረ ነው፡፡ ይህ ወደጥንቱ ዘለግ ተደርጎ ሲወሰድ
እስከባሌና ደዋሮ፤ ግራርያ እና እናርያ አማሮች (ዛሬ የተዋጡና የጠፉ) ድረስ የሚዘረጋ
ነው፡፡
ይህ የህዝብ ትስስርና ቤተሰባዊነት በፖለቲካውና በወታደራዊው መስክ ብቻ
የተገደበ አይደለም፡፡ በሀይማኖታዊውም ዘርፍ እንደዛው ነው፡፡ ተማሪዎች ከሸዋ፡
ከሳይንትና፡ ከጎጃም አቋቋምና ዜማ ለመማር ወደጎንደር ይሄዳሉ፡፡ በአብዛኘውም በዛው
መሪጌታና ደብተራ ሆነው ተጋብተው ተዋልደው ይቀራሉ፡፡ ቅኔ እንዲሁም ዜማ ለመማር
ወደጎጃም ይሄዳሉ፡፡ በዛውም እንደዛው ይሆናል፡፡ በሸዋም፤ በሳይንትም እንዲሁ፡፡
ከአንዱ አካባቢ ወደሌላው ገዳማትና አብያተክርስቲናትን ለመሳለም ይንቀሳቀሳሉ፤
የህዝቡ መተሳሰርም እንደዛው ይሆናል፡፡ ሙስሊም አማሮች በተለይ በንግድ ትስስሩን
ሲያጠብቁት ቆይተዋል፡፡ በትምህርትም ከቦታ ቦታ ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ለምሳሌ ከሳይንትና
ጎንደር እንዲሁም ጎጃም ወደሰሜን ሽሆች እንቅስቃሴ ይደረጋል፡፡ ምነናም ከዚሁ
የሚመደብ ነው፡፡ ከአንዱ ግዛት ወደሌላው ግዛት ገዳማት ይንቀሳቀሳሉ፡፡
አማራ ከሁሉም ግዛቶች ርስትን-ህግን በተመለከተ በሚያደርገው እንቅስቃሴ
ይተሳሰር ነበር፡፡ ለምሳሌ ከጎንደር፡ ጎጃም እና ሳይንት አዲስ አበባ ድረስ ለክርክር (ለእሰጥ
አገባ ክርክር) ይሄዱ ነበር፡፡ ያም ሂደት በእግር የሚደረገውን እንቅስቃሴ ሁኔታ
ስንደምርበት የህዝብ ቅልቅሉን ያሰፋዋል፡፡ የመንግስት መቀመጫዎች በጎንደርና ሳይንት
እዲሁም በጎጃም በነበሩበት ጊዜም እንዲሁ፡፡ በተለይ በተለይ ወታደርነትና ሽፍትነት
አማራን አንድ ወጥ ህዝብ በማድረግ ወደር የለሽ ሚና ተጫውተዋል፡፡ ከአንዱ ግዛት
ወደሌላው የመንግስት መቀመጫ ግዛት ህዝብ ለወታደርነት፤ ለጭቃነት፤ ለምስለኔነት፤
እና ለሌላ አገልግሎት ይገባል፡፡ ለወዶ ዘማችነት እና በዛውም ወታደር ሆኖ ለመቅረት
ይገባል፡፡ ሽፍትነትም እንዲሁ፡፡ ከአንዱ ግዛት ሸፍቶ ወደሌላው ይሄዳል፡፡ በዛውም
ትውልዱን መስርቶ ይኖራል፡፡ ንግድ በበኩሉ አማራን ቤተሰባዊ በማድረግ ትልቅ ሚና
ተጫውቷል፡፡ ከላይ የተጠቀሰው የሙስሊም አማሮች ሚና እንደተጠበቀ ሆኖ
የተቀረውም ህዝብ ለንግድ ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀስ ነው የኖረው፡፡ ጦርነትም አማራን
ትስስሩን ቤተሰባዊ አድርጎታል፡፡ በራሱ በአማራው መካከል በሚነሳ ሆነ በውጫዊ አካል
በሚሰነዘር ጥቃት የአንዱ አካባቢ አማራ ወደሌላው በመሸሽ ክፉ ቀንን ያሳልፋል፡፡
ለምሳሌ ጎንደር በደርቡሽ በጠፋችበት ዘመን የጎንደር አማሮች ሳይንት፤ ጎጃምና ሸዋ
ሄደው ክፉ ቀንን አሳልፈዋል፡፡
~ ግዮናዊነት
ታጋይ አምሓራ
ነፃነት በትግል እንጂ በልመና አይገኝም!
14/3/2017 ዓ.ም