~የሰዎችን መጥፎ ጎን ብቻ ለማስታወስ ከተቀመጥክ ለማንም ውዴታ አይኖርህም። ፍፁም ንፁህ ስለማይኖር ቅርብ ሰዎችህን እንኳን ባልተለመደ መልኩ በጥቁር ዓይን መመልከት ትጀምራለህ። ከዚያ ቀንህም አያፈካህም፣ ሌሊትህም አያሳርፍህም። አንዳንዴ መጥፎ ጎናቸው ጋር ስትደርስ አይንህን ስበር፣ አይቶ እንዳላየና ሰምቶ እንዳልሰማ ማለፍንም ተለማመድ።አንዳንዴ «መርሳት»ን እንደ ትራስ ተደገፈው። አንተም አጠገብህ ያሉትም ሰላም እንዲሆኑ።