The ጀማል (ዘ ጀማል )


Channel's geo and language: Ethiopia, English


🏇 ይህ #the_ጀማል የቴሌግራም ገፅ ነው !
=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል ! ከዓለም 👊
👊 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, English
Statistics
Posts filter


ኢትዮጵያና ሶማሊያ በሶማሊላንድ ወደብ ዙሪያ የነበረውን ውዝግብ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት መስማማታቸውን አስታዉቀዋል።
የሁለቱ አገራት መሪዎች በቱርክ አደራዳሪነት ባደረጉት ስብሰባ፣ ኢትዮጵያ በሶማሊያ ሉዓላዊነት ውስጥ በመሆን የባህር በር ለመጠቀም የሚያስችል የጋራ ተጠቃሚነት ያለው የንግድ ስምምነት ላይ ለመድረስ ተስማምተዋል።
ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሞቃዲሾን ጎብኝተው ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ ጋር ተወያይተዋል። በስብሰባው አጀንዳ ቀዳሚው የዓፍሪካ ቀንድ ደህንነት እንዲሁም ባለፈው ታኅሣሥ በአንካራ እንደተስማሙት የኢትዮጵያ ወደብ ተደራሽነት የቴክኒክ ድርድር መጀመር እንደነበር ተጠቁሟል።
የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሐመድ ዑመር አሊ እንዳስታወቁት፣ ድርድሩ ቀጥሏል፤ ግቡም እስከ ሰኔ ወር ድረስ የአሠራር ማዕቀፍ ላይ መድረስ ነው። ይህ ማዕቀፍ ኢትዮጵያ የምትጠቀምበትን ወደብየሚገኝበትን ቦታና ወጪውን ይወስናል።
ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ፍላጎቷን በሰላማዊ መንገድ እንድታሳካ ትልቅ እድል የሚፈጥር ነው። ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ በሶማሊላንድ በኩል የባህር በር ለመጠቀምያደረገችው ጥረት ውዝግብ አስነስቶ ነበር።
አሁንግን ሁለቱ አገራትበመደራደርና በመስማማት የጋራ ጥቅምን ለማስጠበቅ ቁርጠኝነታቸውን ማሳየታቸውን ዘ ማሪታይም ኤክስኪዩቲቭ ዘግቧል ።
ኢትዮጵያ ከኤርትራ መገንጠል በኋላ የባህር በር አልባ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ የራሷን የባህር በር ለመገንባት ጥረት ስታደርግ ቆይታለች። ይህ ስምምነት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ እድገትየሚያግዝና በክልሉ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሉን Joinበማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://t.me/thejamalnews


ዩናይትድ ከኤፌ ካፕ ውድድር ተሰናበተ !

ፉልሀም ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ያደረገውን የኤፌ ካፕ አምስተኛ ዙር ጨዋታ በመለያ ምት 4ለ3 በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን መቀላቀል ችለዋል።

ሁለቱ ክለቦች መደበኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ግቦችን ለማንችስተር ዩናይትድ ብሩኖ ፈርናንዴዝ እንዲሁም ለፉልሀም ካልቪን ባሴይ ማስቆጠር ችለዋል።

ብሩኖ ፈርናንዴዝ በውድድር ዘመኑ ከየትኛውም የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች በበለጠ ሀያ አራት የግብ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል ሲል ቲክቫ ስፖርት ዘግቧል።

የኤፌ ካፕ ሩብ ፍፃሜ ተጋጣሚዎች ከደቂቃዎች በኋላ በሚደረግ የእጣ ማውጣት ስነስርዓት የሚለዩ ይሆናል። 


  ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሉን Join በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇
https://t.me/thejamalnews
#the_ጀማል


ሰበር -ዜና ‼️
ከደቂቃዎች በፊት  ከበድ የመሬት መንቀጥቀጥ አዲግራት ለይ አጋጥመዋል
ዘሬ ከምሽቱ 12:11 ለይ ነው

ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሉን Join በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇
https://t.me/thejamalnews
#the_ጀማል


ተጠባቂው የቶከዮ ማራቶን በኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸናፊነት ተጠናቀቀ

የቶከዮ ማራቶን በሁለቱም ጾታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በበላይነት አሸንፈዋል።

በወንዶች ታደሰ ታከለ ሲያሸንፍ በሴቶች ደግሞ አትሌት ሱቱሜ አሰፋ በበላይነት አሸንፋለች ።

በአለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃ በተሰጠው ማራቶን በሴቶች አትሌት ሱቱሜ አሰፋ 2:16. 31 በመግባት በአንደኝነት አሸንፋለች ።

በወንዶች የቶክዮ ማራቶን አትሌት ታደሰ ታከለ በ2:03.23 በመግባት የግል ምርጥ ሰአቱን ጭምር በማሻሻል አሸንፈዋል ።

አትሌት ደረሳ ገለታ በ2 :03.51  በመግባት ሁለተኛ ደረጃ ይዞ አጠናቀዋል ።
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሉን Join በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇
https://t.me/thejamalnews
#the_ጀማል


ዓድዋ‼️

"ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል!"
እንኳን ለ129ኛዉ የዓድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

የአድዋ ጦርነት ኢትዮጵያዊያን የአፍሪካ አዉራ ህዝቦች መሆናቸውን ያረጋገጡበት፣ በደም እና በህይወት ነፃነትን የተቀነጀንበት የማሸነፍና የድል ምዕራፍ ነው።

በመላው ኢትዮጵያዊያውያን የተመራዉ የአድዋ ጦር እያቅራራ፣ እየፎከረ እና  እየሸለለ በመዝመት ለመላው የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ምልክት ሆነዋል።

አድዋ ኢትዮጵያዊያንን በአንድነት ያስተሳሰረ የአንድነት ገመድ ነው።

የአድዋ ጦርነት ለኢትዮጵያዊያን የህልውና የነበረ ስሆን ለቅኝ ገዥ ፋሽስት ደግሞ የቅኝ ገዥነት ስሜት ለማርካት ያሰበ ነበር።

ሆኖም ግን ጀግናዉ የኢትዮጵያ ህዝብ የጦርነት ጊዜ ወታደር እና የሰላም ጊዜ ገበሬ አሻፈረኝ በማለት ገፍቶ የመጣዉን የውጭ ጠላት ሀይል በመጣበት እግሩ አንበርክኮ እና ማርኮ ወደ መጣበት ሸኝተዋል።

እኛ ከተባበርን እና አንድነታችንን ካጠናከርን የሀገራችንን ስምና ክብር ከፍ በማድረግ ድህነታችንን ታሪክ ማድረጋችን አይቀርም።

በመጨረሻም የአድዋን የአይበገሬነት ወኔ በመላበስ የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች ወደ መልካም ዕድል በመቀየር ፀጋዎቻችንን በሙላት ለህዝብ የላቀ ተጠቃሚነት ለማዋል ሁላችንም የድርሻችንን በተነሳሽነት እንድንወጣ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

እንኳን ለ129ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሰን ! አደረሳችሁ !!

ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሉን Join በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇
https://t.me/thejamalnews
#the_ጀማል


ሪያል ማድሪድ አሁንም ነጥብ ጣለ


ሪያል ቤቲስ 2-1 ሪያል ማድሪድ

⚽️ብራሂም ዲያዝ
⚽️ጆኒ ካርዶሶ
⚽️ኢስኮ

ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሉን Join በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇
https://t.me/thejamalnews


ማን ሲቲ ከመመራት ተነስቶ ፕሌይመውዝ ን በማሸነፍ በኤፌ ካፑ ቀጣዩን ሩብ ፍፃሜው ዙር ተቀላቅሏል ➡️🏆


ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሉን Join በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇
https://t.me/thejamalnews


እንደምን አደራችሁ አድስ ነጋር የተሰማ ከላ እናቴ ስፍራ ።

ከላ 👉 @Tsedekenews55


በስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ አምበሪቾ ቦራራ ደን ላይ የእሳት አደጋ መከሰቱ ተነግሯል።

የእሳት አደጋውን የወረዳው የፀጥታ መዋቅርና የአካባቢው ማህበረሰብ በጋራ ለመቆጣጠር ጥረት እያደረጉ ሲሆን በአካባቢው የሚገኙ አካላት በሙሉ ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ መቅረቡን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

የካቲት 21/2017 ዓ.ም

ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሉን Join በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇
https://t.me/thejamalnews


ከደቂቃዎች በፊት በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ዛሬ ከቀኑ 5:30 አካባቢ  የመሬት መንቀጥቀጥ ተሰምቷል፡፡ንዝረቱ ከአዲስ አበባ ውጭ:-
📌 ደሴ
📌ኮምቦልቻ
📌አንኮበር
📌ደብረብርሃን
📌አዳማ
📌አልዩ አምባ ድረስ መሰማቱን የደረሱኝ
መረጃ ያሳያል


ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሉን Join በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇
https://t.me/thejamalnews


አርሰናል ከተከታዩ ኖቲንግሃም ፎረስት ጋር ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል።
ኖቲንግሃም ፎረስት 0 - 0 አርሰናል
ቶተነሃም 0 - 1 ማንችስተር ሲቲ
ማንችስተር ዩናይትድ 3 - 2 ኢፕስዊች ታወን

ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሉን Join በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇
https://t.me/thejamalnews


ሰበር -ዜና እሳት‼️

አዲስ አበባ ካራ ቆሬ  ህዳሴ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አካባቢ በሚገኘው ቢቂላ መናፈሻ  እሳት ተነስቷል። በዚህ አካባቢ በአንድ ሳምንት ልዮነት ውስጥ መሠል አደጋ ሲደርስ ይኸ ለሁለተኛ ጊዜ እንደሆነ መረጃው ደርሶናል።



   ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሉን Join በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇
https://t.me/thejamalnews


እስራኤል እና ሃማስ አራት የታጋቾች አስከሬንን በመቶዎች በሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን እስረኞች ለመለዋወጥ ከስምምነት ላይ ደረሱ፡፡

ከአንድ ወር በፊት የተጀመረው እና በርካታ መሰናክሎችን የተጋፈጠው የጋዛው የተኩስ አቁም ስምምነት በተለያዩ ዙሮች በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውን እስረኞች እና በሀማስ ስር የሚገኙ ታጋቾች እንዲለቀቁ ምክንያት ሆኗል፡፡

እስራኤል ከቅዳሜው የእስረኞች እና ተጋቾች ልውውጥ በኋላ ፍልስጤማውያን እስረኞችን የምትለቅበትን ጊዜ ማራዘሟን አስታውቃ ነበር፡፡

ቴልአቪቭ በዚህ ሳምንት እንደምትለቃቸው የሚጠበቁትን 23 ህጻናትን እና አንዲት ሴትን ጨምሮ 620 ፍልስጤማውያን እስረኞችን የመፍቻ ጊዜ ያዘገየችው፤ “ታጋቾች በሚለቀቁበት ጊዜ ሀማስ የሚያዘጋጃቸው መድረኮች የዜጎቼን ክብር የሚነኩ ናቸው” በሚል ነበር፡፡

በቀጣይ ታጋቾች በሚለቀቁበት ጊዜም መሰል የመድረክ ላይ ፕሮግራሞች እንዳይኖሩ ይህ የማይሆን ከሆነ ስምምነቱ አደጋ ላይ ሊወድቅ እንደሚችል አስጠንቅቃለች፡፡

ባለፈው ወር በጀመረው የተኩስ አቁም ስምምነት የመጀመሪያ ምዕራፍ በህይወት የሚገኙ የመጨረሻ ዙር 6 ታጋቾች ቅዳሜ ዕለት በሁለት ህዝባዊ ስነ ስርዓቶች መለቀቃቸው ይታወሳል፡፡

ሀማስ በበኩሉ እስራኤል በዚህ ሳምንት እንደምትለቃቸው የሚጠበቁትን ፍልስጤማውን እስረኞች ካልፈታች የሁለተኛው ምዕራፍ የተኩስ አቁም ድርድር የማይታሰብ ነው ብሏል፡፡

ሁለቱ ወገኖች በግብጽ አደራዳሪዎች በደረሱበት ስምምነት 620 እስረኞችን በአራት እስራኤላውያን ታጋቾች አስክሬን ዛሬ ምሽት ለመለዋወጥ ወስነዋል፡፡
 

   ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሉን Join በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇
https://t.me/thejamalnews


አሳዛኝ ዜና ‼️

አማራ ክልል በትራፊክ አደጋ የ14 ሠዎች ሕይወት አለፈ

በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ወረዳ በደረሰ የመኪና አደጋ የ14 ሠዎች ሕይወት ማለፉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ዐሳወቀ ።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ትምህርትና ሰልጠና ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር ይበልጣል መርሻ፦  እንደገለፁት ተሽከርካሪው ትናንት ከበየዳ ወደ ደባርቅ ሠዎችንና እህል ጭኖ ሲጓዝ ከረፋዱ 3፡30 አካባቢ በደባርቅ ወረዳ ልዩ ሥሙ «አበርጊና» በተባለ ቦታ ላይ ሲደርስ ተገልብጦ 14 ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች በርካቶች ቆስለዋል ።

ተጨማሪ ምርመራዎች እየተደረጉ ቢሆንም፤ ለመኪናው መገልበጥ ምክንያት ነው ያሉትን ኃላፊው ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል ። «ከበየዳ ወደ ደባርቅ ሲመጣ የነበረ በተለምዶ ‘ካሶኒ’ እየተባለ የሚጠራ መኪና ነው፥ በየዳ አድሮ እህል ጭኖ እየመጣ ከበየዳ ወጣ እንዳለ አበርጊና ከተባለች ጎጥ ሲደርስ ተገልብጧል» ብለዋል ።

የአደጋው መንሳኤ አንዱ ከመጠን በላይ መጫን መሆኑን የገለፁት ኃላፊው፦ የመኪናው አቅም ከሚችለው እህል ጭነት በላይ 50 ሠዎችን አሳፍሮ ነበር ብለዋል። ሌላው ለአደጋው መንሳኤ ተብሎ የሚገመተው አሽከርካሪው ለመስመሩ አዲስ በመሆኑ የመንገዱን ባሕርይ ዐለማወቅ ሊኖር እንደሚችል ተናግረዋል ። በአድጋው 12 ሠዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ፤ ሌሎች ሁለት ደግሞ ዛሬ ጠዋት ሕይወታቸው አልፏል ብለዋል ። ቀሪ 37ቱ ደግሞ በተለያዩ የሕክምና ቦታዎች ሕክምና እየወሰዱ እንደሆነና 27ቱ በከባዱ ጉዳት የደረሰባቸው እንደሆኑ መግለጣቸውን ዓለምነው መኮንን ዘግቧል ።
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሉን Join በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇
https://t.me/thejamalnews
#the_ጀማል




ሶማሊያ፡ አልሸባብ በሂራን ክልል በሚገኙ መንደሮች ላይ ጥቃት ሰነዘረ

ሞቃዲሾ፣ ሶማሊያ - ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት ያላቸው ታጣቂዎች በሂራን ክልል በሚገኙ መንደሮች ላይ ከባድ ጥቃት መፈፀማቸውን የአካባቢው ምንጮች ዘግበዋል።
 
ጥቃቱ የተፈፀመው ትላንት ማምሻውን ሲሆን የአልሸባብ ታጣቂዎች በአቦሬ እና በቢራባሌ የመንግስት ወታደራዊ ይዞታዎች ላይ ኢላማ አድርገው እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ለሬድዮ ሸበሌ ተናግሯል።
የአካባቢው የጎሳ ሃይሎች እና ወታደራዊ አባላት አጥቂዎቹን ለመመከት ሙከራ ቢያደርጉም በሁለቱም ወገን ላይ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን የሟቾቹ ትክክለኛ ቁጥር አሁንም እየተረጋገጠ ነው።
 
የዘገበው 👉ፀደቀ

ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሉን Join በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇
https://t.me/thejamalnews
#the_ጀማል




በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ

ዛሬ በ27ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ መርሃ ግብር አራት ጨዋታዎች የሚካሄዱ ሲሆን ምሽት 5፡15 ላይ ቼልሲ ከሳውዝሃምፕተን የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

በዕለቱ በተመሳሳይ ሰዓት ምሽት 4፡30 ላይ ሌሎች ጨዋታዎች የሚደረጉ ሲሆን ብራይተን ከበርንማውዝ፣ ክሪስታል ፓላስ ከአስቶን ቪላ እንዲሁም ወልቭስ ከፉልሃም ይጋጠማሉ።

በተከታታይ ሁለት የፕሪሚዬር ሊግ ጨዋታዎችን የተሸነፈው ቸልሲ በ43 ነጥቦች በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ 7ኛ ላይ ይገኛል።


ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሉን Join በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇
https://t.me/thejamalnews
#the_ጀማል


የእሳት አደጋ 6 ቤቶችን አወደመ

#the_ጀማል /በሀላባ  ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ በሚቶ ዱበላ ቀበሌ በትናትናው ዕለት የካቲት 17/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ ለግዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ክስተት 6 የሳር ቤቶች መውደማቸው ተገለፀ።

በዌራ ዲጆ ወረዳ በሚቶ ዱበላ ቀበሌ በትናንትናው ዕለት  ከቀኑ 8:00 ሰዓት ለግዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ክስተት 6 የሳር ቤቶች መውደማቸው የተገለጸው ።

የዘገበው ፀደቀ .አ

ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሉን Join በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇
https://t.me/thejamalnews
#the_ጀማል


የሱዳን ጦር ወሳኝ ከተማን ተቆጣጠረ


የሱዳን ጦር አርኤስኤፍ እየተባለ የሚጠራውን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል ከበባን በመስበር ኤል ኦቤይድ የተሰኘችውን ቁልፍ ከተማ መያዙን አስታወቀ።

በደቡባዊ ሱዳን የምትገኘውን የዚህችን ከተማ ከበባ ጦር መስበሩ ከመሰማቱ ሰዓታት ቀደም ብሎ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በቁጥጥሩ ሥር የሚኙ አከባቢዎችን ይዞ መንግሥት ለመመስርት በኬንያ መዲና ናይሮቢ ላይ ቻርተር ፈርሟል።
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሉን Join በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇
https://t.me/thejamalnews
#the_ጀማል

20 last posts shown.