በዲሞክራቲክ ኮንጎ ምንነቱ ባልታወቀ በሽታ ከ50 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተሰማ
በአማጺያን እና በመንግሥት ኃይሎች መካከል ጦርነት እየተካሄደባት ባለችው በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ውስጥ የተከሰተ ምንነቱ ያልታወቀ በሽታ ቢያንስ 53 ሰዎችን መግደሉ ተገለጸ።
በአገሪቱ ሰሜን ምዕራብ ክፍል ውስጥ በተከሰተው በዚህ ገዳይ በሽታ የተያዘ ሰው የበሽታው ምልክት ከታየበት በኋላ በአንድ ቀን ውስጥ ለህልፈት እንደሚዳረግ ተነገሯል።
በበሽታው ሰበብ ሰዎች እየሞቱ መሆናቸው የታወቀው እየተጠናቀቀ ባለው የካቲት ወር ውስጥ ሲሆን፣ ስፍራውም ኢኩዌተር በተባለው የዲሞክራቲክ ኮንጎ ግዛት በምትገኘው ባሳንኩሳ መንደር ነው።
የዓለም የጤና ድርጅት እንዳለው ይህ ምንነቱ ያልታወቀ ገዳይ በሽታ በዓለም አቀፍ ደረጃ የመሠራጨቱ ስጋት ዝቅተኛ ነው።
ከሃምሳ በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ገድሏል የተባለው በሸታ መነሻ ምክንያቱ ምን እንደሆነ እና የመተላለፊያ መንገዶቹ እስካሁን በግልጽ አልታወቀም።
በበሽታው ከተያዙ ሰዎች በተወሰዱ ናሙናዎች ላይ በተደረገ ምርመራ፤ ግለሰቦቹን ለሞት የዳረጋቸው ኢቦላ ወይም ማርበርግ የተባሉት በቫይረስ የሚተላለፉ በሽታዎች አለመሆናቸው ተረጋግጧል።
ቢቢሲ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሉን Join በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇
https://t.me/thejamalnews
#the_ጀማል