Posts filter


#Ethiopia

"አንድ ታዳጊ ወጣት ተገሏል ሁለት ደግሞ ቆስለዋል" - የሹፌሮች አንደበት

"ምን አጠፋን? ምን እናድርግ? ህግና መንግስት አለ ብለን ነው በትግስት እየጠበቅን ያለነው የ200 ብር ትራንስፖርት 1000 ብር ከፍለን በየ ቦታው ተሳቀን አሁን ገደሉን፣ አቆሰሉን እያልን፤ ያሳዝናል።

ዛሬ 28-05-2017 ጠዋት 2፡10 ከገንዳውሃ ጎንደር እየተጎዝነ ከ10 በላይ አባዱላ ተዘርፎል በጣም የሚያሳዝነው አንድ ታዳጊ ወጣት ተገሏል ሁለት ደግሞ ቆስለዋል።

እስከመቼ ይሄ ጉዳይ? እንደ ክልል የፀጥታ ችግር ስላለ በትግስት መመልከት ስለሚገባ ሁሉም በየቀኑ እየሞትንና ደም እያነባን ዝም አልን እስከመቼ?

ከገንዳውሃ እስከ ጎንደር ያለው መንገድ ከዚህ በፊት አብዛኛውን ጊዜ የማዕከላዊ ጎንደር የፀጥታ ችግር ይበዛ ነበር። አሁን ግን እነሱ አስተካክለው መንገዱን ሰላም ሲያደርጉ ምዕራብ ጎንደር በእጅጉ ብሷል ለምን?

ትኩረት ለምዕራብ ጎንደር ዞን። የፀጥታ መዋቅር ከማህበረሰቡ ጋር በመሆን ችግሩን ባፋጣኝ እንዲስተካከል ሀሳቤን እያለቀስኩ አካፍላለው። ጎንደር አውሮፖ ሆነብን"
ሲል የሹፌሮች አንደበቶ አስታውቋል።

@ThiqahEth


#Ethopia

በትራፊክ አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት አለፈ።

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞን ሜታ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ።

አደጋው ከጅቡቲ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የጭነት ተሽከርካሪ ከቆቦ ከተማ ወደ ድሬዳዋ ሲያመራ ከነበረ ዶልፊን ጋር በመጋጨቱ ነው የተከሰተው፡፡

በተፈጠረው አደጋም የ8 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የኮሙኒኬሽን ሃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ካስዬ አበበ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በሦስት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ነው የገለጹት፡፡

#ThiqahEth


''ቤታችንን ለቀን አንሄድም'' - ፍልስጤማውያን

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከእስራዔሉ አቻቸው ጋር በተገናኙበት ወቅት አሜሪካ በመልሶ ማልማት እቅድ ጋዛን ማስተዳደር እንደምትፈልግ ተናግረዋል፡፡

በጋዛ የሚገኙ ፍልስጤማውያን ሌላ ቦታ እንዲሰፍሩ ይደረጋል ማለታቸው፤ ነዋሪዎቹን አስቆጥቷል።

ቁጣቸውን ከገለጹ ፍልስጤማውያን መካከል ሳሚር አቡ ባዝል የተባለ የጋዛ ነዋሪ፣ ''ትራምፕ ከነሀሳቡ፤ ከነአመለካከቱ ሲዖል ይግባ፤ የትም አንሄድም፤ እኛ የእሱ የእጅ ገንዘብ አይደለንም'' ሲል ቁጣውን አሰምቷል፡፡

ለፍልስጤም እታገላለሁ የሚለው የሀማስ ቡድን፣ ''ፍልስጤማውያንን የሚጨቁን እና ለቀጠናው መረጋጋት አስተዋጽኦ የማያደርግ'' ሲል ነቅፎታል።

ሳውድአረቢያን ጨምሮ አንዳንድ የአረብ ሀገራት ደግሞ የትርምፕን አስተያየት አሳሳቢ እንደሆነ በመግለጽ ተቃውመውታል፡፡  

በተመሳሳይ መልኩ የአውሮፓ ሀገራት በበኩላቸው ፍልስጤማውያንን የማዘዋወር እቅድ አውግዘዋል፡፡

በርካታ ፍልስጤማዊያኑም፣ "ቤታችንን ለቀን አንሄድም" ሲሉ ከወዲሁ ሞግተዋል።
#anadoluagency #trtworld #easterneye

@ThiqahEth


የአፍሪካ ልማት ባንክ በማዕድን ግብይት እንዲፈጸም የሚያስችል እቅድ አቀረበ፡፡

ባንኩ፣ ''የወርቅ ደረጃ'' ሲል የገለጸው የመገበያያ ዘዴ የአህጉሪቱ ሀገራት ማዕድን ላይ የተመረኮዘ የግብይት ማስተካከያ ላይ እንዲያተኩሩ አሳስቧል፡፡

እንደባንኩ መረጃ ከሆነ በዓለም ላይ ካሉ የተፈጥሮ ማዕድናት 30 በመቶ የሚሆነው አፍሪካ ውስጥ ይገኛል፡፡

እቅዱ ስኬታማ እንዲሆን ሁሉም ሀገራት ቅድመ ስምምነት የተደረገበት የማዕድን ሀብት መጠን ሊያሟሉ እንደሚገባ ባቀረበው እቅድ ገልጿል፡፡

የአፍሪካ ልማት ባንክ አዲስ ያቀረበው እቅድ የአፍሪካ ሀገራት የሀገር ውስጥ መገበያያ ገንዘባቸውን በሌሎች ሀገር ማዕድናት በመለወጥ የንግድ ስርኣትን ማቀላጠፍ እንደሚቻል አስታውቋል፡፡
#iaafrica

@ThiqahEth


''የሚጣልብንን የቀረጥ ስጋት ማሰብ ከሚጣልብን ቀረጥ በላይ ይጎዳናል'' -  ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር

ማሌዥያ የአሜሪካን ቀረጥ ሳያሳስባት የንግድ ልውውጡዋን አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታውቃለች፡፡

የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም ሀገራቸው ከቻይና፣ ሩሲያና ብራዚል ጋር ያላትን የንግድ ግንኙነት አጠናክራ እንደምትቀጥል ተናግረዋል፡፡

አንዋር የአሜሪካ፣ ''ታሪፍ ሊያመጣብን የሚችለውን ጫና ፈርተን ከሌሎች ሀገራት ጋር የምናደርገውን የንግድ ግነኙነት አናቋርጥም'' ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ለፓርላማ አባላት ባደረጉት ንግግር ደግሞ፣ ''የሚጣልብንን ቀረጥን ስጋት ማሰብ ከሚጣልብን ቀረጥ በላይ ይጎዳናል'' ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ #asiaone

@ThiqahEth


''ጊዚያዊ የተኩስ አቁም አውጃለሁ'' - ኤም 23 ቡድን

ኤም 23 ቡድን ጊዚያዊ የተኩስ አቁም ማወጁን ገለጸ።

በሩዋንዳ እንደሚደገፍ የሚነገርለት የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ "አማጺ ቡድን" ''ጊዚያዊ የተኩስ አቁም አውጃለሁ'' ብሏል፡፡

የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከዛሬ ማክሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ቡድኑ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ለአንድ ሳምንት በቆየው ጦርነት ከ900 የሚበልጡ ሰዎች መገደላቸውን የተ.መ.ድ የእርዳታ ድርጅቶች ገልጸዋል፡፡    #france24

@ThiqahEth


ቻይና በአሜሪካ ምርቶች ተጨማሪ ቀረጥ ጣለች፡፡

በፕሬዝዳንት ትራምፕ ምርቶቿ ላይ የ10 በመቶ ታሪፍ የተጣለባት ቻይና ከአሜሪካ በምታስገባቸው የድንጋይ ከሰል እና ነዳጅ ዘይት ላይ የ15 በመቶ ታሪፍ መጣሏን አስታውቋለች፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በግብርና ማሽኖች፣ ረዥም ተሸከርካሪዎቨች እና ፒክ አፕ መኪኖች ላይ የ10 በመቶ ጭማሪ አድርጋለች፡፡

ከቻይና እና ሜክሲኮ ጋር ታሪፍ ተጥሎባት የነበረችው ካናዳም በአሜሪካ ምርቶች ላይ የ25 በመቶ ጭማሪ በማድረግ የአጸፋ እርምጃ ወስዳለች፡፡
#asianews

@ThiqahEth


ካርቱም ውስጥ ገበያ ላይ በተፈጸመ ጥቃት 56 ሰዎች ሲገደሉ፣ ከ150 በላይ ቆሰሉ።

በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም በሚገኘው አትክልት ገበያ ላይ በተፈጸመ የአየር ላይ ጥቃት 158 ሰዎች ቆስለዋል፡፡

ጥቃቱ የተፈጸመው ከሱዳን ጦር ጋር እየተፋለመ በሚገኘው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ አማካኝነት መሆኑን የሱዳን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ "ጥቃቱን አልፈጸምኩም" ሲል አስተባብሏል፡፡

በሁለቱ ኃይሎች ግጭት በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን ሲሞቱ፤ ከ12 ሚሊዮን የሚልቁት ደግሞ ለሀገር ውስጥ እና ለሀገር ውጭ ስደት ተዳርገዋል፡፡  
#dailypost

@ThiqahEth


በአንድ አመት ውስጥ 970,000 ህገ ወጥ የመድሃኒት ምርቶች መያዛቸው ተመላከተ፡፡

ባሳለፍነው የፈረንጆቹ አመት 2024፣ በኦን ላይን በታገዘ ማጭበርበር ህገ ወጥ የመድሃኒት ንግድ ሲያከናውኑ የነበሩ 2,868 ነጋዴዎች መያዛቸውን ተቀማጭነቱን ሲንጋፖር ያደረገው የጤና ሳይንስ ባለስልጣን (HSA) አስታውቋል፡፡

ግብይቶቹ ሚከናወኑት በኢ-ኮሜርስ እና በማህበራዊ ሚዲያ በመሆኑ ለቁጥጥር አስቸጋሪ ሆኖ መቆየቱን ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡

ወጣቶች ለህገ ወጥ የመድሃኒት ምርቶቹን በመጠቀም ተጋላጭ መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡ #thestraightstimes

@ThiqahEth


በሶሪያ ቢያንስ 15 ንጹሐን በቦምብ ጥቃት ተገደሉ፡፡

በሰሜናዊ ሶሪያ በምትገኘው የማንቢጅ ከተማ መኪና ላይ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት የ15 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተዘግቧል፡፡

የጥቃቱ ሰለባዎች በግብርና ስራ ተሰማርተው የሚኖሩ ሲሆኑ፤ ከስራ ሲመለሱ ጥቃቱ እንደተፈጸመባቸው የዓይን እማኞች ተናግረዋል።

ከሟቾቹ መካከል 14ቱ ሴቶች ሲሆኑ፣ አንዱ ደግሞ ወንድ ነው ተብሏል፡፡

ምንም እንኳን በከተማዋ በቱርክ የሚደገፉ የሶሪያ ታጣቂዎች እና በአሜሪካ የሚደገፉ የኩርድ ታጣቂዎች ግጭት ውስጥ ቢገኙም ለደረሰው ጥቃት ኃላፊነት የወሰደ አካል ግን የለም፡፡ 
#sananewsxgency   #apnews

@ThiqahEth


''ሳዑድ አረቢያ ሶሪያን የመርዳት ከፍተኛ የሆነ ፍላጎት አላት''  - አህመድ አልሻራ

የሶሪያ ጊዚያዊ የሽግግር ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት አሕመድ አልሻራ የመጀመሪያ የውጭ ሀገር ጉዟቸውን በሳዑዲ አረቢያ አድርገዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ በሪያድ ከልዑል አልጋ ወራሽ መሃመድ ቢን ሳልማን ጋር ባደረጉት ውይይት፤ በጦርነት የተጎዳቸውን ሶሪያን መልሶ በመገንባት ዙሪያ ሰፋ ያለ ጊዜ ወስደው ተነጋግረዋል ተብሏል፡፡

''ሳዑድ አረቢያ ሶሪያን የመርዳት ከፍተኛ የሆነ ፍላጎት አላት'' ሲሉም ተናግረዋል።

ባሳለፍነው ታህሳስ ወር ላይ የበሽር አላሳድን መንግስት በኃይል ገርስሰው ስልጣን የተቆጣጠሩት አልሻራም፤ የሽግግር ፕሬዝዳንት ተደርገው ሲመረጡ የመጀመሪያው የደስታ መግለጫ የተላከላቸው ከሳውድው ንጉስ ሳልማን ነበር፡፡
#brecorder

@ThiqahEth


የአውሮፓ መሪዎች በሩሲያና አሜሪካ ጉዳይ ለመነጋገር እንግሊዝ ውስጥ ተሰባስበዋል፡፡

27ቱ የአባል ሀገራቱ መሪዎች በዛሬው እለት የሩሲያን ኢኮኖሚ ለመገዳደር በሚያስችላቸው ሁኔታዎች ላይ እየመከሩ ይገኛሉ፡፡

ከዚህ ባለፈም ስብሰባው አውሮፓ ከአሜሪካ ሊቃጣ ስለሚችለው የንግድ ጦርነት ቅድመ ጥንቃቄ ለማድረግ ያስችላል ነው የተባለው፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ በካናዳ፤ ሜክሲኮና ቻይና ላይ የወሰዱትን የቀረጥ መጣል እርምጃ በአውሮፓ ሀገራት ምርቶች ላይም ሊደግሙት እንደሚችሉ ዝተዋል፡፡ #voa

@ThiqahEth


"ካናዳ አሜሪካ ንግድ ላይ ለወሰደችው እርምጃ 155 ቢሊየን ዶላር በሚያወጡ የአሜሪካ ምርቶች ላይ የ25% ቀረጥ መጀመሯን አሳውቃለሁ"  - ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ

ካናዳ በፕሬዝዳንት ትራምፕ ውሳኔ ላይ የአፀፋ እርምጃ ወስዳለች።

ወደ አሜሪካ በሚገቡ ምርቶች ላይ የ25% ቀረጥ የተጣለባት ካናዳ፣ በአሜሪካ ምርቶች ላይም ተመሳሳይ ታሪፍ ጥላለች።

የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ፣ "ዛሬ ካናዳ አሜሪካ ንግድ ላይ ለወሰደችው እርምጃ 155 ቢሊየን ዶላር በሚያወጡ የአሜሪካ ምርቶች ላይ የ25% ቀረጥ መጀመሯን አሳውቃለሁ" ብለዋል።

ከአሜሪካ በሚገቡ የቢራ እና የወይን ምርቶች ላይ ቀረጥ መጣላቸውን አስታውቀዋል።

የነጩ ቤተ መንግሥት እርምጃ እንዳሳዘናቸው ገልጸው፣ ውሳኔው የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች እንደሚጎዳ ግልጽ ነው ብለዋል። #bbc #shine

@ThiqahEth


#BahirdarUniversity

“ስፔሻሊስት ዶክተሩ በተተኮሰባቸው ጥይት ተገድለዋል” - የዓይን እማኞች

የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጥበበ ግዮን ግቢ ስፔሻላንስድ ሆስፒታል የቀዶ ህክምና አገልግሎት ክፍል ዳይሬክተር ዶክተር አንዷለም ዳኘ “በተተኮሰባቸው ጥይት” መገደላቸው ተገለጸ።

ግድያው የተፈጸመው ትላንት ምሽት 12 ሰዓት ከ40 ደቂቃ ገደማ በመሆኑን የገለጹ የዓይን እማኞች፣ “ስፔሻሊስት ዶክተሩ በተተኮሰባቸው ጥይት ተገድለዋል” ብለዋል።

ስለገዳዮቹ ማንነት ገና የታወቀ ነገር የለም ተብሏል።
  
ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ፣ የዶክተር አንዷለምን ሞት በማረጋገጥ የሀዘን መግለጫ አውጥቷል።

የኢትዮጵያ ህክምና ማኀቀር በበከሉ፣ በግድያው የተሰማውን ሀዘን አስታውቆ፣ ለወዳጅ ቤተሰብ መጽናናትን ተመኝቷል።

@ThiqahEth


#Update

"በአምስት ቀናት  ውስጥ ብቻ 700 ሰዎች ተድለዋል፤ 2,800 ሰዎች ቆስለዋል" - ተ.መ.ድ

የመንግስታቱ ድርጅት በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እንደ አዲስ በተለይ ጎማ ከተማ ያገረሸውን ጦርነ፣ "አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ደርሷል" ሲል ገልጾታል።

"በአምስት ቀናት ውስጥ ብቻ 700 ሰዎች ሞተዋል፤ 2,800 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል" ብሏል።

የታጣቂ ቡድኑ ኤም 23 ሙሉ በሙሉ በተቆጣጠራት የጎማ ከተማ ሰብዓዊ ቀውስ መጎባቱንም ገልጿል።

በሩዋንዳ እንደሚደገፍ የሚነገርለት ቡድኑ ሰፋፊ ስትራቴጂካዊ ስፍራዎችን መቆጣጠር ጀምሯል።

የምሥራቅ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጦርነት በአውሮፓውያኑ 1990ዎቹ ቢጀመርም ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ተባብሷል።

የቱትሲ ብሔርን ያቀፈው የኤም23 አማጺያን ለአናሳዎች መብት እንደሚታገሉ ይናገራሉ።

የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግሥት በበኩሉ በሩዋንዳ የሚደገፉት "አማጺያኑ" በማዕድን ሃብታም የሆነውን የምስራቃዊውን ሰፊ ሥፍራ ለመቆጣጠር ይፈልጋሉ ሲል ይወቅሳል።

#Anadoluagency #Bbc

@ThiqahEth


"በዚህ ሰዓት በህይወት የተረፈውን ተጓዥ ማረጋገጥ አንችልም"  - የኤይር አምቡላንስ ካምፓኒ

በፊላደልፊያ አንድ ህፃንና አምስት ሰዎችን ጭና ስትጓዝ የነበረች አነስተኛ የግል አውሮፕላን  ተከስክሳለች።

አውሮፕላኗ አደጋ የገጠማት ጉዞ በጀመረች በ30 ደቂቃ ውስጥ፣ ከፊላዴልፊያ አየር መንገድ ሦስት ማይል ርቀት ላይ ነው።  

አደጋው በደረሰበት አካባቢ የመኖሪያ ቤቶች ላይ እሳት መነሳቱን የአምቡላንስ ካምፓኒው አስታውቋል።   

በሰዎች ላይ የሞት አደጋ ይሁን ከባድ የደረሰው ጉዳት ይህ ዘገባ እስከተዘጋጀበት ጊዜ አልተገለጸም።

ካምፓኒው በበኩሉ፣ "በዚህ ሰዓት በሕይወት የተረፈውን ተጓዥ ማረጋገጥ አንችልም" ብሏል።

ከሁለት ቀን በፊት በአሜሪካ ከካንሳስ ወደ ቨርጂኒያ ሲጓዝ የነበረ አውሮፕላን ተከስክሶ ሁሉም 64 ተጓዦች ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።
#newsmax  #gulfnews

@ThiqahEth


#እንድታውቁት

"ከየካቲት 1 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ልዩ መለያ ኮድ (Unique Qr code የሌለው ደረሰኝ መውሰድ የማይቻል መሆኑ ይታወቃል" - ገቢዎች ሚኒስቴር

የታክስ ደረሰኝ አጠቃቀም እና አስተዳደር መመሪያን ለማሻሻል በወጣ መመሪያ ቁጥር 118/2017 መሠረት ከቀጣይ ወር ጀምሮ ልዩ መለያ ኮድ የሌለው ደረሰኝ መጠቀም የማይቻል መሆኑን ገቢዎች ሚኒስቴር አስታውሷል።

በዚህም ለግብር ከፋዮች የህትመት ፈቃድ አገልግሎቱን ለመስጠት ቅዳሜ ሙሉ ቀን እንደሚሰራ በደብዳቤ ጠቁሟል።


#ኢትዮጵያ #ገቢዎችሚኒስቴር

@ThiqahEth

17 last posts shown.