TIKVAH-MAGAZINE


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን +251913134524

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


ዛሬ የካቲት 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9:33 ሰዓት ላይ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 2 ካራ ቆሬ በተለምዶ ቢቂላ መናፈሻ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ለፍራሽ መስሪያ የሚሆኑ ግብአቶች በተከማቹበት መጋዘን ላይ የእሳት አደጋ ተከስቷል።

የእሳት አደጋዉን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችና የጸጥታ አካላት እንዲሁም የአካባቢዉ ህብረተሰብ በአደረጉት ርብርብ እሳቱ በአቅራቢያዉ ወዳለዉ መስጂድ እና ሌሎች መኖሪያና ንግድ ቤቶች እንዳይዛመት ማድረግ መቻሉን የእሳትና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አሳውቋል።

በእሳት አደጋዉ በሰዉ ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።

@tikvahethmagazine


በአዲስ አበባ አገልጋዮች ሞባይል ስልክ ይዘው ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ ተከለከሉ።

በኢኦተቤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አገልጋዮች በቅዳሴና ለሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎት ሰዓት ሞባይል ስልክ ይዘው ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ መከልከሉን አስታውቋል።

ሀገረ ስብከቱ ለሁሉም ገዳማትና አድባራት በላከው የመመሪያ ደብዳቤ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሚከናወኑ  የጸሎተ ቅዳሴና ሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎቶች የእጅ ሞባይል ስልክ ይዞ መግባት በጥብቅ መከልከሉን ይገልጻል።

የገዳማትና አድባራት አስደዳሪዎችና ሰበካ ጉባኤያት ጥብቅ ክትትል በማድረግ መመሪያውን እንዲያስፈጽሙ ታዘዋል።

መረጃው ከሀገረ ስብከቱ ሚዲያ ክፍል የተገኘ ነው።

@tikvahethmagazine

33.5k 0 90 43 531

በጂንካ ከተማ አንዲት እናት 4 ልጆችን በአንድ ጊዜ ተገላገለች።

° ''ልጆቹን እማሳድግበት የገቢ ምንጭ ባይኖረኝም ፤እግዚአብሔር ግን 4 ልጆች ስለሰጠኝ በጣም ደስተኛ ነኝ'' ወላጅ አባት


በጂንካ ከተማ  በትላንትናው ዕለት የካቲት 18 አንዲት እናት በአንድ ጊዜ አራት ልጆችን በሰላም መገላገሏን የጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል አስታውቆ ነበር።

እናት ሁለት ወንድና ሁለት ሴት ልጆችን በሆስፒታሉ መውለዷን የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ሚስጥሩ ሀምዴክ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።


ህጻናቱ አሁን በምን ጤንነት ላይ ይገኛሉ ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄም ከአራቱ አንዷ ጨቅላ ትንሽ ኪሎዋ አነስ ስላል በአይ.ሲ ክፍል ውስጥ ክትትል እየተደረገላት ከመሆኑ ወጭ ሌሎች ህፃናት በጥሩ ጤንነት ላይ ናቸው ሲሉ ነግረውናል።

ዶ/ር ሚሥጢሩ አክለውም፥ እናትም በጥሩ ጤንነት ላይ ናት እንደምትገኝ እና ልጆቿን በኦፕራሲዮን በመወልዷ በትንሹ እስከ 3 ቀን በሆስፒታሉ ክትትል እየተደረገላት እንደምትቆይ አስረድተዋል።

ሆስፒታሉ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ እንዲህ አይነት ነገር ሲያጋጥም የመጀመሪያ መሆኑንም የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

የልጆቹ ወላጅ አባት ምን አሉ?

የእነዚህ አራት ልጆች አባት አቶ አንጁሎ አዲስ ይባላል። ባለቤቱ 4 ልጆች ስለተገላገለችበት፤ እሱም የአራት ልጆች አባት ስለሆነበት አጋጣሚ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ባለቤቱ አራት ልጆች እንዳረገዘች እስክትወልድ ድረስ የሚያውቁት ነገር እንዳልነበረና አራት ልጅ መሆኑን ሆስፒታል ከደረሱ በኋላ መስማታቸውን ነው የነገረን። ይህንን ሲያቅም ደስታ እና ድንጋጤ የተቀላቀለበት ስሜት ተሰማኝ ብሏል።

ከጂንካ ራቅ ብሎ በሚገኝ በቦታ እንደሚኖሩ የገለጸው አቶ አንጁሎ፤
ወደ ጂንካ የመጡትም ለህክምና ክትትል እንደሆነ ነው የገለጸው።

በትዳራቸው እነዚህ አራት ልጆች የመጀመሪያ እንዳልዎኑ የሚናገረው አባት ከዚህ በፊት አንድ ልጅ መውለዳቸውንና እድሜውም አሁን ላይ የ4 ዓመት እንደሆነው ጠቅሷል።

"ልጆቹ ትንሽ ሰውነታቸው ቀጫጫ ከመሆኑ ውጭ ደህና ናቸው። እናታቸው ማርታ ታከለም ጡቷ ወተት እንደፈለገ አሁን ላይ አይወጣትም እንጂ እሷም ጥሩ ሁኔታ ላይ ትገኛለች" ሲል አሁን ስላሉበት ሁኔታ አስረድቶናል።

"እኔ አሁን ልጆቹን እማሳድግበት የገቢ ምንጭ ባይኖረኝም፤ እግዚአብሔር ግን 4 ልጆች ስለሰጠኝ በጣም ደስተኛ ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን" ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

በተፈጥሮ በአንድ ጊዜ አራት ህጻናትን መጸነስ የሚከሰተው ከ700ሺ እርግዝናዎች በአንዱ ላይ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

#TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine

32.8k 1 52 12 123

" ከፍተኛ የመድኃኒት፣ የሳሙና እና የተለያዩ ግብአቶች እጥረት ገጥሞኛል " ተስፋ አዲስ የካንሰር ህሙማን ህፃናት ማዕከል

ከተቋቋመ 11 ዓመታት ያለፉት ተስፋ አዲስ የካንሰር ህሙማን ህፃናት ማዕከል ሥራውን የጀመረው
በ2005 ዓ.ም ነበር።

ተቋሙ አሁን ላይ ከአዲስአበባ ውጭ በተለያዩ የክልል ከተሞች በጅማ፣ ጎንደር እና በትግራይ  እየተንቀሳቀሰ ይሰራል።

ዋና ዓላማውም አቅም የሌላቸው በካንሰር በሽታ የተያዙ ህፃናትን ሙሉ ወጫቸውን እስከ አስታማሚ ቤተሰቦቻቸው በመሸፈን ማገዝ ሲሆን ላለፉት ዓመታትም ለብዙ ህጻናት እንደደረሰ ይገልጻል።

አሁን ላይ ወደ ማዕከሉ የሚመጡ ህፃናት ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ከፍተኛ የሆነ የመድኃኒት እጥረት መከሰቱን የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሳራ ኢብራሂም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ድርጅቱ ከተመሠረተበት ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ሦስት ሺሕ ገደማ የሚሆኑ የካንሰር ታካሚ ሕፃናትን ታድጓል ሲሉ ዋና ሥራ አስኪያጇ ገልጸዋል።

አሁን ላይ ደግሞ ባሉት የአዲስ አበባ፤ የጅማ፤ ጎንደር እና መቐሌ ማዕከላት ለ260 ህፃናት እና ቤተሰቦች ሙሉ ወጫቸውን በመሸፈን አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

በተጨማሪም በተመላላሽ እና በቋሚ የህክምና አገልግሎት ደግሞ ከ1140 በላይ ለሚሆኑ ማዕከሉ እየሰጠ መሆኑን ሥራ አስኪያጇ ገልፀዋል።

አያይዘውም ህፃናት ሕክምናቸውን እንዳያቋርጡ  ከማደሪያ እስከ ምግብና መድኃኒት፣ የሥነ ልቦና ትምህርት እንዲሁም የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጠን ነው ሲሉ ሥራ አስኪያጇ ተናግረዋል።

እስካሁን ለማዕከላቱ ድጋፍ የሚያደርጉ ድርጆቶች ድጋፋቸውን ባያቋርጡም ድጋፉ ግን በቂ ባለመሆኑ በማዕከሉ ከፍተኛ የሆነ የመድሀኒት እና የሳሙና እጥረት መከሰቱን ወ/ሮ ሳራ ጠቁመዋል።

የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ሳሙና፣ ዱቄት ወተት፣ ስኳር፣ ዘይት እና የመሳሰሉ ድጋፎችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን በመግለጽ አሁን ላይ ግን ድጋፉ መቀዛቀዙን አክለዋል።

የካንሰር በሽታ ረጅም ጊዜ የህክምና ክትትል ስለሚወስድ ማዕከሉ ለታካሚዎች እና ላስታማሚዎች ሲሰጥ የነበረውን አገልግሎት ለመቀጠል የግብአት አቅርቦት እጥረት በመከሰቱ ማኅበረሰቡ በአይነትም ሆነ በገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

ማዕከሉን ማግኘት እና ድጋፍ ማድረግ ለምትፈልጉ

📌አዲስአበባ :- ወ/ሮ ሳራ ኢብራሂም
ስልክ:- 0911725455
📌ጅማ :- ወ/ሮ ብርቱካን
ስልክ:- 0935071136
📌ጎንደር:- አቶ ወንድሙ
ስልክ:- 0928503970
📌መቀሌ:- ወ/ሮ ጺዮን
ስልክ:- 0904231532

እንዲሁም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ Tesfa Addis Parents Childhood Cancer Organization (TAPCCO) 1000036686492

#TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine


አንድ ወር ያስቆጠረውና መጨረሻው ያለየለት የUSAID እግድ

የትራምፕ አስተዳደር ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ ካሳለፋቸው ውሳኔዎች መካከል የUSAID እንቅስቃሴ ላይ የ90 ቀን እቅድ መጣል ሲሆን ይህ እግድ ከተጣለ 35 ቀናት አልፈዋል።

ኢትዮጵያ ከአሜሪካ በUSAID በኩል የምታገኘው ድጋፍ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገሮች ውስጥ ትልቁ ነው። በድርቅና በርስ በርስ ግጭት ውጥ ላሉ ዜጎች የአሜሪካ መንግስት በ2023 1.77 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ አድርጓል።

USAID በኢትዮጵያ ከምግብ እርዳታ ቀጥሎ ሁለተኛው ትልቁ ቅድሚያ የሚሰጠው ዘርፍ ጤና ሲሆን በዓመት 200 ሚሊዮን ዶላር ፈሰስ ይደረግበታል።

USAID በዓመት 200 ሚሊዮን ዶላር ለጤናው ዘርፍ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኩል ፈሰስ ያያደርጋል። ጤና ሚኒስቴር ይህንን ለክልሎች የማከፋፈሉን ሥራ ይሰራል። በተጨማሪም ተላላፊ በሽታዎችና የተመጣጠነ ምግብ ላይ የሚሰሩ ፕሮጀክቶችንም ይደግፋል። ይህ አሁን ላይ ቆሟል።

በኢትዮጵያ በግጭት፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና የገንዘብ እጥረት ምክንያት የወባ ተጠቂዎች በ2019 ከነበረው 900 ሺ በ2024 ወደ 7.3 ሚሊዮን ተጠቂዎች ከፍ ብሏል። የኩፍኝ በሽታም ከ2021 ከ 1,941 ተጠቂዎች ወደ በ2024 ወደ 28,129 ከፍ ብሏል።

ሌላው ትልቁ ጉዳይ ደግሞ የኤችአይቪ ኤድስ የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራዎች ላይ ያለው ድርሻ ነው። ለዚህ ተግባር በ2023 ብቻ 3 ቢሊዮን ዶላር ከአሜሪካ መንግስት ፈሰስ ተደርጓል።

በተጨማሪም በUSAID የሚደገፉ ፕሮግራሞች ለኤች አይ ቪ፣ ለሳንባ ነቀርሳ እና ለወባ መድኃኒቶችን ወደ ገጠር ክሊኒኮች ማድረስም ቆመዋል።

የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር በአሜሪካ እርዳታ የተቀጠሩ ከ 5,000 በላይ ሰራተኞችን ለማባረር ሊገደድ እንደሚችልም መገለጹ ይታወሳል።

በሰብዓዊ እርዳታው በኩልም በተመሳሳይ አሁን ባለው ተጨባጭ ኹኔታ፣ የዓለም ምግብ ፕሮግራም የምግብ አቅርቦቶቹን ከጨረሰ፣ ተጨማሪ የዕርዳታ ምግብ መግዛት እንደማይችል ገልጿል።

ዘጋርዲያን ይዞት በወጣው ዘገባ ማሽላና የምግብ ዘይትን ጨምሮ 2 ነጥብ 1 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎችን ለአንድ ወር መመገብ የሚችል 34 ሺሕ 800 ሜትሪክ ቶን እህል፣ ወደ አገር ውስጥ ለሚያስገቡ አካላት የሚከፈል ገንዘብ ባለመኖሩ ጅቡቲ ወደብ ላይ መቆሙን ገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያ ከፍተኛውን የስደተኞች ቁጥር የምታስተናግድ ሀገር እንደመሆኗ ነገሮችን ከባድ ያደርጉታል።

USAID ለኢትዮጵያ በ2023 የ1.8 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ሲያደርግ በዚሁ ጊዜ ኢትዮጵያ 1.4 ቢሊዮን ዶላር የእዳ ክፍያ ፈጽማለች። የUSAID ድጋፍ መቆም ኢትዮጵያ በጀመረችሁ ኢኮኖሚክ ሪፎርም ላይ የሚኖረው ተጽዕኖም ቀላል አይደለም።

በኢትዮጵያ ከ5 ሺ በላይ የሲቪክ ማኅበራት በUSAID ድጋፍ የጀመሯቸው ፕሮጀክቶች ጭምር በመቆማቸው በእነዚህ ተቋማት እና በየፕሮጀክቱ የሚሰሩ ሰራተኞች ላይ ከፍተኛ ጫናም የፈጠረ ነው።

ሀገራት ለአሜሪካ ድንገተኛ ውሳኔ አማራጭ እቅዶችን መንደፍ ግድ ይላቸዋል። ኢትዮጵያም ከዲፕሎማሲያዊ እስከ ሀገር ውስጥ ገቢን እስከማሳደግ እንዲሁም ወጪ ቅነሳ እና የበጀት ዝውውር እቅዶችን እንደ አማራጭ ልትመለከት ትችላለች።

እውን ይህ ክስተት እንደ የዛምቢያው ፕሬዝዳንት ሃካይንዴ ሂቺሌማ አገላለጽ "የማንቂያ ደውል" ይሆን ?

የትራምፕ አስተዳደር የ90 ቀኑን እግድ ሲጠናቀቅ የመጨረሻ ውሳኔው ምን ይሆን ? የኢትዮጵያ መንግስትስ መፍትሔ?


@tikvahethmagazine


"እናቴም አርጅታለች እስካሁን ከመታገቷ ውጭ በእህቴ ላይ የሚደርስባትን ድብደባ አሳይቻት አላቅም ምክንያቱም ካየች ትሞትብናለች" የታጋች እህት

አዜብ ሽሙየ ትባላለች። በወልቃይት ጠገዴ ቃፍታ ሁመራ ዓዲ ሕርዲ ከተማ ተወልዳ ያደገች የ17 ወጣት እና የ9ኛ ክፍል ተማሪ ነበረች።

ያልፍልኛል ብላ በመስከረም ወር 2017ዓ/ም በሱዳን በረሀ በሊብያ አቋርጣ ስትሰደድ ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም አብሮዋት ከተጓዙ ሁለት የአከባቢዋ ሴት ልጆች ጋር በአጋቾች ስር ትወድቃለች።

የታጋች እህት መሆኗን ጠቅሳ መረጃውን ያደረሰችን ወይዘሮ ናፈቁሽ ሙሉ ስለ ጉዳዩ ስታስረዳ "እኛ ምንም አይነት ገንዘብ የለንም። አባታችን ጥበቃ ነበር የሚሰራው አሁን ጡረታ ወጥቷል። እናቴም አርጅታለች እስካሁን ከመታገቷ ውጭ በእህቴ ላይ የሚደርስባትን ድብደባ አሳይቻት አላቅም ምክንያቱም ካየች ትሞትብናለች" ስትል ትገልጻለች።

"በየቀኑ እየደበደቡ በኢሞ እና በዋትሳብ (Whatsapp) ቪዲዮ ይልኩልናል። በየቀኑ ገንዘቤን ትልኩ እንደሆነ ላኩ ካላካችሁ እህትሽ እንደሞተች ቁጠሪያት ይሉኛል " ስትል በእንባ ጭምር ያለችበትን ሁኔታ ታስረዳለች።

አጋቾቹ 750 ሺሕ ብር መጠየቋቸውን  በመጥቀስ "ገንዘቡን መላክ አልቻልኩም፤ ወላጆቻችን አዛውንቶች ናቸው ፣ ያለሽን ላኪ እና እንልቀቅልሽ ሲሉኝ ጥር 21/2017 ዓ.ም 250 ሺህ ብር  በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር ልኬላቸው ነበር። ነገር ግን እንኳን ሊለቋት ይቅር እና የሚፈፅሙባትን ጥቃት መናገርም መስማትም ይሰቀጥጣል " ስትል ታስረዳለች።

በወልቃይት ጠገዴ ቃፍታ ሁመራ ወረዳ በመንግስት መስሪያ ቤት ተቀጥረው እንደሚሰሩ ገልፀው  አሁን ባላቸው አነስተኛ ደመወዝ የተጠየቁትን ገንዘብ ማሟላት  እንደማትችል አስረድታለች።

የ17 ዓመት ታዳጊዋ አዜብ ላይ እገታው ሲፈፀም አብረዋት ሁለት ኢትዮጵያን ቢኖሩም ሁለቱም ቤተሰቦቻቸው የተጠየቁትን ገንዘብ በመክፈላቸው መለቀቃቸውን ጭምር ገልጻለች።

"የኔ እህት ግን ለአምስት ወራት በአረመኔዎች እጅ ናት፣ ሁሌም የሚልኩልኝን ቪዲዮ እያየሁ ለእህቴም ሳልደርስላት መሞቴ ነው" ስትል ሀዘኗን ገልጻለች።

በመሆኑም ቤተሰቦቻችን የገጠር ነዋሪ ከመሆናቸውም በላይ  በእድሜ የገፉ እና የተጠየቁትን ገንዘብ ለመክፈል ይቅርና ለራሳቸውም እየተጦሩ ነው የሚኖሩት በማለት የቤተሰቦቻቸውን ሁኔታም አስረድተዋል።

"ለቤተሰቦቻችን መታገቷን እንጂ የሚደርስባትን ሲቃይ ነግሬያቸው አላቅም ያም ሆኖ ግን ሁሌም እያለቀሱ ነው። እኔም መኖሬ ትርጉም አልባ ሆኖብኛል" ስትል የታጋች እህት ወይዘሮ ናፈቁሽ ሙሉ ነግረውናል።

የታጋቿ እህት ፣ ታጋቿ  አዜብ በአጋቾች እየደረሰባት ያለውን ስቃይ የሚያሳይ ቪዲዮ የላኩ ሲሆን፣ አጋቾችዋ ኢትዮጵያውያን ወይም ኤርትራውያን መሆናቸው በደብደባ ወቅት ከሚናገሩት የትግርኛ ቃላት መረዳት ይቻላል።

በተጨማሪም እህቷ 250 ሺ ብር የላከችበትን የባንክ መረጃም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አጋርታለች።

መርዳት ለምትሹ 1000456940041 የወይዘሮ ናፈቁሽ ሙሉ የንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር ነው። ወይዘሮ ናፈቁሽን በዚህ ስልክ 0938602801 ማግኘት ይቻላል።

@tikvahethmagazine

33.8k 0 17 11 239

የሶማሊላንድ ፖሊስ ህገ-ወጥ ያላቸውን የኢትዮጵያ ስደተኞችን የማባረር ዘመቻ ጀምሯል።

እሁድ ጠዋት የፖሊስ ተሽከርካሪዎች በሐርጌሳ ገበያ አካባቢዎች ሲዞሩና በህገ-ወጥ መንገድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ሲይዙ ታይተዋል።

ብዙ ኢትዮጵያውያን በሶማሊላንድ በስደተኞች ካርድ፣ በቪዛ ወይም በስራ ፈቃድ ቢኖሩም፣ በየዓመቱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ወደ ሶማሌላንድ በህገ-ወጥ መንገድ ይገባሉ።

የሶማሊላንድ ባለስልጣናት አዲስ ስለተጀመረው እንቅስቃሴ በይፋ የሰጡት አስተያየት የለም።

የሶማሊላንድ ፖሊስ ህገ-ወጥ የኢትዮጵያ ስደተኞችን ለማባረር ዘመቻ የጀመረው የፑንትላንድ ባለስልጣናት ከ1,000 በላይ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ከጋሮዌ እና ቦሳሶ ከተሞች ካባረሩ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ነው።

የፑንትላንድ መንግስት በአል-ሚስካት ተራሮች ውስጥ ከሚንቀሳቀሰው የአይሲስ ቡድን ጋር አንዳንድ የውጭ ዜጎች እንደተቀላቀሉ በሚገልጹ ሪፖርቶች ምክንያት የጸጥታ ስጋትን በምክንያትነት በመጥቀስ ህገ-ወጥ ስደተኞችን ላይ ያለውን እርምጃ ማጠናከሩን ገልጿል።

Source : Hiiraan Online

@tikvahethmagazine

36k 0 25 16 65

ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ በኩሬ ውስጥ ለመዋኘት የገቡ 4 ታዳጊዋች ህይወት አለፈ።

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ጉለሌ ዕጽዋት ማዕከል ግቢ ውስጥ ውሀ በአቆረ ጉድጓድ (ኩሬ) ዉስጥ ዋና ለመዋኘት የገቡ ሦስት ታዳጊዋች ህይወታቸዉ ማለፉ ተገልጿል።

ታዳጊዎቹ ትላንት እሁድ ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ኳስ ሲጫወቱ ቆይተዉ በዕጽዋት ማዕከሉ ጊቢ ዉስጥ ባለው ውሀ በአቆረ ጉድጓድ ዉስጥ ዋና ለመዋኘት በገቡበት ወቅት አደጋው ማጋጠሙን የአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ የታደጊዎቹ ዕድሜ ሁለቱ የ13 ዓመት እድሜ ያላቸው ሲሆኑ አንደኛዉ ደግሞ 16 ዓመቱ መሆኑን በመግለጽ የኮሚሽን መሥሪያ ቤቱ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችና ጠላቂ ዋናተኞች የታዳጊዎቹን አስከሬን አዉጥተዉ ለፖሊስ ማስረከባቸውን ተናግረዋል።

በዚሁ በጉለሌ ዕጽዋት ማዕከል  ዉስጥ ጥቅምት 02 ቀን 2017 ዓ.ም ዕድሜዉ 16 ዓመት የተገመተ ወጣት በተመሳሳይ ሁኔታ  በጉድጓዱ ውስጥ ዋና ለመዋኘት ገብቶ ህይወቱ ማለፉን የኮሚሽኑ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አስታውሰዋል፡፡

በሌላ በኩል ቅዳሜ የካቲት 15 ቀን 2017 ዓ.ም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ክበበ ጸሀይ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ውሀ ባቆረ ጉድጓድ ዉስጥ ዋና ለመዋኘት የገባ የ14 ዓመት ታዳጊ ህይወቱ ማለፉንም ገልጸዋል፡፡ የኮሚሽኑ ጠላቂ ዋናተኞችም የታዳጊዉን አስከሬን አውጥተው ለፖሊስ አስረክበዋል ነው ያሉት።

በአዲስ አበባ በአንዳንድ አካባቢዎች ውሀ ባቆሩ ጉድጓዶች ውስጥ ዋና ለመዋኘትና ለመታጠብ በሚል በተለይ ታዳጊዎችና ወጣቶች እየገቡ ህይወታቸዉ እያለፈ እንደሚገኝ ነው የተገለጸው።

ጉድጓዱን የቆፈሩና በዉሀ የሚጠቀሙ አካላት ተገቢዉን የአደጋ መከላከል ስራ የማከናወን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ እና የአካባቢዉ ማኅበረሰብም ለታዳጊዋች አስፈላጊዉን ጥበቃ እንዲያደርግ ኮሚሽን መሥሪያ ቤቱ አሳስቧል።

ዘገባው የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ነው።

@tikvahethmagazine


📣 ከደቂቃዎች በፊት ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ በተደጋጋሚ ተከስቷል። እናንተ አከባቢ እንዴት ነው ?

@tikvahethmagazine

35.4k 0 51 415 177

ብርሽን አበዛልሻለው በማለት ባጭበረበረው ገንዘብ ባጃጅ የገዛው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ዋለ።

"ባህላዊ መድኃኒት ቀማሚ ነኝ ፀሎት አደርግልሻለው ብርሽንም አበዛልሻለው" በማለት ከአንዲት ግለሰብ ከ736ሺ ብር በላይ በማታለል የተቀበለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ጎፋ ቅዱስ ገብርኤል አደባባይ አካባቢ ነው። ግለሰቡ ከግል ተበዳይ አጭበርብሮ በተቀበለው ገንዘብም ባጃጅ ገዝቶ በተቀመጠበት ቴፒ ከተማ በቁጥጥር ስር መዋሉን የፖሊስ መረጃ ያሳያል።

ተጠርጣሪው የባህላዊ መድኃኒት ቀማሚ እና ፈዋሽ ነኝ በሚል "አባ መንግስቱ" የሚል ማህበራዊ ሚዲያ በመክፈት አንዲት ታዋቂ የኢትዮጵያ አርቲስት የሰጠችውን ኃይማኖታዊ የፈውስ ምስክርነት ከሌላ ሰው ላይ አውርዶ በራሱ አካውንት የፈወስኳት እኔ ነኝ በማለት ይለቃል።

ይህን ቪዲዮ የተመለከተች የግል ተበዳይ ባህላዊ መድኃኒት እፈልጋለሁ በማለት ወደ ግለሰቡ በመደወል ስትጠይቅ እንደሚሰራላት ይነገራታል።

ከጊዜ በኋላ ግለሰቡ አካውንትሽ ላይ ስንት ብር አለ ብሎ ግለሰቧን በመጠየቅ ብርሽን አበዛልሻለው ብሎ በማሳመን በተለያ ስም በከፈተው የባንክ አካውንት በተለያዩ ጊዜያት እና ቀናት በድምሩ 652ሺ ብር ወደ ራሱ አካውንት እንድታስገባለት ያደርጋል።

ይህም አልበቃው ብሎ ከሌሎች ተበድራ 84,800 ብር ተጨማሪ እንድታስገባለት ማድረጉን በጎፋ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የተጣራው የወንጀል ምርመራ መዝገብ ያስረዳል።

ተከሳሽ በአጠቃላይ 736,800ብር እንዲላክለት ያደረገ ሲሆን ብርሽ በዝቶልሽ ይመለስልሻል እያለ ቀጠሮ እየሰጠ ሲጠፋ እና መታለሏ የገባት የግል ተበዳይ ወደ ፖሊስ በመምጣት የተፈፀመባትን ወንጀል ትናገራለች።

ፖሊስም የግለሰቧን አቤቱታ መነሻ በማድረግ እና የምርመራ መዝገብ በማደራጀት ለግለሰቡ የተላከበትን አካውንት ሲያጣራ ግለሰቧ በተለያዩ ቀናት በተለያየ አካውንት ገንዘቡን መላኳን አረጋግጧል።

ግለሰቡ በተለያዩ ስሞችና በተለያዩ ባንኮች አካውንት መኖሩን ያጣራው ፖሊስ ግለሰቡን የፍርድ ቤት መያዣ ትዕዛዝ በማውጣት ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ደቡብ ምዕራብ ክልል በምትገኘው ቴፒ ከተማ ድረስ በመሄድ በቁጥጥር ስር ማዋል ችሏል።

ግለሰቡ በቁጥጥር ከዋለ በኋላ በተላከለት ገንዘብ ኮድ (1) 05224 ደቡብ ምዕራብ  ጊዜያዊ ሠሌዳ ያለው አንድ ባጃጅም የገዛ ሲሆን ተጠርጣሪው ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ ገልጿል።

አሁን አሁን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እፈውሳለሁ ባህላዊ መድኃኒት ቀማሚ ነኝ የሚሉ ምንም አይነት እውቅናና ፍቃድ የሌላቸው ግለሰቦችን እያስተዋሉ መሆኑንና ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ፖሊስ አሳስቧል።

🔗 ከላይ በ Screenshots የተያያዙት ፎቶ 1 እና ፎቶ 2 "አባ መንግስቱ" በሚል ስም የተከፈተ የቴሌግራም ግሩፕ ለማሳያነት የተወሰደ ሲሆን ተጠርጣሪው የዚህ ግሩፕ አስተዳዳሪ ይሁን አይሁን በፖሊስ መረጃ ላይ የተገለጸ ነገር የለም።

@tikvahethmagazine


🟢 "ቤንዚን በ8 ቀን አንደዬ ብቻ ነው የምንሞላው፣ የባንክ ብድራችንን መክፈል አልቻልንም፣ ቤተሰቦቻችን ችግር ላይ ናቸው " - የደሴ ከተማ የቤንዚን ተጠቃሚ ታክሲ አሽከርካሪዎች

🟢 "ተራ አስከባሪዎችን በከተማዋ ሙሉ በሙሉ እንዳይሰሩ ታግደዋል" - የደሴ ከተማ ንግድ ቢሮ

የከተማ አስተዳደሩ የቤንዚል ተጠቃሚ ታክሲዎች በስምንት ቀን አንድ ቀን ብቻ ያውም 50 ሌትር እንድንሞላ በማድረጉ ቤተሰቦቻችን ችግር ውስጥ ናቸው ሲሉ የደሴ ከተማ  አሽከርካሪዎች ቅሬታ አቅርበዋል።

የቤንዚን እና የነዳጅ አቅርቦት ችግር በአገር አቀፍ ደረጃ መኖሩ የሚታወቅ ነው ያሉት የደሴ ከተማ ንግድ ቢሮ መምሪያ ሃላፊ አቶ ዮናስ እንዳለ በደሴ ከተማም የአቅርቦት ችግር መኖሩን ገልፀዋል።


ቅሬታ አቅራቢዎቹ በዝርዝር ምን አሉ?

"እኛ የቤንዚል ተጠቃሚ ታክሲ አሽከርካሪዎች በደሴ ከተማ 18 ነን የከተማ አስተዳደሩ በ8 ቀን አንድ ቀን ብቻ ቤንዚን መሙላት እንድንችል በማድረጉ በወር ውስጥ ለ4 ቀን ነው መስራት የምንችለው" ብለዋል።

በተጨማሪም "ለከተማው ንግድ ቢሮ ቅሬታ ስናቀርብ 'የቤንዚል እጥረት አለ ይለናል' ነገር ግን በከተማችን በየመንገዱ በጥቁር ገበያ ቤንዚን ሲቸረቸር በስፋት ይስተዋላል" ሲሉ አብራርተዋል።

"መኪኖችን የገዛነው በባንክ ብድር ነው፤ አሁን ላይ በየወሩ ለባንክ የምንከፍለውን ብድር መክፈል ባለመቻላችን ባንኮች ማስጠንቀቂያ እየሰጡን ነው ሲሉም" አክለዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ፥ በተደጋጋሚ ለከተማ አስተዳደሩ፣ ለንግድ ቢሮ እና ለብልፅግና ፅህፈት ቤት ቅሬታችንን አቅርበናል፤ ምላሽ የሰጠን አካል ግን የለም ሲሉ ያሉበትን ችግር አስረድዋል።

ስሙን መግለፅ ያልፈለገው አሽከርካሪ ከጥቅምት ወር ጀምሮ እስካሁን ቤንዚል በሳምንት አንድ ቀን ብቻ ከማደያዎች መቅዳት እንድንችል ተደርገናል ሲል ተናግሯል።

አያይዞም ፥"እኔ መኪናውን የገዛሁት 280 ሺ ብር ከባንክ ተበድሬ ነው እሱን የምከፍለው እየሰራሁ በየወሩ ነበር አሁን ግን ያበደረኝ ባንክ ብድርህን በየወሩ መክፈል አልቻልክም ብሎ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶኛል" ሲል ገልጿል።


የደሴ ከተማ ንግድ ቢሮ መምሪያ በጉዳዩ ላይ ምን አለ ?

የደሴ ከተማ ንግድ ቢሮ መምሪያ ኃላፊ አቶ ዮናስ እንዳለ በምላሻቸው ተሽከርካሪዎች ለከተማችን ማህበረሰብ የሚሰጡትን የትራንስፖርት አገልግሎት ታሳቢ በማድረግ የከተማ እና የኤርፖርት ታክሲዎች በ 8 ቀን አንድ ቀን እና ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ደግሞ በየቀኑ መሙላት እንድችሉ አድርገናል ብለዋል።

ይህም የሆነበት ምክንያት አንዳንድ አሽከርካሪዎች የሚሞሉትን ቤንዚን ለትራንስፖርት አገልግሎት ከማዋል ይልቅ በህገወጥ መንገድ እየቸረቸሩ ስላስቸገሩን እንደ ከተማ አስተዳደር ጥናት በማድግ ከክልሉ ንግድ ቢሮ ጋር በመነጋገር በተላከልን መመሪያ መሰረት ነው ሲሉ ገልፀዋል።

አሽከርካሪዎች መመሪያው ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ  የተለያዩ ቅሬታዎችን እያቀረቡ ነው ያሉት ሃላፊው እኛም ቅሬታቸውን ተቀብለን ለክልሉ ንግድ ቢሮ አሳውቀናል፣ ነገር ግን ከክልሉ ቢሮ የተሰጠን አቅጣጫም ሆነ መመሪያ
#የለም ብለዋል።

አያይዘውም በተደጋጋሚ ቅሬታቸውን ስላቀረብን በቅርቡ መመሪያ ይሰጡናል ብለን እንጠብቃለን። ካልሆነ ግን እንደ ከተማ ክልሉን አሳውቀን የምንወስደው አሰራር ካለ እንወስዳለን " ሲሉ አስረድተዋል።

በከተማችን የቤንዚን አቅርቦት መሰረታዊ ችግር ነው ያሉት ኃላፊው በየማደያዎች የሚሰሩ ተራ አስከባሪዎች ግር ግር በመፍጠር ያለአግባብ ገንዘብ እየተቀበሉ ችግር እየፈጠሩ ነበር ብለዋል።

ስለሆነም ለህገወጥ ችርቻሮ መስፋፋት ቁልፍ ሚኒ ስለነበራቸው አሁን ላይ ተራ አስከባሪዎችን በከተማዋ ሙሉ በሙሉ እንዳይሰሩ ታግደዋል ሲሉ አብራርተዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ከከተማ አስተዳደር እና ከፀጥታ ሃይሎች ጋር በጋራ በመሆን በባለፈው ሳምንት በህገወጥ መንገድ ሊቸረቸር የነበረ ከ 620 ሊትር በላይ ቤንዚን በፖሊስ ቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ጠቁመዋል።

በመጨረሻም አሽከርካሪዎቹ ቤተሰብ አስተዳዳሪ በመሆናችን የሚመለከተው አካል ችግራችንን ሰምቶ በአስቸኳይ ምላሽ ይሰጠን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።


#TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine


🔈 #የነዋሪዎችድምጽ

° በዚህ ሳምንት በሸቀጣ ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መኖሩን ባደረግነው ምልከታ ለመረዳት ተችሏል።

° የመርሳ ከተማ ነዋሪዎች የዋጋ ንረቱን በተመለከተ ከሰሞኑ ቅሬታ አቅርበዋል

በአዲስ አበባ ከተማ እና በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች በዚህ ሳምንት በሸቀጣ ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መኖሩን ባደረግነው ምልከታ ለመረዳት ተችሏል።

በአዲስ አበባ ፣ በደሴ እና በመርሳ ከተማ እንዲሁም በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች ከዚህ ቀደም 1300  ብር  ይሸጥ የነበረው አምስት ሊትር የምግብ ዘይት አሁን ላይ 1600 ብር እየተሸጠ ሲሆን ከዚህ በፊት ከነበረው የመሸጫ ዋጋ  ከ200 መቶ እስከ 300 ብር  ጭማሪ አሳይቷል።

እንዲሁም 1 ኪሎ ምስር ከ200 ወደ 280 ፣ እንቁላል ከብር 11 ወደ 19 ፣ 1 ሊትር ዘይት ከ285 ወደ 310 ብር  ከፍ ያለ ሲሆን ሌሎች ምርቶች ላይ በአንድ ሳምንት ውስጥ የተጋነነ የዋጋ ጭማሬ መኖሩን በምልከታችን ወቅት ለማየት ችለናል።

በሌላ በኩል ደግሞ በአማራ ክልል ደሴ ከተማ  3 ሊትር ዘይት ከ 700 ወደ 900 ብር፣ 5 ሊትር ዘይት ከ 1300 ወደ 1550 ብር፣  አንድ ኪሎ ድንች ከ 40 ወደ 80 ብር በእጥፍ መጨሩን ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከሰሞኑ የሰሜን ወሎ ዞን መርሳ ከተማ ነዋሪዎች በየጊዜው በመሰረታዊ ፍጆታ ቁሳቁሶች ላይ የሚታየውን የዋጋ ጭማሪ መቋቋም አልቻልንም ሲሉ ቅሬታ አቅረበዋል።

በተጨማሪም  ቅሬታ አቅራቢዎች በከተማዋ ያለውን የዋጋ ንረት በዝርዝር ያስረዱ ሲሆን " እስካሁን 5 ሊትር ኡመር ዘይት 1300 ብር ነበር የምንገዛው አሁን ግን 1600 ብር ነው ፣ አንድ ሊትር ዘይት 225 ብር እስካሁን እንገዛ የነበረው አሁን ላይ 330 ብር  ደርሷል " ብለዋል።

አክለውም 50 ኪሎ ነጭ ዱቄት እስካሁን 4ሺህ 200 ብር እንገዛ ነበር ያሉት ነዋሪዎች አሁን ላይ ግን 4 ሺህ 600 ብር እየገዛን ነው ሲሉ ገልፀዋል።

ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ያቀረቡት የመርሳ ከተማ ነዋሪዎች በየጊዜው በመሰረታዊ ፍጆታዎች ላይ የሚደረገው የዋጋ ጭማሪ  ኑሮአቸውን ፈታኝ እንዳደረገባቸው ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ መፍትሄ የሚሰጠን አካል ካለ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ በፍጥነት እርምጃ ይወሰድልን ሲሉ ጥሪም አቅርበዋል።


የመርሳ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ሃላፊን አቶ አራጋው ተስፉ ምን አሉ?

የመርሳ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት  ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አራጋው ተስፉ ማህበረሰቡ የቀረበው ቅሬታ አግባብነት ቢኖረውም በዚህን ያክል የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ የለም ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም በከተማዋ
እስካሁን የነበረው የዋጋ ንረት አሁን ላይ በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል ብለዋል።

በተጨማሪም በዚህ ወር በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች የዋጋ ጭማሪ መኖሩን ያነሱት ሃላፊው በመርሳ ከተማም በአንዳንድ ምርቶች ላይ ጭማሪ መኖሩን ጠቁመዋል።

ይሁን እንጂ ይሄ የዋጋ ጭማሪ በነጋዴዎች የመጣ ሳይሆን ምርቶችን ከሚያመርቱት ድርጅቶች ስለመሆኑ ገልፀዋል።

ሃላፊው ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመነጋገር የዋጋ ጭማሪ የሚታይባቸውን መሰረታዊ ፍጆታዎች ለምሳሌ ጤፍ፣ ማሽላ ፣ ነጭ ዱቄት፣ ዘይት፣ ስኳር፣ ፖስታ፣ መኮረኒ እና የመሳሰሉትን የእለት ከእለት ፍጆታዎች  ከተለያዩ ፋብሪካዎች በማስመጣት ለማህበረሰቡ በቀጥታ በማድረስ የገበያ ሥርዓቱን አረጋግተነዋል ብለዋል።

በመሆኑም ከዚህ በፊት የ1 ኪሎ ጤፍ ዋጋ ከ185 ብር በላይ ነበር፣  ከጥር ወር ጀምሮ ከ130 እስከ 140 ብር እየተሸጠ ነው። 50 ኪሎ ዱቄት ከፋብሪካው  የሚወጣው  በ4500 ብር ነው እኛ ጋር እየተሸጠ ያለው የትራንስፖርት ተጨምሮ ከ4550 እስከ 4600 ብር ነው።

ከዚህ በፊት የአንድ ኪሎ ማሽላ ዋጋ ከ 130 እስከ 150 ብር ነበር ያሉት ሃላፊው አሁን ላይ ከ60 እስከ 120 ብር እየተሸጠ ስለመሆኑ ገልፀዋል።

በመጨረሻም ሃላፊው በመርሳ ከተማ አሁን ላይ ከሁሉም የአማራ ክልል ከተሞች በተለየ ታላቅ የሆነ የዋጋ ቅናሽ መኖሩን አመላክተዋል።


#TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine


''በርካታ የልብ ታማሚዎች ወረፋ ሳይደርሳቸው ህይወታቸውን ያጣሉ '' - ዶክተር ፈቀደ አግዋር

በኢትዮጵያ የልብ ህክምና በተሟላ ሁኔታ እየተሰጠ የሚገኘው አዲስ አበባ ከተማ በመሆኑ ወረፋ ሳይደርሳቸው ህይወታቸው የሚያልፉ የልብ ታማሚዎች መኖራቸው ይነገራል።

ዶክተር ፈቀደ አግዋር በኢትዮጵያ የልብ ህክምና ማዕከል ''የልብ ቀዶ ጥገና'' ሀኪም ናቸው። 800 የልብ ቀዶ ጥገና አድርገዋል። በሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ ደግሞ (HVE) 25 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ነፃ የልብ ቀዶ ጥገና ለ30 ታዳጊዎች ሰርተዋል። በተጨማሪም "የልብ ጠጋኙ ማስታወሻ" የተሰኘ መጽሐፍም ለአንባቢ አበርክተዋል።

ዶ/ር ፈቀደ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሀራ በርሀ በታች ባሉ ሀገሮች ላይ በአሁኑ ሰዓት በተደጋጋሚ በሚከሰት ቶንሲል ምክንያት የሚፈጠር የልብ ህመም ከህፃናት እስከ አዋቂዎች ድረስ በከፍተኛ ሁኔታ ለልብ ህመም መፈጠር ምክንያት እንደሆነ ይናገራሉ።

በቅርቡ በሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ (HVE) የነጻ ህክምና ተጠቃሚዋ መሆን የቻለችው የ18 አመቷ ታዳጊም የልብ ህመሟ በቶንሲል ምክንያት የተከሰተ ሲሆን 4 ሰዓታት በፈጀው አንድ የግራ ልብ በር ቀዶ ጥገና በቶንሲል ምክንያት ክፋኛ የተጎዳው የታዳጊዋ የልብ በር በመቀየር የተሳካ ህክምና አድርጋለች።

የልብ ቀዶ ጥገና ህክምና የሚሰጠው ደረት ተከፍቶ፣ ልብና ሳንባ ቁሞ፣ የደም ዝውውር ለማሽን ተሰጥቶ በመጨረሻም ልብ ተከፍቶ ህክምናው እንደሚሰጥና በዚህም ብዙ የህክምና ሂደቶችን እንደሚያልፍ ዶ/ር ፈቀደ ያስረዳሉ።

የልብ ህመም በተፈጥሮ ሊከሰት የሚችል ሲሆን በዓለም ላይ ''ከ1 ሺ ሰው 10 ሰው'' በተፈጥሮ የልብ ችግር ይኖርበታል ተብሎ ይታሰባል።

በሌላ በኩል ደግሞ በደም ግፊት፣ በስኳር በሽታ ምክንያትም የልብ ህመም እንደሚከሰት የልብ ሀኪሙ ዶክተር ፈቀደ ገልፀዋል።

አሁን ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ የልብ ህክምና በተሟላ ሁኔታ የሚሰጠው በአዲስ አበባ በመሆኑ ለታማሚዎች ፈተና እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል።

"በሽዎች እሚቆጠሩ ሰዎች ወረፋ ይጠብቃሉ፣ወረፋ ሳይደርሳቸው በርካቶችም ህይወታቸውን ያጣሉ'' ብለዋል።


በመጨረሻም ተሳክቶላቸው ወረፋ ሲደርሳቸው በጣም ያረፈዱና የተወሳሰቡ ህክምና እንድንሰጥ እንገደዳለን ሲሉ ዶ/ር ፈቀደ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል።

"ለአንድ የልብ ህመምተኛ ህክምና ለመስጠት በርካታ ባለሙያዎች፣ ብዙ ማሽን ጥቅም ላይ ይውላላል ከዚህ አንፃር በአሁኑ ሰአት በኛ ሀገር የልብ ህክምና ገና ጅማሮ ላይ ነው ማለት እንችላለን" ብለዋል።


እንደ መፍትሔ . . .

በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ሁሉንም ነገር ያሟላ የልብ ህክምና የሚሰጠው ተቋም የኢትዮጵያ የልብ ህክምና ማዕከል እንደሆነ ዶ/ር ፈቀደ አግዋር ይናገራሉ።

ይህን ማዕከል አሳድጎ ትምህርት ቤት በማረግ ብዙ የልብ ህክምና ባለሙያዎችን በማፍራት በየከተማው፣ በየክልሉ እንዲሄዱ በማረግ ችግሩን መፍታት የሚቻልበት መንገድ ቢፈጠር ሲሉ ኃሳባቸውን ያቀርባሉ።

በተጨማሪም አሁን ላይ ማዕከሉ ያለውን አቅም አሳድጎ ብዙ የልብ ቀዶ ህክምናዎችንም እንዲሰራ ቢደረግ ለበርካቶች መድረስ እንደሚቻልም ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ የልብ ቀዶ ህክምና እና በደም ስር ገብቶ የሚሰራ የልብ ህክምና የሚሰጡት ቅዱስ ጳውሎስ፣ ጥቁር አንበሳና ኢትዮጵያ የልብ ህክምና ማዕከል መሆናቸውን ከኢትዮጵያ የልብ ህክምና ባለሙያዎች ማህበር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine

47.1k 0 34 17 188

በ6 ወሩ የፎረንሲክ ምርመራ ከተካሄደባቸው ሰነዶች ውስጥ 73 በመቶው ሀሰተኛ ናቸው ተባለ።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በ2017 በጀት ዓመት ስድስት ወራት ከቀረቡለት 191 የወንጀል ጉዳዮች እና 167 ከፍታብሔር ጋር የተያያዙ የምርመራ ጥያቄዎችን ከፖሊስና ከፍርድ ቤት ተቀብሎ በፎረንሲክ ምርመራ ማጣራቱን ገልጿል።

በዚህም የፎረንሲክ ምርመራ ከተካሄደባቸው 358 ሰነዶችን ውስጥ 73 በመቶ የሚሆኑት ሀሰተኛ መሆናቸውን አረጋግጫለሁ ሲል አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ባደራጀው የምርመራ ላብራቶሪ በሰነዶች ላይ የሚፈፀሙ ፊርማዎችን፣ በቲተሮችና በማህተሞች፣ በባንክ ቼኮች፣ በፖስፖርቶች፣ በተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ላይ የተፈፀሙ ድልዝና ስርዞችን፣ በፅሁፎች እና በቁጥሮችን ይመረምራል።

በተጨማሪም ከውርስ ጋር የተያያዙ ሰነዶችን እና ከቦታ ካርታ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በመመርመር ትክክለኛ እና ሀሰተኛ መሆናቸውን የማረጋገጥ ሥራም ይሰራል።

በሀገራችን የፀረ-ሙስና አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 23 ሥር መንግሥታዊ እንዲሁም ሕዝባዊ ድርጅት ሰነዶችን በማስመሰል በሙሉ ወይም በከፊል የለወጠ፤ ያሻሻለ፤ የቀነሰ፤ የጨመረ ወይም በማጥፋት ወደ ሀሰተኛነት የለወጠ እንደ ወንጀሉ ክብደት እስከ እድሜ ልክ ጽኑ እስራት ያስቀጣል።

ኅብረተሰቡም ማንኛውም ዓይነት ውሎችን ሲዋዋል፣ Online ግብይቶች ሲያደርግና ሲፈርም በአጠቃላይ ከሰነድ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በሚገባ ማየትና ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

@tikvahethmagazine


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
📢📢📢 እንዳያመልጦት

የመጨረሻው እና ሶስተኛዉ የሱቅ ሺያጭ በ ፒያሳ (አድዋ 00 )ፊትለፊት  

💥 ከ 3,9 ሚሊዮን ጠቅላላ ክፍያ ጀምሮ በ 900ሽ ቅድመ ክፍያ

💥 እንዲሁም  ፒያሳ ሊሰ ገብረ ማርያም ት/ቤት ጀርባ

💥 ከባለ 1መኝታ ጀምሮ እስከ ባለ 3 መኝታ ዘመናዊ አፓርትመንቶችን

💥 ከ 3,900,000 ሙሉ  ክፍያ ጃምሮ

💥 በተጨማሪ  ግንባታየው ከ 75% በላይ የተጠናቀቁ አፓርትመንቶች

📍 በአያት 1(አንድ) (በካሬ 61 ሺ ብር)
📍በአያት 2(ሁለት ),(በካሬ 69 ሽብር )
📍ሱማሌ ተራ (በካሬ 95 ሺ ብር)
ለሽያጭ አቅርበናል

ለበለጠ መረጃ
               ☎️0944201554
               ☎️0987076900 ይደውሉ


የሊፍት አደጋ!

የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ባለፉት ቅዳሜና እሁድ በአዲስ አበባና አካበቢዋ ወደ 5 አደጋዎች ደርሰው በሰውና በንብረት ላይ ጉዳታ ማድረሳቸውን አስታውቋል።

ከእነዚህ አደጋዎች መካከል በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ዋሪት አካባቢ'' የፍሊንት ስቶን ሆምስ የመኖሪያ ህንፃ ሊፍት ላይ የደረሰው አደጋ አንዱ መሆኑን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ንጋቱ ማሞ ጠዋት ላይ ሰይፉ ሾው ለመቄዶንያ ባዘጋጀው የቀጥታ ሥርጭት የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ መረጃውን አጋርተዋል።

አደጋው የደረሰው የህንጻውን ሊፍት ተጠቅመው ከ6ተኛ ፎቅ ወደ ግራውንድ ለመውረድ ሲሞክሩ በነበሩ 14 ሰዎች ላይ እንደሆነ አስረድተዋል።

በዚህም ሊፍቱ ተበጥሶ አደጋ መድረሱን ገልጸው በዚህ አደጋ የ7 አመት ህፃን ልጅን ጨምሮ 8ቱ ላይ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ህክምና ተቋማት ለህክምና መላካቸውን አስረድተዋል።

ሊፍቱ ከሚይዘው ሰው ቁጥር በላይ ሊፍት ውስጥ ባለመግባት ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ያሳሰቡት አቶ ንጋቱ በተመሳሳይ አደጋ ከዚህ ቀደም ህይወታቸውን ያጡ ዜጎች እንዳሉም ለአብነት ጠቅሰው አስረድተዋል።

በየህንፃው የሊፍት ባለሙያ እንዲኖር በማረግ መሰል አደጋዎችን መከላከል እንደሚቻልና  ኮሚሽኑም ሁሉንም ማዳረስ ባይችል የክትትል ሥራ እንደሚሰራ አስረድተዋል።

በተመሳሳይ በትላንትናው ዕለት ታዋቂው ድምጻዊ አብዱ ኪያር በተመሳሳይ አደጋ ጉዳት ደርሶበት እንደነበረና በተደረገለት ህክምናም አሁን ላይ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

@tikvahethmagazine

56.2k 0 164 21 213


17 last posts shown.