“ ዱባይ ስንሄድ እንነቃቃለን “ - ሚኬል አርቴታ
⏩ “ አስቸጋሪ ውድድር ነው “
የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው ዛሬ ምሽት በመጀመሪያ ደቂቃዎች ያገኛቸውን እድሎች ባለመጠቀሙ ለሽንፈት መዳረጉን ገልጸዋል።
“ በመጀመሪያው ያገኘናቸውን እድሎች መጠቀም ነበረብን ነገርግን ያንን አላደረግንም “ ያሉት አርቴታ በዚህ ምክንያት ጨዋታው ወደሌላ አቅጣጫ ተቀይሯል ብለዋል።
“ ቀጥሎ በረጅም ኳስ የመጀመሪያ ግብ ሲቆጠርብን በስነልቦና ወርደን ነበር ፤ ውጤቱን መቀየር እንደምንችል አስበን ነበር አልሆነም “ ሲሉ አርቴታ አስረድተዋል።
የካራባኦ ካፕን “ በጣም አስቸጋሪ ውድድር “ ሲሉ የገለፁት አርቴታ ለንደን ከተመዘገበው ውጤት በኋላ የሚጠብቀን ሥራ ከባድ እንደሆነ እናውቅ ነበር ብለዋል።
“ አሁን ይህንን ረስተን ወደፊት መመልከት አለብን ዱባይ ስንሄድ እንነቃቃለን በድጋሜ ሀይላችንን እንመልሳለን “ አርቴታ
አርሰናል በቀጣይ ቀናት ወደ ዱባይ በማምራት ልምምዱን በዱባይ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe