#የውብ ዳር !
.
ስቤ በምለቀው ጭስ መሀል
ገፅታሽ ተስሏል
ከጭሱ ቅርፅ ጋር ...
የኔዋ የውብዳር.. .
ትሽከረከሪያለሽ.. .
አንዳንዴም
ቀጥ ባለ መስመር ፏለሽ ትከንፊያለሽ።
.
ይሄ ጭሰት ማለት
ያንቺ ተምሳሌት ነው... ከህይወት ኑባሬ የተቀዳ እውነት
አንዴ በቀጥታ አንዳንዴ በክበብ
ፔንዱለም ዓመልሽ የተከተበበት ።
.
#ይሄ ባንኮኒው አናት ላይ
ተቀምጦ የሚታይ
የድራፍት ብርጭቆ...
የአልኮል መጠጡን በአረፋው ደብቆ
ምሉዕ ነኝ እያለ ጎድሎ የቀረብኝ
ፍቅርሽ ነው መሰለኝ
ሳላጣጥመው ነው ቀድሞ ያለቀብኝ።
.
#አረፋው ሲከስም ...አየሁት ሲጋመስ
በዚህ ምልከታ ነው ቀዬሽ ዘንድ የምደርስ።
.
#ይታይሽ የውብ ዳር !
ደግሞ በሁለቱ ... በሱሳቸው ስሌት
በስካር ስናውዝ.. . ስመሰጥ በጭስ ቤት
ካሰላሁት ሁሉ ገርሞ የሚደንቀኝ
ዛሬ አጭሰሀል
ዛሬ ጠጥተሀል ይበቃል የሚለኝ
ያ ክፉ ልማዴ.. .የርኩሰት መካሪ
ነገ አዲስ ሆኖ ... ሲልክብኝ ጥሪ
ትናንት አጭሻለሁ
ትናንት ጠጥቻለሁ
ብዬ አሻፈረኝ.. . አልደግምም አልልም
ፍቅርሽም እንዲያ ነው... መቋረጥ አይወድም
ትናንት ጭስ ነች እያልኩ እንዳጨስኩኝ ሁሉ
ትናንት ብርጭቆ ነች እያልኩ እንደጠጣሁ ሁሉ
.
ዛሬም ጭስ ቤቴ ውስጥ ዛሬም ግሮሰሪ
በፍቅርሽ ፖስታ በመውደድሽ ጥሪ
የሰው ነጭ በሞላው
መንገድ ዘንድ ፈልጌሽ ላትመጭ ስትቀሪ.. .
.
ድራፍት እየጠጣሁ ሲጃራ እያጨስኩኝ
አንቺን እየሳልኩኝ
ይህቹት የውብዳር
ይኸው ገፅታዋ
አቤት ከባድ ህመም የገዘፈ ዋይታ
ዋ !
እያልህ ትጮሀለህ ይለኛል ታዛቢ
የስካር መዝጋቢ !
።
.
#ይታይሽ የውብ ዳር
አንቺ የኔ ጭሰት.. .አንቺ የኔ ስካር.. .
ከነ በስቲያም ላይ በሚኖረኝ አዳር
ደግሜ ልጮህ ነው እንደ እብድ መንገድ ዳር።
.
አላሳዝንም ወይ ?
.....
©✍ሚካኤል አስጨናቂ
@tsegaye_gebremedihen@tsegaye_gebremedihen@tsegaye_gebremedihen