Forward from: ከአንቂ መጻሕፍት ገፆች
" ... አባቱ ሲገደሉ በዓይኑ አይቷቸዋል ። በራፋቸው ላይ ነው የተገደሉት ። ዳግማዊ አመሻሽ ላይ ወደ ቤት በሚወስደው ጭር ያለ ቀጭን መንገድ እየገሰገሰ ሰፈር ሲደርስ ከወዳጃቸው ጋር እየተጓዙ አባቱን በርቀት አይቷቸዋል። እንዲያዩት ስላልፈለገ ወደኋላ ቀረት ብሎ ከአይናቸው ሰወር አለ ። ቤታቸው መግቢያ ጋር ሲደርሱ የተቃቀፉ መሰለው ። ብዙም ሳይቆይ ግን አባቱ ወደቁ ። ወዳጃቸው አካባቢያቸውን ቃኘት እያደረጉ ከሩጫ ባልተናነሰ ፍጥነት ከዳግማዊ በተቃራኒ አቅጣጫ መሄድ ጀመሩ ። ዳግማዊ እየሮጠ አባቱ ጋ ሲደርስ ጣር ላይ ነበሩ ። ከደረታቸው የሚፈስ ደማቸውን እና በእጃቸው ፍራፍሬና የተጠቀለለ ኬክ መያዛቸውን እኩል ቃኘው ። የቅድስት አስራ አምስት ዓመት ልደት በዓሏ ነበር ። በጣር ስቃይ ውስጥ ሆነው እጁን ጨብጠው ቤተሰቡን እንዲንከባከብ ለመኑት ። ዳግማዊ ገዳያቸውን ከመከተልና አባቱን ከማንሳት የቱ እንደሚቀድም ግራ ገብቶት ዋለለ ። በደመ—ነፍስ የእናቱን፣ የእህቱን፣ የወንድሙን፣ የሚያስታውሰውን ሰው ስም ሁሉ በጩኸት ተጣራ። ... "
ጠበኛ እውነቶች
በሜሪ ፈለቀ
አምስተኛ ዕትም
በመደብሮቻችን ይገኛል !
ጠበኛ እውነቶች
በሜሪ ፈለቀ
አምስተኛ ዕትም
በመደብሮቻችን ይገኛል !