✨✨ሶፊያ✨✨
ረዳቱ ሂሳብ ሲል ነው የባነንኩት። ለምን እንደምሄድ ሳስታውስ ፈገግ አልኩ እየተቁለጨለጨ የሚያየኝን ረዳት ብሩን አውጥቼ ሰጥቼው ወደ ምሰጣዬ ስመለስ "መሳለሚያ መጨረሻ" አለ ረዳቱ ወደ እኔ እያየ መድረሴን አስታወሰኝ። ወርጄ ቤቷን ከርቀት ሳይ እርምጃዬም ከልብ ምቴ እኩል ጨመረ።
በሯ ጋር ደርሼ ሳንኳኳ ራሷ መጥታ ከፈተችልኝ ምን እንደጠበኩ አላውቅም ዘበኛ ወይ ሰራተኛ አላውቅም ብቻ ሽርጧ ላይ እጇን እየጠራረገች በፈገግታ ስትቀበለኝ ገረመኝ
አባቴ የሚያደንቃት ደራሲ ነች እሱ ለራሱ ብዙም ባያነብም አዲስ መፅሐፍ በፃፈች ቁጥር ገዝቶ ይሰጠኛል። እኔም እሷን መሆን እንደተመኘሁ አድጌ በስነፅሁፍ ስመረቅ ራሱ ጥናታዊ ፅሁፌን በእሷ ፅሁፎች ላይ ነበረ የሰራሁት።
ከዛ ግን አዲስ መፅሀፍ ከፃፈች ሁለት አመት አለፋት ሆኖ የማያውቅ ነገር ስለነበረ በየመፅሄቱ መነጋገርያ ሆነ ቆይ አይታወቅም አልተመቻት ይሆናል እየተባለ ሶስተኛ አመቷ መጣ ከሷም ሆነ ከአሳታሚዎቿ ምንም ሳይሰማ አራተኛ አመቷ ሊገባደድ ሲል ቀጥ ብዬ ቤቷ ሄድኩ።
"ወይ የኔ እመቤት" አለች በትህትና በዛውም ማን እንደሆንኩ በሚጠይቅ ቃና "ሳሌም እባላለሁ..."አላስጨረሰችኝም
"ሳሌም?! ብዕረኛዋ ሳሌም?!" ብላ ፊቷ በፈገግታ ደመቀ "ታውቂኛለሽ?!" ልቤ ደስ ደስ ሲለው ይሰማኛል "እንዴት አላውቅሽም ፅሁፎችሽን ተከታትዬ ነበረ የማነበው በየመፅሄቱ የማልፈው ያንቺ ስም ያለበት ፅሁፍ ኖሮ አያውቅም። እስኪ ነይ ግቢ እና በደንብ እናውራ" ብላ አስገባቺኝ።
ግቢዋ በጣም ሰፊ የሚባል አይነት አይደለም። ቅልብጭ ብላ በአበባ እና በሀረግ የተንቆጠቆጠ በባለአንድ ወለል ፎቅ መኖርያ ቤት ከፊት ቆሟል። ድንቅ ሴት ያበጀችው እንደሆነ የሚያስታውቅ ሳሎን ውስጥ ይዛኝ ገባች። "ማንን አግኝተሽ ነው ጥለሽኝ የጠፋሽው" ብሎ በአርባዎቹ መጨረሻ ላይ ያለ ጠይም ሰውዬ በትሪ የተጠባበሱ ነገሮች ይዞ መጣ። (አብረው ሲያበስሉ ነበረ)
"አገኛታለሁ ስል ሳሌም ቤቴ ድረስ አልመጣች መሰለህ" አለችው እንደልጅ እየፈነደቀች እሱም ፈገግታዋ ተጋብቶበት "የሶፊያ ባለቤት ነኝ ሳሌም ስለመጣሽ ደስ ብሎኛል" አለና ወደ ሶፊያ ዞሮ "ሶፊ ልጆቹ እንዳይረብሿችሁ እላይ ብትወጡ አይሻልም" አላት ሽርጧን ከወገቧ ላይ ፈትቶ እየወሰደ
"ይሻላል አይደል?! አዎ ነይ እንሂድ" ብላ ተያይዘን ወጣን "ልታገኚኝ ፈልገሽ ነበር እንዴ?!" አልኳት ደረጃውን እየወጣን "አዎ! ጥናታዊ ፅሁፍሽን ያቀረብሽለት ፕሮፌሰር ጓደኛዬ ስለሆነ በማግስቱ ነበረ ያመጣልኝ እንዴት ደስ እንዳለኝ አታውቂም የሆነ ሽልማት እንዳገኘ ሰው ነበረ ሀሴት ያደረግኩት ምክንያቱም ስነፅሁፍ አለሜ ነበረ በእሱ መመስገን ደግሞ ድርብ ደስታ ነው" አለች ፈገግ ብላ
"ታድያ ለምን መፃፍ አቆምሽ?!" አልኳት ተንገብግቤ "ግልፅ አይደለም እንዴ?!" አለቺኝ ዙርያዋን እያሳየቺኝ እንድታብራራልኝ ዝም ብዬ መጠበቅ ጀመርኩ "ደስተኛ ስለሆንኩ ነዋ" አለቺኝ
"አየሽ ድርሰት አጠቃላይ ኪነ ጥበብ ወይ መደበቂያ ነው ወይ ማምለጫ ወይ ማልቀሻ ነው ከነዚህ ከሶስቱ አይዘልም አሁን የምደበቀውም የማምልጠውም የማለቅስበትም ምክንያት የለኝም
አብዛኞቹን የህይወት ግቦቼን አሳክቻለሁ ስለምን ጓጉቼ ልፅፍ እችላለሁ እንባ እየተናነቀኝ ስለቀረብኝ ቀጠሮ ወይም ስለተካድኩት ክህደትም መፃፍ አልችልም ምክንያቱም የምወደው የሚወደኝ በንግግር የሚያምን ሰው የትዳር አጋሬ ነው። ስለመሀንነት መማረር ወይ ስለመጥፎ ልጆችም መነጫነጭ አልችልም ምክንያቱም የተባረኩ ልጆችን አሳድጊያለሁ።
ስለምን ልፅፍ እችላለሁ?! አሁን ተረጋግቻለሁ ደስተኛ ነኝ ደስታ ደግሞ የሚያጣጥሙት እንጂ የሚያብራሩት ነገር አይደለም ተራ እና ጥልቀት የሌለው ይመስላል ምክንያቱም የሀዘን ጥልቀት ሊያስቀሩት የሚቻል ስላልሆነ ስለሀዘን ብፅፍ ብዙ ወዳጅ እንደማፈራ አውቃለሁ ግን ለምን?! ያላሳለፍኩትን እፅፋለሁ?!
ምንም ያህል አንባቢዎቼን ባያስደስታቸውም እኔ ግን ደስታዬ እና ሰላሜ ይበልጥ ስለሚረባኝ ፅሁፉን እርግፍ አድርጌ ትቼዋለሁ" አለቺኝ ስናወራ ቆይተን አመስግኛት ወጣሁ ግን እያብሰለሰልኩ ቤቴ ደረስኩ "ስነፅሁፍ ማምለጫ ከሆነ ከምንድነው ማመልጠው " ✍️ናኒ