የቅዱሳን ታሪካቸው ህይወታቸው ትምህርቶች


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


⛪️1ኛ ቆሮንቶስ 6÷2፤ቅዱሳን፡በዓለም፡ላይ፡እንዲፈርዱ፡አታውቁምን፧በዓለምስ፡ላይ፡ብትፈርዱ፡ከዅሉ፡ይልቅ፡ትንሽ፡
ስለሚኾን፡ነገር፡ልትፈርዱ፡አትበቁምን፧
@Brkeyazew
@Brkeyazew
https://t.me/yekidusantarikachewhiywetachew

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter










"በልደቱ ተወለድነ፤ ወበጥምቀቱ ተጠመቅነ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ኀበ አቡሁ አቅረበነ።
በልደቱ ተወለድን፤ በጥምቀቱም ተጠመቅን። ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ባሕርይ አባቱ አቀረበን።"
ወካዕበ ይቤ፦ ዳግመኛም አለ፦
"በልደቱ ተርኅወ ሰማይ፥ ወበጥምቀቱ ተዐውቀ መለኮቱ፤ መንግሥቱ ሰፋኒት ዘእምቅድመ ዓለም ንጉሥ ውእቱ ወአልቦ ማኅለቅት ለመንግሥቱ።
በልደቱ ሰማይ ተከፈተ፤ በጥምቀቱ መለኮቱ ታወቀ፤ መንግሥቱ ቅድመ ዓለም ገዢ ናት፤ ቅድመ ዓለም ንጉሥ ነው፤ ለመንግሥቱ ፍጻሜ፥ ማብቂያ (መጨረሻ) የለውም።"
                    ቅዱስ ያሬድ።
ዕንቋዕ ለብርሃነ ጥምቀቱ አብጻሕክሙ፤
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ
አደረሳችሁ!!!


Forward from: ኑ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ
“ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ።”

— ማቴ 3፥13

በመላው ዓለም ያላችሁ ውድ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል ዋዜማ(ከተራ) አደረሳችሁ።

በያለንበት መልካም በዓል ይሁንልን።






"" አንተ የተረገምህ ነህ! "" (ዘፍ. ፬:፲፩)

•ክፍል ፪/2 - ማጠቃለያ

" ስለ በዓለ ጥምቀት . . . "

✝እንኳን አደረሳችሁ !

(ጥር 9 - 2017)

https://t.me/zikirekdusn


"ድንኳን የሚሆነው ምድራዊ መኖሪያችን ቢፈርስ በሰማይ ያለ በእጅ ያልተሠራ የዘለዓለም ቤት የሚሆን ከእግዚአብሔር የተሠራ ሕንጻ እንዳለን እናውቃለን።"

፪.ቆሮ.፭፥፩


" እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤"

(ፊሊ ፫፥፳)


"ሣህል ወርትዕ ተራክባ።
ጽድቅ ወሰላም ተሰዓማ።
ርትዕሰ እምድር ሠረፀት። "

"አቤቱ፥ ለምድርህ ሞገስን አደረግህ፥ የያዕቆብንም ምርኮ መለስህ።
የሕዝብህን ኃጢአት አስቀረህ፥ አበሳቸውንም ሁሉ ከደንህ።
መዓትህንም ሁሉ አስወገድህ፤ ከቍጣህ መቅሠፍት ተመለስህ።
የመድኃኒታችን አምላክ ሆይ፥ መልሰን፥ ቍጣህንም ከእኛ መልስ።
በውኑ ለዘላለም ትቈጣናለህን? ቍጣህንስ ለልጅ ልጅ ታስረዝማለህን?
አቤቱ፥ ትመለሳለህ ታድነንማለህ፤ ሕዝቡም በአንተ ደስ ይላቸዋል።
አቤቱ፥ ምሕረትህን አሳየን፥ አቤቱ፥ መድኃኒትህንም ስጠን።


እግዚአብሔር አምላክ የሚናገረውን እሰማለሁ፤ ሰላምን ለሕዝቡና ለቅዱሳኑ ልባቸውንም ወደ እርሱ ለሚመልሱ ይናገራልና።ነገር ግን ክብር በምድራችን ያድር ዘንድ ማዳኑ ለሚፈሩት ቅርብ ነው፤
ምሕረትና እውነት ተገናኙ፤ ጽድቅና ሰላም ተስማሙ።
እውነት ከምድር በቀለች፥ ጽድቅም ከሰማይ ተመለከተች።
እግዚአብሔርም በጎ ነገርን ይሰጣል፥ ምድራችንም ፍሬዋን ትሰጣለች።
ጽድቅ በፊቱ ይሄዳል፥ ፍለጋውንም በመንገድ ውስጥ ያኖራል።"


(መዝሙር ፹፬)


"" የሰላም አለቃ! "" (ኢሳ. ፱:፮)

"የበዓለ ልደት ትምህርት"

(ታኅሣሥ 29 - 2017)

https://t.me/zikirekdusn


"" ምድርን አንድ ጊዜ አናውጣታለሁ! "" (ዕብ. ፲፪:፳፮)

"ትምህርት - በተለይ ለሴቶች"

(ታኅሣሥ 27 - 2017)

https://t.me/zikirekdusn


እናቴ ከአባቴ እኩል ጽናት ያላት ሴት ነበረች :: እርሷ አስቀድማ እግዚአብሔርን ካወቁ እና ከከበሩ ወገን ነበረች ::እንዲህ አይነት ጠንካራ ሴት ለቤተክርስቲያን ጠባቂ ለምእመናን መሪ ለሆነው አባቴ የምትመጥን ነበረች ::በሁለንተኛው እግዚአብሔርን ከሚያመልክ ቤተሰብ የተገኘች በጹማዊ ሕይወቷ ሰውን በመውደዷ ለስላሳ በነበረው ባሕርይዋ ከቤተሰቧ በበለጠ ራሷን አሳልፋ ለእግዚአብሔር የሰጠች ንቁ እና ቀልጣፋ ክርስቲያን ነበረች ::እናትና አባቴ በሚኖሩበት ማኅበረሰብ ውስጥ መንፈሳዊ ዝናን ያተረፉ የሚወደዱ እና የተከበሩ ነበሩ ::ሕይወታቸውም እኩል የተጣጣመ ነበር :: ለዚህ ቃሌ እውነትነት ማንን ምስክር ልጥራላችሁ?! ይህንንስ ቃሌን የማንን ስም ጠርቼ ላረጋግጥላችሁ?! የአፌ ቃል ቀጥተኛ ምስክርነቴም እውነት መሆኑን ትመሰክር ዘንድ እራሷን ልጥራላችሁ :: እናቴ የእውነት ቃል የሚናገር ቃል አቀባይ ናት ና ::በአንደበቷም ከእውነት ውጭ ሌላ ነገር አይታሰብምና : እና አንድ ነገር ልትነግራችሁ ዝግጁ ናት :: የተለመደ እና እውነት የሆነ ከንቱ ውዳሴን ሽታ ከንቱ የሆነ ነገርን አትናገርምና ::

እግዚአብሔርን መፍራት የመጀመሪያም የመጨረሻም መታወቂያዋ የሕይወቷም መመሪያ ነው ::በሁሉም ነገር እርሱን ታስቀድማለች ::

(ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ስለ እናቱ ቅድስት ኖና የተናገረው.... ይቀጥላል )


    ዘላለም  ሥላሴ   

†  እንኩዋን ለአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ  ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ  †


❝ በሥላሴ ገመድ ፍጹም ታስረናል ፤ ከልባችን በማይነቀል በቅንዋተ ፍቅሩ ተቸንክረናል ፣ እርሱ ወዶናል አይጠላንም። እኛም በእምነት ይዘነዋል አንተወውም። ❞

     [  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ  ]

❝ እምነታችንም እንዲህ በባሕርይ በመለኮት አንድ ፤ በአካል ፤ በገጽ ሦስት ብለን ነው፡፡ እነዚህ በቅድምና የነበሩ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡ አስቀድመን መላልሰን እንደ ተናገርን ቀዳማዊ ወልድ ሰው ስለ መሆኑና ስለ ቅድስት ሥላሴ የምናምነው እምነት ይህ ነው ፤ ከተማሩ ከሚያስተምሩ ተስፋን ከሚያስረዱ ቅዱሳን ሊቃውንት ለምዕመናን ሁሉ ገልጠን የምናስተምረው ፤ እውነተኛ ሃይማኖትን ከሚያስተምሩ የሰማይ አምላክ ከሾማቸው ከሐዋርያትም ሲያያዝ የመጣልን እጅ ያደረግነው እምነት ነው፡፡ በንጹሕ ልቡና በአፋችንም በልባችንም በዚህ ሃይማኖት እንመን ፤ ያለ ጥርጥርም በበጎ ግብር በቅን ሕሊና እናስተውል ፤ በዚህ እንድንድን መንግሥተ ሰማያትንም እንድንወርስ እንረዳለን፡፡ ❞

[    ሃይማኖተ አበው   ]


ጥር ፯ [ 7 ]

ሕንጻ ሰናዖርን ማፍረሳቸውና ቅዳሴ ቤታቸው በዓል ይከበራል።

የሰናዖርን ሕንጻ ያፈረሱ ሥላሴ : የኃጢአታችንን ሕንጻም በቸርነታቸው ያፍርሱልን አሜን በእውነት !


Forward from: የቅዱሳን ታሪካቸው ህይወታቸው ትምህርቶች
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
⛪️ #መንፈሳዊ_ፊልም 👉 #የቅዱስ_ስምኦን_ጫማ_ሰፊው ታሪክ_የመጨረሻው_እነሆ_ #ክፍል2⃣

🌹አዳምጡ መልካም ቆይታ🍀🌼🌺

@yekidusantarikachewhiywetachew


Forward from: የቅዱሳን ታሪካቸው ህይወታቸው ትምህርቶች
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
⛪️ #መንፈሳዊ_ፊልም 👉 #የቅዱስ_ስምኦን_ጫማ_ሰፊው ታሪክ_እነሆ #ክፍል 1⃣

🌹አዳምጡ መልካም ቆይታ🍀🌼🌺

@yekidusantarikachewhiywetachew


⛪ ጭፈራ ቤት ገብቶ ሳይቃጠል
      የሚወጣ አለ ?

      
#ፍትሐ ነገስት አንቀፅ 1⃣1⃣
     
#በሊቀ ሊቃውንት ስምዓኮነ

  🌹መልካም ቆይታ አድምጡ 👂🥀


@yekidusantarikachewhiywetachew


✝ስንክሳር - ጥር ፮/6

✞በዓለ ግዝረቱ ለመድኅን

ወተዝካሮሙ ለቅዱሳን ኖኅ፥ ወኤልያስ ወባስልዮስ ዐቢይ

(ጥር 5 - 2017)

https://t.me/zikirekdusn


ቡዙ ሴቶች ድንግል ትጸንሳለች የሚለውን ትንቢት የነገሥታት ሴቶች ልጆች እና የባለጸጋ ልጆች መሲሁን ሊወልዱ በተስፋ ተጠባበቁ :: እርሱ ግን ከድሆች ልጅ ተወለደ ::ጌታ ሆይ በአንተ ምክንያት የነገሥታት ልጆች በድሆች ልጅ ቀኑ ::ወደ ድሃዋ ቤትም ነገሥታት እጅ መንሻን ይዘው ሄዱ ::¹


መኝታውን በወርቅ ያጌጠ ማድረግ ሲችል በግርግም ውስጥ ማድረግን መረጠ :: እናቱንም ከነገሥታት አንዲቱ ማድረግ ሲችል አላደረገም ²

፩,ማር ቅዱስ  ኤፍሬም

፪,ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ

20 last posts shown.