✞ ጋሜል - የመዝሙር ግጥሞች ✞


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Religion


✟ የኦርቶዶክሳውያን የመንፈሳዊ ምስጋና ቤት ✟
ቤተ ክርስቲያንን አንተውም ከቶ
የሰጠንን አምላክ በደሙ መስርቶ
የሰጠንን ጌታ በመስቀሉ ሞቶ
የአምላካችንን ቤት አንተውም ከቶ
💿 የተዋሕዶ የመዝሙር ግጥሞች 💿
   ✍ / ትምህርቶችን ለማግኘት ✍
👇👇👇
https://t.me/maedot_ze_orthodox
| ለማስታወቂያ ሥራዎች ➢ @EOTC24bot

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Religion
Statistics
Posts filter


ከ17 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል

የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ  ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ


​​​​​​✞ ዘመነ ጽጌ ✞

ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6

"ልጄን ከግብፅ ጠራሁት"
ት.ሆሴዕ ፲፩፥፩

ከመምህር ዮሐንስ ለማ

ክፍል ዘጠኝ [፱]

ሐ፥አድባረ ሊባኖስ ፦
እመቤታችን ከዮሴፍ እና ከሰሎሜ ጋር በደብረ ታቦር ጥግ አልፋ ወደ ተወለደችበት ወደ ደብረ ሊባኖስ ወጣች፡፡

ኰኵህ ከሚባለ ዛፍ ስር ተቀምጣ አለቀሰች፡፡ እንዲህም አለች፡፡"አቤቱ እሰከመቼ ድረስ ካንዱ ሀገረ ወደ ሌላው ሀገር ስዞር እኖራለሁ ነፍሴስ ምን ያህል ጸናች፡፡ ከዚህ በኋላ ያለችበትን ቦታ ሰው እንዳያውቅ ወደ ጫካው ገባች ለአሥር ቀናት ያህል ሰው ሳያያት ተቀመጠች፡፡

ከዚህ በኋላ አንድ አውሬ አዳኝ ከሩቅ ሆኖ አያት፡፡ አውሬ አዳኙ ውሾች ነበሩት፡፡ ውሾቹ ጌታቸውን ትተው እየሮጡ ሄዱና ከእመቤታችን እግር በታች ሰገዱ፡፡ እመቤታችንም በእግርዋ የረገጠችውን መሬትም ይልሱ ነበር፡፡

አውሬ አዳኙ ከሩቅ ሆኖ ውሾቹን ጠራቸው፡፡ ውሾቹ ግን ወደ አንተ አንመጣም አንተ ምን ትሰጠናለህ ከአንድ ጉራሽ በቀር የዕለት ምግባችን ዕንኳ አትሰጠንም አሁንስ ፈጣሪያችንን አግኝተናል ይሉት ነበር፡፡

ድንግል ማርያም ውሾቹ የተናገሩትን ሰምታ አደነቀች፡፡ ፍጥረት ሁሉ ለሚፈሩህ ፈጣሪ ምስጋና ይገባሃል ብላ አመሰገነች፡፡ ውሾቹም ከእመቤታችን እግር ስር ተኙ የሰው ልቡና በተንኮል ሲሞላ እና ከሰው ቅንነት ሲጠፋ ለሰዎች መገለጥ የሚገባው ምሥጢር ለእንስሳት ይገለጣል፡፡

የእግዚአብሔር መልአክ ለበለአም ሳይገለጥ ለተቀመጠባት አህያ እንደተገለጠ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል ዘኁ ፳፥፪፥፴፪-፴፫።

የበለአም ታሪክ በዚህ አውሬ አዳኝ ላይ ተደግሞአል፡፡  ሄሮድስ ፈጣሪውን ወደ በረሃ አሳደደው፡፡ ውሾቹ ግን ወደ በረሃ ለተሰደደው ፈጣሪያቸው እና ለእናቱ ሰገዱ፡፡ ይህ ትልቅ ትምህርት ነው፡፡ ሰዎች በገንዘብ ፍቅር እና በሥልጣን ጥማት ሲቃጠሉ ከውሾቹ ያንሳሉ ማለት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ አውሬ አዳኙ ውሾቹን እየፈለገ መጣ፡፡ እመቤታችን ቅድስት ማርያም ከልጅዋ ጋር ጫካውን ስታበራ አያትና እጅግ አደነቀ፡፡ መንፈስ /ምትሐት/ እየታየው መሰለው፡፡

እመቤታችን ምን ትፈልጋለህ አለችው፡፡ አውሬ አዳኙ ውሾቼን እፈልጋለሁ አላት፡፡ እመቤታችንም ውሾች ምን ያደርጉልሃል አለችው፡፡ አውሬ አዳኙ ውሾች አውሬዎችን ይገሉልኛል፡፡ የአውሬዎችን ሥጋ እበላለሁ ቆዳቸውንም እሸጣለሁ አላት፡፡

እመቤታችንም ዛሬ ከምታድናቸው አውሬዎች የበለጠ ነገር አግኝተዋል የእግዚአብሔርን መሲሕ አይተሃልና ወደ ሀገርህ ግባ እኔ በዚህ ጫካ መኖሬን ለማንም አትንገር አለችው፡፡ ውሾቹንም ወደ ጌታችሁ ሂዱ አለቻቸው፡፡ውሾቹም ለፈጣሪያቸው እና ለእመቤታችን ከሰገዱ በኋላ ወደ ጌታቸው ሄዱ፡፡ አውሬ አዳኙም እያደነቀ ሄደ፡፡

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ግን በጫካው ውስጥ ነበረች፡፡ በኤልያስ ዘመን ጣዖት አምላኪዋ ኤልዛቤል ነቢያትን ካህናትን ባስገደለቻቸው ጊዜ እግዚአብሔርን ከኤልዛቤል ዓይን የሠወራቸው በጫካ የሚኖሩ ጻድቃን እየመጡ ከእመቤታችን ይባረኩ ነበር፡፡
እመቤታችንና ንጉስ ደማትያኖስ
አውሬ አዳኙ ከሰባት ቀን በኋላ ደማትያኖስ ለተባለው ንጉሥ ያየውን ሁሉ ነገረው፡፡ ደማትያኖስም አውሬ አዳኙ የነገረው እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ አሥር የቤተመንግስት ሰዎችን ከአውሬ አዳኙ ጋር ላከ፡፡ የተላኩት ሰዎች በደረሱ ጊዜ እመቤታችንን ከልጅዋ ጋር አገኝዋት፡፡ እመቤታችን ግን ለማንም አትንገር ያለችውን ስለተናገረ አውሬ አዳኙን በቁጣ ተመለከተችው፡፡ አውሬ አዳኙም የጨው ድንጋይ ሆነ። ማቴ ፰፥፬ የሎጥ ሚስት ታሪክ በአውሬ አዳኙ ተደግሞአል፡፡ እግዚአብሔር ሎጥን በእሳት ከምትጋየው ከሰዶም ባወጣው ጊዜ ወደ ኋላህ አትመልከት ብሎት ነበር፡፡ የሎጥ ሚስት ግን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ በመተላለፍ ወደ ኋላዋ ወደ ሰዶም ተመለከተችና የጨው ሐውልት ሆነች።ዘፍ

ከቤተ መንግስት የተላኩት ሰዎችም እመቤታችን ያደረገችውን ተአምር አይተው በጣም ደነገጡ፡፡ እመቤታችን እኔም እንደ እናንተ ሰው ነኝና አትፈሩ ብላ አረጋጋቻቸው፡፡ መልእክተኞችም ንጉሡ ደማትያኖስ እንደላካቸው ነገርዋት፡፡ ከዚህ በኋላ ወደ ቤታቸው ተመልሰው እመቤታችንን ከልጅዋ ጋር እንደአገኝዋት እና አውሬ አዳኙ የጨው ድንጋይ እንደሆነ ለደማትያኖስ ነገሩት፡፡

በማግስቱ ደማትያኖስ ብዙ ሠራዊት አስከትሎ ወደ እመቤታችን ሄደ፡፡ ብዙ ሠራዊቱን ከተራራው ስር ትቶ ከሰባቱ ጋር እመቤታችን ወደ አለችበት ጫካ ገባ፡፡ እመቤታችን እንደ አጥቢያ ኮከብ ስታበራ አገኛት፡፡ ንጉሡ ደማትያኖስ ለእመቤታችን ከሰገደ በኋላ አንቺ ከማን ወገን ነሽ ከየት ሀገርስ የመጣሽ ነሽ ብሎ ጠየቃት፡፡

እመቤታችንም እኔ እስራኤላዊት ነኝ፡፡ የይሁዳ ክፍል ከምትሆን ከቤተልሔም ነው የመጣሁት አለችው፡፡ እመቤታችንም ሄሮድስን ፈርቼ ነው አለችው፡፡ ንጉሡም ሄሮድስ ለምን ይጠላሻል አላት፡፡ እመቤታችንም እንዲህ አለችው፡፡

ሁለንተናው እሳት የሆነ ግሩም መልአክ ገብርኤል መጥቶ ፀጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ እነሆ ወንድ ልጅ ትወልጃለሽና ስሙንም አማኑኤል ትይዋለሽ  አለኝ፡፡ እንደነገረኝ ይህን ሕፃን በድንግልና ጸንሼ በድንግልና ወለድኩት፡፡ ከተወለደ በኋላ ሰብአሰገል የተወለደው የእስራኤል ንጉሥ የት ነው እያሉ መጡ፡፡ ይህን ነገር ሄሮድስ ሰማ፡፡

ስለዚህ እኔን እና ሕፃኑን ሊገድለን ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በፊት በዚህ ቦታ አባቴና እናቴ ነበሩ እኔም የተወለድኩት በዚህ በደብረ ሊባኖስ /በሊባኖስ ተራራ/ ነው አለችው፡፡ ደማትያኖስም የአባትሽ እና የእናትሽ ስም ማን ይባላል ? አላት፡፡ እመቤታችንም አባቴ ኢያቄም እናቴ ሐና ይባላሉ አለችው፡፡ ደማትያኖስም እነዚህን ሰዎች አውቃቸዋለሁ አላት፡፡ ደማትያኖስ ብዙ ሠራዊት ያለው ኃያል ንጉሥ ስለሆነ ከዚህ በኋላ አሥር ነገሥታት እንኳ ቢገቡ አንቺን ማግኘት አይቻላቸውም አትፍሪ አላት፡፡

ወደ ኃላውም በተመለሰ ጊዜ የጨው ድንጋይ የሆነውን ሰው አየውና ይህ ሰው ለምን የጨው ድንጋይ ሆነ አላት፡፡ እመቤታችንም በኃጢአት ነው አለችው፡፡ ከዚህ በኋላ እመቤታችን ወደ እግዚአብሔር ጸለየች፡፡ የጨው ድንጋይ የሆነውን ሰው አስነሳችውና ለማንም አትንገር ብዬህ ነበር ለምን ነገርህ አለችው፡፡ የጨው ድንጋይ የሆነው ሰው ኃጢአቱን አምኖ ይቅርታ ጠየቀ፡፡ የተነገረንን ምስጢር እንጠብቅ፡፡ ብዙ ጊዜ ኃጢአት የሚፈትነን በንግግራችን ነው፡፡ ንጉሡ ግን ይህን ተአምር ባየ ጊዜ እጅግ ደነገጠ፡፡

እመቤታችን በቀኝ እጅዋ ይዛ አትፍራ አለችው፡፡ እመቤታችን ስትይዘው ድንጋጤውና ፍርሃቱ ለቀቀው፡፡ ከዚህ በኋላ ንጉሡ ለእመቤታችን ሰገደላትና አባቴና እናቴ ስማቸውን ሲጠርዋቸው በልጅነቴ የምሰማቸው ሚካኤልና ገብርኤል ሩፋኤል ከሚባሉት አንዱ አንቺ ነሽ አላት ከማድነቁ የተነሣ፡፡

እመቤታችንም እኔ የእነሱ የጌታቸው ባሪያ ነኝ አለችው፡፡ ንጉሡም ብዙ ገጸ በረከት ገንዘብ ይዞ እመቤታችንን ተቀበይኝ አላት፡፡ እመቤታችን ግን ምንም ስደተኛ ብትሆንም አልተቀበለችውም፡፡ ለድሆች ስጣቸው በሰማይ መዝገብ ታገኛለህ አለችው፡፡

ከዚህ በኋላ ንጉሡ ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ እመቤታችንም በደብረ ሊባኖስ ሦስት ወር ያህል ተቀመጠች፡፡ ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሊባኖስ በተባለው ተራራ እነ ዮሴፍ መኖራቸውን ሰምቶ በሠራዊት አስከብቦ ሊይዛቸው ሞከረ፡፡

ክፍል አስር ይቀጥላል...

   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
    @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


​​✞ ዘመነ ጽጌ ✞

ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6

"ልጄን ከግብፅ ጠራሁት"
ት.ሆሴዕ ፲፩፥፩

ከመምህር ዮሐንስ ለማ

ክፍል ስምንት [፰]

እመቤታችን ከልጇ ጋር በስደት ከተጓዘችባቸው ሀገራት መካከል፦

የድንግል ማርያም የስደትዋ ምስጢር ጸጋው የበዛላቸው ሊቁ  ቅዱስ አባት አባ ጽጌ ድንግል "በሰቆቃወ ድንግል" በስፋት እንደገለጹት በዚህ ዓለም ላይ የኖረና ለወደፊትም የሚኖር ፍጡር እንደ ድንግል ማርያም አለመኖሩ አበክረው ያሰምሩበታል፡፡

ሊቁ ይህንን ድርሰታቸው
ሲጀምሩም፡-ማኅሌተ ጽጌ፡-በስመ እግዚአብሔር ሥሉስ ሕጸተ ግጻዌ ዘአልቦ ሰቆቃወ ድንግል እጽሕፍ በቀለመ አንብዕ ወአንጠብጥቦ ወይሌ ወላህ ለይበል ለዘአንበቦ ከማሃ ሀዘን ወተሰዶ ሶበ በኩለሄ ረከቦ ርእዮ ለይብኪ ዓይነ ልብ ዘቦ.... ብለው ነው፡፡ ይኸውም እንኳንስ በዓይነ ሕሊና ወደ ምድረ ግብፅ ወርዶ ያየውና የሰማው አይደለም እንዲሁ ለይኩን ብሎ ያዳመጠው እንኳ ሳይቀር ከብዝሐ መከራዋ ተነስቶ እንደሚያለቅስ ይገልጽልናል።

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ስደት መንፈሳዊ ዓላማና በምሥጢረ ድኅነት ውስጥ የራሱ የሆነ ድርሻ ያለው እንጂ በአጋጣሚ የተገኘ እንዳልሆነ እንዲሁም የተነገረው ቃለ ትንቢት ለመፈጸም እንደሆነ ከላይ ተመልክተናል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ሲያትቱ ከተነገሩት ትንቢቶች መካከል፡-"ወፍኖቶሂ ዘእም ዓለም ርኢኩ አዕፃዳተ ኢትዮጵያ ይደነግፃ" ከጥንት የታሰበ መንገዱን አየሁ የኢትዮጵያ አውራጃዎችም ይደነግጣሉ።እንባቆም፫፥፮፯ የሚለው ትንቢት በማራቀቅ እመቤታችን በመዋዕለ ስደቷ ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ በመምጣት ሃገራችንን ጎብኝታ ሕዝባችንን በአሥራት ተሰጥታ (ከልጇ ተቀብላ) እንደሄደች በመተረክ ሊቃውንት መምህራኑ ያራቅቃሉ።

እመቤታችን ስትሰደድ ያልደረሰበት መከራ፣ ያልተፈራረቀባት ችግር ... አልነበረም፡፡ ይህም ሆኖ ግን ስለሚደርስባት ነገር ፈጽሞ አታስብም ነበር፡፡ የምታስበው ልጇ እንዳይሞትባት ብቻ ነው፡፡"ይእቲ ትበኪ ወትቤ ቀቲሎትየ ይቅድሙ፣ እም ይርአይ ለወልድየ ዘይትከአው ደሙ "ትርጉም እርሷም ይህንን ሰምታ አለቀሰች የልጄ ደሙ ሲፈስ ከምመለከትስ እኔን ያስቀደሙ፣(ሰቆቃወ ድንግል) እንደለ ደራሲ፡፡

ሀ.ገዳመ ጌራራል/ጌራራል ከተባለ ጫካ /፦


መልአክ ለዮሴፍ ሕፃኑን እና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ ካለው በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአመቤታችን ጠባቂ ዮሴፍ የእመቤታችን አክስት ወይም የሐና እህት ሰሎሜ አራቱ ጉዞአቸውን ጀምረዋል፡፡

ወደ ግብፅ እንዲሰደዱ የተነገራቸው ቢሆንም ወደ ግብፅ ከመሄዳቸው በፊት ብዙ አገሮችን ዙረዋል፡፡ ከቤታቸው እንደወጡ ጌራራል ወደተባለ ጫካ ነበር የሄዱት ማቴ ፪፥፲፫።

እነ ዮሴፍን በገዳመ ጌራራል መላዕክት እየመጡ  እያጽናኑዋቸው አርባ ቀን ተቀምጠዋል፡፡ ከአርባ ቀን በኋላ አንድ አውሬ አዳኝ አያቸው፡፡ እርሱም በፍጥነት ሄዶ ማርያምንና ዮሴፍን ሰሎሜንም በጌራራል ጫካ ትላንትና አየኋቸው ብሎ ለሄሮድስ ነገረው፡፡ ሄሮድስም በጌራራ ጫካ መኖራቸውን በሰማ ጊዜ ደስ ተሰኘ፡፡ ይህንን ወሬ ላመጣለት አውሬ አዳኝ እነ ዮሴፍን ካሳየህኝ የመንግስቴን እኩሌታ እሰጥሃለው ብሎ በጣኦቱ ማለለት፡፡ ሄሮድስ በሀገሩ ሁሉ አዋጅ ነጋሪ /መልእክተኛ/ ላከ፡፡ አዋጅ ነጋሪው በሀገሩ እየዞረ ሁላችሁም የሄሮድስ ወታደሮች ነገ በሄሮድስ ቤተመንግስት እንድትገኙ በማለት አስጠነቀቀ፡፡ ወታደሮቹም የሄሮድስን ቤተመንግስት አጥለቀለቁት፡፡ ሄሮድስም ወደ ጌራራል ጫካ ላካቸው፡፡ የሄሮድስ ወታደሮች የጌራራልን ጫካ ከበቧት፡፡ ነገር ግን እነ ዮሴፍን አላገኙዋቸውም፡፡ ወታደሮቹ እርስ በራሳቸው እንዲህ ተባባሉ፡፡ እነዮሴፍ የትሄዱ ምድር ዋጠቻቸውን ?  ይሉ ነበር ። እነ ዮሴፍን ግን የእግዚአብሔር መልአክ ወርዶ የሄሮድስ ሰራዊት በማያውቁት መንገድ ወሰዳቸው፡፡

ለ.ጥብርያዶስ ፦

ከዚህ በኋላ የእመቤታችን ዘመድ የኬፋዝ ንጉሥ ወደ አለበት ወደ ጥብርያዶስ ሄዱ፡፡ እመቤታችንም ሄሮድስ እንደሚያሳድዳት ዘመዷ ለሆነው ንጉሥ ነገረችው፡፡ ንጉሡም ሄሮድስ የሚያሳድድሽ በምን ምክንያት ነው ብሎ ጠየቃት፡፡ ይህን ሕፃን ለመግደል ስለሚፈልግ ነው አለችው፡፡

ንጉሡም እመቤታችነን ከዚህ ከእኔ ቤት ተቀመጪ አላት፡፡ ቤተሰቦቼንም ማርያም ከእርሱ ቤት መኖርዋን ለማንም እንዳይነግሩ አስጠነቀቃቸው፡፡ ሄሮድስ ግን በብዙ ሀገሮች እየዞረ ቢፈልጋት ሊአገኛት አልቻለም፡፡ ሄሮድስ እንዲህ ይል ነበር፡፡ ማርያምን ምድር ዋጠቻትን? ሄሮድስ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመግደል ያደረገው ጥረት የደከመው ድካም እጅግ ብዙ ነው ያለውን ኃይል አሟጦ ተጠቅሞአል የሚፈልገውን አለማግኘቱ ደግሞ ድካሙን ውጤት አልባ አድርጎታል፡፡

ከብዙ ቀናት በኋላ ሄሮድስ ጥብርያዶስ በሚባል ሀገር እመቤታችን መኖርዋን ሰማ፡፡ እመቤታችን ወደ አለችበት ንጉሥ ደብዳቤ ጽፎ መልእክተኛ ላከ፡፡ ሄሮድስ የጻፈው ደብዳቤ እንዲህ ይላል፡፡

ንጉሥ ሆይ ሰላምታ ይገባሃል፡፡ ማርያምን ከነልጅዋ ያዝልኝ ብዙ ወርቅ እና ብር እሰጥሃለሁ በእኔ እና በአንተ መካከል ጽኑዕ ፍቅር ይሆናል፡፡ ንጉሡም የሄሮድስን ደብዳቤ አንብቦ በጣም ተገረመ፡፡ እንዲህም አለ፡፡ ማርያም በእኔ ቤት መኖርዋን ለሄሮድስ ማን ነገረው? መቼም ሰው አልነገረውም ሰይጣን ነግሮታል እንጂ፡፡ የእመቤታችን ዘመድ የሆነው ንጉሡም ሄሮድስ የላከውን መልዕክት ለእመቤታችን ነገራት፡፡ እመቤታችንም በጣም ደነገጠች፡፡ ንጉሡም እኔ ከሞትኩ ትሞቻለሽ እኔ ከዳንኩ ትድኛለሽ አትፍሪ፣ ለሄሮድስ አሳልፌ አልሰጥሽም አላት፡፡"ወትቤ ማርያም ዘፈቀደ አምላከ እስራኤል ለይኩን /ማርያምም የእስራኤል አምላክ የፈቀደው ይሁን" አለች/፡፡ በዚያች ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ  መጥቶ ሲነጋ ይህን ሀገር ለቀሽ ወደ አድባረ ሊባኖስ ሂጂ አላት፡፡ በዚያም እኔ መጥቼ ተነሺ እስክልሽ ድረስ ተቀመጪ አላት፡፡ በነጋ ጊዜ መልአኩ የነገራትን ለንጉሡ ነገረችው፡፡ ንጉሡም ደስ ብሎት የሦስት ቀን መንገድ እሰከ ዛብሎን እና እስከንፍታሌም ድረስ ሸኛቷት  ወደ ሀገሩ ተመለሰ፡፡

ሐ.አድባረ ሊባኖስ ፦

ክፍል ዘጠኝ ይቀጥላል.....

   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
    @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●
•┈┈┈


​​✞ ዘመነ ጽጌ ✞

ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6

"ልጄን ከግብፅ ጠራሁት"
ት.ሆሴዕ ፲፩፥፩

ከመምህር ዮሐንስ ለማ

ክፍል ሰባት [፯]

ጥጦስና ዳክርስ (ሁለቱ  ወንበዴዎች)

ጥጦስ እና ዳክርስ ሁለት ወንበዴዎች መተዳደሪያቸው ቅሚያ ነበር፡፡ እነ ዮሴፍ ከገሊላ በወጡ ጊዜ ወንበዴዎቹ ተከተልዋቸው፡፡ በበረሃ ቢፈልጓቸውም እስከ ስድስት ቀን አላገኝዋቸውም፡፡

በሰባተኛው ቀን አገኝዋቸውና ዛሬስ እግዚአብሔር ከእጃችን ጣላችሁ ብለው እየሮጠ ሄዱባቸው፡፡ ሰሎሜ አስቀድማ ልብሷን ጥላላቸው ሸሸች፡፡ወንበዴዎቹ ከእነዮሴፍ እጅ የተገኘውን ቀምተው ከሄዱ በኋላ ጥጦስ ዳክርስን እንዲህ አለው፡፡

ይቺ ሴት የነገሥታት ወገን ትመስለኛለች፡፡ ሕፃኑም ከነቢያት አንዱ ይመስለኛል፡፡ የቀማናቸውን እንመልስላቸው? ዳክርስም ጥጦስን እንዲህ ያለውን ርኅራኄ ከየት አገኘኸው? ይህን ውንብድና ያስተማርከኝ አንተ ነህ፡፡ ሌላው ደግሞ ዛሬ የቀማነው የእኔ ድርሻ ነው የራስህን ድርሻ ወስደህ የእኔን ድርሻ እንመልስላቸው ትላለህ ? አለው፡፡

እነዚህ ሁለት  ቀማኞች አንድ ቀን የቀሙትን አንደኛው ሲወስድ በሌላ ቀን የቀሙትን ደግሞ ሁለተኛው ይወስድ ነበር፡፡ በዚህ ዕለት የቀሙት የዳክርስ ድርሻ ነበር፡፡ ጥጦስም ከገሊላ እስከዚህ የቀማነውን አንተ ውሰድ ይህን ለእኔ ስጠኝና ልመልስላቸው አለው፡፡

ዳክርስም በዚህ ሐሳብ ተስማማ፡፡ ዳክርስ ያልታደለ ሰው ነው፡፡ ጥሩ እድል ገጥሞት ነበር አልተጠቀመበትም፡፡ በትንሽ ርኅራኄ ብዙ በረከት አመለጠው፡፡ ወደ አርሱ ያንዣበበውን ፀጋ ለጓደኛው ሰጠው፡፡

እመቤታችን ሁለቱ ወንበዴዎች ቁመው በዚህ ሐሳብ ሲወያዩ አይታ ፈራች፡፡ ወንበዴ የቀማውን ይዞ ይሄዳል እንጂ ለምን ቁሞ ይማከራል? ምን አልባት ልጆቻቸው የሞቱባቸው ሰዎች ይሆናሉ፡፡ በዚህ ሕፃን ምክንያት ልጆቻችን ሞቱብን ብለው ልጄን ሊገሉብኝ ይሆናል ብላ ጽኑዕ ለቅሶን አለቀሰች፡፡

ሕፃኑ ኢየሱስ ክርስቶስም እናቱም ድንግል ማርያምን እንዲህ አላት፡፡ አይዞሽ እናቴ አታልቅሺ አይገሉኝም እንመልስላቸው እያሉ ነው፡፡ እኔ በቀራንዮ ስሰቀል እነሱም በቀኜ እና በግራዬ ይሰቀላሉ አንዱ አምላክነቴን አምኖ ይድናል ሁለተኛው ግን አይድንም፡፡

ከዚህ በኋላ ጥጦስ የተባለው ወንበዴ ገንዘባቸውን መለሰላቸውና ጌታን አቅፎ ይዞ ሲሄድ ሰይፉ ወድቆ ተሰበረበት፡፡ በጣም አዘነ፡፡ ጌታ የሰይፍህን ስብርባሪ ሰብስብ አለው፡፡ ጥጦስ የሰይፉን ስብርባሪ ሰበሰበ፡፡ ጌታም እንደቀድሞው ይሁንልህ አለው፡፡ሰይፉም እንዳልተሰበረ ሆነ፡፡

ጥጦስ ሕፃኑ ከነቢያት ወገን ይመስለኛል ብሎ የገመተው ግምት እውን ሆነለት፡፡ ተአምራቱን አየና አደነቀ፡፡ ጌታ ጥጦስን እንዲህ አለው፡፡ አዳምን ቀድመኸው ገነት ትገባለህ፡፡ ጥጦስም ሄዶ ጌታ የነገረውን ሁሉ እና ያደረገለትን ተአምራት ለጓደኛው ነገረው፡፡ ጓደኛው ግን አላመነም፡፡ ጥጦስ የተባለው ወንበዴም ጌታ በተሰቀለ ጊዜ በጌታ ቀኝ ተሰቅሎ ፀሐይ ስትጨልም አይቶ የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት አምኖ "ጌታ ሆይ በመንግስትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ አለው፡፡ኢየሱስም እውነት እልሃለሁ ዛሬ ከኔ ጋር በገነት ትሆናለህ"ሉቃ፳፫፥፵፪። ጌታ አዳምን ቀድመኸው ገነት ትገባለህ ብሎ በጫካ የሰጠውን ተስፋ በመስቀል ላይ ፈጸመለት፡፡

እመቤታችን ከልጇ ጋር በስደት ከተጓዘችባቸው ሀገራት መካከል፦

ክፍል ስምንት ይቀጥላል.....

   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
    @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●
•┈┈┈


​​✞ ዘመነ ጽጌ ✞

ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6

"ልጄን ከግብፅ ጠራሁት"
ት.ሆሴዕ ፲፩፥፩

ከመምህር ዮሐንስ ለማ

ክፍል ስድስት [፮]

ንጉሥ ሄሮድስ እና የ144000 ሕፃናት ሞት በቤተመንግስት

ከዚህ በኋላ ብዙ ሕፃናት ከእናቶቻቸው ጋር በሄሮድስ ትዕዛዝ  በቤተመንግሥት ለመታረድ ተሰበሰቡ፡፡ ልጅ ያላቸው ወላጆች ልጆቻቸውን እየያዙ ሲሄዱ ልጅ የሌላቸው ድሃዎች ደግሞ ሀብት ንብረት ልብስ ቀለብ  ለመቀበል የሀብታሞችን ልጆችን እየተዋሱ ይዘው ሄደው ነበርና በጠቅላላው  በሄሮድስ ቤተመንግስት 144 000 ሕፃናት ተሰበሰቡ፡፡

ሄሮድስ በተንኮል የሰነቀው የተስፋ ዳቦ ሕፃናቱንም ወላጆችንም የሚያጠግብ መስሎ ስለቀረበ በቤተልሔም አንድ ሕፃን አልቀረም፡፡ ሄሮድስ የሚፈልገው የአይሁድ ንጉሥ የተባለው ሕፃን ክርስቶስ ግን ከ 144 000 ሕፃናት መካከል አልነበረም፡፡

ሄሮድስ በግብዝ አእመሮው ከ 144 000 ሕፃናት መካከል አንዱ የአይሁድ ንጉሥ የተባለው ሕፃን ሳይሆን አይቀርም ብሎ ሕፃናቱ እስኪገደሉ ይቸኩል ነበር፡፡ ሁሉንም ሕፃናት ግደሉ ብሎ ለወታደሮቹ ንጉሳዊ ትዕዛዙን አስተላለፈ፡፡ የሄሮድስ ወታደሮች በአንድ ቀን 144 000 ሕፃናትን አረዱ፡፡ በየሰፈሩ ለቅሶና ዋይታ ሆነ፡፡

የንጉሡ ወታደሮችም በእርዳታ ስም የሰበሰብዋቸውን ሕፃናት እጅግ በሚዘገንን መልኩ  የእናቶቻችውን  ጡት እንኳ በአግባቡ ጠጥተው ሳይጨርሱ አንገት አንገታቸውን በሰይፍ ቆራርጠው ጨረስዋቸው፡፡ይሁን እንጂ ይህ የሕፃናት እልቂት በንጉሱ ትእዛዝ ምክንያት ከመፈጸሙ አስቀድሞ ንጉሡ ይህንን እኩይ ሐሳብ ሲያስብ በዮሴፍ ጠባቂነት፣ በእመቤታችን እናትነትና በቅድስት ሶሎሜ ረዳትነት ያድግ የነበረው ጌታችን ይህ አዋጅ ከመታወጁና እልቂቱም ከመፈጸሙ አስቀድሞ መልዓከ እግዚአብሔር በሌሊት ለቅዱስ ዮሴፍ ተገልጾ "ተንሥእ ወንሣእ ሕፃነ ወእሞ"  ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው፣ አለጊዜውም ደሙን ሊያፈሰው አጥብቆ ይፈልገዋልና እናቱንና ልጁን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ። ማቴ፪፥፩-፳፫

በማለት ተናግረውና በዚያች ሌሊት ወደ ምድረ ግብፅ ጉዞ ጀመሩ፡፡ ታሪኩ በማቴዎስ ወንጌል እና ጥር ሦስት ቀን በሚነበበው በመጽሐፍ ስንክሳር ተመዝግቧል፡፡ ነቢዩ ኤርምያስ ስለዚህ ጽኑዕ ኀዘን ትንቢት ተናግሮ ነበር፡፡"ድምፅ በራማ ተሰማ ለቅሶና ብዙ ዋይታ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች መጽናናትንም  አልወደደችም የሉምና" የተባለው ተፈጸመ።ማቴ፪፥፲፰ ,ኤር ፴፩፣፲፭
ራሔል የያዕቆብ ሚስት የዮሴፍና የብንያም እናት መሆንዋ/በዘፍጥረት ፴፥፳፪ እና ፴፭፥፲፮ተጽፏል፡፡ የቤተልሔም ሕፃናት በሄሮድስ ሰይፍ በታረዱ ጊዜ ራሔል አልነበረችም፡፡ ሆኖም ልጆቻቸው የታረዱባቸው እናቶችና የታረዱ ሕፃናት የራሔል የልጅ ልጆች ስለሆኑ በልጆቻቸው ሞት መጽናናት ያቃታቸውን እናቶች በራሔል ወክሎ ይናገራል፡፡ ኤርምያስ በልጆቻቸው ሞት የሚያነቡትን የእስራኤልን ሴቶች ራሔል ብሏቸዋል፡፡

ከእመቤታችን ስደት ጋር  ታሪክ ያስተናገደው የዮሴፍ ልጅ ዮሳ

የዮሴፍ ልጅ ዮሳ ከእነ ዮሴፍ ጋር አልተሰደደም ከአባቱ ቤት ቀርቶ ነበር፡፡ ሄሮድስ እነ ዮሴፍን ለመያዝ ብዙ ጭፍራ ላከ፡፡ የሄሮድስን የተንኮል ምሥጢር የሚያውቁ ሰዎች ሄሮድስ ዘመዶችህን ሊያስገድል ብዙ ጭፍራ /ወታደር/ ላከ ብለው ለዮሳ ነገሩት፡፡ የዮሴፍ ልጅ ዮሳ እየሮጠ ወደ ዘመዶቹ ሲሄድ ሰይጣን ሰው መስሎ መንገድ ዳር ተቀምጦ የት ትሄዳለህ አለው፡፡ ወደ ዘመዶቼ አለ ዮሳ፡፡ የሄሮድስ ወታደሮች ለጥቂት ቀደሙህ እሰከአሁን ዘመዶችህን ገለዋቸው ይሆናል፡፡ ምን ያደክምሃል ተመለስ አለ ሰይጣን፡፡ ዮሳም ዘመዶቼ ሞተው ከሆነ  እቀብራቸዋለሁ አልሞቱም  ከሆነ ሄሮድስ እያስፈለጋቸው መሆኑን አነግራቸዋለሁ ብሎ የሰይጣንን ምክር ሳይቀበል መንገዱን ቀጠለ፡፡ እግዚአብሔር ለዮሳ የአንበሳን ኃይል ሰጠው፡፡ እነ ዮሴፍ ሦስት ቀን የተጓዙትን መንገድ በአንድ ቀን ተጓዘና እነ ዮሴፍ ከደረሱበት ቦታ ደረሰ፡፡ እነ ዮሴፍ ሦሰት ቀን በተከታታይ ስለተጓዙ ደክሞቸአው አርፈው ነበር፡፡ ሰሎሜ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ስታጥበው አገኛቸው፡፡ዮሳ ሰላም ዋላችሁ ሰላም አደራችሁ ሳይል እንደደረሰ በጣም የሚያስደነግጥ ቃል ተናገረ፡፡ እንዲህም አላቸው በቤተልሔም እና በይሁዳ ሕፃን ያዘለች ሴት አትገኝም፡፡ ሁሉንም ሕፃናት ሄሮድስ በሰይፍ አሳርዷቸዋል፡፡ ይህን ሕፃን ኢየሱስ ክርስቶስን ልታስገድሉት ከዚህ ተቀምጣችኋል፡፡ እመቤታችን የዮሳን ቃል በሰማች ጊዜ ሕፃኑን ኢየሱስ ክርስቶስን ከሰሎሜ እጅ ተቀበለችና አቅፋ ይዛ በሌሊት ብርድ እና በፀሐይ ቃጠሎ መከራ የምቀበለው ከሞት ላላድንህ ነው ብላ ጽኑዕ ልቅሶን አለቀሰች፡፡
ሕፃኑ ኢየሱስ ክርሰቶስ ዮሳን እንዲህ አለው ድካምህ ዋጋ የሚያሰጥ ነው ነገር  ግን እናቴን ስለአስደነገጥካት ይችን ድንጋይ ተንተርሰህ ተኛ አለው ፡፡ ወዲያውም  ነፍሱ ከሥጋው ተለየች፡፡ አባቱ ዮሴፍ ቀበረው፡፡ እንደ እኛ እንደሰዎች አመለካከት ዮሳ የሚሸለም ሰው ነበር እንጂ የሚቀጣ ሰው አልነበረም፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ዮሳ ባጠፋው ትንሽ ጥፋት በሥጋው ተቀጥቶ በነፍሱ ሕያው እንዲሆን አደረገው ፡፡ የአግዚአብሔር ወዳጆች ትንሽ ጥፋት ሲአጠፉ በሥጋቸው ይቀጣሉ፡፡ ለምሳሌ አሮን እና ሙሴ የእግዚአብሔር ወዳጆች ነበሩ፡፡ አንድ ቀን ባጠፉት ጥፋት ተቀጡ፡፡ ወደ ተስፋይቱ ምድር ሳይገቡ በመንገድ ሞቱ "እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን በእስራኤል ልጆች ፊት ትቀድሱኝ ዘንድ በእኔ አላመናችሁምና ስለዚህ ወደ ሰጠኋችሁ ምድር ይህን ጉባዔ ይዛችሁ አትገቡም" አላቸው። ዘኁ፳፥፩-፲፫

ጥበበኛው ሰሎምንም እንዲህ ይላል "ልጄ ሆይ የእግዚአብሔርን ተግሣጽ አትናቅ በገሠጸህም ጊዜ አትመረር እግዚአብሔር የወደደውን ይገሥጻልና አባት የሚወደውን ልጁን እንደሚገሥጽ" ምሳ፫፥፲፩ 
ዛሬስ በጌታ ላይ፣ በእመቤታችን ላይ፣ በቅዱሳን ላይ ያልተገባ የሰነፍ ንግግርንስ የሚናገሩ ምንኛ በነፍስ በሥጋ ይቀጡ ይሆን ?

ጥጦስና ዳክርስ (ሁለቱ  ወንበዴዎች)

ክፍል ሰባት ይቀጥላል.....

   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
    @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


​​✞ ዘመነ ጽጌ ✞

ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6

"ልጄን ከግብፅ ጠራሁት"
ት.ሆሴዕ ፲፩፥፩

ከመምህር ዮሐንስ ለማ

ክፍል አምስት [፭]

ንጉሥ ሄሮድስ እና ሰብአ ሰገል

ከሩቅ ምሥራቅ የመጡት ነገሥታት (ሰብአ ሰገል) ለዓመታት ያህል ተጉዘው ኢየሩሳሌም ከደረሱ በኋላ፡

"አይቴ ሀሎ ንጉሠ እስራኤል ዘተወልደ ከመነሃብ ሎቱ አምሃ ወሰጊድ" ..... ይዘን የመጣነውን መባዕ እና ስግደት እናቀርብለት ዘንድ የተወለደውሕፃን ወዴት ነው ‘’ ? ወርቅ ለመንግስቱ፣ ዕጣን ለክህነቱ፣ ከርቤ ስለሞቱ እና በረክትለት ዘንድ የተወለደው የዓለም ንጉሥ የት አለ ? እያሉ ሲፈልጉና ሲያፈላልጉ በመልእክተኞቹ አማካኝነት የሰማው የኢየሩሳሌም ንጉሥ ሄሮድስ ይህ ምን ዓይነት ነገር ነው ? የትስ ያለ የዓለም ንጉሥ ነው ? የሚወለደውስ ከማንና መቼ ነው ? አሁን ገና በተወለደ ጊዜ እንዲህ ነገሥታትን ያሰገደ ሕፃን ሲያድግማ እኔንም ያሰጋኛል፤ አልፎም ያጠፋኛል ብሎ እጅግ ከመፍራትና ከመደንገጡ የተነሳ ነገሥታቱን አስጠርቶ ስለ ነገሩ አስፍቶ ጠየቃቸው፡፡ እነርሱም በኮከብ መሪነት ለዓመታት ያህል መጓዛቸውንና አጠቃላይ የአመጣጣቸውን ታሪክ ተረኩለት፡፡ ታሪኩን ሰምቶና ተረድቶ ከበቃ በኋላ ንጉሡ ሄሮድስ ለነገሥታቱ ስለ ሕፃኑ ጠቅላላ ሁኔታ እንዲያጠኑ ሲመለሱም ምስጢሩን እንዲገልጹለት አደራ ብሎ ካሰናበታቸዉ በኋላ መልዓከ እግዚአብሔር ተገልጾ በሌላ መንገድ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ስለነገራቸውና ምስጢሩንም ስለገለጸላቸው የሄሮድስ ተንኮላዊ አደራን ወደ ጎን ትተው መልአኩ እንደነገራቸው በሌላ መንገድ ወደሃገራቸው ተመለሱ፡፡ከሰብአ ሰገል መረጃን ለማግኘት ያደረገው ጥረት ሳይሳካለት ቀርቷል፡፡

ሰብአ ሰገል ወደ እርሱ ባለመመለሳቸው የተበሳጨው ሄሮድስ የራሱን እርምጃ ለመውሰድ ወሰነ፡፡ ምንጊዜም ሄሮድስ የሚፈልገው በቤተልሔም የተወለደውን የአይሁድ ንጉሥ የተባለውን ሕፃን ክርስቶስን አግኝቶ መግደል ነው።

ስለሆነም ሕፃኑ ክርስቶስ ያለበትን ቦታ የሚጠቁም ሰው አላገኘም፡፡ ትክክለኛውን መረጃ ባያገኝም ከሰብአ ሰገል አንደበት የሰማውን ለእንቅስቃሴው መነሻ አድርጎ ተነሣ፡፡

ሄሮድስ እንደመረጃ የተጠቀመው ፡- ሰብአ ሰገልን የመራቸው ኮከቡ የተገለጠበትን ዘመን ነው፡፡ ሰብአ ሰገልን ጠይቆ የኮከቡን ዘመን ተረድቶ ነበር፡፡ ኮከቡ ለሰብአ ሰገል ከተገለጠ ወይም ሰብአ ሰገልን መምራት ከጀመረ ሁለት ዓመት እንደሆነው በጥንቃቄ ተረድቷል፡፡ ሰብአ ሰገልን የመራቸው ኮከብ ሁለት ዓመት ከሆነው የአይሁድ ንጉሥ የተባለው በቤተልሔም የተወለደው ሕፃን ክርስቶስም ሁለት ዓመት ሊሆነው ይችላል የሚል ግምት መገመት ጀመረ ፡፡

ቦታው ቤተልሔም መሆኑ እና የአይሁድ ንጉሥ የተባለው ሕፃን የሁለት ዓመት ሕፃን መሆኑ በመረጃ ተደግፏል፡፡ ነገር ግን በቤተልሔም ብዙ የሁለት ዓመት ሕፃናት ይኖራሉ፡፡ የአይሁድ ንጉሥ የተባለውን ሕፃን እንዴት ለይቶ ማወቅ ይቻላል?የሄሮድስ ልቡ የሚረጋጋበት መፍትሔ አላገኘም፡፡ ሌላ አማራጭ መፈለግ ግድ ሆነበት፡፡ ከዚህ በኋላ ሄሮድስ በቤተልሔምና በአውራጃዋ የሚኖሩትን ሁለት ዓመት የሆናቸውን እና ከሁለት ዓመት በታች የሆኑትን ሕፃናት መግደል አማራጭ የሌለው የጭንቀቱ መፍትሔ አድርጎ ወሰደው፡፡

መፍትሄውም በቤተልሔም ሕፃናት ላይ ይህን የእልቂት ትእዛዝ ማስተላለፍ በማሰብ ነው፡፡ ሄሮድስ ከቤተልሔም ሕፃናት አንዱ ተነስቶ እንዳይቀር እጅግ ይጠነቀቅ ነበር፡፡ ወታደሮቼ በየሰፈሩ እየዞሩ ሕፃናትን ቢገድሉ ብዙ ወላጆች ልጆቻቸውን ይሰውራሉ ሕፃናቱም ከሞት ያመልጣሉ ከሚያመልጡትም ሕፃናት አንዱ ክርስቶስ ሊሆን ይችላል፡፡

ሌላው ደግሞ የሚገደሉት ሕፃናት ከሁለት ዓመት በታች መሆናቸው በግምት አይታወቁም በማለት ይጨነቅ ነበር፡፡ ሄሮድስ ብዙ ሐሳቦችን ሲያንሸራሸር ከቆየበኋላ ሁሉም ሕፃናት በቤተመንግሥቱ አንድ ቀን ቢገኙ የተሻለ ነገር እንደሆነ አሰበ፡፡ ነገር ግን ሕፃናቱ እንዴት እንደሚሰበሰቡ ሌላ ፈተና ሆነበት በንጉሣዊ ትእዛዝ ወላጆች ልጆቻቸውን እየያዙ እንዲመጡ ቢደረግ በኃይል ወይም በግድ የሆነ ነገር ውጤታማ እንደማይሆን እና ብዙ ሕፃናት እንደሚቀሩ መገመት አላቃተውም፡፡

የቤተልሔም ሕፃናት አንድ ሳይቀር እንዲሰበሰቡ ለማድረግ የወላጆች ፈቃደኝነት አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል፡፡ ንጉሥ ሄሮድስ በቤተልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን ሁለት ዓመት የሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ።
ማቴ፪፥፲፮-፲፰

ሄሮድስ ሕፃናትን ለመግደል በቤተመንግሥቱ ለመሰብሰብ የተጠቀመበት ምክንያተ ፈጠራ

የሄሮድስ ቅንዓት እጨመረ ከመሄዱም በላይ ነገሥታቱን ሲጠብቅ ሁለት ዓመት መሆኑን ተከትሎ በነገሩ ተሳልቀውበት (አታልለውት) በሌላ መንገድ መሄዳቸዉን  ከተረዳ በኋላ ሰይጣን የጭካኔ ጦሩን መዞ አንድ ጊዜ በልቦናው ላይ ስለተከለበት ሁለት ዓመትና ከዚያ በታች ያሉ ሕፃናት ሁሉ በእርዳታ ስም በየሀገሩ እንዲሰበሰቡ የሚል ሰይጣናዊ የአረመኔነት መግለጫ የሆነ አዋጅ በብሔራዊ ደረጃ አሳወጀ፡፡

ሄሮድስ ሕፃናትን በቤተመንግሥቱ ለመሰብሰብ አንድ  ምክንያት ፈጠረ፡፡ እንዲህም አለ የሮሙ ንጉሥ ቄሣር የላከው መልእክት ከእኔ ደርሷል፡፡

ሁለት ዓመት የሆናቸውን እና ከሁለት ዓመት የሚያንሱትን ሕፃናት እንድቆጥር ቄሣር አዞኛል፡፡ ለሕፃናቱ ወላጆች ገንዘብ እና ልብስ ይሰጣቸዋል፡፡ ሕፃናቱም በቤተመንግስት በመልካም አስተዳደግ ያድጋሉ፡፡ ማርና ወተት እየተመገቡ ጥበብ እየተማሩ በቤተመንግስት አድገው የመንግስት ሠራተኞች ይሆናሉ፡፡ ይህንም የተንኮል አነጋገር በአዋጅ አስነገረ፡፡ ያን ጊዜ አይሁድ የሮሙ ንጉሥ የቄሣር ቅኝ ተገዦች ነበሩን ፡፡
ሄሮድስም የአይሁድ ንጉሥ ሊሆን የቻለው ከቄሣር ተወክሎ ነው፡፡ ስለሆነም ትእዛዙ ከቄሣር እንደመጣ አድርጎ በውሸት ማዕበል ቤተልሔምን አጥለቀለቃት፡፡ ትእዛዙ ግን ከሮሙ ንጉሥ ከቄሣር የመጣ ሳይሆን የሐሰት አባት ከሆነው ከዲያብሎስ የመጣ ነው፡፡ዛሬም  ሐሰት ከዲያብሎስ እየተወለደ በቤተመንግስት ያድጋል፡፡ ሐሰት ለገዢዎች የሥልጣናቸው እድሜ ማራዘሚያ ይመስላቸዋልና ነው።
ዮሐ፰፥፵፬

ንጉሥ ሄሮድስ እና የ144000 ሕፃናት ሞት በቤተመንግስት

ክፍል ስድስት ይቀጥላል.....

   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
    @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


✞ ባለ ጸጋ እመቤት ✞

ባለጸጋ እመቤት ባለጸጋ እናት
አፍሰናል ከደጅሽ ብዙ በረከት
ወጀቡን ቀዝፈናል ብለን ማርያም
እንዘምራለን እስከ ዘለዓለም (፪)

     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ሠው በሌለበት ከተማ
ሞት በከበደው ጨለማ
ሞገስ ገንዘቤ ዘመዴ
በምልጃሽ ቀንቷል መንገዴ
ፋና ሆነሽኝ መብራቴ
በክብርሽ ደምቆልኝ ቤቴ
ሐሴት አረኩኝ ደስታ
ያዘነው ገፄ ተፈታ

     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
እንደኔ ኃጢአት በደል
ይገባኝ ነበር መስቀል
ጽኑ ከዳኗ ጋረደኝ
እንባ ጸሎቷ ታደገኝ
እስኪ ልናገር ስራዋን
የምሕረት እናት  መሆኗን
ጽዮን እጆቿን ዘርገታ
አስታርቃኛለች ከ ጌታ

     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
የክብርቅ ሰንደቅ አርማዬ
ወደ መቅደሷ መግቢያዬ
አንችን ይዤአለሁ ጠበቃ
የሞቴ ታሪክ አበቃ
እልል እላለሁ ከልቤ
ለቅሶዬ ሠምሮ ሐሳቤ
ድንግል ፍቅር ናት ሠላም
ለክብሮ ይስገድ ዓለም

     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
የልፍኜ ማማር ውበቴ
ትሩፋቴ ነሽ ሙላቴ
ስምሽ መቀነት ሆኖኛል
የዛለው ክንዴ በርትቷል
ባማረው ቤትሽ አድጌ
በልጅሽ ጸጋ በልፅጌ
በእናትነትሽ በረከት
ይኸው ቆሜያለሁ በሕይወት

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://t.me/
yem rel='nofollow'>ezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/y
emezmur_gexe href='m

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥' rel='nofollow'>m

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥/b>


​​✞ ዘመነ ጽጌ ✞

ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6

"ልጄን ከግብፅ ጠራሁት"
ት.ሆሴዕ ፲፩፥፩

ከመምህር ዮሐንስ ለማ

ክፍል አራት [፬]

ለ.ጣኦታተ ግብጽን ለማጥፋትና ለመደምሰስ ወደ ምድረ ግብጽ ተሰደዱ

ግብጽ ከነገሥታቶቿ ጀምሮ ጣኦትን የሚያመልኩ አህዛብ የነበሩ ህዝቦች ነበሩ፡፡እነዚህ ጣኦታት ደግሞ የበሬ፣ የላም፣  የአንበሳ፣ የወፍ ምስል አስቀርጸው ያመልኩ ስለነበር ለዚህም ከሙሴና ከአሮን ጸሎት የተነሳ የግብጻውያን የእጃቸው ሥራ መጥፋቱን፣ እግዚአብሔር በናቡከደነጾር አድሮ ወደ ግብጽ መምጣቱን፣ ጣዖታትን ማጥፋቱን የተነበየበት ከመሆኑ በላይ በዘባነ ማርያም ኅዙል /በማርያም ጀርባ ታዝሎ/ በፈጣን ደመና በተመሰለች ከእመቤታችን ጋር ወደ ግብጽ ተሰዳለች፡፡ሊቃውንት እመቤታችንን ሲመስሏት ደመና ኢሳይያስ የሚሏትም ስለዚህ ነው፡፡በዚህ ትንቢት ላይ እንደተገለጸው ግብጽ በጣዖታት የተሞላች በመሆኗ የጌታችን ስደት በግብጽ ያሉ ጣዖታትን ለማጥፋት እንዲሆን ተጠቅሷል።

ግብጻውያን ከጥንት ጀምሮ በማስመሰል ደንጊያ ጠርበው እንጨት አለዝበው ማዕድን አቅልጠው  የእንስሳትን ምስል  የላም፣ የፍየል፣ የአንበሳ የወፍ  ምስልን በመቅረጽ ያመልኩ ስለነበር ከተማዋ በጣኦታት የተሞላች ነበር ፡፡ 

እነዚህን ለማጥፋት የጌታ ስደት ወደ ግብጽ ይሆን ዘንድ ትንቢት አናገረ።ጌታችን ጣኦታትን ሊያፈርስ ወደ ግብጽ ተሰደደ ገና ከተማዋ ሲገባ በጣኦታቱ ላይ ያደሩ አጋንንት ይጮሁ ጣኦታቱም ይሰባበሩ ጀመር ። ከዚህም ባሻገር በኛ ሕይወትም ውስጥ ጌታን ለመቀበል ጌታ ስራ እንዲሰራብን በቅድስና ለመኖር የልብን ጣዖታት ማጥፋት ማጽዳት ይገባል።

አልያ ጌታንና ጣዖትን በልባችን ማኖር አንችልም ቅዱስ ጳውሎስ "መኑ ደመሮ ለብርሃን ምስለ ጽልመት" "ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? ክርስቶስ ከቤልሆር ጋር መስማማት አለው ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ከጣዖት ጋር ምን መጋጠም አለው።እኛ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነንና፡፡ያለው ለዚሁ ነው፡፡ 

ቅዱስ ዳዊት፡- መዝ፹፫፥፫ "ወፍ ለእርስዋ ቤትን አገኘች ዋኖስም ጫጭቶችዋን የምታኖርበት ቤት አገኘች።" በማለት ሲተነብይ ወፍ ለእርስዋ ቤትን አገኘች ሲል ነቢያት የተነበዩት ፍጻሜውን በእመቤታችን ማግኘቱን አንድም እመቤታችን በስደት ግብጽ መኖርያዋ ማድረጓንዋኖስም ጫጭቶችዋን የምታኖርበትሲል ዮሴፍና ሰሎሜም የሚኖሩበት ቤት ማግኘታቸውን ተናገረ።

ለእመቤታችን ማደሪያ ጠፍቶ ማደሪያዋንግብጽ ማድረጓን ተንብየዋል፡፡ነቢዩ ሆሴዕ፡- "እስራኤል ሕጻን በነበረ ጊዜ ወደድኩት ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት" ሆሴ ፲፩፥፩

እስራኤል በግብጽ ሳሉ እንደተመረጡ ከ፤ዚያም አገር አውጥቶ መንግስት ይሆኑ ዘንድ እንዳበቃቸው የተናገረበት ትንቢት ከመሆንና፥ ጋር የጌታችን ወደ ግብጽ መሰደድ ሔሮድስ እስኪሞት በዚያ መቀመጡን ከዚያም መመለሱን የሚያመለክት መሆኑን ቅዱስ ማቴዎስ የነቢዩን ቃል ፍጻሜአድርጎተናግሯል። ማቴ ፪፥፲፭

ሐ ሰው መሆኑን ለመግለጽ  ወደ ምድረ ግብጽ  ተሰደደ

ኢየሱስ ክርስቶስ አገሩን ሳይለቅ ከሄድሮስ ዓይን መሠወር ይችል ነበር።ነገር ግን በአምላካዊ ጥበቡ ከሄሮድስ ዓይን ተሰውሮ ቢሆን ሥጋ መልበሱ ሰው መሆኑን አይገለጽም ነበር።በሄሮድስ ዓይን የማይታይ ከሆነ ሥጋ ሳይለብስ የለበሰ መስሎየተገለጸ ሥጋና አጥንት የሌለው/ምትሐት/ ነው በተባለም ነበር።

ከአዳም አካል አንድም ያልጎደለው ሙሉ ዳግማዊ አዳም መሆኑን እና የለበሰው ሥጋ የሚደማ የሚቆስል በሰይፍም ሆነ በጦር ቢወጋ ጉዳት የሚደርስበት ሰብአዊ ባሕርይ ያለው መሆኑን ለማስረዳት ስደተኛ ሆነ።

ሥጋ የለበሰ ሁሉ ከጠላቱ ማምለጥ የሚችለው ከጠላቱ ፊት ዞር በማለቱ እና በመሸሹ ስለሆነ ጌታም ከጠላቱ ከሄሮድስ ለማምለጥ ሰው እንደመሆኑ ወደ ግብጽ ሸሸ፡፡

መ.ዲያብሎስን ለማሳደድ ወደ ምድረ ግብጽ  ተሰደደ

አዳም ዕፀ በለስን በልቶ ከፈጣሪው ጋር ተጣልቶ ከገነት ከወጣ በኋላ የእግዚአብሔርና የሰው ግንኙነት እየራቀ ሄደ፡፡ይህን የፈጣሪና የፍጡር መራራቅ ያመጣው ዲያብሎስ ሲሆን በፈጣሪ መራቅ ፈንታ እርሱ መቅረብ ይፈልግ ነበር፡፡

 ስለሆነም ፈጣሪው ከሰው ጓሮ ወደ ወጣበት የሰው ልጅ ሳይጠራ መምጣት ወይም መቅረብ ጀመረ።

ዲያብሎስ የአዳምን ልጆች ተቆጣጠራቸው።ልባቸውን በፍቅረ ጣኦት ሸፍኖ አምልኮተ እግዚአብሔር እንዳያዩ አደረጋቸው ብዙ የአዳም ልጆችም የአግዚአብሔርን ፈቃድ ሳይሆን የሰይጣንን ፈቃድ ሲፈጽሙ ኖሩ።ጌታም "አሁን የዚህ ዓለም ገዥወደ ውጪ ይጣላል" ዮሐ፲፪፥፴፩በማለት ሰይጣን ዓለሙን ተቆጣጥሮት እንደነበረ ይገልጻል።

እግዚአብሔር ወልድ የሰውን ሥጋ በለበሰ ጊዜ የፈጣሪና የፍጡር ግንኙነት እንደገና ተመሠረተ።

ኢየሱስ ክርስቶስ አገሩን ለቆ በመውጣቱ ዲያብሎስን ከተቆጣጠረው ከሰው ልቡና አስወጣው ጌታ ከሄሮድስ ፊት እየራቀ ሲሄድ ዲያብሎስም ከሰው ፊት እየራቀ ሄደ።

የጌታ ስደት በተዘዋዋሪ የዲያብሎስ ስደት ሆነ ጌታ የሚቀበለው መከራ ሁሉ ዲያብሎስን በርቀት የሚመታ መሣርያ ነበር፡፡ በመጨረሻም በመስቀል ላይ የሆነው የጌታ ሞት የዲያብሎስ ሞት ሆነ፡፡

በቀጣይ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም  በስደቷ ወቅት  ያሳለፈቻቸውን  ውጣ ውረድና ተያያዥ ክስተቶችን  እንዲሁም የጉዞዋን ዋና ዋና መዳረሻዎችን ጭምር ለማስነበብ እንሞክራለን፡፡

ክፍል አምስት ይቀጥላል....

   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
    @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


✞ ዮሐንስ ሆይ ✞

ዮሐንስ ሆይ ታድለሃል
አጽናኝ እናት ተሰጥቶሃል
ከመስቀሉ በግርጌው ሥር
ላሳየኸው ታማኝ ተግባር (፪)


የቀያፋ ጅራፍ ቁጣ
ጌታ ያለው ቀን ሲመጣ
ሁሉም ፈርተው ሲበተኑ
አይተንሃል ቆመህ ጽኑ

     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
የክርስቶስ ክቡር ደሙ
ቁልቁል ሲፈስ ከመስቀሉ
ይህን አይተህ አንብተሃል
በትዕግስቱም ተደንቀሃል

     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ማዕከለ ቀራንዮ
እያነባህ ስትል ወዮ
ልጇ ልትሆን የመረጠህ
ታማኝ ወዳጅ አገልጋይ ነህ

     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ስለ ሰው ልጅ እዳ በደል
አማኑኤል ሞት ሲቀበል
ፊትህ በሐዘን ተቋጠረ
መከራውን እያሰበ

           ድምጽ|
      ወልደጊዮርጊስ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://t.me/
yem rel='nofollow'>ezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/y
emezmur_gexe href='m

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥' rel='nofollow'>m

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥/b>


ማዕረር በጽሐ አመ ወርኀ ገቢር ግዜ
ኢያደንግጸነ በምድረ ትካዜ
ዮሐንስ ነዓ ለኑዛዜ
   ትርጉም
የሚያሳዝን ተግባር  በደረሰ ጊዜ
በምድር ትካዜ እንዳንደነግጥ 
ዮሐንስ ና አረጋጋን

     ✞ ዮሐንስ ዛሬ ና ✞

ዮሐንስ ዛሬ ና ተራራው የሰው ልብ ጠማማ እንዲቀና
መጥምቀ መለኮት(፪)ዮሐንስ ዛሬ ና

ገለባን ከስንዴ በእሳት ሊያጠራ
ፍሬ አልባው ለምሳር ምርቱን በጎተራ
መንሹ በእጁ ያለ ሰማያዊ ብርቱ
መድኃኒት ክርስቶስ ይኸው ቆመ ፊቱ
     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
የአምላኩን ክብር ለራሱ አልተመኘ
ከሰገነት ወርዶ ወድቆ አልተገኘ
እውነትን ሰባኪ ለራሱ አላደላ
ዮሐንስ አሳየ ጌታውን ከኋላ
     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ዘመን ተርፎ አይደለም የዮሐንስ ክብሩ
በአምላክ ተወዶ ነው ለእውነት በመኖሩ
በመንፈስ የሚሄድ ራሱን የሰጠ
ኃያል አምላክ ጌታን ለዓለም ገለጠ
     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ዘካርያስ አየ ኤልሳቤጥን ጸኗት
አምልኮ ስግደትን ስላስተናገደች
ለወላዲተ እምላክ ስግደት እንዲገባ
ዮሐንስ ሰበከ ወደ ዓለም ሳይገባ

           መዝሙር|
     ዘማሪ| ዘውዱ ጌታቸው

"በዚያም ወራት መጥምቁ ዮሐንስ። መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ ብሎ በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ።"
             ማቴ፫፥፩-፪
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://t.me/
yem rel='nofollow'>ezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/y
emezmur_gexe href='m

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥' rel='nofollow'>m

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥/b>


​​✞ ዘመነ ጽጌ ✞

ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6

"ልጄን ከግብፅ ጠራሁት"
ት.ሆሴዕ ፲፩፥፩

ከመምህር ዮሐንስ ለማ

ክፍል ሦስት [፫]

1⃣የእመቤታችንና የልጅዋ  ምክንያተ ስደት ወደ ምድረ ግብጽ

የእመቤታችን ስደት ብለን ስንናገር ከልጅዋ ጋር መሆኑን አንባቢ ሁሉ ልብ ሊለው የተገባ ሲሆን ስለ የእመቤታችን ስደት ምክንያት አበው ያስተማሩንን፣ መጽሐፍት የመዘገቡልንን በጥቂት እንዘረዝራለን፤ 

ትንቢተ ነቢያት እግዚአብሔር ሊያደርግ ያሰበውን ፈቃዱን ሁሉ ለሰው ልጅ እየገለጠ ነቢያትን ትንቢት እያናገረ መምህራንንእየላከ መጽሐፍትን እያጻፈ መሆኑን ልብ ማለት ተገቢ ነው። 

"እግዚአብሔር ይነግሮሙ ለሕዝቡ በመጽሐፍ" እግዚአብሔር ለህዝቡ በመጽሐፍ ይናገራቸዋል መባሉ "በቀንና በሌሊት ባሪያዎቼን ነቢያትን ሁሉ ልኬባቸው ነበር፣ አዎ ልኬባቸዋለሁ"
ኤር ፯፥፳፭ በማለት ገልጧል።

ከነዚህም ትንቢታት መካከል ስለ እመቤታችንና ጌታ ስደት ሲሆን፡- 
ነቢዩ ኢሳይያስ፦ኢሳ፲፱፥፩
"ናሁ እግዚአብሔር ይነብር ዲበ ደመና ቀሊል ፤" "እነሆ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና እየበረረ ወደ ግብጽ ይመጣል።"
ትንቢተ ስምዖን፦
"ባንቺ ደግሞ ሰይፍ ያልፋል አላት።"ሉቃ ፪፥፴፬ ስምዖን በንጉሡ በጥሊሞስ ጊዜ መጻህፍተ ብሉያትን/ ከጥንቱ ዕብራይስጥ ወደ ግሪክኛ /ለማስተርጎም ሰባ ሊቃናትን ባዘዘበት ወቅት ስምዖን የኢሳያስ መጽሐፍ ይደርሰዋል፡፡ "እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅንም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች"።የሚለው ቃል ሲተረጎም ቢከብደው እንዴት ድንግል ትጸንሳለች ብዬ ልተርጉም ብሎ ሴት ትወልዳለች በማለት ቢጽፍ ተኝቶ ሲነሣ የጻፈው ጠፍቶ ድንግል ትጸንሳለች የሚል ተጽፎ ያገኛል፡፡ይህ መሆኑ ቢገርመው መልአኩ መጥቶ ይህንን ሳታይ አትሞትም ብሎት ተሰወረ።
በዚህም የትንቢቱን ፍጻሜ በቤተመቅደስ እጅግ አርጅቶ ሳለ ጠበቀ።ዮሴፍና እመቤታችን እንደ አይሁድ የመንጻት ሕግ በስምንተኛው ቀን ወደ ቤተመቅደስ ሲወስዳት ትንቢቱን ይጠብቅ የነበረው አረጋዊውስምዖን የጌታን ማዳን አየ "እነሆ የብዙዎች ልብ አሳብ ይገለጥ ዘንድ ይህ በእስራኤል ላሉት ለብዙዎቹ ለመውደቃቸውና ለመነሳታቸው ለሚቃወሙት ምልክት ተሾሞአል፡፡
በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል አላት"
ሉቃ፪፥፴፬ በማለት ትንቢቱ መፈጸሙን ሲያይ ይህንንካየሁ ባሪያህን በሰላም አሰናብተው ብሎሲለምን ገና ወደፊት የሚሆነውን የእመቤታችንን ስደት በልጇ አማካኝነት ወደፊት የሚደርስባትን መከራ ተነበየ፡፡

"ወለኪሰ ይበውእ ውስተ ነፍስኪ ኩናተ ኑፋቄ" ሰይፍ ያረፈበትን ለሁለት እንደሚከፈል ሁሉ የእመቤታችን ልብ ከሐዘን ምሬት የተነሣ እንደምትጎዳ የተነበየው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ከልጅዋ ጋር ተሰደደች።

ልብዋን  እንደ ሰይፍ የከፈሉት የእመቤታችን አምስቱ ሐዘናት የሚባሉት፤

💧አይሁድ እንዲገድሉት በቤተመቅደስ ስምዖን ትንቢት በተናገረ ጊዜ።ሉቃ፪፥፴፬

💧እጅና እግሩን አስረው በጲላጦስ አደባባይ በገረፉት ጊዜ።ዮሐ ፲፱፥፩

💧ጌታን ከኢየሩሳሌም ለበዓል ሔደው ሲመለሱ በመንገድ ባጣችው ጊዜ።ሉቃ ፪፥፵፩

💧በዕለተ ዓርብ ዕራቆቱን ተቸንክሮ በሁለት ወንበዴዎች መካከል በሰቀሉት ጊዜ። ማቴ፳፯፥፴፰

💧ወደ አዲስ መቃብር ውስጥ ባወረዱት ጊዜ ያዘነችው ሐዘን።ማቴ ፳፯፥፶፱

አረጋዊው ስምዖን የተናገረው ትንቢት በእመቤታችን የሕይወት ዘመን ሁሉ በልጅዋምክንያት ሰይፍ የተባለ መከራ አልፎባታል በዚህም ሊቁ አባ ሕርያቆስ የእመቤታችነን ምልጃ ሲጠይቅ "አዘክሪ ድንግል አንብዐ መሪረ ዘውኀዘ እም አዕይንትከ ወወረደ ዲበ ገጸ ፍቁር ወልድኪ"ድንግል ሆይ በልጅሽ ፊት የወረደውን ከአይንሽ የፈሰሰውን ዕንባ አሳስቢ በማለት ለኛ ለኃጢአተኛ ልጆችዋ የምታማልደን ስለእንባዋ ይቅር እንደሚለን የተናገረው፡፡

ሀ.ስደተ ቅዱሳንን ለመባረክ  ወደ ምድረ ግብጽ ተሰደዱ

የክርስትና ህይወት የመስቀል ላይ ጉዞ በመሆኑ ክርስቶስን አምነው ለተከተሉት ሁሉ በመከራና በስደት እንደሚያልፍ ጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ከአለም ተመርጠው ለተከተሉት ደቀ መዛሙርቱ ሲያስተምር "እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ" በማለት ተናገረ ።"ማቴ ፲፮፥፳፬

በዚህም ቃል መሠረት ከቅዱሳን ሐዋርያት ጀምሮ የተነሡ ክርስቲያኖች በብዙ መከራ ውስጥ አለፉ በበረሃ ተሰደዱ፣ በዱርበገደሉ ተቅበዘበዙ በሰይፉ ተተረተሩ፣ በድንጋይ ተወገሩ፡፡ዛሬም ቢሆን በእምነት የተሰደድን የተጨነቅን የምንጸልየው ስደትን ከኛ በፊት በሕጻንነቱ በቀመሰ ስደትን በሚያውቅ አምላክ ፊት ነው።
ለ.ጣኦታተ ግብጽን ለማጥፋትና ለመደምሰስ ወደ ምድረ ግብጽ ተሰደዱ

ክፍል አራት ይቀጥላል....

   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
    @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


​​✞ ዘመነ ጽጌ ✞

ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6

  "ልጄን ከግብፅ ጠራሁት"
     ት.ሆሴዕ ፲፩፥፩

       ከመምህር ዮሐንስ ለማ

      ክፍል ሁለት [፪]

በዚህ በወርኃ ጽጌ ( በዘመነ ጽጌ )   የሚጾሙ ክርስቲያኖች ሲኖሩ ጾመ ጽጌ መንፈሳውያን ሰዎች ሳይታዘዙ በራሳቸው ፈቃድ የሚጾሙት ጾም ነው።ወይም የትሩፋትጾም ይባላል።በቀኖና ከታዘዙት ከ7ቱ አጽዋማት ውጪ ትርፍ ጾም ማለት ነው፡፡ከታዘዘው አትርፎ የጾመ ሰው የመጾሙን ዋጋ ያገኛል።

ብዙ መንፈሳዊ ሥራ የሰራ ሰው ብዙ ክብር እንደሚያገኝ መጽሐፍ ይናገራል፡፡ "እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ሐጢአትዋ ተሰርዮላታል።ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል።"ሉቃ፯፥፵፯ የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች በክብርም ከእመቤታችን ጋር ይተባበራሉ፡ነገር ግን የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች ለመመጻደቅ መጾም የለባቸውም፡፡የማይጾሙ ሰዎችንም መንቀፍና መክሰስየለባቸውም።የጽጌ ጾም እንዲጾም በቀኖና ቤተክርስቲያን ከሰባቱ አጽዋማት አንዱተደርጎ ስላልተወሰነ የማይጾሙ ሰዎች ሕገ ጾምን እንዳፈረሱ አድርጎ መውሰድ ስሕተት ነው።

ይልቁንም የሚጾሙ ሰዎች ቢችሉ መጾማቸው እንዳይታወቅባቸው ቢያደርጉ የተሻለ ነው።"ስትጾሙ እንደግብዞች አትጠውልጉ"ማቴ፮፥፲፮ የተባለው ለዚህ ዓይነቱ ጾም ነው፡፡

ጽጌ ማለት አበባ ማለት  ሲሆን  ምድሪቱ  በአበባ  የምትሞላበት ጊዜ በመሆኑ አበው ሊቃውንት እመቤታችንን በብዙ ኅብር መስለዋታል፡፡ በአበባ /ጽጌ/፣ በወይን ሐረግ፣መልካሙን የወይን ፍሬ አስገኝታለችና አበባ ፍሬን እንዲያስገኝ ድንግል ማርያምም ለሰው ያልተቻለውንና የማይቻለውን አንዴ ብቻ የሆነውን መለኮትን በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት በማህፀንዋ ወሰነችው።

አዳምና ልጆቹ እንዳይበላ በተከለከለችዋፍሬ ምክንያት ገነትን ከሚመስል ቦታ እግዚአብሔርን ከሚያክል ጌታ ተለዩ የሰው ልጅ ድቀት ተጀመረ ሁሉን አጣ የመጀመሪያ በደል/ጥንተ አብሶ/ ማለት ይህ ነው።
የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር የመለየትን ረጅም ግዜን ገፋ ገዥ የነበረው የሰው ልጅተፈጥሮ ሰለጠነበት፣ ጠላት በዛበት፣ ምድሪቱ ከፋችበት አዳምም ባለቀሰው መሪር እንባ 5500 ዘመን ሲፈጸም ከልጅ ልጅህተወልጄ አድንሐልሁ የሚል ተስፋ ተሰጠው የህይወት ፍሬንም ዳግም እንዳይበላ በሱራፊ ታጠረችበት።

ይህም የሚያመላክተው ሞትን የምታመጣ ዕፀ በለስን የበላ አዳም ደግሞ ዕፀ ህይወት ቢበላ ኖሮ ካሳ የማያስፈልገው ኢመዋቲ(immortal sinner) እንዳይሆን የእግዚአብሔር ቸርነት ከለከለችው፡፡

ያ የጨለማ ዘመን ፍጹም ተስፋ ያልጠፋበት ፍጹምም ተስፋ ያልተፈጸመበት ዘመን ነበር።እግዚአብሔር ከአዳም ጀምሮ ለአርእስተ አበው ቃል ኪዳን ይገባ ነበር።

በዚህም ቃል ኪዳን ውስጥ እመቤታችን በተስፋ አበው ውስጥ ታልፍ ነበረ ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በድጓ "ማርያምሰ ተሐቱውስተ ከርሱ ለአዳም ከመ ባህርይ ጸአዳ ፤ ማርያምም በአዳም አብራክ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራ ነበር"በማለት ቅ ገልጦአታል።

ነገር ግን የአበው ተስፋ፣ የነቢያት ትንቢትሲፈፀም የድንግል ማርያም የህይወት ፍሬ/በገነት ተከልክላ የነበረችው የገነት ፍሬ/ አማናዊው ጌታ የሚበላ የሕይወት ፍሬ ሆኖ ከእመቤታችን ተወለደ ቅዱስ ኤፍሬም በሐሙስ ውዳሴ ማርያም ሲናገር " ከፈለነ ንብላዕ እምዕጸ ሕይወት ዘውዕቱ ሥጋሁ ለክርስቶስ ወደሙ ክቡር በእንተ ፍቅረ ዚአነ መጸአ ወአድኅነነ ፤  ዳግመኛ ከዕፀ ኅይወት  እንበላ ዘንድ አደለን ይኸውም እኛን  ስለመውደድ ሰው ሆኖ ያዳነን የክርስቶስ ክቡር ሥጋው  ክቡር ደሙ ነው "በማለት እንደገለጸው፡፡

በወርኃ ጽጌ እመቤታችን ጌታን በጀርባዋአዝላ በረኀ ለበረሃ ለሦስት ዓመት ከስድስት ወር የተሰደደችበትን ሙሉ  ታሪክ  በጥልቀት ስንመለከት ፡፡
 ከላይ በርእሱ የተጠቀሰውን ቃል ልጄን ከግብፅ ጠራሁት።ትሆሴዕ፲፩፥፩
የሚለውን  የትንቢት ቃል የተናገረው ከክርሰቶስ ልደት በፊት በስምንተኛው ምእተ ዓመት አጋማሽ ገደማ የነበረው  የብኤሪ ልጅ ነቢዩ ሆሴዕ   ነው ።  ሆሴዕ  ማለት  እግዚአብሔር ያድናል ማለት ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ታሪኳ ከተዘረዘሩላት ሀገሮች መካከል ግብጽ አንዷ ስትሆን ግብጽ የብዙኀን አባት አብርሃም በረሃብ ምክንያት የተሰደደባት፣ ዮሴፍ በባርነት የተሸጠባት፣ ወገኖቹ እስራኤላውያን ለሁለት መቶ አስራ አምስት ዓመታት ያህል በባርነት የተገዙባት በኋላም የአለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር የተሰደደባት ሀገር ስትሆን መሪዎቿም አህዛብ አማልዕክቷም ጣኦታት ነበሩ።

ነቢዩ ሆሴዕ የጌታችንን ሥደት ቀድሞ በትንቢት ከተናገሩት ውስጥ  አንዱ ሲሆን ልጄን ከግብፅ ጠራሁት በማለት የስደቱን ማብቃት ተናግሯል።

በዚህ ትንቢት መሰረት መሰደዱን አልተነበየም።ነገር ግን ከስደት መመለሱን መናገሩ ካልተሰደደ መመለስ የለም በመመለሱመሰደዱን ተናገረ።

የጌታን ሕይወት ከእመቤታችን የእመቤታችንን ከጌታ ለያይቶ ማየት አይቻልም መለኮታዊ ተግባራትን እና የማዳን ስራዎችን  ካልሆነ በቀር ምክንያቱም ለእርሱ ብቻ የተወሰነና ሊያደርገው የተገባ የአባቱ ተልዕኮ ስለነበረ "ፈቃዴን ለማድረግ አይደለም አንጂ የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ ከሰማይ ወርጃለሁ"ዮሐ፮፥፴፰ ፣ ዮሐ ፭፥፴። 
ነቢያት የተነበዩት ጊዜ ደርሶ በነቢዩ በሆሴዕ እንዳለውና መልአኩ ገብርኤል ለዮሴፍ ተገልጦ እንደነገረው አንድ ልጇን ይዛ ወደ ግብጹ ተሰደደች ማቴ ፪፥፲፫

1⃣የእመቤታችንና የልጅዋ  ምክንያተ ስደት ወደ ምድረ ግብጽ

ክፍል ሦስት ይቀጥላል....

   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
    @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


​​✞ ዘመነ ጽጌ ✞

ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6

"ልጄን ከግብፅ ጠራሁት"
ት.ሆሴዕ ፲፩፥፩

ከመምህር ዮሐንስ ለማ

ክፍል አንድ [፩]

እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተክርስቲያን  ሕግና ስርአት መሰረት ከመስከረም 26 ቀን  እስከ ሕዳር 6 ቀን  ያለው40 ቀን  የእመቤታችንን እና የልጇን ስደትበማሰብ ወርኃ ጽጌን (ዘመነ ጽጌን) ታከብራለች።ይህ 40ው ቀን የእመቤታችንና የጌታችን ስደት የሚታሰብበት ዘመን ነው።

ወቅቱ የአበባና የፍሬ ወቅት በመሆኑ እመቤታችን በአበባ ጌታችን በፍሬ እየተመሰሉ ጌታችን በአምልኮት እመቤታችን በፈጣሪ እናትነቷ በተለየ ምስጋና ይመሰገናሉ ፡፡
 በስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሳው ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ አምሥቱን ጸዋትወ ዜማ ሲደርስ በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሳው አባ ጊዮርጊስ ደግሞ ሰዓታትን ደርሷል፡፡

በዚሁ ዘመን ከአባ ጊዮርጊስ ጋር ጥልቅ መንፈሳዊ ፍቅር የነበረው አባ ጽጌ ድንግል  ማኅሌተ ጽጌ  የተባለውን ድርሰት ደርሷል፡፡
 
ማኅሌተ ጽጌ ግጥማዊ አካሄድ ያለው ድንቅ ኢትዮጵያዊ ድርሰት ሲሆን  ይህ ድርሰት በማንኛውም ጊዜ የሚጸለይ ቢሆንም በተለየ ሁኔታ ወቅት ተለይቶለት በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ የሚውለው ግን   በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና በልጇ የስደት ዘመን  ማለትም  ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ቀን ድረስ ባለው  ዘመን ውስጥ ነው፡፡

በዚህ ወቅት በየሳምንቱ እሑድ ሌሊቱን በሙሉ የእመቤታችንን ከልጇ ጋር ወደ  ምድረ ግብፅ መሰደድና መንከራተት እየታሰበ በሊቃውንቱ  የሚደርስ የምሥጋና ጸሎትም  ነው።
ይህ ድርሰት በግጥም መልክ የተደረሰ  ሲሆን በአብዛኛው አምስት ስንኞች ሲኖሩት ብዛቱም 158 ያክል ነው፡፡እመቤታችን ጣዕሟንና ፍቅሯን እንዲሁም ምስጋናዋን ሲናፍቁ የነበሩትን ቅዱስ ኤፍሬምንና አባ ሕርያቆስን ውዳሴዋንና ቅዳሴዋን እንደገለጸችላቸው  ሁሉ ለፍቅሯ ሲሳሳ ለነበረው ለአባ ጽጌ ድንግል ደግሞ ይህንን የማኅሌተ ጽጌን ድርሰት  እንዲደርስ ምስጢርን ገልጻለታልች ።
 
በቅድስት ሐገር ሐገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ  የመስከረምና የጥቅምት ወራት የአበባ ወራት ወርኅ ጽጌ (ዘመነ ጽጌ) ናቸው።ይህም ወቅት ተራሮች በአበባ የሚያጌጡበትና ለዓይን ማራኪ የሚሆኑበት ጊዜ ነው፡፡

በዚህም ዘመን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "ስለ ልብስ ስለምን ትጨነቃላችሁ ? የሜዳ አበቦች እንዴት እንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፡፡አይደክሙም፣ አይፈትሉም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፣ ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩ ሁሉ ከእነዚህ እንደ አንዱ አልለበሰም፡፡እግዚአብሔር፣ ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፣ እናንተ እምነት የጐደላችሁ፣ እናንተንማ ይልቁን እንዴት፡፡ እንግዲህ ምን እንበላለን፣ ምንስ እንጠጣለን፣ ምንስ እንለብሳለን ብላችሁ አትጨነቁ።"ማቴ ፭÷፳፰-፴፫
በማለት የተናገረውን ቃል በማሰብ መጨነቅ የሚገባን መንግሥተ ሰማያት ለመግባት እንጂ በዚህ ዓለም ስላለው ነገር እንዳልሆነ ተራሮችን በአበባ ያለበሰ አምላክ በአርአያውና በአምሳሉ የፈጠረንን እኛን ለኑሮ የሚያስፈልገንን ምግብና ልብስ እንደማይነሳን እያሰብን የምንዘክርበት ወቅት ነው።

የሊቁ  ድርሰትም ፍሬ ከአበባ÷ አበባም ከፍሬ እንደሚገኘ ሁሉ ማኅሌተ ጽጌም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ልጇን መድኃኒታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን በአበባና በፍሬ እየመሰለ የሚ
ያስረዳ ድርሰት ነው።እርሷን በአበባ ሲመስል ልጇን በፍሬ እርሷን በፍሬ ሲመስል  ልጇን ደግሞ በአበባ እየመሰለ ይናገራል

ነቢዩ ኢሳይያስ "ትወጽእ በትር እምሥርወ እሴይ፣ ወየዓርግ ጽጌ እም ጕንዱ - ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል፤ ከሥሩም ቁጥቋጦ ያፈራል።"ኢሳ ፲፩÷፩ብሎ ከእሴይ ዘር የምትገኘውን እመቤታችንን በበትር ፣ ከርሷ የሚገኘውን ክርስቶስን ደግሞ በጽጌ መስሎ ትንቢቱን ተናግሯል፡፡

አባ ጽጌ ድንግልም ድርሰቱን በዚሁ አንጻር በመቀመር እያንዳንዱን መልክዕ እመቤታችንንና ልጇን አስተባብሮ በጽጌና በፍሬ በመመሰል፣ ከዚያው በማያያዝ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ በምሥጢር፣ በታሪክ፣ በጸሎትና በመሳሰለው መልክ ድንቅ በሆነና በተዋበ ሁኔታ አዋሕዶ ደርሶታል።

ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል በማኅሌተ ጽጌ ድርሰቱ እመቤታችንን በአበባ እየመሰለ ከተናገረው   ድርሰቱ መሐከል አንዱ  "ማዕረረ ትንቢት ማርያም ዘዘመነ ጽጌ እንግዳ ወዘመነ ፍሬ  ጽጋብ  ዘዓመተ ረኃብ ፍዳ  ብኪ ተአምረ ዘይቤ ኢዩኤል ነቢየ ኤልዳ ያንጸፈጽፍ እምአድባሪሁ ወእምአውግሪሁ ለይሁዳ  ፀቃውዐ   መዓር  ቅድው (ጥዑም) ወሀሊብ ፀዓዳ" በመከር ጊዜ አበባ፣ በአበባ ጊዜ ደግሞ መከር አዝመራ ማጨድና መሰብሰብ የለም፡፡ምክንያቱም ጊዜያቸው የተለያየ ስለሆነ።

ለምሳሌ በመስከረም ወር የአበባ ጊዜ በመሆኑ አዝመራ መሰብሰብ የለም፡፡ የትንቢት መከር መካተቻ የሆንሽ እንደ ዘመነ ጽጌ የረሃብን ዘመን ያስወገድሽ ማርያም ሆይ፣ የኤልዳ ነቢይ ኢዩኤል ከይሁዳ ተራሮች ጣፋጭ ማርና ፀዐዳ ወተት ይፈሳል ብሎ የተናገረው ትንቢት በአንቺ ታወቀ፣ ተፈጸመ።
እመቤታችን ነቢያት የተናገሩት የትንቢት ዘር ተፈጸመባት ማለትም ነቢያት የአምላክን ሰው የመሆን ነገር በተለያየ ሁኔታ ተናግረዋል።

ጌታችን ነቢያት የተናገሩት ትንቢት መፈጸሙንና ይህንን ፍጻሜ ለማየት የታደሉት ሐዋርያት መሆናቸውን "አንዱ ይዘራል አንዱም ያጭዳል"የሚለው ቃል እውነት ሆኗል፡፡
"እኔም እናንተ ያልደከማችሁበትን ታጭዱ ዘንድ ሰደድኳችሁ።ሌሎች ደከሙ እናንተም በድካማቸው ገባችሁ።"በማለት ተናግሮአልዮሐ.፬÷፴፯-፴፰)፡፡ 
ይህም ነቢያት የዘሩት ትንቢት በሐዋርያት ዘመን ለአጨዳ ለፍሬ መድረሱን መናገሩ ነው።ስለሆነም "ማዕረረ ትንቢት"የትንቢት መካተቻ ማርያም አላት።
በሌላ በኩል ደግሞ ፍሬ ክርስቶስን ያስገኘችና ከእሴይ ሥር በትር ትወጣለች እየተባለ የተነገረላት በመሆንዋ ድንግል ማርያም  በአበባ ትመሰላለች፡፡
ስለዚህ እመቤታችን በመከር ወራት የምትገኝ አበባ ናት።በመከር ጊዜ የአበባ መገኘት ያልተለመደ ስለሆነ "ወዘመነ ጽጌ እንግዳ "እንግዳ የሆነ አበባ አላት፡፡ ከዚህ በኋላ "ብኪ ተአምረ ዘይቤ ኢዩኤል ነቢየ ኤልዳ፣ ያንጸፈጽፍ እምአድባሪሁ ወእምአውጋሪሁ ለይሁዳ፣ ፀቃውዓ መዓር ጥዑም ወሀሊበ ፀዓዳ"በማለት ነቢዩ ኢዩኤል የተናገረውን ትንቢት አፈጻጸም ይናገራል፡፡

ነቢዩ ኢዩኤል በዘመኑ ጽኑ ረኅብ ነበር፡፡እግዚአብሔር ሕዝቡን በምሕረት እንደሚጐበኛቸውና ረሃቡ እንደሚጠፋ ይነግራቸው ነበር፡፡ 
"ብዙ መብል ትበላላችሁ÷ ትጠግቡማላችሁ፣ ከዚህ በኋላ እንዲህ ይሆናል፣ ተራሮች በተሃ ጠጅ ያንጠበጥባሉ÷ ኮረብቶችም ወተትን ያፈስሳሉ÷ በይሁዳም ያሉት ፏፏቴዎች ሁሉ ውኃን ያጐርፋሉ"
ኢዩ ፫፥፲፰፣ ፪፥፳፮

ክፍል ሁለት ይቀጥላል....

   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
    @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●
•┈┈┈


✞ ያንቺን ዝና ✞

ያንቺን ዝና ያንቺን ክብር
    ከቅዱሳን ማኅደር
   ስንጠይቅ ስንሰማ
    ልዩ ነሽ አርሴማ
(፪)

ከቤተመሳፍንቱ ምቾት ከነገሰበት
ተጠርተሻል አርሴማ ለማይሻረው ሕይወት
የሥጋ ጦማር ስለወደቀ ከልቦናሽ
በደም ተፃፈ ዜና እረፍትሽ [፪]

     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ከአትናስያ ደስታ ከቴዎድሮስ መጽናናት
ተሻግሯል ያንቺ ዝና ትውልድ እንዲማርበት
ለገብረ ጻድቅ ለዓለሙ ሁሉ ለዘላለሜ
ቅድስት አርሴማ ነይ በሰላሜ [፪]

     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
በአርማንያ ንጉሥ ትእዛዝ አለ ተላልፎ
ጤልሜዎስን ሳትፈሪ እምነትሽ ታየ ገዝፎ
መስተጋድሉን ሰማዕታቱን ነፍስሽ ተጣምራ
በሠገነት ላይ ገድልሽ አበራ [፪]

     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ሰይጣን ተንቀጠቀጠ በስምሽ ኃይሉን አጣ
የደዌ ጉልበት ታጥፎ የፈውስ ፀሐይ ወጣ
የእጅሽ ዘንባባ ነክቶናልና አናቃስትም
ቃልኪዳን ሰጠሽ መድኃኔዓለም [፪] 

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://t.me/
yem rel='nofollow'>ezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/y
emezmur_gexe href='m

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥' rel='nofollow'>m

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥/b>


✞ አርሴማ ቅድስት ✞

አርሴማ (፪) ቅድስት (፪)
ምስክር ፅኑ ሠማዕት
አርሴማ (፪) ቅድስት


     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
አርሴማ - በፍቅሩ ተስበሽ
አርሴማ - ዓለምን ንቀሽ
አርሴማ - ሰማዕት ልትሆኝ
አርሴማ - ሄደሽ በፈቃድሽ
     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
አርሴማ - የአትኖስያ ለቅሶ
አርሴማ - ሆድሽን ሳያባባው
አርሴማ - መስቀሉን አንግበሽ
አርሴማ - ጌታን ተከተልሽው
     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
አርሴማ - ላይዙሽ ሲቀርቡ
አርሴማ - ምድር ተንቀጥቅጧል
አርሴማ - ልብስሽን ሳይነኩ
አርሴማ - ሁሉም ፈርተውሻል
     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
አርሴማ - ሚካኤል ገብርኤል
አርሴማ - ከጌታ ተልከው
አርሴማ - እረዱሽ አርሴማ
አርሴማ - በዙሪያሽ ተገልጠው
     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
አርሴማ - በጥፊ ሲመታሽ
አርሴማ - የንጉሱ ወታደር
አርሴማ - ተከፍታ ዋጠችው
አርሴማ - እንደ ዳታን ምድር
     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
አርሴማ - አውሬ እንድበላሽ
አርሴማ - የፊጥኝ ታስረሽ
አርሴማ - መጥቶ ሠገደልሽ
አርሴማ - እግርሽን ሳመሽ
     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
አርሴማ - ለጣኦት እንድሰግጅ
አርሴማ - በሳት ሲያስፈራሩሽ
አርሴማ - አማትበሽ በመስቀል
አርሴማ - ተወርውረሽ ገባሽ
     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
አርሴማ - ሰማዕታት ሁሉ
አርሴማ - ገቡ ተከትለው 
አርሴማ - የእምነትሽ ጽናት 
አርሴማ - እሳቱን አጠፋው

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://t.me/
yem rel='nofollow'>ezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/y
emezmur_gexe href='m

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥' rel='nofollow'>m

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥/b>


✞ ማን አለን ✞

ማን አለን ጌታ ሆይ ካንተበቀር [፪]
በሰማይ ሆነ በዚህ ምድር
ማን አለን ካንተበቀር


     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ዛሬ ወዳጅ ነገ ጠላት
ይለወጣል የሰው ሕይወት
ያመናቸው ገፍተው ጣሉን
አንተ ብቻ አትለየን

     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ሕይወታችን መልኩ ወይሞ
መንገዳችን በእሻ ተከቦ
ጠላት በዝቶ ስንሰቃይ
ታገልክልን ነህ ኤልሻዳይ

     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ባይደላንም የምድር ኑሮ
ብናሰማ ለቅሳና እሮሮ
ባይሳካ ውጥናችን በአንተ
ያምራል ፍጻሜችን

     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
እንኳ ጮህን ሳንለምን
አፍሮ አይገባም ባዶ እጃችን
ስቦ ማውጣት እስኪያቅተን
በዓሳ ሞላ መረባችን

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://t.me/
yem rel='nofollow'>ezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/y
emezmur_gexe href='m

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥' rel='nofollow'>m

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥/b>


✞ ዘጸዓት ነው ለሕዝቡ ✞

ዘጸዓት ነው ለሕዝቡ
በደም ታስሯል ወጀቡ
ጽኑ ክብርን ያየነው
ኢየሱስን ይዘን ነው
ክርስቶስን ለብሰን ነው[፪]


የግብፁ ፈርኦን
በግፍ ሲያስጨንቀን
ክቡደ መዝራዕት ሙሴ
ተነሳና ከራምሴ
መንጋውን ይዞ ወጣ እየቀና
በኀቅለ ቃዴስ በሲና
ያ መንፈሳዊ መጠጥ ያ መንፈሳዊ መብል
ክርስቶስ ነበረ እኛን የሚከተል


     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►

በራፍዴም እንዳንቀር
ተወልን ምስክር
በኢያሱ ወልደ ነዌ
እያዳነን ከአርዌ
ከንዐን ሄደ ከፊት እየመራን
ስሙ መድኃኒት ሆነን
እስራኤል ዘነፍስ ነን ድል በአደረገው ጌታ
ኢያሪኮ ሲዖል ፈርሷል በእልልታ


     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►

በፋርስ ነገሥታት
ወድቆብን ባርነት
በኤርምያስ የነውጽ በትር
እየታየን በምሥጢር
እንደ ብረት አምድ ቅጥር አድርጎን
የእሳቱን ወጀብ አለፍን
በምልክት በራዕይ ተስሎ በሰማይ
ማምለጫችን ሆነ በጎለጎታ ላይ


     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►

ከጠላታችን መዳፍ
መከራ ቢወነጨፍ
የጠበቅነው መሲህ ደርሷል
ሸክማችንም ተራግፏል
የመቤዠት ቀን ቀርቦ ዘጸዓት
ጠቅልለን ወጣን ከሞት
በደሙ አጊጠናል እርስቱን እንወርሳለን
በጽዬን ተራራ ለበጉ እየዘመርን


መዝሙር|
| በዘማሪ ገብረዮሐንስ ገብረጻድቅ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://t.me/
yem rel='nofollow'>ezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/y
emezmur_gexe href='m

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥' rel='nofollow'>m

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥/b>


✞ ዝቅ ብዬ ላመስግነው ✞

ዝቅ ብዬ ላመስግነው
ጉግበቴ ነው ላወድሰው
የፍቅሩ እሳት ልቤን ነክቷል
የድል ዜማ በአፌ ሞልቷል[፪]


     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ምን አገኘህ ሰው ይለኛል
ላያኖረኝ ይጨነቃል
መኖርያዬ በሰማይ
አባት አለኝ ኤልሻዳይ
አባት ና ንጉሥ ጌታ ቅዱስ ለነብስ
      ሕይወቴ ነው ክርስቶስ


     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ተራመድኩኝ በጉልበቴ
ስላቆመኝ ደ
አባቴ
እሩቅ አይደል ቅርቤ ላ
ለው
ምስጋናዬ ለእርሱ ይድረሰው
አባት ና ንጉሥ ጌታ ቅዱስ ለነብስ
      ሕይወቴ ነው ክርስቶስ


     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
የከበረ የተፈራ
ምሕረት ያለው የ
ሚራ
ያገኘኝን አይቻለው
ሞት አ
ያየኝ ፊቱ እያለው
አባት ና ንጉሥ ጌታ ቅዱስ ለነብስ
      ሕይወቴ ነው ክርስቶስ


     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ርህራሄው ስላኖረኝ
ከሰው ድንኳን
ን ትርፍ አለኝ
የኔስ ጌታ ያ
ስደንቃል
በልቤ ላይ ቤቱን ሰርቷል
አባት ና ንጉሥ ጌታ ቅዱስ ለነብስ
      ሕይወቴ ነው ክርስቶስ



               መዝሙር|
  ዘማሪ| ዲያቆን አቤል መ
ክብብ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
👇
               
➢ ሼር // SHARE

https://t.me/yemezmur_gexem
https
://t.me/yemezmur href='_gexem
https://t.me/yemezmu' rel='nofollow'>_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈
•✥


✞ ኖላዊነ ሔር መድኃኔዓለም ✞

ኖላዊነ ሔር መድኃኔዓለም
ለነፍስ ወለ ሥጋ ወለ ኵሉ ዓለም
ዕቀበነ
(፫) ለዓለመ ዓለም

ድም
ጼን ይለዩታል በጎቼ በሙሉ
አይስታቸውም መንገደኛ ሁሉ
በራሱ በአምላክ የተባለላችሁ
በጎች ተሰብሰቡ ወደ በረታችሁ

     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►

ነቢይ ነኝ የሚል የሰፈር ዜናዊ
አድርጎ የሾመ ራሱን ወንጌላዊ
ነጣቂ ተኩላው ተበራክቷል እና
መንጋህን ጠብቀው በእምነት እንዲጸና

     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►

ከአምላክ የተላከ እውነተኛ እረኛ
ለመንጋው የሚያስብ ያይደለም እንደእኛ
ፊት የተማረ ነው ኋላም የተሾመ
በሐዋርያዊ ክህነት በእውነት የታተመ

     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►

ከጌታ የመጣ ካልሆነ ክህነቱ
ከአበው የተለየ ከሆነ ትምህርቱ
በበሩ ያልገባ ሌባ ነው ስላለ
ምእመናን አትስሙት አሳቹ ስላለ

     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►

ጩኸታችን ሰምተህ ጭንቀታችን አይተህ
በየዘመናችን የሚታደግ ልከህ
እውነተኛው መምህር የበጎች እረኛ
አንተው አሰማራን ተመልከት ወደ እኛ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://t.me/
yem rel='nofollow'>ezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/y
emezmur_gexe href='m

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥' rel='nofollow'>m

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥/b>


✞  አክሊለ ጽጌ ማርያም ✞

ክበበ(፪) ጌራ ወርቅ(፪)
ክበበ ጌራ ወርቅ
አክሊለ ጽጌ ማርያም(፪)አክሊለ ጽጌ


አክሊለ ጽጌ ማርያም አክሊለ ጽጌ(፪)

ስሟ ማርያም ነው -  - አክሊለ ጽጌ
የጌታ እናት -  - አክሊለ ጽጌ
እናት አባቷ  -  - አክሊለ ጽጌ
ያወጡላት  -  - አክሊለ ጽጌ
ከምድር ማር -  - አክሊለ ጽጌ
ከሰማይ ያም -  - አክሊለ ጽጌ
ብለው ሰየሟት  -  - አክሊለ ጽጌ  
ድንግል ማርያም   - - አክሊለ ጽጌ

አክሊለ ጽጌ ማርያም አክሊለ ጽጌ(፪)

የስሟ ጣዕም  - - አክሊለ ጽጌ
ከማር ይበልጣል - - አክሊለ ጽጌ
እንደሷ ያለ - - - አክሊለ ጽጌ
ከየት ይገኛል  - - አክሊለ ጽጌ
የፍቅር መዝገብ  - - አክሊለ ጽጌ
ነቅ የሌለባት - - አክሊለ ጽጌ
ለክብሯ ወደር - - አክሊለ ጽጌ
ማን አግኝቶላት - - አክሊለ ጽጌ

አክሊለ ጽጌ ማርያም አክሊለ ጽጌ(፪)

የከበረ ዘውድ  - - - አክሊለ ጽጌ
የወርቅ ሙዳይ  - - አክሊለ ጽጌ
የሽቶ ብልቃጥ - - - አክሊለ ጽጌ
የነፍሴ ሲሳይ - - አክሊለ ጽጌ
ከጥፋት ውሃ -  - አክሊለ ጽጌ
ኖህ የዳነብሽ - - - አክሊለ ጽጌ
የሰላም መርከብ - - - አክሊለ ጽጌ
ቤቱ አንቺ ነሽ - - - አክሊለ ጽጌ

አክሊለ ጽጌ ማርያም አክሊለ ጽጌ(፪)

በቤተ መቅደስ - - - አክሊለ ጽጌ
ስትኖር ተመርጣ - - - አክሊለ ጽጌ
ምግቧን ይዞላት - - - አክሊለ ጽጌ
ፋኑኤል መጣ - - - አክሊለ ጽጌ
አስራ አምስት ዓመት  - - - አክሊለ ጽጌ
ሲሆናት ድንግል - - - አክሊለ ጽጌ
በገብርኤል ብስራት - - - አክሊለ ጽጌ
ተጸነሰ ቃል - - - አክሊለ ጽጌ

            መዝሙር|
    ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ


     ┈┈┈┈••●◉❖◉●••
┈┈
      @yemezmur_gex
em
      ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

20 last posts shown.