የአኺራ ስንቅ زاد الآخرة


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


قالَ اللهُ تباركَ وتعالى: ﴿وَتَزَوَّدُوا فإنَّ خَيْرَ الزَّاد التَّقْوَى﴾ [ سورة البقرة،ءاية 197]

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


የሸይጣን አምባሳደር አትሁን
የሸይጣን አምባሳደር ማለት ሰዎች በረመዳን አፉው እንዳይባበሉ የሚያነሳሳና በረመዳን ይቅርታ መጠያየቅን የሚያሳንስ ሰው  ነው።አንዳንዶች ይቅርታ እንዳንባባል «አመቱን ሙሉ የት ነበራችሁ?»  እያሉ አሁን ይቅርታ መጠየቃችንን አላግባብ እንደሆነ ሊያንጓጥጡ ይፈልጋሉ።አንዳንዶችም ቢድዐ ነው ይላሉ።
  በዚህ ወር ዐፍው ካልተባባልን መች ልንባባል ነው?  እስከዛሬ ሸይጣንና ነፍስያ ይዘውን ይቅርታ ለመጠየቅ ኮርተን ሊሆን ይችላል። አሁን ደግሞ ነፍስያችንን ለማሸነፍ ፈልገን ይቅርታ ጠየቅን። ምንድን ነው ነውራችን?  ወይስ በዚያው በነፍስያችን ላይ መቀጠላችን ነበር አግባብ?
አላህ በቂያማ እለት በዳይና ተበዳይን ያገናኝና ተበዳይ አፉው አልልም ይላል። አላህም ግዴለህም ይቅር በለው ይህን ህንፃ እሸልምሀለሁ ብሎ አንድ የጀነት ህንፃን ያሳየዋል። ባሪያውም አፉው ይላል። አላህ ባሮቹን ይቅር ለማባባል እዚህ ድረስ ሽልማት ያዘጋጃል።
የኛዎቹ ደግሞ እዚሁ ዱንያ ላይ አፍው የመባባያ መድረክ ላይም ይቅርታ እንዳንባባል ያሳንፉናል። ይህ የሸይጣን አምባሳደርነት እንጅ ምንድን ነው?  ሰዎች ከልባቸው ይቅር እንዳሉህ እያሰብክ ወደ አላህ ለመቃረብ መጓዝ የቀልብ እርጋታን ይሰጣል!  እኔ አፍው ብያለሁ አፍው በሉኝ ያ አሕባብ! 
አላህ ከእሳት ነፃ የምንባልበት የዒባዳ ወር ያድርግልን! 
ረመዳን ሙባረክ! 
የቴሌግራም ቻናል ፦ t.me/ismaiilnuru


* የሰው ሐቅ ተሸክመህ ወደ ረመዳን አትግባ። መክፈል እየቻልክ የሰው ሐቅ ይዘህ አታጉላላ። አቅቶህ ከሆነ ጊዜ እንዲሰጡህ በትህትና አስረዳቸው።
* የበደልከውን ይቅርታ ጠይቅ። የበደሉህን ይቅር በል።
* መክፈል የማይችል ሰው ላይ ሐቅ ካለህ ብትችል እለፍ ወይም ቀንስላቸው። ካልሆነ ጊዜ ስጣቸው። "የትም ገብታችሁ አምጡ" አትበል። ወንጀል ላይ ገብተው ቢሰጡህ ሐላል አይሆንልህም።
* ስትሸጥም ስትገዛም ገር እና ቅን ሁን። ገዥም ሻጭም ሆነህ ሶደቃ የምታደርግበት ሁኔታ እንዳለ አስተውል።
* ግብይትህ ላይ ከውሸት፣ መሀላ ከማብዛት፣ ከማታለል፣ ... ተጠንቀቅ። ጊዜ ካለህ ቁርኣን ቅራ። ዚክር አድርግ።
* ቤትህ ውስጥ ሰላም ሁን። ከጭቅጭቅ ራቅ። ሶብር ይኑርህ። ለሚስትህ፣ ለልጆችህ አሳቢ፣ ተቆርቋሪ ሁን። ከአላህ በታች ያላንተ ማን አላቸው? ለባልሽ ምቹ ሁኚ። አንቺ ፈተና ከሆንሽበት ውሎውን ሁሉ ሰላም ያጣል።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor


📃የረመዳንን መድረስ አስመልክቶ ታላቅ ምክር

ሸይኽ ሳሊሕ ኢብኑ ፈውዛን አል ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸው ተጠየቁ:-

“የረመዳን ወር በመቃረቡ ምክንያት ምን ትመክራላችሁ?”

ሸይኽ ሳሊሕ ፈውዛን:-

"አንድ ሙስሊም አላህ ለረመዳን ወር እንዲያደርሰው እና አድርሶትም ፆሙ ላይ፣ ስግደቱ ላይ እና ሌሎች አምልኮዎች ላይ አላህ እንዲያግዘው አላህን መለመን አለበት። ምክንያቱም ይህ ወር በአንድ ሙስሊም ህይወት ዕድል ነው።

ረሱል ( ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) እንዲህ አሉ:-

"ረመዳንን አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ ከጅሎ የፆመ ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል።"

በሌላ ሃዲስ ደግሞ እንዲህ ብለዋል:

"ረመዳንን አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ ከጅሎ የሰገደ ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል"

ስለዚህ ይህ ወር ላይመለስ የሚችል ዕድል ነው። ሙስሊም የሆነ ሰው ረመዳን ሲመጣ ይደሰታል፣ ተስፋም ያደርጋል፣ በደስታ እና ነው የሚቀበለው፣ እድሉን በደንብ በአላህ ትዕዛዝ ላይ ነው ሚያሳልፈው።

ሌቱን በመቆም፣ ቀኑን በመፆም፣ ቁርዓን በመቅራት እና አላህን በማስታወስ ነው የሚያሳልፈው። ትልቅ ዕድል ነው።

ነገር ግን አንዳንዶቹ ግን ረመዳን ሲደርስ አዘናጊ ፕሮግራሞችን፣ ፊልሞችን፣ ዝባዝንኬዎችን፣ ውድድሮችን የሚያዘጋጁ አሉ። እነዚህ የሸይጣን ወታደሮች ናቸው። ሸይጣን ነው ለዚህ ተግባር ያዘጋጃቸው። አንድ ሙስሊም የሆነ ሰው ደግሞ ከነዚህ ሰዎች እና ከተግባሮቻቸው መጠንቀቅ አለበት።

ረመዳን የፍንጥዝያ፣የጨዋታ፣ የፊልም፣ የውድድር ወር አይደለም።"

አላህ የረመዳን ወር በሰላም አድርሰን፣ደርሶም ከሚጠቀሙበት አድርገን ያ ረ ብ ያ ረ ብ!

#ዝክረ_ረመዳን
_


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
"እራስ ሳይጠና ጉተና መነቃቀሱ ፈተና!"
~
አሁን ይሄ ሳይሞቅ ፈላ "ው ር - ጋ ጥ" ቢባል የሚከፋችሁ ትኖራላችሁ። ይሁና! ግን እንዴት ነው የሚሰራው?! እንዴት ነው የሚያደርገው? ራሱን ምን አድርጎ ነው የሚያስበው? እንዴት ነው የሚበጣጠስብን? ምስኪን! ወላሂ እንዲህ አይነቱን የጥጃ ቀን ~ ዳ ም መድረክ የሚሰጡ ሰዎች ናቸው በጠዋቱ ያመከኑት። ተው ለማይሆኑ ሰዎች መድረክ እየሰጣችሁ ሞኝ አንጋሽ አትሁኑ። እነዚህ አጥፍቶ ጠፊ ናቸው። ﻍሩር በጣም መጥፎ ነገር ነው። አስክሮ ሲያበቃ ገደል እየከተታቸው ነው።
የኹጥባ አካሄዶች ላይ ካሉ ክፍተቶች በላይ በነዚህ ወጠ ~ ጤዎች የሚደርሰው ጥፋት የከፋ ነው። ሺርክና ቢድዐ አይጎረብጣቸውም። በየደረሱበት ደዕዋ ገምጋሚ ናቸው። ለራሳቸው ሳይማሩ የደዕዋ ስልጠና መስጠት ይፈልጋሉ። በራሳቸው የቃላት ኳኳታ ተደፍነዋል። ኃላፊነት የጎደላቸው የሚዲያ ሰዎች መድረክ ይሰጧቸዋል። በቲቪ መስኮት ላይ ያየውን ሁሉ የሚሰቅል እ^ብ *ድ አንጋሽ መንጋ ያጨበጭብላቸዋል። ተያይዞ መዝቀጥ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor




Video is unavailable for watching
Show in Telegram




Forward from: ተቀርተው የተጠናቀቁ ደርሶች
√ የረመዳን ወር ፆምን የተመለከቱ ደርሶች

ኪታቡ ሶውም ሚን ቡሉጊል መራም
በሸይኽ አወል አሕመድ አልኸሚሲ

ኪታቡ ሶውም ሚን ቡሉጉል መራም
በሸይኽ ሙሐመድዘይን አደም

ኪታቡ ሶውም ሚን ቡሉጊል መራም
በአቡ አዩብ ሙሐመድ ሰይድ


ኪታቡ ሶውም ሚን ጃሚዒ ቲርሚዚ
ኪታቡ ሶውም ሚን ሶሒሒል ቡኻሪ
ኪታቡ ሶውም ሚን ሱነኒ አቢ ዳውድ

የሰለፎች ሁኔታ በረመዷን በኢብኑ ሙነወር
ስለ ረመዳን በአብዱሶመድ ሙኑር

ኪታቡ ሲያም ከዑምደቱል አሕካም
በኡስታዝ ኸድር አሕመድ አልኸሚሲ

ኪታቡ ሲያም ከዑምደቱል አሕካም
በሸይኽ አወል አሕመድ አልኸሚሲ

ኪታቡ ሲያም ከዑምደቱል አሕካም
በኡስታዝ ሙሐመድሲራጅ ሙኑር


መጃሊሱ ሸህሪ ረመዳን በኢብኑ ኸይሩ
ኢትሓፉ አህሊል ኢማን በአቡ ረይስ
ረመዷናዊ ግሳፄዎች በሸይኽ ሙሐመድዘይን

ረመዳንን እንዴት እንቀበለው?
በኡስታዝ አቡ ሙስሊም ዑመር

ረመዳንን እንዴት እንቀበለው?
በአቡ ፈውዛን አብዱ ሸኩር


ረመዳንን እንዴት እንቀበለው?
በኡስታዝ አቡ ረያን ሰዕድ


የሴቶች ስህተቶች በረመዳን
በኡስታዝ አቡ ሙስሊም አልአሩሲ


ረመዳን በኡስታዝ ሳዳት ከማል
የረመዳን ወር መጣ በአብዱረሕማን ሹመት
ረመዳን የቁርአን ወር በኢብኑ ኸይሩ
በይነ የደይ ረመዷን በኡስታዝ በሕረዲን ከማል
ደሊሉ ሷኢም በኡስታዝ በሕረዲን ከማል
ኸሷኢሱ ሸህሪ ረመዷን በአቡ ሙስሊም
ኢዓነቱል ኢኽዋን በአቡ ሒዛም ዐብዱረሕማን

ኢስቲቅባሉ ሸህሪ ረመዷን
በኡስታዝ ኸድር አሕመድ


ኢስቲቅባሉ ሸህሪ ረመዷን
በአቡ ሒዛም ዐብዱረሕማን ሰዒድ


ሙዘኪረቱን ፊ አሕካሚ ሲያም
በኡስታዝ አቡ ረያን ሰዕድ


ሙዘኪረቱን ፊ አሕካሚ ሲያም
በሸይኽ ሙሐመድዘይን አደም


ሙዘኪረቱን ፊ አሕካሚ ሲያም
በአቡ ዑሠይሚን ዐብዱረሕማን


ሙዘኪረቱን ፊ አሕካሚ ሲያም
በአቡ ረይስ ሙሐመድ ኢማም


ሙዘኪረቱን ፊ አሕካሚ ሲያም
በአቡል ዐባስ ናስር ሙሐመድ


ተልኺሱ አሕካሚ ሲያም
በሙሐመድ ዐብዲላህ ባቲ


አሕካሙ ሶውሚ በጀላሉ ሑሰይን
ፈድሉ ሲያሚ ረመዷን ወቂያሚህ
በአቡ ዑሠይሚን ዐብዱረሕማን

ኪታቡ ሲያም ሚን ዑምደቲ ሳሊክ
በሙሐመድ ዐብዲላህ ባቲ


ስለ ረመዳን በዐብዱሶመድ አልጀበርቲ
ተከታታይ የፆም ትምርት በአቡ ረይስ
አልሙየሰሩ ፊ አሕካሚ ሶውም በአቡ አዩብ
ተስቢሩ ነፍስ ፊማ በቂየ ሚን ረመዷን
በአቡ አዩብ ሙሐመድ ሰይድ ሙሐመድ

ኪታቡ ሲያም ሚን ዑምደቲል ፊቅህ
በአቡ ሙዓዊያ ሰዒድ ሙሐመድኑር


ኪታቡ ሲያም ሚን ዑምደቲል አሕካም
በኡስታዝ አቡ አዩብ ሙሐመድ ሰይድ


አልሙየሰሩ ፊ አሕካሚ ሲያም
በአቡ ፈውዛን አብዱሸኩር ሙሐመድ


ጥንታውያኑ ቻይናውያን በሰላም መኖር ቢያምራቸው ታላቁን የቻይና ግንብ ገነቡ። ቁመቱ ክፍ ያለ ከመሆኑ የተነሳ ማንም አይወጣበትም፣ ማንም አይደርስብንም ብለው አምነዋል። ነገር ግን...
ግንቡ በተገነባ የመጀመሪያው መቶ አመት ውስጥ ብቻ ቻይና ሶስት ጊዜ ለጠላት ወረራ ተጋለጠች። በያንዳንዱ ወረራ ጊዜ ግዙፉ ወራሪ ሀይል ታላቁን የቻይና ግንብ መስበርም መንጠላጠልም አላስፈለገውም ነበር። እናስ? ሰተት ብለው ነበር በበሩ የሚገቡት። እንዴት አድርገው? ቀላል ነበር። ለግንቡ በረኞች፣ ለዘበኞቹ ጉቦ ይሰጣሉ። ከዚያ ነገሩ ሁሉ ያልቃል።

ቻይናውያን በዙሪያቸው ግዙፍ ግንብ በመገንባት ሲጠመዱ ዘበኛ መገንባት ግን ዘንግተዋል። ስብእናን መገንባት ሌሎች ነገሮችን ከመገንባት የሚቀድም ነገር ነው። ይሄ ጉዳይ ትኩረት ሊቸረው የሚገባ ጉዳይ ነው። አንዱ የምስራቁን ታሪክና ትውፊት የሚያጠና ተመራማሪ እንዲህ ይላል፡-

“የአንድን ህዝብ ስልጣኔ ማፈራረስ ከፈልግክ ሶስት መንገዶች አሉልህ፡-
1. ቤተሰብን ማፍረስ
2. የትምህርት ስርአቱን ማፍረስ
3. መልካም ምሳሌና አርኣያ የሆኑ ሰዎችን ስብእናቸውን ማጠልሸት

* ቤተሰብን ለማፍረስ እናት ሚናዋን እንዳትወጣ አድርጋት። “የቤት እመቤት” በመባሏ እንድታፍር አድርጋት።
* የትምህርት ስርኣቱን ለማፍረስ አስተማሪው ላይ አነጣጥር። ህብረተሰቡ ጋር ያለውን ቦታ አሳጣው። ተማሪዎቹ ይንቁት ዘንድ ደረጃውን አውርደው። * አርአያዎችን ለማፍረስ ዓሊሞች ላይ አነጣጥር። አንቋሻቸው። ዋጋ አሳጣቸው። ማንነታቸውን ሰዎች እንዲጠራጠሩ አድርግ። ያኔ ሰዎች አይሰሟቸውም። ምሳሌም አያደርጓቸውም።

• አስተዋይ እናት ከጠፋች
• ከልቡ የሚሰራ አስተማሪ ከጠፋ
• ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉት ዋጋ ካጡ
ማነው ትውልዱን በመልካም ስነ-ምግባር የሚያንፀው?!

ከዐረብኛ የተመለሰ
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 25/ 2007)
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor




የልጆች ትምህርትን የመያዝ አቅም ይለያያል። በቁርኣን፣ በኪታብ፣ በትምህርት፣ በሙያ አንዳንዶች ጎበዝ ሆነው እንደሚያስደስቱን ሁሉ አንዳንዶች ደግሞ ቀዝቀዝ ያሉ ሊሆኑ ይችላሉ። ሁሉም ልጆች አንድ አይነት አቅም ሊኖራቸው አይችልም። ስለዚህ በሌሎች ተሰጥኦ ባላቸው ልጆች እየለኩ ታዳጊዎችን ከአቅማቸው በላይ ማስጨነቅ፣ ስነ ልቦናቸውን መጉዳት አይገባም።

ከነ ጭራሹ አርግፈን እንተዋቸው ማለቴ አይደለም። ማገዝ፣ ማበረታታት፣ እንዲጥሩ መምከር፣ ሲዘናጉ መቆጣት፣ ማኩረፍ፣ እንዳስፈላጊነቱ መቅጣት ድረስ ልንሄድ እንችላለን። አንዳንዶቹ ልጆች እምቅ አቅም እያላቸው ያልታወቀላቸው ወይም እነሱም ራሳቸውን የማያውቁ ሊሆኑ ይችላሉ። አንዳንዶቹ በሂደት የሚለወጡ ይሆናሉ።

እንዳ'ጠቃላይ ደካማም ሆኑ ጠንካራ የሚጥሩ እና የማይጥሩ ፍሬያቸው አንድ አይደለም። አእምሮ ማለት ልክ እንደ ጡንቻ በጣረ እና በሰራ ቁጥር የሚጠነክር፣ ስራ ፈቶ ሲቆይ የሚደክም አካል ነው። ስለዚህ ልጆች ላይ ትኩረት ልናደርግ የሚገባው መጣርን፣ መታገልን ልማዳቸው፣ ባህላቸው እንዲያደርጉ እንጂ በውጤት ብቻ ልንለካቸው አይገባም። የሚጠበቅበትን አድርጎ አመርቂ ውጤት ያላመጣን ልጅ ማስተዋሉ ካለን ደካማ ጎኑን ነቅሶ በማሳየት ውጤታማ የሚሆንበትን መንገድ ማሳየት እንጂ ማሸማቀቅ አይገባም። ብዙም ሳይጥር ውጤታማ የሚሆነውንም እንዲሁ በውጤቱ ብቻ ከመቦረቅ በጊዜ ሂደት ነገሮች በተለያዩ ምክንያቶች ሊለዋወጡ እንደሚችሉ በማስታወስ ጥረትን ልምዱ እንዲያደርግ መምከር ያስፈልጋል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


Video is unavailable for watching
Show in Telegram




ከሁሉም ተግባብቶና ተረዳድቶ መኖር

አል ኢማሙጦበራኒ ከጃቢር ኢብኑ ዐብዲላህ رضي الله عنهما
እንደዘገቡት ነቢዩ صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ብለዋል፥
(ሙእሚን ከሰዎች ጋር -በቀላሉ- ይግባባል፤ ሰዎችም ከርሱ ጋር በቀላሉ ይግባባሉ።
ከሰው ጋር የማይግባባና ሰዎችም ከሱ ጋር መግባባት የማይችሉ ሰው እርሱ ዘንድ መልካም ነገር የሌለ -ክፉ- ሰው ነው!
የሰው ልጆች ሁሉ ምርጥ ማለት ሰዎችን ይበልጥ የሚጠቅም ሰው ነው)
ጦበራኒ:-5949

ዛዱል መዓድ
https://telegram.me/ahmedadem


“ አላህም መልካም ስሞች አሉት። በነዚያም መልካም ስሞቹ ለምኑት።
እነዚያንም ስሞቹን የሚያጋድሉና የሚያጣሙ ሰዎችን ተዋቸው ይሰሩት
የነበሩትን ነገር በእርግጥ ይመነዳሉ ”(አል-አዕራፍ፡ 180)






Video is unavailable for watching
Show in Telegram


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


በቁርአን ውስጥ ስሟ የተጠቀሰ ሴት
Poll
  •   አሚና
  •   ሀፍሷ
  •   መርየም
  •   ፋጢማህ
14 votes

20 last posts shown.