ለህዝብ እየተከፈለ ያለ ውድ መስዋትነት !
>
....ከብዙ ተማፅኖና ውትወታ በኃላ የጤናው ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ስለነበር ፣ አዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ከሚገኘው የማሰቃያ እስር ቤት ሪፈር ተፅፎለት ወደ አዲስአበባ ( ሚክሲኮ ፌደራል ፖሊስ እስር ቤት ) መጣ። ከህመሙ ጋር ተዳምሮ አካሉ ተጎሳቁሎ ፣ ፀጉርና ፂሙ አድጎ ቢታይም ፣ መንፈሱ ግን ፍፁም ጠንካራ ነበር። ሁላችንም ተቀብለን ወደማረፊያው አስገባነው።
ከቀናት በኃላ ወደተለያዩ ሆስፒታሎች ሄዶ ምርመራውን አደረገ። ከደም ግፊቱና ስኳር በተጨማሪ እግሩ ከውስጥ እየቆሰለ ይፈርጥ ነበር። ሀኪሞችም በሁለት የተለያዩ ኬዞች ምርመራ ካደረጉ በኃላ ህክምናውን ለመቀጠል ፣ የአንድ ሳምንት ቀጠሮ ሰጥተውት ተመለሰ።
ከትንሽ ከትልቁ ጋር ተግባብቶ መኖር የሚችልበት ፣ ጨዋታው ጥርስ የማያስገጥመውና የሁላችንም መካሪ አባት የነበረው ጆን ፣ ከህክምና ቀጠሮ ይዞ በተመለሰ 24 ሰአት ሳይሞላው ፣ ከእስር ቤቱ ክሊኒክ ለህክምና እንደሚፈለግ በተደጋጋሚ ተጠራ። ሁኔታው ቀድሞ ገብቶት ስለነበር ፣ ''ተረጋጉ የሚሆነውን በትእግስት እናያለን!'' ብሎን ወደተባለው ክሊኒክ ሄደ።
ነገርግን እዚያ ሲደርስ ለህክምና አልነበረም። ወታደሮች መንገድ ዘግተው ወደተዘጋጀው መኪና እንዲገባ አመለከቱት። > ቢላቸውም ሊገባቸው አልቻለም። ያለው አማራጭ > ብሎ ወደእኛ መጣ። ወደውስጥ ገብቶም > ብሎን እቃውን ይዞ ወጣ። ከነህመምና ስቃዩም ወደአዋሽ አርባ ኮንሰንትሬሽን ካምፖ ብቻውን ታጅቦ ተመለሰ።
የሚገርመው እኔና በላያ ከመሰል ወንድሞች ጋር ፣ በወርሀ ህዳር/2016 ዓ.ም ''አመፅ በመምራት ...!'' የሚል ታፔላ ተለጥፎልን ወደ አዋሽ አርባ ተጭነን ስንሄድ ፣ በስፍራው ከተቀበሉን መካከል ጆንን ጨምሮ ስንታየሁ ቸኮልና ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ዘርፉን ፣ እኛ በመጣንበት መኪና አፋር ክልል/ሰመራ በግለሰብ መኖሪያ ግቢ የተከፈተ አዲስ እስር ቤት አዘጋጅተው ጭነዋቸው መሄዳቸው ነበር። ይህ እስር ቤት የተከፈተው በ3ቱ ወንድሞቻችን ቢሆንም ከዚያ በኃላ በርካቶች እየታፈኑ ተወስደው እስከሞት የደረሰ መከራን ሲቀበሉ እንደነበር የሚታወስና ሁሉም የሚረዳው የአደባባይ ሀቅ ነው። እነጆንም ወደእኛ የተመለሱት ያለአንዳች ምክንያት ሰመራ በአንዲት ጠባብ ክፍል ለወር ከ15 ቀን ያህል ሲሰቃዩ ከቆዩ በኃላ ነበር።
አስታውሳለሁ! አዋሽ በነበርንበት ሰአት የሆኑ የገዢው ባለስልጣናት ግቢውን ሊጎበኙ መጡና እኛ ለሽንት ተሰልፈን ስንወጣ ፊት ለፊት ተገጣጠምን። አጃቢዎቹ ሹማምንቱ እስኪያልፉ ባለንበት እንድንቆም ቀጭን ትእዛዝ አስተላለፉ። ታዲያ በዚህ መሀል ግቢውን የሚያስጎበኘው ባለማእረግ ሰውዬ በጣቱ የእኛን ማጎሪያ መጋዘን እየጠቆመ > በማለት በአሸናፊነትና በኩራት በሚመስል መልኩ የስላቅ ሳቅ ሲስቅ ፣ የተሰማንን ስሜት ፈፅሞ አልረሳውም። ይህ ሁሉ የሚከፈለው ለህዝባችንና ለህልውናው መከበር ሲባል ነው! ይህ ሁሉ ሰቆቃ እያለፈ ያለው ለግላዊ ፍላጎትና መሻትም አይደለም!
ወንድማችን ዮሐንስ ቧያለውን ጨምሮ ክርስቲያን ታደለ ፣ ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃይለማርያም ፣ ዶ/ር ካሳ ተሻገር ፣ ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱ ፣ ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ንብረት ፣ ዶ/ር ዘሪሁን ፣ ሺበሺ ፣ ወተቱ ፣ መሪጌታ በላይ ፣ ሻምበል አድማሱ ፣ ......ወዘተረፈ ዘርዝሬ የማልጨርሳቸው ወንድም እህቶቻችን ፥ ከህዝባቸው ጎን በመቆማቸውና በማንነታቸው ብቻ ''አሸባሪ'' የሚል ታፔላ ተለጥፎላቸው ፣ ዛሬም በቂሊንጦና ቃሊቲ ማረሚያ ቤቶች ፥ ነግቶ እስከሚመሽ የሰቀቀንና የሰቆቃ ጊዜን እያሳለፉ ይገኛሉ። የአንዳንዶቹ ቤተሰቦቻቸው ተበትነው ፣ ተቸግረውና ልጆቻቸው የለመዱትን አጥተው ፣ በናፍቆት ሰቀቀን እየተቀጡም ናቸው።
ታዲያ እኛ እኚህን ወገኖቻችንን ሂደን መጠየቅና ማበረታታት ፣ ቤተሰቦቻቸውን አለንላችሁ ማለት ይቅርና ስንቶቻችን ነን የምናስታውሳቸው ? ስንቶቻችን ነን አስታውሰንስ ድምፅ እየሆንንላቸው ያለነው ? መልሱን ለእናንተ ለአንባቢያን ተውኩት!
እኔ ግን እላችኃለሁ! ለህዝብ ሲሉ ዋጋ የሚከፍሉትን መደገፍና ከጎናቸው መቆም ፣ እነርሱን ሳይሆን ህዝባዊ ትግሉን መደገፍ ብሎም ብዙ ለመስዋዕትነት የተዘጋጁ ጀግና የህዝብ ልጆችን መፍጠር ነው!
#ፍትህ ማንነታቸው እንደወንጀል ተቆጥሮ ፣ በየወህኒ ቤቱ እየተሰቃዩ ለሚገኙ ወንድም እህቶቻችን!