አቡነ ሲኖዳ፡-
✝ሲኖዳ ማለት ‹‹ታማኝ›› ማለት ነው፡፡
ትውልድ ሀገራቸው ጎጃም ሲሆኑ የሸዋ ባላባት ልጅ ናቸው፡፡
✝በጎጃም ደብረ ዲማህ አጠገብ ደብረ ፅሞና በተባለው ቦታ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ያመልኩት የነበረውን ትልቅ ዘንዶ አቡነ ሲኖዳ በመስቀል ባርከው ከሁለት ሰንጥቀውታል፡፡ ሰዎቹንም አስተምረው አሳምነው አጥምቀው የእመቤታችንን ቤተ ክርስቲያን ሠርተውላቸዋል፡፡
✝ ጻድቁ የሊቀ ሰማዕታት የቅዱስ ጊዮርጊስ ዓይነት ገድል አላቸው፡፡ ለዘንዶ ምግብ እንዲትሆን ግብር ሆና የተሰጠችውን ሴት ልጅ ከጫካ አግኝተው ዘንዶውን በመስቀላቸው አማትበው ገድለው ልጅቷን አድነዋታል፡፡
በዘመናቸው ነግሦ የነበረው ‹‹ሕዝበ ናኝ›› የተባለው ንጉሥ በሰዎች ወሬ ‹‹ንግሥናዬ ለሌላ ይሰጣል ትላለህሳ›› በማለት ጻድቁን እጅና እግራቸውን አስሮ ካሠቃያቸው በኋላ እጃቸውን አስቆረጣቸው፡፡ ነገር ግን ለአቡነ ሲኖዳ እመ ብርሃን የብርሃን እጅ ተከለችላቸው፡፡
✝በጌቴሴማኒ ያለችው ሉቃስ የሳላትና ስርጉት የተባለችው የእመቤታችን ሥዕል በየጊዜው እየተገለጠች ታነጋግራቸው ነበር፡፡ ንጉሡ በስደትና በግዞት ብዙ እያሠቃያቸው ሳለ መልአክ መጥቶ ዕለተ ዕረፍታቸውን ነግሯቸው እሳቸውም ደቀ መዛሙርቶቻቸውን ጠርተው ከተሰናበቷቸው በኋላ ነው ንጉሡ በኅዳር 17 ቀን አንገታቸውን ያሰየፋቸው፡፡
ከአንገታቸው ውኃ፣ ደምና ወተት ፈሷል፡፡
✝ለመካኖች ቃልኪዳን የተሰጣቸው ናቸው
የካቲት1 ፍልሠተ አጽማቸው ይከበራል።
@በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን
" 🔶ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::🔸
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
https://t.me/zikirekdusn