¶🌹የፍቅር ልብ❤️‍🩹¶™


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Quotes


🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን 𝚜𝚑𝚊𝚛𝚎 ያድርጉ 🙏

Cross and Promotion @adnisam

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Quotes
Statistics
Posts filter


የምትወዳትን ልጅ ስታገኝ የምታወራው ይጠፋብሀል ⁉️


👉ከስር ነበብ ነበብ አርገህ ፍጠንባት‼️

⚜ወንድ እስከሆንክ ድረስ ቀልጠፍ ማለት አለብህ‼️


😋 ከስር view የሚለውን በመጫን ያገኙታል
👇👇👇👇👇👇👇👇👇


❗የአለማችን አስፈሪ ቦታዎች የት ይገኛሉ ? ስለ ቤርሙዳ ትሪያንግል ያልተሰሙ አዳዲስ የሳይንሳዊ ምርምሮች ውጤት ይፋ  ሆነ⁉️ 🙀👇
https://t.me/+0DesHT7bdg40NmM0


‍ ​​​​​​​​══•⊰❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦


             🌹የፍቅር ንቅሣት♥

                              የመጨረሻው   ክፍል  🔚


✅በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✅



    ምንም አልመለስኩላትም ጓደኛዬ ግን በሀሳቧ ተስማምታ ውጪ ሆነን መጠበቅ ጀመርን፤ግን እኔ ከ5 ደቂቃ በላይ አብሬያቸው ሆኜ ለመጠበቅ ፍቃደኛ አልሆንኩም።ሮቢ አጠገቤ መጥቶ ግን የኔ አለመሆኑን ማሠብ ሞት ስለሆነብኝ ወደ ቤቴ መሄድ ፈለኩኝ፤ጓደኛዬም እያመመኝ ስለነበር ተጨንቃ ወደ ቤት አብራኝ ሄደች።እቤት ካደረሰችኝ በኀላ ተመለሠች፤ልክ እሧ ስትወጣ ጠብቄ ባለቅስ ምመልሠው ይመስል ስንት ዘመድ የሚቀብረውን እንባዬን አፈሠስኩ።ሣላስበው የእናቴ ባል መጥቶ ከተኛሁበት አልጋ አጠገብ ከተቀመጠ በኀላ በጣም ደንግጦ ሮቢ ምን ሆነ ብሎ ጠየቀኝ፤እኔም ግራ እንየተጋባው ሮቢ የሆነ ነገር ሆኖ ነው ብለህ እነሸዴት አሠብክ አልኩት፤ያው ሠሞኑን ሀሳብሽም ጭንቀትሽም እሡ ስለነበር ነው አለኝ።ከመጀመሪያው ይበልጥ በጣም እያለቀስኩ የተፈጠረውን ሁሉ ነገርኩት፤ምንም ሊያምን አልቻለም ሮቢ አንቺ ላይ ይሄን አያደርግም አለኝ።እናቴ ጉዳይ ለማስፈፀም ሌላ ቦታ ነበረች፤በስልክ ነግሯት ነው መሠለኝ በነጋታው ት/ቤት መጣች።እሧ ስትመጣ የወደ ቤት ሠአት ደዉል ሊደወል የመጨረሻው ክፍለ ጊዜ ነበር፤ከክፍል ካስጠራችኝ በኀላ ት/ቤት ግቢ ውስጥ እንዴት እንደገባ ባላውቅም ሮቢ እኛ ወደቆምንበት ቦታ እየመጣ ነበር፤እየተንተባተብኩ ሮቢ አልኳት ለእናቴ ዞራ አየችውና ጎሽ እንደውም አናግረዋለው አለችኝ።እኔ ግን ልጅቷ የነገረችኝ ጆሮዬ ላይ ሲያቃጭልብኝ በፊት እንደዛ ለማቀፍ ምስገበገበውን ሮቢ ዛሬ ግን አጠገቡ መቆም አልሆንልሽ ቢለኝ አጠገባችን ሣይደርስ ከሩጫ ባልተናነሰ እርምጃ ወደ ክፍል ተመለስኩ።ክፍል እንደገባው ወዲያው ስለተደወለ ለጓደኛዬ የሆነውን ነግሬያት ቦርሳችንን ይዘን ወደ ውጪ ወጣን፤ሮቢ እና እናቴ እያወሩ ነበር።ከግቢው ከወጣን በኀላ እናቴ ትንሽ ቆይታ መጥታ ሮቢን ድጋሜ ስለምታዋራው እዚው ከኤልሹ(ጓደኛዬ) ጋ አብረን እንድንሆን ነገረችን።ሮቢም ብዙም ሣይቆየሸ ወጥቶ ከእናቴ ጋ ቆመው ብዙ ሲያወሩ ከቆዩ በኀላ እናቴ ተመልሳ መጣች።ሮቢ ያላትንም እየነገረችኝ ወደ ቤት መሄድ ጀመርን።ሮቢ እኔ ላይ እንደዛ ያደረገበት ምክንያት በጣምምምም ሚገርም ነበር፤አስት ከኔ ጋ ያለውን ግንኙነት እንዲያቋርጥ ስለነገረችው ነበር፤ይገርማል አይደል እንዴ በጣምምም እንጂ ምክንያቱም ለኛ አብረን እንዳንሆን መከልከል ብርቃችን አልነበረማ፤በጣም ብዙ ችግሮችን አልፈን ፍቅራችንን ማንም እንዳይንደው አጠንክረነው ነበራ፤የኔ እናት ከአንዴም ሶስቴ ስትከለክለን ለፍቅራችን ቦታ ሠጥቼ አብረን እንዳልተጋፈጥን እሡ ይሄ ከብዶት ከኔ ወደ ሌላ ሴት ፊቱን አዞረ።ሮቢ ሊያገኘኝም ሆነ ሊያዋራኝ ምንም አልሞከረም ነበር፤እንዲያውም ይባስ ብሎ ለኔ ስሜት ምንም ሳይጨነቅ ፍቅሬ ምኔ እያለ ከልጅቷ ጋ ሚነሡትን ፎቶ fb ላይ በጣም በብዛት መልቀቅ ጀመረ።ከዛ በኀላ የነበሩት በወራት የሚቆጠሩ ወራቶች ለኔ እጅግ በጣም አስቸጋሪ እና አሳሳቢ ነበሩ።በአባቴ በእናቴ እና በተለያዩ ሠዎች ምክር ወደ ራሴ መመለስ ጀመርኩ። ያ ሀገር ምድሩን ያሰቀናና ምሣሌ የነበረው ፍቅር ዛሬ ሰብሳቢ አጥቶ ተበትኗል፤ሮቢን ከማንም ይበልጥ ማመኔ በብዙ ነገሮች ጎዳኝ።አንተ ለፍቅራችን ምንም መሰዋትነት መክፈል አልቻልክም፤መቼም ቢሆን ግን አንተ ላይ ፈርጄብህ አላውቅም ያዋጣህ መስሎህ ንፁህ ፍቅሬን ረግጠህ ሄደሀል።
     ህይወት ሠንሠለት ናት፤አንዱ አንዱን ሲፈልግ ሚፈለገው ደሞ ሌላ ይፈልገል።ህይወት የማትፈታ ቅኔ ናት፤እጅግ ብዙ ነገሮችን አሠባጥራ የያዘች።ህይወት ስሌት ናት፤አንዱን እየቀነስን ሌላውን ምንተካባት።ግን ከምንም በላይ ሀያል የሆነው ፍቅር ህይወት ነው ይሄን ሁሉ ነገር አንድ ላይ አቀናጅቶ የያዘ፤ሁሉም ሠው ልብ ውስጥ ያለ ግን አውቆ ለተጠቀመበት ብቻ ደስታን ምታጎናፅፍ።።።።።።።።
                     
                  
                  ተፈፀመ

ምስጋና ፦ ታሪኩን በመከታተል ሀሳባችሁን ላደረሳችሁኝ በሙሉ ምስጋናዬ ይድረስልኝ
          ፦ ሁላችንንም በአንድ አደርጎ እውቀቶችን ላስጨበጠን እንቁ ቻናላችንን 
          ፦  ሁላችሁንም ክበሩልኝ በቅርቡ በአዲስ ስራ እመጣለሁ ሀሳባችሁን


‍ ​​❦ ​​​​​​══•⊰❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦


             🌹የፍቅር ንቅሣት♥

                                     ክፍል 1⃣5⃣


✅በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✅



የጓደኛዬ ብዬ የነገርኩሽ ታሪክ ሁሉ ያንቺ ነበር አለችኝ።😂😂😂እንዴት ያስቃል ለካ የራሴን ጉድ ነበር ምክር ስሰጥበት የቆየሁት ሁሌ ክፍል በመጣች ቁጥር ቅድስት እኮ አብርሽ እንዲህ አርጓት እያለች የራሴን ታሪክ ትነግረኛለች፤አንቺ ብትሆኚ ምን ታደርጊ ነበር እያለች ስለምትጠይቀኝ እኔም ራሴን በቦታው አድርጌ እያሠብኩ እነግራት ነበር።የነገረችኝ ታሪክ ስትለኝ አልኳት።እሧም እንደመናደድ እያለችትለኝ ነበር።እኔም በሀሳቧ ስላልተስማማው የሁል ጊዜ ጭቅጭቃችን ነበር።እና የነገርኩሽ ታሪክ ያንቺ ነው ያለችኝ ይሄ ነበር፤እኔ እያለቀስኩ ከዚ በላይ እንዳትነግረኝ በአይኔ ከመለማመጥ ውጪ ምንም አላደረኩም።እሧ ቀጠለችአለችኝ።ከዚ በላይ መስማት አልቻልኩም፤በጣም አመመኝ። እረፍት ሠአት ደርሶ ስለነበር እንደ ምንም ጓደኞቼ አረጋግተውኝ ስላላመንኳቸው ስልኩን ነግሬያቸው tg ላይ search አድርገው profilun አሣዩኝ፤ከዚ በላይ ለሡ ምከራከርበት አቅም አጣው።profilu ላይ የሧ በዛ ያሉ ፎቶዎች እና ሁለቱ የተፃፃፉትን screenshot ተደረጎ ነበር፤ፅሁፉ የሚለዉ

ነበር።ፓርቲው ላይ የነበሩ ከግማሽ የማያንሱ የክፍላችን ተማሪዎችም ሲሳሳም እንዳዩት ነገሩኝ።ግን በጣም የሚገርመው እስካሁን የሇነ ስህተት እንዳለ እንጂ ሮቢ ይሄን ያደርጋል ብዬ መቀበል አልቻልኩም።አለማመኔ የገባቸውም ጓደኞቼ በምሳ ሠአት ላይ እውነቱን ሁሉ እሧ እንድትነግረኝ የልጅቷ ክፍል ይዘውኝ ሄዱ።ልጅቷን ጠርተናት ከመጣን በኀላ ጓደኛዬ ሁሉን ነገር እንድትነግረኝ ጠየቀቻት፤ልጅቷ መጀመሪያ ልትሸፋፍነው ብትሞክርም ጓደኛዬ አፋጣ ስለያዘቻት ሁሉንም ነገረችኝ ጓደኞቼ ከነገሩኝም ሌላ ብዙ ነገር ነገረችኝ አሁንም ካላመንሽ ደሞ እደውልለታለው ብላ ደወለችለት፤መቼም እኔ ከሣምንት የበለጠ ጊዜ ስደዉልለት ሣያነሳ ለሧ እንደማያነሳ እርግጠኛ ሆኜ ነበር፤ግን እሡ ምን በወጣው ብዙም ሣይጠራ አንስቶላት በኅላ ት/ቤት መጥቶ እንደሚያገኛት ተነጋግረው ስልኩ ተዘጋ።እኔም ጉዴን አውቄ እንባዬን እየዘራው ወደ ክፍል ሄድኩኝ፤ምንም ሣልናገር ሣልጋገር ወደ ቤት መሄጃ ሠአታችን ደረሠ።ልጅቷ መጥታ ለምን አሁን ሲመጣ ሁለታችን አብረን ሆነን አናፋጥጠውም አለችኝ፤ምንም አልመለስኩላትም ጓደኛዬ ግን በሀሳቧ ተስማምታ ውጪ ሆነን መጠበቅ ጀመርን።

✎ ክፍል አስራ ስድስት (16) የመጨረሻው ክፍል ይቀጥላል... 
ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
            

2.7k 0 10 12 63

‍ ​​❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦


             🌹የፍቅር ንቅሣት♥️


                                     ክፍል 1️⃣4️⃣


✅በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✅



       ✍️ ሮቢ promise ካረገልኝ በኀላ ፀባዩ ቀስ በቀስ መለወጥ ጀመረ።በዛ ላይ እኔም ስልኬ ጠፍቷል እንደ በፊቱ አናወራም፤አሁን ገና ርቀታችን እየተሠማኝ መጣ።ሮቢን እንደ በፊቱ ባላገኘውና ባላወራውም ለሡ ያለኝ ፍቅር ቅንጣት እንኳን አልቀነሠም ነበር፤እንዲያውም ከነሠፍቆቱ ጋ ተደምሮ ፍቅሩ እጅግ በረታብኝ።ከ9 ወደ 10ኛ ክፍል ያለፍኩት ያው እንደተለመደው በደረጃ ቢሆንም የዘንድሮ ግን ያሳስባል፤ጥር ወር ውስጥ የ1st semester final exam ስለነበር ለማጥናት ብሞክርም አልቻልኩም፤ሀሣቤ ሁሉ ሮቢ ሆኗል።አሁንማ በስልክ እንኳን ካወራን 1 ሳምንት ከ3ቀን ሆኖናል።ጥር 14/2010አ.ም ማክሰኞ ቀን ከጊዜ በኀላ እንዳመጣሁት የባህሪይ ለውጥ ክፍል ውስጥ ቆዝሜ ተቀምጬ አንድ ጓደኛዬ መጥታ አጠገቤ ተቀመጠችናአለችኝ።ለራሴ ግራ ገብቶኝ ብቻዬን እያወራው መሄድ ነው የቀረኝ እሧ እንደዛ ብላኝ አዞረችብኝ።ግን ለሮቢ ያለኝ እምነት እንዲህ በቀላሉ ሚበገር ስላልነበር

4k 0 11 4 53

‍ ​​•⊰❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦


             🌹የፍቅር ንቅሣት♥️

                                     ክፍል 1️⃣3️⃣


✅በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✅
        
 
ሁሉንም ፎቶዎች በቅርፅ ከቆራረጥኳቸው በኀላ ያዘጋጀሁት ማስታወሻ ደብተር ላይ ለጠፍኳቸው።የቀረው ቦታ ላይ የፍቅር ጥቅሶች በመፃፍ፣የተለያዩ ስዕሎችን በመሣል እና ለየት ያሉ ፅሁፎችን በመፃፍ ደብተሩን በደምብ ካስዋብኩት በኀላ ከጀርባው የቀረው ቦታ ላይ ከተዋወቅን ጀምሮ ያሣለፍነውን የማይረሣ ጊዜ ፅፌ ካሠብኩት ቀን ቀድሜ ጨረስኩ።ምንም እንኳን ከነ ሮቢ ቤት ብንወጣም አንድ ቀን እንኳን ርቀታችን እንዲሠማኝ አያረግም ነበር፤በቻለው ሁሉ ባገኘው አጋጣሚ ያገኘኛል።በስልክ ምናወራበት ሠአትም በጣም ብዙ ስለሆነ ሁለታችንም አብረነሸ ያለን ያህል ነበር ሚሠማን ግን ከኔና ከሡ ችግር ፍቅር የያዘው ይመስል ሁሌ አብሮን ነው።ጥቅምት ወር መጨረሻ አከባቢ እኔ ስልኬን ት/ቤት ተሠረኩኝ፤ያው ስልኬ ለኔ ስልክ ብቻ አልነበረችም ሮቢ አጠገቤ እንዳለ እንዳስብ ምታረግ ትልቅ ሀይልም ነበራት።ነገር ግን እናቴ ሁሉንም ነገር ስለምታውቅ በሷ ስልክ መደዋወል ጀመርን፤መቼም ከምንም ይሻላል።ህዳር 4 የሮቢ ልደት ነበር፤ምንም እንኳን ስልክ ባይኖረኝም ከሁሉም ሠው ቀድሜ ሮቢዬን መልካም ልደት የምልበት እድል አላጣሁም ነበር።የልደቱ ቀን እኔ ከቤት መውጣት ስላልቻልኩ እሡ እቤት መጥቶ ተገናኝተን በዛውም ያዘጋጀሁለትን ስጦታ ሠጥቼው ብቻውን እንዲያየው ነገርኩት።ሮቢ ስጦታውን እንዳየው ደውሎልኝ ብዙ አወራን፤በጣም ደስ ብሎት ነበር እኔም የሡ ደስታ ተጋብቶብኝ ደስተኞች ሆንን።ሰከንድ ሰከንድን፤ደቂቃ ደቂቃን፤ሠአት ሠአትን፤ቀናት ቀናትን እየተኩ ህዳር 15 ቀን ፍቅር ከጀመርን 9ወር ከ10 ቀን በኀላ ቀለበት አደረገልኝ።በጣም የተለየ ስሜት ነበር የተሠማኝ እንዴት ብዬ ላስረዳቹ በቃ ያላያችሁ ስታዩት ያያችሁ ደሞ የተሠማችሁን አስታውሣቹ ትንሽ ከገባቹም ተረዱኝ።ቀኑን ሙሉ ማታም ቁጭ ብዬ ቀለበቴን ሣየው አደርኩኝ።ሮቢ promise ካረገልኝ በኀላ ፀባዩ ቀስ በቀስ መለወጥ ጀመረ።

✎ ክፍል አስራ አራት (14) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗💗------


•⊰❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦


             🌹የፍቅር ንቅሣት♥️

                                     ክፍል 1️⃣2️⃣


✅በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✅


     የኔና የሮቢ ፍቅር በድጋሚ ሊፈተን ነው፤የኔና የሮቢ እናት ተጣሉ።ሮቢ ነገሩ ስላስጨነቀው ሁሉቱን ለማስታረቅ የአስትን እናት ሊያመጣት ወደ አሠላ ሄደ።ሮቢ ስልኩ ተበላሽቶበት ስለነበር እሡ በሌላ ሠዉ ስልክ ሲደዉልልኝ ብቻ ነበር ማገኘው፤እናቴም ቤቱን ለመልቀቅ አስባ ለጊዜው እዛው ሠፈር አገኘች።ለሮቢ እንኳን ነግሬው እንዲያስቆማት ማድረግ አልቻልኩም ነበር ምክንያቱም ሮቢ አልደወለልኝም፤ሮቢ አርፍዶ ነበር ቤቱን ለቀን አዲሡ ቤት እቃውን አስገብተን ስንጨርስ ደወለልኝ።ሮቢ በጣም ባይናፍቀኝ ኖሮ ቀዛ ሠአት ባላወራው ደስ ይለኝ ነበር፤አነሳሁና አዋራሁት በጣም ቅዝቅዝ ብዬበት ስለነበር ምን እንደሆንኩ ሲጠይቀኝ ሁሉንም ነገር ነገርኩት ሮቢ ምንም አላለኝም ሣወራም አይመልስልኝም በጣም ጨነቀኝ ስሙን ደጋግሜ ብጠራውም መልስ የለም ከብዙ ዝምታዎች በኀላ ያለ ምንም መልስ ስልኩ ተዘጋ።ሮቢ በጣም ሲከፋው ምንም አይናገርም ዝምታን ነው ሚመርጠው፤ምንም አያጠያይቅም አሁን ሮቢ በጣም ከፍቶታል።እኔም ሀዘኔን ዋጥ አድርጌ እሡን እንዳላፅናናው እንኳን እንደ ሌላው ጊዜ አብረን አይደለንም ሌላው ቢቀር እንኳን ስልኩ አይሠራም።ሮቢ በነጋታው ከተረጋጋ በኀላ ደወለልኝ እዛ ምንም እንደማይሠራ እና ቶሎ እንደሚመጣ እቤትም መጥቶ እንደምንገናኝ ነገረኝ።ሮቢ በነገረኝ ቀን እቤት መጣ።ሮቢዬን ከ3 ቀን ናፍቆት በኀላ አገኘሁት፤ሁሉንም ሠላም ብሏቸው እኔ ጋ ሲደርስ ተያየን እና ተቃቀፍን።እስኪሄድ ድረስ አቅፎኝ ቁጭ አልን፤ማም እያየችን ትገረማለች ምንም ብንፈተን ፍቅራችን ይበረታል እንጂ ቀዝቅዞ አያውቅም ነበር።ከሮቢ ጋ በዚህ መንገድ እሡ እቤት እየመጣ መገናኘት ጀመርን።ከነ ሮቢ ቤት ነሀሴ 21/2010አ.ም ነበር የወጣነው፤ማም የተሻለ ቤት ስታገኝ ነሀሴ 28/2010አ.ም ጭራሽ ሠፈሩን ለቀን ወደ ሌላ ሠፈር ገባን።የገባን ቀን ለሮቢ በምልክት እየነገርኩት መጣ።ሮቢ አዲስ የተከራየንበት ቤት ሁሌ ይመጣል፤ቢያንስ አሁንም ሮቢዬን አገኘዋለው ለኔ ይሄ በቂ ነበር።እንግዲህ በዚህ ሁኔታ 2011 መጣው መጣው ተቀበሉኝ ማለት ጀመረ።መስከረም 1/2011አ.ም ሮቢዬ ወደ ከሠአት እቤት መጥቶ አብረን በአሉን ደስ ብሎን አሣለፍን።ለ10ኛ ክፍል ሁለታችንም መዘጋጀት ጀመርን፤ት/ትም ተጀምሮ እንደ በፊታችን ት/ቤት መገናኘት ጀመርን ቅዳሜ ቅዳሜ ደግሞ ሮቢ እቤት እየመጣ አብረን እንውል ነበር።የሮቢ ልደት ህዳር ወር ላይ ስለነበር እኔ ልሠጠው ያሠብኩት ስጦታ ደሞ ጊዜ ስለሚፈልግ ስልኬ ያሉትን ፎቶዋችንን ቶሎ በማሳጠብ ጀመርኩኝ።ሁሉንም ፎቶዎች በቅርፅ ከቆራረጥኳቸው በኀላ ያዘጋጀሁት ማስታወሻ ደብተር ላይ ለጠፍኳቸው።

✎ ክፍል አስራ ሶስት (13) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗
💗------ -

¶🌹የፍቅር ልብ❤️‍🩹¶™
•───────────────•🌐

#📱ከወደዱት ሼር ማድረግ አይረሳ


•⊰❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦


             🌹የፍቅር ንቅሣት♥️

                                     ክፍል 🔟 እና 1️⃣1️⃣


✅በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✅



       የምርቃቱን ዋዜማ ደስ ብሎን አሣልፈን ማታ ላይም ስራ ሲሰራ ስለነበር አብረን ብዙ አመሸን።ነገ እኔና ሮቢ የማም ባልን ልናስመርቀው ስለምንሄድ ተኛን።ቀኑ በጣም ደስ ይል ነበር አይነጋ የለ ነግቶ እኔና ሮቢ የማም ባልን ልናስመርቅ ሄድን።የማም ባል ወንድሙና እናቱም አብረውን ነበሩ።አብረን ብዙ ፎቶ ተነስተን እቤት ወደተዘጋጀው ዝግጅት ስንሄድ ድምቅ ብሏል ሁሉም ነገር ቦታ ቦታውን ይዞ ደስ ይላል።የተጠሩ ሠዎች መምጣት ሲጀምሩና ሁሉም busy ሲሆኑ ሮቢ ጠርቶኝ እነሡ ቤት ሄድኩ።እንዲህ ብቻችንን ከተገናኘን ስንት ጊዜ ሆኖን ነበር ሄጄ ጥምጥም ብዬ አቀፍኩት እሡም አቀፈኝና ይሄን ያሣለፍነው ጊዜ እንደማይደገምና በራሡ መንገድ እንደሚያስተካክለው ቃል ገባልኝ።በምን አድርጎ እንደሚያስተካክለው ግራ ቢገባኝም ሁሌም ሮቢ ላይ ትልቅ እምነት አለኝ።በተለይ የአባቴ ምትክ ነሽ ካለኝ በኀላ በምንም means እንደማይተወኝ እርግጠኛ ነበርኩ።እኔም አባቴን ካሉኝ ነገሮች ሁሉ አብልጬ ነው ምወደው ከአባቴ በኀላ በዚ መጠን የወደድኩት የመጀመሪያው ወንድ ሮቢ ነው።ማም ከፈለገችኝ እንዳታጣኝ ብዬ ቶሎ ወጣው፤እኔ እንደወጣው ሮቢም ትንሽ ቆይቶ መጣና ማም ጋ ሄዶ በጆሮዋ የሆነ ነገር ሲላት እሧም አንገቷን ወደ ላይና ወደ ታች ነቀኘቀችለት።
      ከዛ ተከታትለው ከግቢ ውጪ ወጡ፤የዛን ጊዜ የተሠማኝ ፍርሀት እና ድንጋጤ መቼም አጋጥሞኝ አያውቅም ነበር።ቆይተው የገቡት ቢያንስ ከ10 ደቂቃ በኀላ ቢሆንም ለኔ ግን ከሮቢ ጋ በነፃነት ሣንገናኝ ያሣለፍነዉን 10 ቀን ያህል ነበር የረዘመብኝ፤ሮቢ ከማም ጋ አውርቶ ሲጨርስ በምልክት ወደ ቤት ጠራኝ።ሲጀምር ባይጠራኝም እኔም ልሄድ ነበር ወዲያው ሄድኩ፤ልክ ሣየው የከፋው ይመስላል ቃል ማውጣት አልቻልኩም በቃ መጥፎ ዜና ምሰማበት አቅም አልነበረኝም።ዝም ብዬ አየሁት እስካሁን እንዳቀረቀረ ነው ሁለታችንም ዝም ዝም ብቻ እንደምንም አፌን አላቅቄ ሮቢ አልኩት መጥቶ አቀፈኝ።

ክፍል 1️⃣1️⃣


👉  ሁለታችንም ዝም ዝም ብቻ እንደምንም አፌን አላቅቄ ሮቢ አልኩት፤ መጥቶ አቀፈኝ።ይኸዉልሽ ርብቂ ሚም ፈቅዳለች አለኝ እየሣቀ እስካሁን እንዳዘነ ያስመሠለው surprise ሊያረገኝ ፈልጎ እንደሆነ ነገረኝ።ደስታዬ አሳብዶኝ ዘልዬ ተጠመጠምኩበት።ሁሉንም ነገር ያወሩትን አንድ በአንድ ነገረኝ፤ማምን ጠርቷት ውጪ እንደወጡ እሡ ምንም ሣያወራብላው ፍቅራችንን እነሸደመረቀችልን እና እሡንም ብዙ እንደመከረችው ነገረኝ።
     የዛሬው ደስታዬ ልክ አጣ፤ወደ ማታ አከባቢ የተጠራው ሠው ሁሉ ተሸኝቶ እኛ ተሠብስበን መጨዋወት ጀመርን።ሌሎቹ ምርቃቱን ሲያከብሩ እኔና ሮቢ ደግሞ የፍቅራችንን የነፃነት ቀን እያከበርን በጣም ተደስተን አሣለፍን።ከዛ በኀላ ያሉት ቀናቶች ሁሉ በጣም ደስተኛ እየሆንን የፍልሠታ ፆም ደረሠ።ፍልሠታን አብረን ማስቀደስ ጀመርን፤የ6 ወራችን ማግስት ጊዜ አልሄድንም ነበር ሳናስበው በጣም ለየት ባለ መንገድ አከበርነው፤ቤቱን ቀለም እየቀባን🤗🤗 ደስ የሚል ቀን ነበር አንዴ ፊታችንን አንዴ ፀጉራችንን እየተቀባን ቤቱን ቀብተን ጨረስን።ነሀሴ 14/2010አ.ም እኔና ሮቢ መንገድ ላይ ቆመን እያወራን ሶስት ወንዶች ከፊታችን መጡ፤ልክ አጠገባችን ሲደርሱ ቆሙና አንዱ ልጅ እኔን ጎተተኝ ሮቢ እኔን ሊያስለቅቀኝ ሲሌ የቀሩት ሁለት ልጆች ከሗላ ይዘውት ቸመዞሪያ እንኳን ጊዜ ሣይሠጡት በጩቤ ወጉት፤ሮቢ አይኔ እያየ ከፊቴ ሲወድቅ ነበር ከዚ እውነት ከሚመስል አስፈሪና አስቀያሚ ቅዠት የነቃሁት፤ልክ እንደተነሳው የእውነት የሆነ ይመስል የሆነውን እያስታወስኩ አለቀስኩ።ከእናቴ ጋ ስለነበር የተኛሁት ሳለቅስ ተነስታ ምን እንደሆንኩ ስትጠይቀኝ ነገርኳት፤እሧም ሁኔታዬ አስገርሟት እየሣቀች ጠግቦ በልቶ ስለተኛ ነው አለችኝ፤እኔም የሠጠችኝ ምክንያት ፈገግ ቢያስብለኝም ሮቢን እስካገኘው እና ምንም እንዳልሆነ እስካረጋግጥ አላመንኩም።አይነጋ የለ ያ የጭንቅ ለሊት ነግቶ ሮቢን አገኘሁት፤ያየሁትን ህልም ስነግረው ሆዱን እስኪያመው በኔ እንደዛ መሆን እየሣቀ እሡም እናተሰ እንዳለችኝ ጠግቦ በልቶ ስለተኛ እንደሆነ ነገረኝ።እኔም እያሾፍኩ ሁለተኛ ጠግበህ እንዳትበላ አልኩት፤ሁለታችንም ተሣሣቅን።
     ቀናቶችም እየበረሩ መቼም ህይወት ብዙ ስሜቶች ሚፈራረቁባት ናት፤ደስታ ሲኖር ሀዘን ይኖራል።የኔና የሮቢ ፍቅር በድጋሚ ሊፈተን ነው።

✎ ክፍል አስራ ሁለት (12) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗💗------


═ •⊰❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦

             🌹የፍቅር ንቅሣት♥️

                                     ክፍል 9️⃣


✅በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✅


    አንዳንዴ ባልሄድ እንኳን አስት ፍቅርን እየላከቻት ትጠራኝ ነበር።ሀምሌ 5/2010አ.ም ከሮቢዬ ጋ 5 ወር ሞላን፤የአመቱ አቡኤ ስለነበር እኔ ሮቢ አስት እና ፍቅር ልናነግስ ቤተ ክርስቲያን ሄድን።ሮቢን የመጀመሪያ ልጃችን ስም ማን ቢሆን ደስ ይልሀል ስለው በጣም ነው የገረመኝ እኔም ያሠብኩትን ስም ነበር የነገረኝ "ቅዱስ" የሁለታችንም ምርጫ ነበር ደስ ሲል!ቀኑ የሠኔ ፆም መፍቻ ስለነበር ወደ ቤት ሄደን አስት ወጥ መሠራራት ጀመረች።እነ ማም ከስራ ሲመጡ ሁላችንም አንድ ላይ በላን።ሀምሌ 11/2010አ.ም(ርብቃ ምክንያቱን መጥቀስ አልፈለገችም) በድጋሚ እናቴ ከሮቢ ጋ እንድንለያይ ጥብቅ የሆነ ትዕዛዝ ሠጠችኝ።እናቴ ውሳኔዋ የሚሻር አይመስልም ነበር።የሚያፈቅሩትን ሠው ለማጣት ማሠብ በጣም ከባድ ነው።ለመጀመሪያ ጊዜ የእናቴን ትዕዛዝ ተላለፍኩ፤ከሡ መለየት እንደማልችል ቃል በቃል ነገርኳት።እሧም በሠአቱ በጣም ተናዳ ስለነበር ያለችኝን ካላደረኩ ቤቱን እንደምትለቅ ነገረችኝ።ግን ማነው እስቲ እኔ በዛ ሠአት የተሠማኝ ስሜት የገባው ለማንም የማይገባ ስሜት ነበር።አልኳት።እናቴ ንዴቷ ጠፍቶ በንግግሬ እየተገረመች አንቺ እኮ ገና ልጅ ነሽ ብዙ ህይወት ይጠብቅሻል አለችኝ።የኔ ማዘን ቢያሣዝናትም በሠአቱ በሮቢ ተናዳበት ስለነበር ውሣኔዋን ሊያስቀይራት አልቻለም።ቀናቶች እየተቆጠሩ በመጡ ቁጥር እኔና ሮቢ በነፃነት የመገናኘት ፍላጎታችንና ሀዘናችን እየበረታ መጣ።እንደ በፊቱ አንድ ላይ መዋል የለ አብረን ምግብ መብላት የለ በቃ ለደቂቃ ያህል ግቢ ውስጥ እንገናኝና ሌላዉን በtg ነበር ምናወራው ለማያውቀው ቀላል ሊመስል ይችላል ግን እጅግ በጣም ከባድ ነበር ቢሆንም ከዛ ግቢ ወጥተን አይኑን ካለማየት እንዲህ ይሻል ነበር።እናቴ ከከለከለችኝ በኀላ ያመጣሁት የባህሪይ ለውጥ ቢያሣስባትም መሸነፍ ስለማትወድ በውሣኔዋ እንደፀናች ነው።እናቴ ግንኙነታችን እንዲቀጥል ባትፈቅድም ሮቢ ላይ ግን ምንም አልተለወጠችበትም ነበር።ሀምሌ 21/2010አ.ም የማም ባል ምርቃት ስለነበር ዛሬ ሽር ጉዱ ተጧጡፏል፤በዚ አጋጣሚ እኔና ሮቢም የቤቱን decor ስንሠራ ያለ ማንም ከልካይ አብረን ዋልን።ወደ ማታ ላይ ማም እና አስት ፕሮግራሙ እንዴት እንደሚያደርጉ እያሠቡ እኔና ሮቢን የተከራዩትን ድንኳን እንድናመጣ ሂዱ ተባልን፤አቤት ደስታ እንኳን ለቀናት የናፈቅነውን ነፃነት አግኝተን አይደለም ምክንያት እየፈለግን አብረን ስንሆን እንኳን ደስታ ልዩ ነው።ድንኳኑን ለማምጣት ስንሄድ ቦታውን ስለማናውቀው የማም ባል አብሮን ነበር የመጣው፤የምርቃቱን ዋዜማ እጅግ ደስ ብሎን አሣልፈን.............⏩

✎ ክፍል አስር (10) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗💗------


¶🌹የፍቅር ልብ❤️‍🩹¶™
•───────────────•🌐

#📱ከወደዱት ሼር ማድረግ አይረሳ


═ •⊰❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦


             🌹የፍቅር ንቅሣት🧡

                                     ክፍል 8️⃣


✅በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✅


      🔹  መጋቢት 21/2010አ.ም ነበር ሠማይ የተደፋብኝ እስኪመስለኝ የጨለመብኝ በጣም ከባድ ቀን ነበር።እናቴ ከሮቢ ጋ ያለኝን ግንኙነት እንዳቆም አንዴ እየተቆጣች አንዴ ደሞ እያለቀሠች ነገረችኝ።መጀመሪያ ላይ የቀልዷን ቢመስለኝም እያለቀሠች ስትለምነኝ እና ስትቆጣኝ ነው የእውነቷን መሆኑ የገባኝ።ከሡ ተለይቼ እንደማልኖር እምባዬን እንደ ዝናብ እያወረድኩ ብነግራትም ልመናዋን ወደ ትዕዛዝ ለወጠችው።ከሡ ጋ እንድለያይ የፈለገችው ብዙ ጊዜ ከሠዎች ጋ ስለሚደባደብና ስለሚጣላ እሡን እንጎዳለን ብለው እኔን የሆነ ነገር እንዳያረጉኝ በመፍራት ቢሆንም ከሡ ተለያዪ ከምባል ሞት ሺ ጊዜ ይሻለኝ ነበር።ስለዚህ ግንኙነታችንን በድብቅ ለማድረግ አሠብኩ።በጣም ከባድ ነበር ለሮቢ 3ቀን ብደብቀውም ጭንቀቴ በግልፅ ያስታውቅ ስለነበረ በጣም እንድነግረው ሲያስጨንቀኝ ነገርኩት።በኔ ጥፋት ምክንያት እንዲህ ስላሰቃየሁሽ ይቅርታ ርብቂ ሁሉንም አስተካክለዋለው ብሎኝ ደግመኛ እንደማይጣላ ቃል ገብቶልኝ ሚምንም ይቅርታ እንደሚጠይቃት ነገረኝ።የስንት ቀን ጭንቀቴን እሡ በአንድ አ.ነገር አጠፋልኝ በጣም ደስ አለኝ።የአክስቴ ልጅም ጭንቀቴ በጣም ስላስጨነቃት እናቴን ደዉላ አናገረቻት።እናቴ ባይዋጥላትም ደስተኛ እንድሆን ፈቀደች።በጣም ነበር ደስተኛ የሆንኩት ያፈቀሩትን ሠው በነፃነት ማግኘትን የመሠለ ምን አለ።መጋቢት 30/2010አ.ም እሁድ ቀን የፋሲካ በአል ነበር።ሮቢዬ ከአባቴ ጋ ምኖርበት ሠፈር መጥቶ ተገናኘን።በጣም ናፍቆኝ ነበር ትንሽ ብቻ አብረን ከቆየን በኀላ የገዛሁለትን ሠአት እንደተጠቀለለ ሠጥቼው ቶሎ ወደ ቤት መሄድ ስለነበረበት ሄደ።እኔና ሮቢ በፍቅራችን እንኳን ሌሎች እኛ ራሡ እንቀና ነበር ከሮቢዬ ጋ 3ወር ሞልቶናል ኧረ እንደውም ለልደቴ የሆነ መናፈሻ ሄደን የአንገት ሀብል አደረገልኝ።ከዛ ወደ እናቴ ቤት ስለነበር ምሄደው አብረን ወደ ቤት እየተመለስን cupcake ገዝተን እየበላንና ክሬሙን እየቀባኝ ነበር የሄድነው።እቤት ልንደርስ ስንል አብረን እንደነበርን እንዳያውቁ እኔ መጀመሪያ ገባሁና እሡ ትንሽ ቆይቶ መጣ።

       እቤት ልንደርስ ስንል አብረን እንደነበርን እንዳያውቁ እኔ መጀመሪያ ገባሁና እሡ ትንሽ ቆይቶ መጣ።ልደቴን ደስ ብሎኝ አሣለፍኩ።ሮቢ ለእናቱ የፍቅር ግንኙነት እንደጀመርን እንደነገራት ነግሮኝ ነበር ቢሆንም አስት አሁንም እንደ በፊቷ ነች ምንምአልተለወጠችም😊። ግንቦት 12/2010አ.ም ሁላችንም ተሠብስበን ቤተ ክርስቲያን ሄድን ንግስ ነበር።ከዛ ሮቢ እዛው ቁጭ ብለንአለኝ።ሮቢ ለአባቱ ያለውን ፍቅር ጠንቅቄ ስለማውቅ ደስታዬ ወደር አጣ።ወደፊት ተጋብተን ለሚኖረን ህይወት ማረጋገጫ ፊርማ የሠጠኝ ስለመሠለኝ ምን አይነት ህይወት እንደሚኖረን እያሠብኩ በደስታ ክንፍ አውጥቼ ልበር ምንም አልቀረኝም ነበር።ሮቢ የአባቱን ያህል እንደሚወደኝ ሣስብ መቼም እንደማይተወኝ ከመቼውም ጊዜ የበለጠ እርግጠኛ ሆንኩኝ።ቀናት ቀናቶችን እየተኩ final exam ከወሠድን በኀላ ከአክስቴ ልጅ ጋ ትንሽ ተጋጭተን እናቴ ጋ መኖር ጀመርኩ።(ርብቃ ምክንያቱን በሙሉ ልትነግረኝ ባትፈልግም በሮቢ ምክንያት እንደሆነ አጫውታኛለች)አሁን ክረምት ነው ስለዚህ ት/ት የለም በዛ ላይ ከሮቢ ጋ አንድ ግቢ ነው ምንኖረው።ጠዋት ነግቶ የመኝታ ሠአት እስኪደርስ እኔና እሡ አንድ ላይ ነን።ቀናቹብኝ አይደል ከሚያፈቅሩት ሠው ጋ አንድ ላይ እየኖሩ አብሮ መዋል አቤት ለዚህ ደስታ ሚሆን ቃል የለኝም።ጠዋት ከነጋ እኔ የለሁት አሸነ ሮቢ ቤት ነኝ፤ይሄ ልምድ እንኳን እኔና ሮቢ አስቱም ለምዳዋለች።አንዳንዴ ባልሄድ እንኳን አስት ፍቅርን እየላከቻት ትጠራኝ ነበር።
      ሀምሌ 5/2010 አ.ም የእኔና የሮቢ ልዩ ቀን ነበር ..........

✎ ክፍል ዘጠኝ (9) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗💗------


​​​​═ •⊰❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦

             🌹የፍቅር ንቅሣት♥

                     ፀሀፊ፡ኮዜት ዳንኤል

                                     ክፍል 7⃣


✅በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✅


    ✍ ሮቢ ከሁሉም ጋ አስተዋወቀኝ ዘመዶቹ ነበሩ።ከዛ እራት እየበላን ድንገት ሮቢ ተነስቶ መናገር ጀመረ።ብሎ ተቀመጠ።ማስተዋል በተሞላበት ንግግሩ ኮራሁበት።እናቴ ቡና አፍዪ ብላኝ ቡና እያፈላው ብዙ ስነወራ ካመሸን በኀላ ሁሉም ወደ ቤት መሄድና የቀሩት መተኛት ሲጀምሩ እኔና ሮቢ ቁጭ ብለን እያወራን እጄን የሡ እጅ ላይአድርጎ ጣቴን መለካት ጀመረ፤ሮቢ ምን እየሠራህ ነው ስለው ደሞ ሠፊ ቀለበት ገዝቼልሽ የሠው መሣቂያ እንዳልሆን ነዋ አለኝ።ሁለታችንም እየተሣሣቅን እናቴ ድንገት መጥታ እናንተ ከተገናኛቹ በቃ ወሬ አያልቅባችሁም አይደል ነገ እኮ ት/ት አለ ነይ በይ ተኚ አለችኝ እየሣቀች አንተም ደክሞሀል ሮቢ ከትላንት ጀምሮ አልተኛህም በል ተኛ አለችው።አቅፌው ቻው አልኩትና ወደ ቤት ሄድኩኝ።መጋቢት ሰባት ማታ ላይ የኔ ቤተሠቦች አስት የሮቢ ጓደኞች ሌሎች ተከራዮችና እኔና ሮቢ ግቢ ውስጥ ቁጭ ብለን እራት እየበላን እየተጨዋወትን ነበር።ሁሉም እራት በልቶ ጨርሶ የየራሡን ወሬ ማውራት ሲጀምር እኔና ሮቢም ከጓደኞቹ ጋ ማውራት ጀመርን።ሁሉም ቀስ በቀስ ወደ ቤት ሲገባ የሮቢ ሁለቱ ጓደኞቹ ደሞ በ pc film ማየት ጀመሩ እኔና ሮቢ ፊልሙ ስላልተመቸን የራሣችንን ወሬ ማውራት ጀመርን።ከሮቢ ጋ ቁጭ ብለን የባጥ የቆጡን ስነሠወራ ለካ ሠአቱ ሄዶ ነበር፤ከሡ ጋ ስሆን በጣም ነው ደስ የሚለኝ ልክ እንደ ሁል ጊዜው እጄን ይዞኝ እያወራን   ጓደኞቹ ተነስተው በቃ እንሂድ ሲሉ አስትም ወጣችና አው መሸባቹ ሂዱ እናንተም ግቡና ተኙ መቼም እናንተን መለያየት ችግር ነው አለችን።ቅር እያለንም ቢሆን ተነስተን ገባን።ፍቅር ለኔም ሆነ ለሮቢ የመጀመሪያችን ነው። ለኔ በጣም ለብዙ ነገር መጀመሪያዬ ሮቢ ነው።ብዙ ነገሮችን በሡ አይቻለው፤ተምሬያለው።ደስ የሚል እና ሁሌም ቢያስቡት የሚያስቀና የማይሠለች የፍቅር ጊዜ አብረን አሣልፈናል።ቅዳሜ ቀን እኔ ግቢ ውስጥ ለማፍላት እቃ አቀራርቤ ቡናውን እየቆላው አጠገቤ መጥቶ ቁጭ አለና earphone አድርጎልኝ ላንቺ ነው ውዴ ስሚው አለኝ።የናቲ ማን የመጀመሪያዬ ሚለው ዘፈን ነበር።ዘፈኑ ገና መውጣቱ ነው ተነሣሁና ጉንጩን ስሜው ቁጭ አልኩኝ በጣም ደስ ብሎኝ ነበር።እንዴ ቆይ ሌላም አለ ድጋሜ ትስሚኛለሽ ብሎኝ አሁንም የናቲ ማን track 01 ሚለውን ዘፈን ከፈተልኝ።ሀሣባችንን በደንብ ሚገልፅ ግጥም ስለነበረው በጣም ነው የወደድኩት ቅዳሜን በጣም ደስ ብሎን አሣለፍን።ማታ ላይ እናቴ የኔና የሮቢ ቅርበት በጣም በዝቶባት ስላጠራጠራት ያለንን ግንኙነት እንድነግራት ጠየቀችኝ።እኔም ምንም ሣልደብቅ ሁሉንም ነገር ነገርኳት፤ሁሉንም ስለነገርኳት ደስ ብሏት ሮቢንም ስለምታውቀው ምንም አላለችኝም።ሁሉም ነገር ሲመቻች እንዴት ደስ ይላል ከሮቢ ጋ ያለን ፍቅር በጣም እየጨመረ መጣ በቃ ሁሉም እስኪቀናብን ነበር ምንፋቀረው፨ሮቢ ከጋበዘኝ ዘፈኖች ውስጥ የናቲ ማን(የመጀመሪያዬ እና ተነፋፍቆ)፤የያሬድ(ዘለላዬ)፤የታሜ(ሀኪሜ ነሽ)፤የሳንቾ(አታሣዩኝ) ሁሌ ስሰማቸው እስካሁን እሡን ነው የሚያስታውሱኝ ግን ከምንም በላይ የብስራት ሱራፌል(ቃል በቃል)ብሎ ያዜመውን ሙዚቃ ስሰማው ሮቢ አብሮኝ ያለ አጠገቤ የተቀመጠ ነው ሚመስለኝ ሁሌ ከሮቢ ጋ አብረን ስንሆን ስለምንሠማው ነበር።አንድ ቀን እንኳን ሣንኮራረፍ ሁለተኛ ወራችን እየቀረበ መጣ።መጋቢት 21/2010አ.ም ነበር ሠማይ የተደፋብኝ እስኪመስለኝ የጨለመብኝ በጣም ከባድ ቀን  ነበር

✎ ክፍል ስምንት (8) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗💗------

7k 0 16 2 71

═ •⊰❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦

             🌹የፍቅር ንቅሣት♥️

                                     ክፍል 6️⃣


✅በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✅



     📝 በቃ ቀኑንም ለሊቱንም ነበር ምናወራው።ት/ት ሲከፈት እሡም እኛ ት/ቤት ለወደ ቤት ሠአት እየመጣ መገናኘት ጀመርን።ከሠኞ እስከ ሀሙስ እሡ ት/ቤት እየመጣ እንገናኛለን አርብ ደሞ እኔ እናቴ ጋ ከት/ቤት ስወጣ ስለምሄድ ቅዳሜ እና እሁድ አብረን እየዋልን ሠኞ ደሞ አብረን ወደ ት/ቤት እንሄዳለን።የፍቅር ምሣሌዎች እስክንባል ፍቅራችን ገዘፈ።አንዳንዴ ወደ ውጪ ወጣ ስንል ከአባቴ ጋ ምኖርበት ሠፈር እየመጣም እንገናኝ ነበር።ፍቅራችን እንኳን ለሚያቀን መንገድ ላይ ላየን እንኳን የሚያስቀና ነበር።እንዲህ እየተባለ አንድ ወራችን ደረሠ ግን አልተገናኘንም ነበር ምክንያቱም በማግስቱ በጣም የሚወደው አባቱ ሙት አመት ነበር።ስለዚህ ት/ቤት አልሄደም።እኔም ቀኑ ረቡዕ ስለነበር እናቴ ጋ አልሄድኩም አርብ ቀንን ምመርጠው ሁለቷን የእረፍት ቀኔን እሧ ጋ ለማሣለፍ እንጂ ሌላ ምክንያት ኖሮኝ አይደለም።ረቡዕ ወደ ቤት ስገባ አስት ደወለችልኝና ነገ እንዳትቀሪ ብላ በአደራ እና በማስጠንቀቂያ ነገረችኝ።እኔም እንቢ ማለት ስለከበደኝና ለሮቢ እንደማስፈልገው ስለማውቅ እሺ አልኳት።የሧን ስልክ እንደዘጋሁት ወዲያው እናቴ ደወለችና እሧም እንዳትቀሪ ነይ አለችኝ።ለአባቴ ሀሙስ እንደምሄድና ሠኞ እንደምመጣ ነገርኩት።መጋቢት 6/2010አ.ም ሀሙስ ቀን ከት/ቤት ስወጣ እነ ሮቢ ቤት መሄድ ጀመርኩኝ።ድንገት ሄጄ ደስ ላሠኘው ፈልጌ ለሮቢ እንደምመጣ አልነገርኩትም ነበር።ልክ የውጪው በር ጋ ስደርስ ሮቢ እየወጣ ነበር ልክ ሲያየኝ በጣም ደስ አለው።አልመጣም ብዬው ስለነበር ሲያየኝ አላመነም መጥቶ አቀፈኝና ሠላም አለኝ።አብረን ወደ ውስጥ ገባን ግቢ ውስጥ ብዙ ሠው ነበር ሠላም አልኳቸውና አስት እና እናቴን ስሜያቸው ወደ ውስጥ ገባው።ልብሴን ቀያይሬ የሠው ብዛት እስኪቀንስ ትንሽ ጋደም አልኩኝ።ማታ ላይ አስት ጠራችኝና እነሡ ቤት ሄድኩኝ።እናቴ ነበረች ሌሎች ማላውቃቸው ሠዎች ነበሩ።ሮቢ ከሁሉም ጋ አስተዋወቀኝ ዘመዶቹ ነበሩ።ከዛ እራት እየበላን ድንገት ሮቢ ተነስቶ መናገር ጀመረ።

✎ ክፍል ሰባት (7) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗💗------


❦ ══ •⊰❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦

             🌹የፍቅር ንቅሣት♥️

                                     ክፍል 4️⃣ እና 5️⃣


✅በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✅



      የካቲት 4/2010አ.ም እሁድ ቀን እነ ሮቢ ቤት ቁጭ ብዬ ስልኬን ወሠደብኝ።እኔም የሡን ስልክ ወስጄ ፎቶ እያየው ድንገት የኔ ስልክ ላየሸ text ገባ።ማነው ስለው በአንዴ ፊቱ ተቀያይሮ ስልኬን ወርውሮልኝ ወደ ውጪ ወጣ።እኔ በጣም ደንግጬ ስልኬን ሣየው እኛ ት/ቤት የሚማር የጓደኛዬ ፍቅረኛ ነበር text የላከልኝነበር ሚለው።እሡ ሁሉንም ሠዉ እንዲ እያለ ነው ሚጠራው የሡ text ምንም አልገረመኝም።ይልቅስ የገረመኝና ጥያቄ የሆነብኝ የሮቢ እንዲህ መሆን ነው ለምን እንዲህ ተናደደ።እንደውም ስልኬን ወርውሮብኝ ጥሎኝ ስለወጣ ተናድጄ እኔም ወደ ቤቴ ሄድኩኝ።ማታ ላይ ፍቅር መጥታ አስት እየጠራችሽ ነው ብላኝ እነሡ ቤት ሄድኩኝ።ከዛ እቤት ስገባ ሮቢ ሶፋ ላይ ተኝቶ በearphone ሙዚቃ እያዳመጠ ስልኩን እየነካካ ነበር ድምፁን በጣም ከፍ ስላደረገው ሚሠማው ዘፈን ይሠማ ነበር
የሚለው ነበር።እቤት ገብቼ እሡ ከተኛበት ሶፋ አጠገብ ከተቀመጥኩ ብዙ ቆየው ግን እሡ እስካሁን አላዋራኝም ከአስት ጋ ብቻ ነበር ሣወራ የነበረው።አስት ተነስታ ወደ kitchen ስትገባብዬ text አረኩለት።አይቶት ዝም ሲለኝ በጣም ከፍቶኝ እንደ ሌላው ጊዜ አብሬያቸው እራት ሣልበላ ደና ደሩ ብዬ ወጣው።ልክ እቤት ስገባ text ገባልኝ፤ሮቢ ነበርይላል።ብዬ ወዲያው መለስኩለት።አለኝ።እኔም ነገሩን ከሡ መስማት ፈልጌ እንጂ መጀመሪያም ገብቶኝ ስለነበር ልጁ ምኔም እንዳልሀቀነ እንዲያውም የጓደኛዬ ፍቅረኛ እንደሆነ ላስረዳው ሞከርኩኝ።እሡ ግን ወይ ፍንክች እኔ እኮ የምር ወድጄሽ ነበር አንቺም እንደዛ ይመስለኝ ነበር ሲለኝ አልተሣሣትክም እኮ ታድያ ብዬ ስልክለት balance ጨርሼ ነበር።

​ክፍል 5

   ✍️  እሡ ግን ወይ ፍንክች እኔ እኮ የምር ወድጄሽ ነበር አንቺም እንደዛው ይመስለኝ ነበር ሲለኝ አልተሣሣትክም እኮ ታድያ ብዬ ስልክለት balance ጨርሼ ነበር።ደግሞ ሌላ text ላከልኝአለኝ።balance እንደጨረስኩኝ አውቆ ነው እንዴ አልኩኝ ለራሴ ከ5 ደቂቃ በኀላአለኝ።ጠዋት ደርሶ ምን ብዬ እንደማስረዳው ሣስብ ለሊቱ ሲጋመስ ነበር እንቅልፍ የወሠደኝ።አይደርስ የለ ያቺ ጠዋት ደረሣ ተገናኘን።እንደ ሌላዉ ቀን እንኳን አቅፎ ሠላም ሊለኝ ይቅርና ለአይኑ ራሡ ያስጠላሁት መሠለኝ ዛሬም አብሬያቸዉ ሣልበላ ስትጨርስ ጥራኝ ብዬው ወጣው።ብዙም ሣይቆይ ፍቅር መጥታ ውጪ እየጠበቀሽ ነው አለችኝ።እኔም ወድያው ወጣውና መሄድ ጀመርን።ማታ እንቅልፍ አሣጥቶኝ ያደረውን ስብሰለሰልበት የነበረውን ልነግረው አላስጨረሠኝም።ሲለኝ ሊፈስ የደረሠውን እንባዬን ዋጥ አድርጌው በዝምታ መጓዝ ጀመርን።ለሁለታችንም እኩል በሚሆነወሸ መንገድ ስንሄድ ይበልጥ ዝምታ ነፈሠ እያንዳንዷ ምንራመዳት እርምጃ የ10 ሠዎችን ያህል ጩኸት ገዘፈብኝ።ጩሂ ጩሂ ሁላ አለኝ።ምንም ትንፍሽ ሣንል መለያያችን ጋ ስንደርስ ተቃቀፍንና ሁለታችንም ጀርባችንን ተሠጣጥተን በየ መንገዳችን ሄድን።ክፍል ውስጥ ያለመደብኝን ጥግ ላይ ሄጄ ተቀመጥኩ።እረፍት ሠአት ላይ ጓደኞቼ በግድ ይዘውኝ ወጡ።ግን ድንገተኛ ረብሻ በአከባቢው ላይ ስለተነሣ ሁሉም ወላጅ እየመጣ ልጆቹን መውሠድ ጀመረ።ሁሉም ጓደኞቼ ከሄዱ በኀላ አባቴ በድንጋጤ እየበረረ መጣ።ልክ ሣየው ሄጄ ተጠመጠምኩበት።በጣም ፈርቼ ነበር።አባቴም አቅፎኝ ድንጋጤው ሲለቀው ወደ ቤታችን ሄድን።አይገርምም ሮቢ ነበር ለእናቴ ደውሎ ብጥብጥ እንደተነሣ ነግሯት ለአባቴ ደውላ የነገረችው።ሮቢ ለኔ እንደዚ ማሠቡ አስደስቶኝ ወደ ቤት እንደገባው በሠላም ገባህ የሚል text ላኩለት።እሡም ወድያው በሠላም እንደገባ ነግሮኝ የኔን ደህንነት ጠየቀኝ።እናም በዚ ተነስቶ እኔ በጣም እንደምወደው ነገርኩት እሡም ለኔ ተመሣሣይ ስሜት እንዳለው ነግሮኝ የፍቅራችንን የመጀመሪያ ቀን ሀ ብለን ጀመርን።በተነሣው ረብሻ ምክንያት ለ3ቀን ት/ት ተዘግቶ ነበር።በቃ ቀኑንም ለሊቱንም ነበር ምናወራው።

    ገና ትምሀርት ከመከፈቱ .......

✎ ክፍል ስድስት(6) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ


❦ ══ •⊰❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦

             🌹የፍቅር ንቅሣት♥️


                                     ክፍል 3️⃣


✅በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✅


..... ▶️    እኔም ወደ ቤት ተመልሼ አያቴንና ትንሿን እህቴን ስሜያቸው ወጣው።ከሮቢ ጋ እየሄድን ሁሌም እንደምናወራ እና እንደምንደዋወል እየተነጋገርን ለኔ ት/ቤት በሚቀርበኝ መንገድ ከሸኘኝ በኀላ ተቃቅፈን ቻው ተባባልን።ለኔ ት/ቤት በሚቀርበው መንገድ ስለሄድን ቶሎ ነበር የደረስኩት።ቀኑን ሙሉ እሡን እያሠብኩ ምሣ ሠአት ደርሶ ከጓደኞቼ ጋ ከበላን በኀላ ከጓደኛዬ ጋ ላይብረሪ ገባን ግን ምንም ማጥናት አልቻልኩም።እሧም ጨንቋት ምን እንደሆንኩኝ ስትጠይቀኝ እኔም ፈገግታ ሣይለየኝ ሁለት ቀኑን እንዴት እንዳሣለፍኩኝ ነገርኳት።በጣም በግርምት እያየችኝአለችኝ ፍርሀት በሞላው ድምፅ!ላይብረሪ ገብተን ምንም ሣናጠና ተደውሎ ወጣን።ቀሪውን ሁለት ክፍለ ጊዜ ምንም ሣልሠማ የወደ ቤት ሠአት ደውል ተደወለ።ቶሎ ከአባቴ ጋ ምኖርበት ቤት ሄጄ ቦርሣዬን ብቻ አውልቄ fb ላይ ተጣድኩኝ የአባቴ እናት መጥታ መክሰስ ብዪ እንጂ ብላ እስክትቆጣኝ ስልኬ ላይ ተደፍቼ ነበር።ከዛ ዩኒፎርሜን አወላልቄ እና ተጣጥቤ መክሰስ ከበላው በኀላ ለቀጣዩ ቀን የሚሆነኝን ፕሮግራም ካዘጋጀው በኀላ ትንሽ አጥንቼ መልሼ የፈረደበት ስልኬ ላይ ተደፋው።ከሮቢ ጋ ካወራን በኀላ አባቴ ሲመጣ ሁላችንም እራት በልተን ተኛን።ከሮቢ ጋ በዚ መልኩ በጣም እየተግባባን መጣን።ቀናቶች በቀናቶች እየተተኩ የገና በአል ደረሠ።ሮቢ ትንሽ አሞት ስላልጠየኩት ቅጣት ነበረብኝ።እና የገና ስጦታ ሠጠሁት እሡም ሠጠኝ።ይሄ እንግዲ ፍቅር ከመጀመራችን በፊት የተሠጣጠነው የመጀመሪያ ስጦታ ነው።
የካቲት 4/2010አ.ም እሁድ ቀን እኔ እነ ሮቢ ቤት ቁጭ ብዬ.........

✎ ክፍል አራት(4) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ


¶🌹የፍቅር ልብ❤️‍🩹¶™
•───────────────•🌐

#📱ከወደዱት ሼር ማድረግ አይረሳ


❦ ══ •⊰❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦

             🌹የፍቅር ንቅሣት♥️

                                     ክፍል 2️⃣


✅በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✅


    ▶️  ታድያ እኔም ስልኩን ሽምድድ አድርጌ እቤት ገብቼ ስልኬ ላይ save አደረኩት።ከዛ እነ ሮቢ ዛፉን ቆርጠው ጨርሠው አጠገቤ መጥቶ ተቀመጠ።አልኩት ፈገግ እያልኩ እሡም አለኝ እየተገረመ።ስለው አለማመን በሚመስል አነጋገር አለኝ።እኔም ነገርኩት በጣም እደተገረመ ገና ከተዋወቅን 24ሰአት እንኳን ሣይሆነን ከየት እንዳመጣሁት ጠየቀኝ እኔም እያሾፍኩበት ወፏ ነግራኝ አልኩት።ሁለታችንም ከተሣሣቅን በኀላ accountun እንዳላገኘሁትና እሡ friend request እንዲልክልኝ ጠየኩት።እሡም ወዲያው ላከልኝና እኔም ተቀበልኩት።አጠገብ ለአጠገብ ተቀምጠን chat ማረግ ጀመርን። ሁላችንም ወደ ቤት ስንገባ ሮቢ እና የእናቴ ባል ስፖርት መስራት ጀመሩ።የእናቴ ባል ወደ ቤት ሲመጣ ስፖርቱን እንደጨረሡ ስለገባኝ ለሮቢ normal text ላኩለት።ሮቢም ወድያው መለሠልኝና ብዙ አወራን።እኔ እና ሮቢ የተዋወቅንበት ቀን እንዲህ አምሮበት አልቆ ቀጣዪ ቀን እሁድ መጣ።እሁድ በጠዋት ፍቅር እቤታችን መጥታ አስቱ እየጠራችሽ ነው ብላኝ ቤታቸው ይዛኝ ሄደች።ከዛ አስቱ ስገባ በሚያምር ፈገግታ ተቀብላኝ ከፊት ለፊቷ ያለውን የምግብ ጠረጴዛው ጋ ያለውን ወንበር በእጇ እያሣየችኝ ቁጭ እንድል ጋበዘችኝ።እኔም በ1 ቀን ውስጥ ከሁሉም ጋ በጣም ስለተግባባው እንደ ቤቴ አየሁት።አብረን ቁርስ ከበላን በኀላ እኔ ወደ ቤት ሄድኩኝ።እቤት መቀመጥ ስለደበረኝ ውጪ ወጥቼ ስቀመጥ ሮቢም ትንሽ ቆይቶ ወጣ ብቻችንን ስለነበርን የራሣችንን ወሬ ማውራት ጀመርን።ሮቢ ደስ የሚል ልጅ ሆኖ ነው ያገኘሁት።ከሮቢ ጋ ብዙ ከተጨዋወትን በኀላ ጠዋት አብረን ት/ቤት እንደምንሄድ ተነጋግረን ወደየ ቤታችን ገባን።ማታ በfb ብዙ አወራን።አይነጋ የለ ነግቶ እነ ማም ስራ ከሄዱ በኀላ እኔ ደሞ እነ ሮቢ ቤት ሄድኩኝ።እነ ሮቢ ቁርስ እየበሉ ነበር ደና አደራቹ ብያቸው እኔም አብሬያቸው ተቀመጥኩ።አስት ቁርስ ብዪ ስትለኝ አሁን ነው የበላሁት ብዬ ሻይ ብቻ ቀድቼ መጠጣትጀመርኩኝ።ለሚያየን ለብዙ አመት በፍቅር የኖርን ቤተሠቦች እንጂ በፍፁም የ1ቀን ትውውቅ ያለን አከራይ እና ተከራይ አንመስልም።እኔ እና ሮቢም ቦርሣችንን ይዘን ለመውጣት እየተነሣን አርብ ከት/ቤት መልስ እመጣለው ብያቸው አስቱን አቅፌያት ቻው ስላቸው ፍቅር መጥታ አቅፋ ሣመችኝና ቻው አለችኝ።እኔም ወደ ቤት ተመልሼ አያቴንና ትንሿን እህቴን ስሜያቸው ወጣው::

   ከሮቢ ጋ መንገድ ጀመርን ...........


✎ ክፍል ሶስት (3) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ


¶🌹የፍቅር ልብ❤️‍🩹¶™
•───────────────•🌐

#📱ከወደዱት ሼር ማድረግ አይረሳ

7k 0 31 2 56

‍ ​​ተከታታይ ልቦለድ

             🌹የፍቅር ንቅሣት♥

                                     ክፍል 1⃣


✅በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✅

       ▶️  የካቲት 5/2010አ.ም ለኔ ልዩ ቀን ነበረች።ለኔ ብቻ ሣይሆን ለሮቢዬም እንደዛው ርብቃ እባላለው።የካቲት 5 ከሮቢዬ ጋ የፍቅር ጊዜያችንን ሀ ብለን የጀመርንባት የቀኖች እና የፍቅራችን የመጀመሪያ ቀን ሠኞ ነበረች።ከሮቢዬ ጋ የተዋወቅንበት አጋጣሚ እነሆ እናት አና አባቴ ስለተለያዩ እኔ የምኖረው ከአባቴ ጋ ነው ይሁንና የሣምንቱን መጨረሻ የእረፍት ቀነሠቶች እናቴ ገረ ነበር ማሣልፈው እኔ እና ሮቢ በተገናኘንበት ጊዜ እናቴ ከአባቴ በኀላ ካገባችው ባሏ ከአንድ ልጃቸው(ከእህቴ) እና ከእናቷ(ከአያቴ) ጋ እነ ሮቢ ግቢ ተከራይተው ነበር ሚኖሩት።እለተ ቅዳሜ ነበር ህዳር 23/2010አ.ም እናቴ እነ ሮቢ ቤት በቅርቡ ስለሆነ የተከራየችው እኔ ስለማላውቀው ልትወስደኝ ነበር ከአባቴ ጋ ምኖርበት ቤት የመጣችው ከእናቴ ጋ ተያይዘን ወደ አዲሡ ቤታቸው ሄድን።ስንደርስ በሩን የከፈተችልን ሮቢ ልክ እንደ እህቱ የሚያያት ፍቅር ነበረች።ማም ከፍቅር ጋ ካስተዋወቀችን በኀላ ወደ ውስጥ ገባን።ወደ ውስጥ ስንገባ የት/ቤት ልብስ ታጥቦ ተሠጥቶ ነበረ።የዩኒፎርሙ አሠፋፍ የወንድ ይመስል ነበር ደሞ አልተሣሣትኩም የሮቢ ነው።እቤት ገብቼ ትንሽ አረፍ እንኳን ሣልል ፍቅር ብዙ ደብተሮች ይዛ መጥታ አስጠኚኝ አለችኝ።ይሄ የማም ስራ ነው።ሁሌ በሄደችበት ሁሉ ከአባቴ ስለወረስኩት ት/ት ላይ ስላለኝ ጉብዝና ታወራለች።ለነገሩ ፍቅር የ3ተኛ ክፍል ተማሪ ነበረች።እናም ፍቅርን እያስጠናሇት እቤት ውስጥ፡ስለሞቀን ወደ ውጪ ወጣን።ውጪ ሮቢ ልብስ እያጠበ እናቱ ደግሞ ቡና እየወቀጠች ነበር።ከዛ እናቱን ሄጄ ሠላም አልኳት ተዋወቅን አስቴር እባላለው ስትለኝ ርብቃ አልኳትኝ።አለችው።ከዛ ከሮቢ ጋ ተዋወቅን።የኔና የሮቢ የመጀመሪያ ትውውቃችን እንዲ ነበር።እኔም ፍቅርን ማስጠናት ጀመርኩኝ።ሮቢ ልብሡን አጥቦ ሲጨርስ አጠገቤ መጥቶ ቁጭ አለና አንድ አንድ እያልን በደንብ መተዋወቅ ጀመርን።ሮቢ ልክ እንደኔ የ9ኛ ክፍል ተማሪ ነበር።ወደ አመሻሹ ላይ ሁሉም ውጪ ተቀምጦ እኔ ቡና አፈላው።ስጨርስ ሮቢ እና የማም ባል ዛፍ መቁረጥ ጀመሩ።ሮቢ ሲቆርጡ ስልኩ እንዳይወድቅበት ብሎ ዘፈኑን እንደከፈተው lock አድርጎት ለፍቅር ሠጣት።ከዛ ፍቅር አጠገቤ መጥታ ተቀመጠች ድንገት ዞር ስል emergency call ሚለው ላይ ስልክ እየፃፈች ነበር የማነው ፍቅር ስላት የሮቢ ነዋ አለችኝ ታድያ እኔም ሰልኩን ሽምድድ አድርጌ እቤት ገብቼ ስልኬ ላይ save አደረኩት።

ይቀጥላል...

    ✎ ክፍል ሁለት (2) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር


¶🌹የፍቅር ልብ❤️‍🩹¶™
•───────────────•🌐

#📱ከወደዱት ሼር ማድረግ አይረሳ


💚 የፍቅር ንቅሳት 💚

          🤍●▬ተከታታይ ታሪክ▬●🤍

   💞●
#እውነተኛ ልብ አንጠልጣይ  የፍቅር ታሪክ●💞

♨️ለመጀመር የእናንተ ፍላጎት ያስፈልገናል LIKE አርጉ ለማንበብ የሚፈልግ የ♥️ ምልክቱን በመንካት VOTE ያድርጉ
              ,,,,,🌹❣️🌹❣️🌹❣️🌹,,,,,


❤️ ፍቅር ሲፈርድ 📕

#ተከታታይ ልቦለድ

#ክፍል 1️⃣5️⃣



#እውነተኛ አሳዛኝና አስተማሪ ታሪክ


#የመጨረሻው ክፍል


በጩቤ ስትወጋ ተዘረረች ይሄኔ የነሳራ ግቢ ተከራዮች ይመለከቱ ስለነበር በጩኸት ሰፈሩን አደበላለቁት ሁሉም ከዛ የሳራ እንጀራ እናት ለማምለጥ ስትሞክር ባካባቢው የነበሩ ሰዎች ያዟት ወደጣብያም ተወሰደች ... ሰው በመግደል ሙከራ ተከሳ ወደ ማረፍያ ቤት ተላከች... ለምለምንም ወደሀኪም ቤት ከወሰዷት ቡሃላ ለልኡል አባት ደወሉለት የልኡል አባት ደግሞ ብዙነህ ጋር ደውሎ እሱ ከባህርዳር እስኪመለስ ለምለም ጋር እንዲቆይለት ጠየቀው ብዙነህ ኧረ ችግር የለውም ሲል የለምለምን ክፋትና በደል እረስቶት ነበር ...

ብዙነህ ለምለም የገባችበት ሆስፒታል ደርሶ ቀጥታ ወደ ድንገተኛ ክፍል አመራ በሩ ላይም ራሄል ልጇን አቅፋ ታለቅሳለች ብዙነህም አይቷት አለቃሽ በመታመሟ ነው እንዲ እምባሽ የሚዘምበው አላት ቡዜ እስቲ ዛሬ እንኳ ላሳዝንክ እኔኮ የልጅህ እናት ነኝ አለችው እሱም ትቷት ለምለም ጋር ሊገባ ሲል ዶክተሮቹ ብዙ ደም ስለፈሰሳት ባፋጣኝ ሌላ ሀኪም ቤት ሄዳ መታከም አለባት ብለው ሪፈር ፃፉላት ብዙነህም ለልኡል አባት ሁኔታውን አስረድቶ ወደ የካቲት ሆስፒታል ተወሰደችና አልጋ ያዘች ብዙነህና ራሄል ውጪ ቆመው ሳለ እሺ ለምን ነበር የምታለቅሽው አላት ራሄልም ልጇን በስስት እያየች ወ/ሮ ለምለም ልጄ የልጇ እንዳልሆነ አወቀች እናም አይንሽን እንዳላይሽ አለችኝ ማንም ምንም እንደሌለኝ እያወቀች ...ስትል ድሮስ እውነት ተደብቆ የሚቀር ይመስልሻል ራሄል አሁንም ልምከርሽ ከጥፋትሽ ተመለሽ ውሸት ይብቃ ተመልከች ሁሉም የስራውን...ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ የልኡል አባት ደወለና ስንት ቁጥር ናቹ አለ ብዙነህም ያሉበትን ነገረው...

ልክ ወደ ክፍሉ ሲሄዱ ራሄል ደንግጣ ቆመች ብዙነህም ድንጋጤዋ አስደንግጦት ምን እንዳየች ለማየት አይኗን ተከትሎ ዞረ ይሄኔ እሱም ተገረመ ሳራና ልኡል ከልኡል አባት ፊት ፊት ይሮጣሉ ብዙነህ በደስታ ሰከረ እሩጦ ሁለቱም ላይ ተጠመጠመ ምንድን ነው የማየው በፈጣሪ እውነት ነው ግን እያለ ሁለቱንም በየተራ ሳማቸው የመጡበትን ጉዳይ ለትንሽ ደቂቃ እረሱትና በብዙነህ ሁኔታ እንባቸው ፈሰሰ ከዛም የልኡል አባት ናልጄ በቃቹ እናትህን እንይ አለ ... ብዙነህም ውስጥ ዶክተሮቹ ስላሉ ሲወጡ እንገባለን አለ ሁሉም መንቆራጠጥ ጀመሩ ...

በመሀልም ሳራ ግንኮ አልገባኝም ወይዘሮ ለምለምን ማን ሊወጋት ይችላል አለች ሁሉም ቀጥ ብለው ወደሷ ተመለከቱ ልኡልና ሳራ በርግጥም አላወቁም ነበር ... አብረው የመጡት እማማ ሳራን እያረጋጉና በቀን በቀን ቤተክርስትያን እየሄደች እንድትፀልይ አድርገው ወደራሷ ሲመልሷት ሳሚ ደግሞ ልኡል የተኛበት ሆስፒታል ድረስ ሄዶ ያኔ ባለማወቅ ስለሚያፈቅራት ብቻ እንደዛ እንዳለና እሷ ግን ካንተ ውጪ ማንንም አታፈቅርም ባለማወቅ ለዚ ስለዳረኳቹ ይቅርታ በማለት ልኡል በድጋሚ ከሳራ እንዲገናኙ አድርጎ ልክ የልኡል አባት ልኡልን ይዘው እነሳራ ቤት ደርሰው ልኡልና ሳራ ሲተቃቀፉ ነበር ለምለም ተጎድታለች ተብሎ ለልኡል አባት የተደወለው...

ዶክተሩ ወቶ የለምለም ቤተሰቦች አለ ሁሉም አቤት አሉ ወደዶክተሩ እየተጠጉ ለምለም ከፍተኛ ደም ስለፈሰሳት ደም የሚለግስ ሰው ያስፈልጋል ከመሀላቹ ሲባል በቅድሚያ ባሏ ገባ ግን ባልየው መስጠት አይችልም ምክንያቱ ደግሞ የደም ታይፓቸው አንድ አይደለም ቀጥሎ ልኡል ገባ ልኡል ደግሞ ሙሉ ጤነኛ ባለመሆኑ እንደማይችል ነገሩት ብዙነህ እኔ እሰጣለው በቃ ብሎ ሲገባ የሱም እንደማይሄን ተነገራቸው ይሄኔ የልኡል አባት ዘመድ ጋር ለመደወል ስልካቸውን ሲያነሱ ሳራ እኔ አለው አለች ሁሉም ደነገጡ ያን ሁሉ በደል ያሳለፈች ሴት እንዴት ዛሬ ለበደለቻትና ህይወቷን ላበላሸች ሴት ደም እለግሳለው ትላለች እውነትም ሳራ እንቺን ያገኘሽ ልጄ ፈጣሪ ልቡን አይቶ ነው ተባረኪ አላት አጋጣሚ ደግሞ የሳራና የለምለም ደም ተመሳሳይ ነበርና ዶክተሮቹ ከሳራ ደም ወስደው ለለምለም ተኩላት ለምለም ስትነቃ ካጠገቧ የተኛችውን ሴት ሳራን ተመለከተች ለምን ከጎኗ እንደተኛች ለማወቅ ግዜ አልፈጀባትም ...

ለምለም መቃብሯን የቆፈረችላት ሴት ዛሬ ህይወቷን ስታድናት ከማየት በላይ ምን አለ ፀፀት ውስጧን አሰቃየው በተንጋለለችበት እምባዋ ቁልቁል ወደጆሮዋ ፈሰሰ... ለምለም ድና ስትወጣ በቅድሚያ ሳራንና ልጇን ድል ባለ ሰርግ ለመዳር መዘጋጀት ጀመረች ባሏንም ለልኡል አባቱ እንዳልሆንክ ይነገረው ስትል የልኡል አባት ግን በፍፁም አለ ልጄ የኔ እንደሆነ ይቀጥላል እስከዛሬ ያልተነገረውን ዛሬ መናገር የለብንም አለ ለምለምም በቃ አንተ እንዳልክ አለች ...

ለምለም ጠበቃ ቀጥራ የሳራን እናት በመግደል ወንጀል ከሰሰቻት ሳራም የአባቷን ሀብት ይገባሻል ሲባል ተፈረደላት ከብዙ ምርመራ ቡሃላም በለምለም ጥረት የሳራ እንጀራ እናት እድሜ ልክ እስራት ተፈረደባት ልኡልና ሳራም ድል ባለ ሰርግ እንዳዲስ ተጋቡ ...እማማም ባህር ዳርን አለቅም ብለው የነበረ ቢሆንም በሳራ ልፋት የአባቷን ቤት ሰታቸው መኖራቸውን ቀጠሉ ለምለምም ካሳ ይሁነኝ ስትል ጥሩ ቤትና መኪና ገዝታ ለሳራና ለልኡል ስጦታ ሰጠቻቸው ... የልኡል አባትም አሜሪካ ከመመለሳቸው በፊት ፍቅር ያሸንፋል ሲሉ ራሄልን አፈላልገው ከብዙነህ ጋር በማስታረቅ ለልጃቸውም ሲባል አብረው እንዲኖሩ አደረጉ ... ደስታ በየቤቱ ገባ ........

..................ተፈፀመ....................

ፍ ቅ ር ❤️ ሲ ፈ ር ድ



#ይህ ነው ፍቅር ሲፈርድ ❤️😘

አብራችሁን በመሆን ሀሳብ አስተያየት እንዲሁም መስተካከል ያለባቸውን ነገሮች ለነገራችሁን ..
የተለያዩ አስተማሪ ታሪኮችን በመልቀቅ አብራችሁን ለሆናችሁ..
በእውነት በቻናላችን ስም🙏

የቀረ ሀሳብ ካላቹ 👉
@adnisam

ከ ❤️
እ ና መ ሠ ግ ና ለ ን


‍ ​​​​​​​​​​​​​​​​​​❤️ፍቅር ሲፈርድ 📕

#ተከታታይ ልቦለድ
        
#ክፍል 1️⃣4️⃣


#እውነተኛ አሳዛኝና አስተማሪ ታሪክ

#በቀጣዩ ክፍል1️⃣5️⃣ ይጠናቀቃል
ስለምትከታተለሉን እናመሠግናለን🙏


ሳራ እንደ እብድ ስትጮህና ልብሷን ስትቀድ ሰዎች ያዟትና አስቆሟት ሳሚም በጣም ደነገጠ እግሯ ላይ ተንበርክኮ ይቅርታ እንድታረግለት ለመናት እማማም በአምላክን አቅፈው ያለቅሳሉ ሳራ ልኡል ወደተወሰደበት ሆስፒታል ሄደች ነገር ግን ልኡል ማንንም ማየት እንደማይፈልግ ተናግሮ ስለነበር ዶክተሮቹ እንዳትገባ ከለከሏት ትሄኔ ወደቤት ተመልሳ ተቀመጠች ሳራ ከቀን ወደቀን እየገረጣች መጣች ምክንያቱ ደግሞ ምግብ ስለማትበላ ነበር...
የሳራን መምጣትና የልኡልን በሷ ምክንያት ሆስፒታል መግባት የሰማችው የልኡል እናት እየከነፈች ባህር ዳር ገባች ሳራን አፈላልጋም ልትገላት ፈለገችና ባሏ ጋር ደወለችለት ባልየውም ባህር ዳር ሆቴል ይዞ ስለነበር ልኡልን እያስታመመ የነበረው ወደ ሆቴሉ ቀጠራት ከዛም ለምን መጣሽ አላት ለምለምም የልጄን ህይወት እያመሰች ያለችውን ሴት ልገላት አለች አባትየውም ትንሽ የምፀት ፈገግታ ፈገግ ብሎ ቆየና ቆየሽኮ ከገደልሻት ምን እሷን ብቻ ልጅሽንም ገለሽዋል ሲል ካፉ ነጥቃ እንደዚ አትበለኝ እኔ ልጄን ስለምወደው ነው ለሱ ብዬ ነው አለች እንባ እየተናነቃት ....
ለምለም እስቲ ንገሪኝ እጅግ በጣም ከሚያፈቅራት ልጅ ነጥሎ ለውሸታምና አስመሳይ መዳር ነው መውደድ እስቲ መልሺልኝ ከገዛ ልጂ ይልቅ የሌላን ልጅ የእንጀራ አባት ሆኖ እንዲያሳድግ መፍረድ ነው ነው መውደድ ሲል ምንድን ነው የምታወራው ራሄልኮ የልጄን ልጅ ነው አቅፋ ያለችው እራሱ ታሞ በልኡሌ ደም ነው የተረፈው ሲል ከት ብሎ ስቆ ስሚ ለሌባውም ከሱ የተሻለ ሌባ እንዳለ አትርሺ ራሄል አንቺን ፈራታ እንጂ ልጁ የብዙነህ ነው በድንጋጤ የምትጠጣው ውሃ ትን አላት ይሄኔ እረጅም ሰአት አስላ ጋፕ ሲልላት የሳራ አሳዳጊ ሳራ ገፊ እንደሆነች ነግራኛለች ቤተሰብ የላትም ይሄን ታውቃለህ በሷ ምክንያት ሞተዋል ሲል ለምለም እኔ ይህን ካንቺ አልጠብቅም ምን አይነት እራስ ወዳድ ነሽ እንደዚህ አይነት አስተሳሰብ ይኖርሻል ብዬ አስቤም አላውቅም!!!
ሳራ ፍትህ የተጠማች ሴት ናት አሳዳጊዋ ነኝ ብላ የመጣችው ሴት ሀብት ፍልጋ አባቷን በግፍ የገደለች ሴት ናት ከአባቷ አልፋ እሷን በጎረምሳ ልታስደፍራት ስትል ነው ሳራ ቤቱን ለቃላት የጠፋችው ግን ሳራ ማንም ሰው ስላልነበራት እንዴትም ብላ ፍትህ ማግኘት አልቻለችም ለልጄም ቢሆን ታማኝ አፍቃሪው ነች ህግ ተምራ የእንጀራ እናቷን ለፍርድ ልታቀርባት ህልም ነበራት ግን ውዴ አንቺ መሀል ገብተሽ የምስኪኗንም የልጅሽንም ህይወት አበላሸሽ ... እያለ ስለሳራ ሲነግራት ፀፀትና ሀዘን ፊቷ ላይ ጥላ አጠሉ እራሷን ወቀሰች .... ባሏ የተከራየው ሆቴል ክፍል ውስጥ ለ3 ቀናት አለቀሰች እሷን ለማፅናናት አቃተው ከዛም ከምታለቅስ ይቅርታ ጠይቃ ብትክሳቸው እንደሚሻል ደጋግሞ መከራት እሷ ግን ልጄስ ልጅ ነው እሷ
ትዝ ይልሃል እኔ ሴተኛ አዳሪ ነበርኩ ከዛ አንተ እኔን አፈቅርሻለው ብለህ አገባኸኝ ከዛ ግን እኔ ልኡልን ስትል አቋረጣትን አንቺ ልኡልን ከሌላ ወንድ አርግዘሽው ነበር ይሄን ላመታት ደበቅሽኝ እኔ ግን እጠረጥር ስለነበር የ DNA ምርመራ አረኩ ልኡል ልጄ እንዳልሆነ ሳውቅ ላብድ ነበር ግን ለ15 ቀን ገዳም የቆየውትን አስታወሽ አለና መልሷን ሳይጠብቅ ያኔ እዛ ሄጄ ስቆይ ነገሮችን ማገናዘብ ጀመርኩ ልኡልን ልጄ ብዬ አምኜ ተቀበልኩ አንቺም እንዳትጨናነቂ ሳልነግርሽ ዝም አልኩ ምክንያቱም በጣም አፈቅርሻለሁ... አለ ለምለም ማመን አቃታት የሷን ስራና የባልዋን መልካምነት እያሰበች በራሷ አፈረች...
በነጋታው ጠዋት ተነስታ አ.አ ሄደች እንደደረሰችም ቀጥታ የሳራን እንጀራ እናት ማፈላለግ ጀመረች እንዳገኘቻትም በዚ ሁለት ቀን ውስጥ እጇን ካልሰጠች ሰው በመግደል ወንጀል እንደምትከሳት አስጠነቀቀቻት የሳራ እንጀራ እናትም ደነገጠች ስለፈራችም ሳትቀድመኝ ልቅደማት ብላ ለምለምን በስለት ወጋቻት.....
..... .....   ......   .......  .....



     ከወደዳችሁት ቢያንስ ለ 5 ሰው share በማድረግ ተባበሩን 🙏

..............ይቀጥላል.............✍️

#ክፍል1️⃣5️⃣እንዲቀጥልLike👍ማድረግ እንዳይረሳ ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ


¶🌹የፍቅር ልብ❤️‍🩹¶™
•───────────────•🌐

#📱ከወደዱት ሼር ማድረግ አይረሳ


❤️ ፍቅር ሲፈርድ📕

#ተከታታይ ልቦለድ

#ክፍል 1⃣3⃣


#እውነተኛ አሳዛኝና አስተማሪ ታሪክ


         ሳራ ጓዟን ጠቅላ ሀገር ቤት ልትገባ መዘጋጀት ጀመረች ይሄኔ ሳሚ ቃል ተገባብተውና ቀለበት አድርገው እንትሄድ በጓደኞቹ አስጠየቃት ሳራ ግን ባሁን ሰአት ቃል የምትገባባበት ግዜ እንዳልሆነና ልቧ ለመጣመር ዝግጁ እንዳልሆነ አረዳችው ይሄኔ ሳሚ በጣም ተናደደ ልብሽ ሳይወደኝ ነበር አብረን የቆየነው ሲል ጠየቃት እሷም ውለታው ስለከበዳት ምርጫ አታ እንደሆነ ነገረችው ሳሚም የውሸት ተስፋን ስለሰጠችው በጣም ከፋው ሊበቀላትም ፈልጎ ቤተሰብ ልጠይቅ በሚል ተልካሻ ምክንያት አብሯት ኢትዮጵያ እንደሚሄድ ነገራት ሳራም መቃወም ስላልፈለገች እብረው ወደ ኢትዮጵያ ገቡ...

     ሳራና ሳሚ አ.አ ኤርፖርት እንደደረሱ በቃ ቻው እኔ ወደ ባህር ዳር ነው የምሄደው አለችው ሳሚም አብሬሽ መጥቼ ልጅሽን መተዋወቅ እፈልጋለሁ እናም ደግሞ የጓደኛዬ እናት እማማን መጠየቅ አለብኝ አለ ሳራ በግዜው የልጇ መታመም ስለነበር ያስጨነቃት መልስ ሳትሰጠው እነማማጋ ደውላ መምጣቷን አበሰረች እማማም ዛሬ ስለመሸ ነገ ትመጫለሽ ልጄ እዛው እደሪ አልዋት እሷም ያን ቀን በጣም ስለመሸ አንድ ሆቴል ውስጥ ሁለት የተለያየ ክፍል ይዘው አደሩ ...

      በነጋታው ጠዋት ኮንትራት ታክሲ ይዘው ወደ ባህር ዳር ተጓዙ በመንገዳቸውም ላይ ሳራ በትዝታ ተዋጠች ከልኡል ጋር ያሳለፉትን ግዜ እያሰበች ሳታስበው እንባዋ መውረድ ጀመረ የእንጀራ እናቷን መበቀል አለመቻሏ እንዲያውም በተቃራኒው ህይወቷ መመሰቃቀሉና ክፉዋን ለሚመኙት ሁሉ ማሸነፍ አለመቻሏ ተደማምሮ ደም እምባ አስለቀሳት ሳሚም እንደህፃን ደረቱ ላይ ለጥፎ አባበላት የሱን እምባ መውረድ እንኳ ያስተዋለው ሳራ ስትጠርግለት ነው ...

       ባህር ዳር  እንደደረሱ ሳራ ልቧ ይመታ ጀመር የሆነ አዲስ ነገር ያለ ይመስላታል ልክ በራፋ ላይ ደርሰው የውጪ በር ስታንኳኳ ቤቲ ነጭ በነጯን ለብሳ በጣም አምራና ተውባ በር ከፈተችላቸው ሳራም ቤቲንና የግቢውን ዲኮር ስታይ ግራ ገባት እንዴ እኔን ለመቀበል ነው ይሄ ሁላ ነገር ብላ ቤቲን ሰላም እያለቻት ሳለ ትንጡና ፍልቅልቁ ልጇ በአምላክ እየተሯሯጠ ሲጫወት ተመለከተች በሰአቱ ልጇን ስታይ ታሞአልና ቶሎ ድረሺ መባሏ ትዝ አላላትም ነበር እንባዋ እየቀደመ ልጇን እሩጣ አቅፋ እያገላበጠች ሳመችው ሳራ በሁኔታዋ ሁሉንም አስለቀሰች ይህ እየሆነ እያለ ቤቲ ከሳሚ ጋር ታወራ ነበር ይሄኔ ሳሚ ለቤቲና አጠገቧ ላሉት የሳራ ፍቅረኛ ነኝ እሷን ብዬ ነው የመጣሁት ልንጋባም ወስነናል አለ ይሄኔ ሁሉም ሰው ሲንጫጫ ሳራ ልጇን እንዳቀፈች ወደነሱ ዞር ስትል ውሃ አምጡ ደሞም ንፋስ ስጡት  ....ሲባል ደንግጣ ቀረበቻቸው አይኗን ማመን አቃታት ልኡል እራሱን ስቶ ወድቋል... አፋፍሰው ሀኪም ቤት ወሰዱት

       ነገሩ እንቆቅልሽ ሆነባት እማማም እያለቀሱ ልጄ በልጅሽ አሟርቼ የጠራሁሽ ታሪኩ ቢረዝምም ብቻ የልኡል አባትና ብዙነህ ልኡልን ይዘውት መተው አንቺን ሰርፕራይዝ አርገን ሁለታቹን ልናገናኝ ነበር ግን ልጄ ክፉ እድል አለሽ መሰል አንቺ እዛ ያጨሽው እጮኛሽ ልትጋቡ እንደሆነ ሳይጠየቅ ዘባርቆ ... ሲሉ ምን እማማ ሳሚ ምኔም አይደለም ቆይ ምንድን ነው ነገሩ እኔን የፈጠረኝ አምላክ ዙርያዬን የሚያስቀምጣቸው ሰዎች ሁሉ እንዲገሉኝ ነው እንዴ ይሄ የቁም ቅዠት ህልም መሆን አለበት እያለች በእልህ መጮህ ጀመረች ሳራ ሰው ሁሉ እያያት ፀጉሯን አንጨባራ ልብሷን እላይዋ ላይ መቀዳደድ ጀመረች የሚያይዋት ሁሉ ያበደች መሰላቸው እማማም አታፍጡ አስቁሟት እንጂ እያሉ ሰውን መቆጣት ጀመረ ... ... ..


  ❤️ከወደዳችሁት ቢያንስ ለ 5 ሰው share በማድረግ ተባበሩን 🙏

..............ይቀጥላል.............✍

#ክፍል1⃣4⃣እንዲቀጥልLike👍ማድረግ እንዳይረሳ ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ

20 last posts shown.

125 916

subscribers
Channel statistics
Popular in the channel

•⊰❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦              🌹የፍቅር ንቅሣት♥️                                      ክፍል 🔟 እ...
•⊰❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦              🌹የፍቅር ንቅሣት♥️                                      ክፍል 1️⃣...
‍ ​​•⊰❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦              🌹የፍቅር ንቅሣት♥️                                      ክፍል...
‍ ​​❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦              🌹የፍቅር ንቅሣት♥️                                      ክፍል ...
‍ ​​❦ ​​​​​​══•⊰❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦              🌹የፍቅር ንቅሣት♥                                ...