ከማጠልሸትና ከመኮነን ይልቅ መዋቅራዊ ጥቃት እየደረሰበት ላለው ህዝባችን መዋቅራዊ አደረጃጀት መፍጠር ብቸኛ መዳኛው ነው ብለን እናምናለን። በመሆኑም የአማራ ፋኖ ምክርቤት እንደ ቀጠና የጎጃምን እዝ ክንፍ ያላወያዬ መግለጫ ከማውጣቱም ባሻገር የሙሉ መግለጫውን ሐላፊነት የተሰጠው ቡድንም ሆነ ግለሰቦች ላይ እውቅና ስለሌለን በድጋሜ እንዲጤን እንጠይቃለን። በሌላ በኩል ሚዲያ ከወታደራዊ ክንፉ ያልተናነሰ ጉልበት አለው። በዚህም በርካታ ሚዲያዎች የአማራን ህዝብ የሕልውና ትግል በማስተጋባት ደማቅ አሻራን እያሳረፉ ነው ። ሁሉም ትግሉን የሚደግፉ የሳተላይትና የዩቲዩብ ሚዲያዎች የጠላትን የፕሮፓጋንዳ ክንፍ በመስበርና ህዝባዊ የሆነውን የአማራ ፋኖ ተጋድሎ አጉልቶ በማውጣት ለትግሉ የቀጣይ አቅጣጫ አሰላለፍና ረድፈን አሳይተውናል። በመሆኑም ለአማራ ህዝብና ምድር ለነኩ ሐቀኛ ታጋዬችና አደረጃጀቶች ማስተላለፍ የምንፈልገው መልዕክት ቢኖር የአማራን ህዝብ እሴት ያከበረ፣ ከመነቃቀፍ ይልቅ "ሳር ሲነባበር ዝናብ ይከላከላል" ብሂልን የተከተለ፣ አንድነትን የትግል መርሑና የማይደፈር ቀይ መስመር ያደረገ፣ 'እኔ' ከሚል መታበይ ይልቅ 'እኛ' የሚል ትህትናን ያዘለ ጉዞን እንድንከተል ስንል በጥብቅ እያሳሰብን የተገኙ ድሎች ሁሉ በህዝባዊ ተጋድሎው የተመዘገቡ የቡድን ስራ ውጤት መሆናቸው እንዲሰመርበት በአፅንኦት እንገልፃለን።
9ኛ.በመጨረሻም የጎጃም ዕዝ ሁሉም ማህበረሰብ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ለህልውና ዘመቻ እንዲዘጋጅ አቅጣጫ በማስቀመጥ የዕዙን የመጀመርያ ስብሰባ በስኬት አጠናቋል ።
ድል ለተገፋው የአማራ ህዝብ!
ጎጃም ደጋ ዳሞት
ፈረስ ቤት