ከመላው ኢትዮጵያ ለሚመጡ ተማሪዎች በታዋቂዉ በሊሴ ገብረማርያም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲቀላቀሉ እድል የሚሰጠዉ ስምምነት ኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ አደረጉ።
በኢትዮጵያ ከ 77 ዓመታት በላይ በመማር ማስተማር ዘርፉ ላይ የሚገኘዉ ታሪካዊዉ ትምህርት ቤት እንደሆነ የሚነገርለት ሊሴ ገብረማሪያም በአዲሱ አሰራር ከመላዉ ሀገሪቱ የሚመጡ ተማሪዎች መቀበል እንደሚጀምር ተገለፀ።
ይህ ስምምነት የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከፈረንሳይ የአውሮፓ እና ውጭ ጉዳይ ስምምነቱን የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከፈረንሳይ የአውሮፓ እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጂያን ኖኤል ባሮት ጋር ተፈራርመዋል።
የፈረንሳይ የዉጪ ጉዲይ ሚኒስትሩ ጂያን ኖኤል የዚህን ስምምነት ዓላማ ሲናገሩ " ምንፈርመው ከ77 ዓመታት በፊት የተጀመረውን ሥራ ለማራዘም ያስችላል" ብለዋል ።
ሊሴ በአዲስ አበባ የሚገኝ የፈረንሳይ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት ሲሆን ትምህርት ቤቱ የተከፈተው እኤአ በ1947 መሆኑን የታሪክ ማህደሩ ያሳያል ። በዚህ ትምህርት ቤት ያለፉ ተማሪዎች በሀገሪቷ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ትልቅ ተፅዕኖ መፍጠር እንደቻሉ ይነገራል ።
ዛሬ የተደረገዉ ስምምነት አዲስ አሰራር እንደሆነ የተናገሩት ሚኒስትሩ በዚህም ከመላው ኢትዮጵያ ለሚመጡ ተማሪዎች የሊሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲቀላቀሉ እድል የሰጠ መሆኑን ጠቁመዋል ።
ይህም በሁለቱ ሀገራት ቅድሚያ የሚሰጠውን የትምህርት ጥራት ለሁሉም ተደራሽ እንደሚያደገዉ የገለፁ ሲሆን ስምምነቱ ሁለቱን ሀገሮቻችንን የሚያስተሳስረው አዲስ የመተማመን ግንኙነት መገለጫ ጭማር መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዉበታል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፊሰር ብርሃኑ ነጋ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ፈረንሳይ ለኢትዮጵያ የተለያዩ ነጻ የትምህርት እድሎችን ለመስጠት፣ እንዲሁም በሊሴ ገብረማሪያም ትምህርት ቤት የስኮላር ሺፕ መርሃ ለማጠናከር ያስችላል ሲሉ ተደምጠዋል።
ከፈረንሳይ መንግስት ጋር የተደረሰው ስምምነትም ኢትዮጵያ በትምህርት መስክ የያዘችውን ዓላማ ከግብ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ አስረድተዋል።
ለጥቆማ 👉
@atc_newsbot➡️
https://t.me/atc_news