ባሕርን መሆን
ባንድ ወቅት በሕይወቱ ደስታን ያጣው ወጣት ለአንድ የዕድሜ ባለጸጋን ሽማግሌ ሕይወት እንዳማረረችው ገልጾ መፍትሄ እንዲጠቁሙት ጠየቃቸው፡፡
ሽማግሌው የወጣቱን ሀሳብ በጥሞና ካደመጡ በኋላ በእፍኙ ሙሉ ጥሬ ጨው በብርጭቆ ውሃ ውስጥ ጨምሮ በጥብጦ እንዲጠጣው አዘዙትና “ጣዕሙ እንዴት ነው?” በማለት ጠየቁት፡፡ ፊቱን አኮሳትሮ “በጣም አስቀያሚ ነው!” ሲል መለሰላቸው፡፡
ሽማግሌው ፈገግታ እያሳዩት ወጣቱን ወደ ባሕር ዳርቻ ወስደው ሌላ ጭብጥ ሙሉ ጨው ባሕሩ ውስጥ እንዲጨምርበት አመላከቱት፡፡ በመቀጠልም ከባሕሩ ጨልፎ እንዲጠጣ ካደረጉ በኋላ “ጣዕሙ እንዴት ነው?” ሲሉ በድጋሜ ጥያቄ አቀረቡለት፡፡ ጥሩ ነው በማለት መለሰ ታዳጊው፡፡ አስከትለውም የጨው ኮምጣጣነትና ያ አስቀያሚው ስሜት ተለይቶሃል? በማለት ጠየቁት፡፡ “በፍጹም” ሲል መለሰ ወጣቱ፡፡
ከዚህ ሁሉ የተግባር ትምህርት ቀጥሎ ሽማግሌው የወጣቱን እጅ ይዘው ከጎኑ ተቀመጡና ይሄንን መከሩት፡፡ በሕይወት ጎዳና የምታደርጋቸው ትግሎች እንደ ንጹህ ጥሬ ጨው ናቸው፡፡ ነገር ግን የስቃዩ መጠን ተመሳሳይ ቢሆንም የምንሸከመው ስቃይ የሚወሰነው በምንይዝበት ዕቃ መጠን ይወሰናል፤ ችግሩን የምናስተናግድበት አግባብም የሚፈጥረውን ጫና በዛው ልክ ይለያየዋል፡፡ ችግሩ ሲጠናብህ ልታደርገው የሚገባው ዋናው ነገር ምልከታህን ማስፋት ብርጭቆውን ሳይሆን ባሕሩን መሆን ነው ትልቁ የአኗኗር መላው፡፡ እናም ብርጭቆ መሆንህን አቁመህ ባሕሩን ሁን አሉት፡፡
join us...
@Ab_book