ፈጣን ውጤት አትጠብቅ!
(“ራስን ማሸነፍ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)
የምንኖርበት ዘመን ሁሉንም ነገር “አሁኑኑ” ማግኘት እንደምንችልና እንደሚገባንም የሚነግረን ዘመን ነው፡፡ “ፈጣን የገንዘብ ዝውውር … ፈጣን በርገር … ፈጣን አገልግሎት … ፈጣን ዲግሪ …”፡፡ እነዚህ የፈጣን አገልግሎት “ቃል-ኪዳኖች” ሲሳኩና ሲሆንልን ከብዙ ልፋት ያድኑናል፤ ጊዜአችንንም በተሻለ ሁኔታ እድንጠቀም ድጋፍን ያደርጉልናል፡፡ ሆኖም በተያያዥነት፣ ትንሽ ጊዜን የሚወስድን ሁኔታ መታገስ የማንችልበትን አመለካከት አዳብለው ይሰጡናል፡፡
ምንም እንኳን የቀለጠፈ ነገር አስፈላጊ ቢሆንም፣ ሰርተህና ጊዜን ወስደህ ማግኘት የሚገቡህ ነገሮች እንዳሉ ማሰብም አስፈላጊ ነው፡፡ ትእግስት የተሰኘው ራስን የማሸነፍ ዘርፍ ሁኔታዎች በጠበካቸው ፍጥነት በማይመጡ ጊዜ አልፈህ እንድትሄድ ያግዝሃል፡፡ ይህ አይነቱን ራስን የማሸነፍ ብቃት ካላዳበርክ ሁሉን ነገር በአቋራጭ ለማግኘት ወደመሹለክለክ ጎጂ ልማድ ይወስድሃል፡፡ በተቃራኒው፣ ትክክለኛውን ነገር በተገቢው ትጋትና በትክክለኛው ጊዜ ለማግኘት የተረጋጉ ሰዎች ሕይወታቸው ከሌሎች የላቀ ነው፡፡
ፈጣን ውጤት ትጠብቃለህ?
ራስህን መዝነው
1. የሚያስጠብቅና ረጅም ጊዜ የሚፈጅ ነገር ፋይዳ ቢስ እንደሆነ ታስባለህ?
2. ምንም እንኳን ውጤቱ ጥሩ ቢሆን አንድን ነገር ለማግኘት መጠበቅ ጊዜ ማባከን ነው ብለህ ታስባለህ?
3. ትእግስት የሚባለው ልማድ እንደሌለህ ታስባለህ?
4. በአንድ ነገር ላይ ፈጣን ውጤት ካላገኘህ ነገሩ እንደማይሳካ የማሰብ ዝንባሌ አለህ?
5. ሁሉም ነገር አሁኑኑ ካልተከናወነ የሚል አመለካከት አለህ?
6. የምትፈልገውን ነገር ለማግኘት ጤና ቢስ የሆኑ አቋራጭ መንገዶች መፈላለግ ይቀናሃል?
7. ሌሎች ሰዎች አንተ በምትሄድበት ፍጥነት ካልሄዱ ትበሳጫለህ?
8. የአንድን ነገር ውጤት ባሰብከው ፍጥነት ካላገኘህ ተስፋ ትቆርጣለህ?
9. ባወጣኸው ግብ ላይ መቆየት ያታግልሃል?
10. አንድን ነገር ለማከናወን ምን ያህል ጊዜ ሊፈጅ እንደሚችል የማስላት ችግር አለብህ?
ከላይ ለተጠየቁት አስር ጥያቄዎች ከግማሽ በላይ ለሆኑት “አዎ” የሚል መልስ ከሰጠህ በዚህ ምእራፍ ለተጠቀሱት ነጥቦች አስፈላጊ ትኩረት በመስጠት ለውጥን ለማስተናገድ ጥረት አድርግ፡፡
join us...
@Ab_book