Forward from: Bahiru Teka
🔷 ማንን ነበር ምታመልከው ?
ረመዳን ላይ ጀለብያ አመኢማ ኮፍያ ገዝተህ
አዛን ሳይደርስ መስጂድ ገብተህ ሰፈል አወል የነበርከው ማንን ነበር ምታመልከው ?
የዒድ ለሊት ዒሻእ ላይ ሁሉን ጥለህ እርጥብ እሳት ይዘህ ጎዳና ላይ የወጣኸው ያኔ ማንን ነበር ምታመልከው ?
ረመዳ ማለት አምላክ ሳይሆን እሱን ማምለኪያ ዘመን ነበር እንዴት አምላክ አደረከው ?
ወሩን አምልከህ በዛው የጠፋኸው ያኔ ማንን ነበር ያመለክኸው ?
ቀንና ለሊት የሚቀይር ፍጥረተ ዐለሙን ሚያስተናብር የሁሉንም ስራ ሚመረምር አማኙንም አማፂውን በችሮታው የሚያከብር ጊዜ ሰጥቶ ለኛን ተግባር ምንዳ የሚጨምር
አለያም ወደ ውርደት ሚወረውር አምላክ አለ ሊመለክ የሚገባው ። እሱን ትተህ ማንን ነበር ምታመልከው ?
አላህ ማለት ሁሌም አለ በአመት አንዴ ወይም በሳምንት አይደለም ሚመለከው ።
ፍጥረተ ዐለሙ የሱ ስለሆነ በቀንና በማታ ነው ሚመለከው ።
ተው እንጂ አንተ ሰው ተመለስ ወደ ልብህ በብልጭልጭ መታለሉ ይቅርብህ ።
ለቁም ነገር ነበር የፈጠረህ ከዓላማህ ምን ይሁን ያዘናጋህ ?
ሊረሱት የማይገባ ቀብር እያለብህ ምን ይባላል መዘንጋትህ ?
ተው ተመለስ ወደ መስጂድ መዘናጋቱ ይብቃህ ።
ምን ይሉታል ለቁም ነገር ተፈጥረህ በብልጭልጭ መታለልህ ።
ኧረ ተው ተመለስ ወደ ልብህ ይበቃሀል መሸንገሉ ቀጠሮ የማይሰጥ ሞት አለብህ መንገድ ዳር ላይ ቁጭ ብለህ እንዳይቀድምህ ።
ጌታህን ተገዛ ወደ መስጂድ ተመልሰህ ለአንድ ወር ሙእሚን ሆነህ ማንን ነበር ምታመልከው ?
አላህ እነደሁ ሁሌም ካንተው ጋር ነው ፅናቱን ለምነው ሁሌም ልታመልከው ተመላሽን የሚቀበል ውድ አምላክ ነው ።
ይወደሀል ሁሌም እሱን ብቻ ካመለክኸው ።
አላህ ሁሌም አማኝ ባሪያ ያድርገን ።
https://t.me/bahruteka