አዲስ የተዋሕዶ መዝሙር


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Religion


በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
#አዲስ_የተዋሕዶ_መዝሙር
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ያሬዳዊ መዝሙሮችን እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ።
እንዲሁም አዳዲስ የሚወጡ የኦርቶዶክስ መዝሙሮችን በትንሽ ሜጋባይት በዚህ ቻናል ያገኛሉ
#ሼር በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ🙏

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Religion
Statistics
Posts filter


#ሰንበተ_ክርስትያን

በኩር ናት የበዓላት
ኑ ከፍ ከፍ እናድርጋት
በእሷ ደስ ይበለን
በሰንበተ ክርስቲያን

በዝማሬ እንበርታ በገናውን እንያዝና
መልካም ስራ የሚሰራባት
ሰንበት ቅድስት ናት እና
ከጨለማ ብርሀን ከመገዛት ነፃነት
እግዚአብሔር ይህን ሰጠን
ደስ ይበለን በሰንበት
#አዝ
ለአብርሃም ተገልጣለች
ለሙሴም በደብረ ሲና
በነቢያት የታወቀች
ሰንበት ዳራዊት ናት እና
በሳምንቱ ሰለጠነች
ተሰበከች በሐዋርያት
ሃሌ ሉያ ዕለተ ሰንበት
ተሰጠችን ልናርፍባት
#አዝ
በእልልታ እንሞላ እንደ ነቢዩ አሳፍር
በከበረች የሰንበት ቀን ኑ ለቅኔ እንሰለፍ
በመቅደሱ ናቸው እና ቅዱስነትና ግርማ
ውዳሴያችን ይሰማልን
ከምድር እስከ እዮር እራማ
#አዝ
እግዚአብሔር አብ የባረካት
እግዚአብሔር ወልድ የቀደሳት
ከእለታት ሁሉ መርጦ
መንፈስ ቅዱስ ከፍ ያደረጋት
በእርሷ ሀሴት እናድርግ
እናክብራት እንድንከብር
የደጀሰላሙ ታዛ በመቅደሱ እንሰብሰብ

💚 @Addis_Mezmure 💚
💛 @Addis_Mezmure 💛
❤️ @Addis_Mezmure ❤️


#ቅድስት

ይህ የሁለተኛው ሰንበት ስያሜ ሲሆን የተባለበትም ምክንያት ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ስለሚያወሳ ነው፡፡ እንዲሁም ይህ ዕለት ዕለተ እግዚአብሔር የተባለች የሰንበት ክርስቲያን ቅድስናን ያመለክታል ምክንያቱም የዚች ዕለት ጌታ እርሱ ቅዱስ እግዚአብሔር ነውና ስለዚህም ዕለተ ሰንበት ቅድስት ተብላለች፡፡

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
             •➢ ሼር // SHARE
       🙏 @Addis_Mezmure 🙏


…………ቅድስት…………
"ሰንበትን እግዚአብሔር እንደቀደሰ"

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
             •➢ ሼር // SHARE
       🙏 @Addis_Mezmure 🙏


🔴 "አንዱ ለሁሉ ሞቷልና" ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
🕯 @Addis_Mezmure 🕯
🕯 @Addis_Mezmure 🕯


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
🔴 "አንዱ ለሁሉ ሞቷልና" ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
🕯 @Addis_Mezmure 🕯
🕯 @Addis_Mezmure 🕯


ዘወረደ
"በእርሱ ፍቃድ"

በእርሱ ፍቃድ በአባቱ ፍቃድ
በመንፈስ ቅዱስ ፍቃድ
ከሰማያት ወረደ
ከድንግል ማርያም ተወለደ

ዓለሙን እንዲሁ ወደደና
ከሰማያት በላይ ወረደና
በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት
ተወሰነ አምላከ አማልክት
ከሰማያት የወረደው
ፍቅር ስቦት የመጣዉ
ወልደ አብ ወልደ ማርያም
ኢየሱስ ፈራጅ ነዉ
#አዝ
ቅድመ ዓለም ተወልዶ ያለ እናት
ድህረ ዓለምም ያለ አባት
የእግዚአብሔር ልጅ በእርግጥም ሰው ሆነ
ሁሉ በእርሱ ይኸው ተከናወነ
ከሰማያት የወረደው
ፍቅር ስቦት የመጣዉ
ወልደ አብ ወልደ ማርያም
ክርስቶስ አምላክ ነዉ
#አዝ
የማይታይ ታየ በምድር
ረቂቁ ገዘፈ ስለፍቅር
ሥጋን ተዋህዶ ሆነልን ፈውስ
አማኑኤል የነገስታት ንጉሥ
ከሰማያት የወረደው
ፍቅር ስቦት የመጣዉ
ወልደ አብ ወልደ ማርያም
እግዚአብሔር እርሱ ነዉ
   
ዲ/ን ቀዳሜጸጋ
       💚 @Addis_Mezmure 💚
       💛 @Addis_Mezmure 💛
       ❤️ @Addis_Mezmure ❤️


1. #ዘወረደ
የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሰንበት ሲሆን ይህም ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን ፈጥሮ የሚኖር አልፋና ኦሜጋ ከሰማየ ሰማያት መውረዱንና ከእመቤታችን ከቅድስተ ቅዱሳን ከንጽሕተ ንጹሐን ከድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመለክት ሥያሜ ነው፡፡
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
       🙏 @Addis_Mezmure 🙏


እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

                 #መልካም_በአል
       💚 @Addis_Mezmure 💚
       💛 @Addis_Mezmure 💛
       ❤️ @Addis_Mezmure ❤️


እንኳን ለጥምቀት #ከተራ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን
   💚 @Addis_Mezmure 💚
   💛 @Addis_Mezmure 💛
   ❤️ @Addis_Mezmure ❤️


“ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።”
   📖ሉቃስ 2፥10📖

እንኳን ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤አደረሰን !!!

        🙏መልካም በዓል🙏
   💚 @Addis_Mezmure 💚
   💛 @Addis_Mezmure 💛
   ❤️ @Addis_Mezmure ❤️


#ጥምቀተ_ባሕር

ጥምቀተ ባሕር ዮርዳኖስ ነያ /2ጊዜ/
ሀሌ ሉያ /4ጊዜ/

ጌታችን ሲጠመቅ ባሕር ምን አለች
አልችለውም ብላ ወደ ፊት ሸሸች
ብርሃነ መለኮት በወንዙ ሲሞላ
ዮርዳኖስም ሸሸ ቀረ ወደ ኋላ
#አዝ - - - - -
አብ በመጣ ጊዜ ደመናውን ጭኖ
መንፈስ ቅዱስ ታየ በርግብ አምሳል ሆኖ
ለልጁ ምስክር ሊሆን ፈለገና
ቃሉን ተናገረ ሆኖ በደመና
#አዝ - - - - - -
ጌታችን ሲጠመቅ በ30 ዓመት
ባሕር ኮበለለች ግዑዟ መሬት
ሰማይ ተከፈተ ሆነልን ፀአዳ
ከሩቅ መቷልና አብ ታላቁ እንግዳ
#አዝ - - - - - - -
እልል በይ ዮርዳኖስ የጥምቀት መገኛ
የፃድቃን መሰላል ድህነታችን ለእኛ
ቀላያት አብርህት ብዙዎች እያሉ
እንደምን ተመረጥሽ ዮርዳኖስ ከሁሉ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
              •➢ ሼር // SHARE
  💚 @Addis_Mezmure 💚
   💛 @Addis_Mezmure 💛
   ❤️ @Addis_Mezmure ❤️

8.2k 0 112 2 56

#ሆረ_ኢየሱስ

ሆረ ኢየሱስ (2)
እምገሊላ ሀበ ዮርዳኖስ

ሄደ ኢየሱስ (2)
ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ

አዝ......................

ኢየሱስ ሊጠመቅ መጣ ከገሊላ
ዮርዳኖስም ሸሸ ሄደ ወደሃላ
ተፈወሰ (3) ያዳም ልጅ በመላ

እም ገሊላ (3) ሀበ ዮርዳኖስ

አዝ............................

አብም መሰከረ ተገልጦ ነገረ
የባህሪ አምላክ እግዚአብሄር ነው አለ
መንፈስ ቅዱስ በርግብ ተገልጦ ሲበር
መሰከሰ (3) የወልድን ክብር

አዝ...........................

የእዳ ደብዳቤው አለ ዮርዳኖስ
ፅፈቱ ተሻረ ተጠምቆ ኢየሱስ
ተሰረዘ (3) የአዳም ልጅ ክስ

አዝ..................................

ሚስጥረ ስላሴ ታየ በገሀድ
በባሪያው ሲጠመቅ እግዚአብሄር ወልድ
ተይዞልን (3) በፍቅር ገመድ


   💚 @Addis_Mezmure 💚
   💛 @Addis_Mezmure 💛
   ❤️ @Addis_Mezmure ❤️


#ዮሐንስኒ_ያጠመቀ
ዮሐንስኒ ያጠመቀ/2/
በሄኖን/4/ በማዕዶተ ዮርዳኖስ

እዩት ትህትናውን__ያጠመቀ
ፅድቁን ተመልከቱ__ያጠመቀ
በባሪያው እጅ ሆኖ__ያጠመቀ
የጌታ ጥምቀቱ__ያጠመቀ
#አዝ_
አንተ መናኙ ሰው__ያጠመቀ
ቅዱስ ባህታዊ__ያጠመቀ
በእጅህ ተጠምቆ__ያጠመቀ
ኢየሱስ ናዝራዊ__ያጠመቀ
#አዝ_
ተሰውሮ ሳለ__ያጠመቀ
ካለም ተለይቶ__ያጠመቀ
አዋጁን ስሙ አለ__ያጠመቀ
በጉን አሳይቶ__ያጠመቀ
#አዝ_
ንስሐ እየገቡ__ያጠመቀ
እየተናዘዙ__ያጠመቀ
በዮሐንስ ስብከት__ያጠመቀ
ለእግዚአብሔር ተገዙ__ያጠመቀ
#አዝ_
የሰማዩን ጌታ__ያጠመቀ
ምድራዊ ሲያጠምቀው__ያጠመቀ
ሚስጢር ተገለጠ__ያጠመቀ
ዓለም ሁሉ አወቀው__ያጠመቀ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
  💚 @Addis_Mezmure 💚
   💛 @Addis_Mezmure 💛
   ❤️ @Addis_Mezmure ❤️


#እግዚኡ_መራ
እግዚኡ መራ ዮርዳኖስ ዘአብጽሃ፤(2)
ወበ ህየ ዮሐንስ (2) ፍጽመ ተሰብሃ

ጌታውን መራና ዮርዳኖስ አደረሰው (2)
በዚያች ዕለት ዮሐንስ (2) በፍፁም ደስ አለው
   💚 @Addis_Mezmure 💚
   💛 @Addis_Mezmure 💛
   ❤️ @Addis_Mezmure ❤️


#መጻ_ቃል
መጻ ቃል እም ደመና ዘይብል (2)
መጻ ቃል እም  ደመና ዘይብል(2)
ዝንቱ ውዕቱ ወልድየ  ዘአፈቅር

መጣ ቃል  ከደመና እደዚክ የሚል (2)
የምወደው የማፈቅረው ልጄ ይህ ነው
    አዝ
አደም የለው የእዳ ፅፈት
በዮርዳኑስ ሲወርድ እሣት
በክርስቶስ ተሽሮልን
የልጅነት ክብር አገኛን

#አዝ_

ባህር አይታው ኮበለለች
ታላቅ ንጉስ መጣ እያለች
ተራሮችም እደኩርማ
መሰከሩው የሡን ግርማ

#አዝ_

ከእግዚአብሔር ዘንድ መወለድክ
ክርስትና ሞልቶ ክብርክ
ሊቀ ካህን ስራዬህ
አደረገክ በአለ ሟልህ

#አዝ_

የትትና አስተማራይ
ሠማይ ምድሩን ሁሉን መሪይ
በፍጡሩ በዮሐንስ
ተጠመቀ የእግዚአብሔር ልጅ :::
   💚 @Addis_Mezmure 💚
   💛 @Addis_Mezmure 💛
   ❤️ @Addis_Mezmure ❤️


#በዛሬው_ጥምቀቱ

በዛሬው ጥምቀቱ እሰይ እሰይ 
ተነግሮ አዋጅ እሰይ እሰይ 
ነጻነት አገኘን እሰይ እሰይ 
በእግዚአብሔር አብ ልጅ እሰይ እሰይ 
እሰይ እሰይ ተወለደ
እሰይ እሰይ ተተመቀ/2/ 
ከሰማየ ሰማይ ወረደ/2/ 
ከድንግል ማርያም ተወለደ
አዝ------------
አብም መሰከረ እሰይ እሰይ 
ቃሉን አላበየም እሰይ እሰይ 
የምወደው ልጄ እሰይ እሰይ 
ይሄ ነው እያለ እሰይ እሰይ
አዝ------------ 
ጌታ በዮሐንስ እሰይ እሰይ 
ሊጠመቅ ሲል ገና እሰይ እሰይ 
ወደ ኋላ ሸሸ እሰይ እሰይ 
ዮርዳኖስ ፈራና እሰይ እሰይ 
አዝ------------ 
ተራሮች ዘለሉ እሰይ እሰይ 
እንደ ጊደር ሁሉ እሰይ እሰይ 
እፁብ ነው ድንቅ ነው እሰይ እሰይ 
ምን ይገርም እያሉ እሰይ እሰይ 
አዝ------------ 
ውኃን ወይን አረገ እሰይ እሰይ 
በተጠራበት ቤት እሰይ እሰይ 
የብርሃናት ጌታ እሰይ እሰይ 
የዓለም መድኃኒት እሰይ እሰይ 

   💚 @Addis_Mezmure 💚
   💛 @Addis_Mezmure 💛
   ❤️ @Addis_Mezmure ❤️


#ዮሐንስኒ

ዮሐንስኒ ያጠምቅ/2/
በሄኖን/4/ በማዕዶተ ዮርዳኖስ

ዮሐንስ ሲያስተምር ያጠምቅ
በጫካ በሜዳ ያጠምቅ
የበግ ፀጉር ለበሶ ያጠምቅ
ሆኖ ምድረ በዳ ያጠምቅ

አዝ___

አምላኩን የሚወድ ያጠምቅ
ብዙ ሰው እያለ ያጠምቅ
ጌታውን ለማጥመቅ ያጠምቅ
ዮሐንስ ታደለ ያጠምቅ

አዝ___

ተራራው ዝቅ ይበል ያጠምቅ
ጎባጣውም ይቅና ያጠምቅ
ብሎ ያስተማረው ያጠምቅ
ዮሐንስ ነውና ያጠምቅ

አዝ___

ከሐጢያት ተለዩ ያጠምቅ
በውሀ ተጠመቁ ያጠምቅ
መንግስተ ሠማያት ያጠምቅ
እንዳለች እወቁ ያጠምቅ
   💚 @Addis_Mezmure 💚
   💛 @Addis_Mezmure 💛
   ❤️ @Addis_Mezmure ❤️


🔴 አዲስ የልደት ዝማሬ "ተወለደ " በዘማሪ ሊቀ ዲያቆናት ነቢዩ ሣሙኤል
   💚 @Addis_Mezmure 💚
💛 @Addis_Mezmure 💛
❤️ @Addis_Mezmure ❤️


#በቤተልሄም

በቤተልሄም ድንግል ወለደች
አማኑዔልን ታቅፋ ታየች
እረኞች ተቀኙ መላዕክት ዘመሩ
ስብሀት ለእግዚአብሔር በሠማይ በምድሩ

የያዕቆብ ኮከብ ከሩቁ ያየነው
በኤፍራታ ዋሻ በዱር አገኘነው
ድንቅ መካንሀያል ወንድ ልጅ ተሠጠን
በከብቶቹ ግርግም ተወልዷል ሊያነፃን
       ድንግል ያጠባችው
       ማርያም ያዘለችው
       ሁሉ በእርሱ የሆነ እግዚአብሔር ነው

#አዝ___

ያረምና ሠባ የቴርሠሥ ነገስታት
ከሩቅ ምስራቅ መጡ ወድቀው ሊሰግዱለት
አንቺ ቤተልሄም የይሁዳ ምድር
እልልታሽ ተሰማ የዳዊት ሀገር
     ድንግል ያጠባችው••••••

#አዝ____

ማርያምን ለመውሰድ ዮሴፍ ሆይ አትፍራ
ከመንፈስ ቅዱስ ነው ይሄ ድንቅ ስራ
ያለዘራ በዕሲ ጌታን የወለደች
የያቄም ልጅ ፅዮን እመብርሀን ነች
     ድንግል ያጠባችው•••••••

#አዝ___

በስጋና በደም ስለተካፈለ
ፍፁም አምላክና ፍፁም ሰው ተባለ
ወልደ-ማርያም ነው ወልደ-እግዚአብሔር
ለአለም የሠጠህ ሠላምና ፍቅር
    ድንግል ያጠባችው••••••••

   💚 @Addis_Mezmure 💚
   💛 @Addis_Mezmure 💛
   ❤️ @Addis_Mezmure ❤️


#በእደ_ዮሐንስ_ተጠምቀ

በእደ ዮሐንስ ተጠምቀ
ኢየሱስ ናዝራዊ (2)
ሰማያዊ [5] እየሱስ ናዝራዊ
እኽ
ሰማያዊ [5] ኢየሱስ ናዝራዊ

#አዝ....
አዳም ያጠፋውን ልጅነት ሊያስመልስ
በሰላሳ ዘመን ተጠመቀ ኢየሱስ
እረሱ አምላክ ሲሆን ፈጥሮ የሚገዛ
ወርደ ወደ ምድረ እንዲሆነን ቤዛ

እኽ 
ሰማያዊ [5] ኢየሱስ ናዝራዊ

#አዝ.....
ሊያጠፋው አቅልጦ እንደ አምላክነቱ
ረግጦ ሊሰረዝ እንደሰውነቱ
የፍጥረቱ ጌታ በዮረዲያኖስ ቆሟል
የእዳውን ፅፍት በስልጣኑ ሽሯል
እኽ
ሰማያዊ [5] ኢየሱስ ናዝራዊ

#አዝ....
የአድነት ሶስትነት ተገልጧል ሚስጥሩ
በእደ ዮሐንስ ተጠምቆ መምህሩ
አብም በደመና ለልጁ መስክሯል
በሃምሳለ ርግብ መንፍስ ቅዱስ ወረዷል
እኽ
ሰማያዊ [5] ኢየሱስ ናዝራዊ

#አዝ.....
ሲነገር እንዲኖር የረሱ ትህትና
ለዓለም እንዲገለጥ የባሪያው ልዕልና
ተጠማቂው ሔደ ወደ አጥማቂው
አምላክ የሰራልን ስረዓቱ ይህ ነው

በእደ ዮሐንስ  ተጠምቀ
እየሱስ ናዝራዊ  [2]
ሰማያዊ  [5 ] ኢየሱስ ናዝራዊ

     ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
  💚 @Addis_Mezmure 💚
   💛 @Addis_Mezmure 💛
   ❤️ @Addis_Mezmure ❤️

20 last posts shown.