TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
አዲስ ሪፖርተር - NEWS

18 Mar, 10:17

Open in Telegram Share Report

ያሳዝናል‼

የሀገሪቱ ወርቅ በባእዳን እየተዘረፈ ነው።

ከኢትዮጵያ እስከ ዱባይ የተዘረጋው የወንጀል ሰንሰለት ውስጥ መሪ ተዋንያኑ የቻይና ተወላጆች መሆናቸውን ጥናቱ ያሳያል ። እነዚህ ዘራፊዎች በተለይ በጋምቤላ እና በቤን ሻንጉል ጉሙዝ የተከማቸውን የወርቅ ማዕድን ያለ ከልካይ እያፈሱ በጎረቤት ሀገራት በኩል በማዉጣት የዱባይ፣ የህንድ እና የቻይና የወርቅ ገበያን መቆጣጠራቸው የአደባባይ ምስጢር ሆኗል።

በቤን ሻንጉል ጉምዝ የዘረፋው ቡድን አለቃ ሱዛን ትባላለች። ሴትየዋ የክልሉን መንግሰት የማዘዝ ስልጣን እንዳላት የአይን እማኞች ይናገራሉ። የራስዋን ሀይል በማደራጀት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን የወርቅ አምራቾችን ጭምር ከአካባቢው ማባረርዋን የሚኒሰቴሩ ምንጮች መስክረዋል። ይህች የቻይና ተወላጅ የክልሉን መንግስት በጉልበት አልያም በጥቅም በመያዝ አቅም አልባ እንዲሆን አድርጋ የሀገሪቱን የወርቅ ክምችት እያሟጠጠችው ትገኛለች።

በጋምቤላ  የተሰማራችው ደግሞ ቼሪ (በፎቶ ያለችው) ትባላለች። ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ወንጀል ሶስት አመት ተፈርዶባት ከእስር  የተለቀቀች ፍርደኛ ናት። የክልሉን የጸጥታ ሀይል የግልዋ እስኪመስል የማዘዝ ስልጣን አግኝታ ወርቁን ቀን እና ሌሊት በማፈስ ላይ እንደምትገኝ የአይን  እማኞች ይመሰክራሉ።

በጋምቤላ ክልል የዲማ ወረዳ ማዕድን ጽ/ቤት ኃላፊና የወረዳው ኮማንድ ፖስት ምክትል ሰብሳቢ አቶ ኡቦንግ ኡቶው ባለፈው ሳምንት ለዶይቼ ቬሌ ሲናገሩ የተሰጣቸውን ፈቃድ ለህገወጥ ተግባር አውለዋል የተባሉና በወርቅ ማውጣት ሥራ ተሰማርተው የነበሩ አካላት ፈቃዳቸው መሰረዙን ገልፀዉ ነበር፡፡ 

እንደ አቶ ኡቦንግ በወረዳው ከነበሩ 47 አነስተኛ የወርቅ አምራቾች ውስጥ 36ቱ የተሰጣቸው ፈቃድ ተሰርዞ ከስራ እንዲሰናበቱ መደረጉን፣በወርቅ ግብይት ማእከል ከተሰማሩት 34 ማዕከላት መካከል 33 በህገወጥ ስራ ተሰማርተው በመገኘታቸው ፈቃዳቸው መሰረዙንም አስረድተዋል፡፡ ይህ ገለፃ ግን ለሜዲያ ፍጆታ ካልሆነ በስተቀር በተግባር የሚታየው ግን ሌላ ነው።

ፍቃዳቸውን ከተነጠቁት  ከነዚህ ሀገወጥ የወርቅ አምራች እና ነጋዴዊች ውስጥ ቼሪ አንድዋ ብትሆንም ፈቃድዋ ተሰርዞም ስራዋን አላቆመችም።  የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት በክልሉ ሀይል ጥበቃ እየተደረገላት የዲማን ወርቅ በተጠናከረ መልክ እየዘረፈች ትገኛለች ( ዘሀበሻ)።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter

5.5k 0 9 35
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Blog Telegram Research 2019 Telegram Research 2021 Telegram Research 2023
Contacts
Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot