TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
አዲስ ሪፖርተር - NEWS

18 Sep, 07:59

Open in Telegram Share Report

የሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ምልክት ተደርጎ የሚወሰደው ህንፃ በእሳት ጋየ

በሱዳን ዋና ከተማ በጦር ኃይሉ እና በተፋላሚ ሃይሎች መካከል ከፍተኛ ጦርነት ከተፈጠረ በኋላ ሕንፃዎች ሲቃጠሉ ታይተዋል።በትላንትናው እለት በተሰራጩ ቪዲዮዎች መሰረት የታላቁ ናይል ፔትሮሊየም ኦይል ኩባንያ ታወር በእሳት ጋይቷል።

የሕንፃው መሐንዲስ ታግሬድ አብዲን ቀደም ሲል ትዊተር ተብሎ በሚጠራው በአሁኑ ኤክስ ላይ በለጠፉት ጽሑፍ “ይህ በእውነት በጣም ያማል ሲሉ አጋርተዋል። ጦርነቱ በሚያዝያ ወር ከተቀሰቀሰ በኋላ በካርቱም እና በሌሎች ከተሞች የአየር ድብደባ እና የምድር ጦርነቶች ቀጥለዋል። ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሀገሪቱን ለቀው ለመሰደድ መገደዳቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል።

በናይል ወንዝ አቅራቢያ የሚገኘው ባለ 18 ፎቅ የነዳጅ ኩባንያ ሰማይ ጠቀስ ህንጻ በካርቱም ውስጥ በጣም ከሚታወቁ የከተማዋ ምልክቶች አንዱ ነው። ወይዘሮ ታግሬድ አብዲ የከተማዋን ገጽታ እንደሚገልፅ ተናግረው “እንዲህ ያለ ትርጉም የለሽ ውድመት” ያስቆጫል ስትል ተናግራለች። በመስታወት የተሸፈነው የሕንፃው ሾጣጣ መሰል መዋቅር በእሳት የተቃጠለበት ምክንያት ምን እንደሆነ እስካሁን አልታወቀም። በደረሰው ውድመት በሰው ላይ የአካል ጉዳትም ሆነ ሞት አልተመዘገበም።

በሱዳን ያለው ጦርነት የጀመረው በሚያዚያ አጋማሽ በሱዳን ጦር መሪዎች እና በፓራሚትሪ የፈጣን ድጋፍ ሰጭ ሃይሎችመካከል በተፈጠረ የስልጣን ሽኩቻ እንደነበር ይታወሳል። የግጭት ትንተናን የሚያቀርበው የሱዳን ዋር ሞኒተር በበኩሉ አርኤስኤፍ ቅዳሜ ዕለት በፍትህ ሚኒስቴር ውስጥ የሚገኘውን ፅህፈት ቤት ጨምሮ በሰራዊቱ ቁጥጥር ስር ያሉ ቦታዎች ላይ ጥቃት ማድረሱን ገልጿል። በጥቃቱ ምክንያት በርካታ የመንግስት ህንጻዎች መቃጠላቸው ተዘግቧል።

በከተማዋ ደቡባዊ ወረዳ የሚኖሩ ነዋሪዎች ሰራዊቱ የአር ኤስ ኤፍ ጦር ሰፈሮችን ኢላማ ያደረገበትን ጥቃት ከእንቅልፋቸው ሲነቁ "ትልቅ ድብደባ" እንደሰሙ ለኤኤፍፒ ተናግረዋል። የጤና ባለስልጣናት እሁድ እለት በካርቱም የሚገኙ ዋና ዋና ሆስፒታሎች እንዲሁም የዳርፉር ክልል ከአገልግሎት ውጪ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

ከካርቱም በስተደቡብ 400 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ኤል-ኦበይድ ከተማ ከባድ ውጊያ መካሄዱ ታውቋል። አርኤስኤፍ ዋና ከተማዋን ለመቆጣጠር ሲታገል የቆየ ሲሆን ወታደራዊ ኃይሉ በበኩሉ በአርኤስኤፍ ይዞታዎች ላይ የአየር ጥቃት በመፈፀም ቡድኑን ለማዳከም ያለመ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን የዳጉ ጆርናል ዘገባ ያሳያል።

በግጭቱ ወደ 7,500 የሚጠጉ ሰዎች እስካሁን የተገደሉ ሲሆን ከአምስት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከመኖሪያ ስፍራቸው ተፈናቅለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter

5.3k 0 8 29
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Blog Telegram Research 2019 Telegram Research 2021 Telegram Research 2023
Contacts
Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot