ማስጠንቀቂያ የኮንዶሚኒየም ዕጣ ለወጣላችሁ
ኮርፖሬሽኑ የጋራ መኖሪያ ቤት ባለቤቶች እስከ ጥቅምት 30/2017 ድረስ ወደ ቤታቸው የማይገቡ ከሆነ ውላቸው እንደሚቋረጥ ገለጸ!
በተለያዩ ጊዜያት በዕጣ እና በጨረታ ተላልፈው ነዋሪ ያልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ እስከ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ድረስ የቤት ባለቤቶቹ የማይገቡበት ከሆነ፤ ውሉ ተቋርጦ ቤታቸው በዕጣ ወይ በሽያጭ ለሌላ ነዋሪ እንደሚተላለፍ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ።
ኮርፖሬሽኑ በተለያዩ ጊዜያት ገንብቶ በዕጣ እና በጨረታ ያስተላለፋቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ እስከ አሁን ነዋሪ ባለመግባቱ ምክንያት፤ በመኖሪያ ቤቶቹ ውስጥ የተለያዩ ሕገ ወጥ ተግባራት እየተፈጸሙ እንደሚገኝ ገልጿል።
በመሆኑም ነዋሪ ያልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ እስከ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ድረስ ባለቤቶቹ እንዲገቡ ኮርፖሬሽኑ ጥብቅ ማሳሰቢያ አስተላልፏል።
የቤት ባለቤቶቹ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ወደ ቤቶቹ የማይገቡ ከሆነ፤ የሽያጭ ውላቸው ተቋርጦ በዕጣ እና በሽያጭ ለሌላ ነዋሪ የሚተላለፉ መሆኑንም ኮርፖሬሽኑ ገልጿል።
@Addis_Reporter