የሶማሊያ የቀድሞ መሪ ሀሰን ሼክ መሀሙድ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ
የሶማሊያ የቀድሞ መሪ ሀሰን ሼክ መሀሙድ ለሀገሪቱ የፓርላማ አባላት ብቻ ክፍት በሆነው የመጨረሻ ድምጽ አሰጣጥ ሂደት ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል። ከ 2017 ጀምሮ በስልጣን ላይ የሚገኙትን የወቅቱ ፕሬዝዳንት መሀመድ አቡዳላሂ ፋርማጆ በምርጫው ተሸንፈዋል።እ.ኤ.አ ከ2012 እስከ 2017 በፋርማጆ ከመሸነፋቸው በፊት ሼክ መሀሙድ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ነበሩ።
ምርጫው በፀጥታ ስጋት ምክንያት በሶማሊያ 328 የፓርላማ አባላት ብቻ ተገድቦ የተከናወነ ሲሆን ከመካከላቸው አንድ የምክር ቤቱ አባል ድምጽ አልሰጡም። በምርጫው ማሸነፋቸው የታወጀው መሀሙድ 214 ድምፅ ያገኙ ሲሆን ተቀናቃኛቸው ፋርማጆ 110 ድምፅ አግኝተዋል። ሶስት የፓርላማ አባላት በምርጫው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ላይ ስህተት በመፍጠራቸው ድምፁ ውድቅ ሆኗል።
መሀሙድ ቃለ መሃላ የፈፀሙት የመጨረሻው ውጤት ከተገለጸ በኋላ ሲሆን ፣በመዲናዋ የሚገኙ ደጋፊዎቻቸው በደስታ ጩኸት ያሰሙ ሲሆን በአየር ላይ በደስታ ሲተኮስ እንደነበር ተሰምቷል። ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት በስልጣን ላይ ይቆያሉ።ድምፅ በሚሰጥበት ወቅት በአካባቢው ፍንዳታ ይሰማ የነበረ ሲሆን ፖሊስ ግን በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ገልጿል።
ተመራጩ ፕሬዝዳንት መሀሙድ 3.5 ሚሊዮን ሶማሊያውያን ለከፋ የረሃብ አደጋ እንዲጋረጡ ያደረገውን የድርቅ ተፅእኖ መቋቋም የመንግስታቸው ዋንኛ ፈተኛ ይሆናል።የሶማሊያን ግዛት ከአልሸባብ እጅ መንጠቅ ሌላኛው ፈተና ሲሆን ቡድን ሰፊውን የሀገሪቱ ክፍል መቆጣጠሩን እንደቀጠለ ይገኛል። በሞቃዲሾ እና በሌሎችም ቦታዎች ተደጋጋሚ ጥቃቶችን እየፈፀመ ነው።
@Addis_Reporter