የሰሜን ኮሪያ መሪ የኮቪድ ወረርሽኝን ለመግታት ወታደራዊ ትዕዛዝ አስተላለፉ
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ የመድኃኒት አቅርቦት እንዲረጋጋ ወታደራዊ ትእዛዝ መስጠታቸውን በመንግስት የሚተዳደረው የኮሪያ ማዕከላዊ የዜና አገልግሎትዘግቧል። ሰሜን ኮሪያ ባለፈው ሳምንት እንቅስቃሴ የሚከለክል ህግ ካወጁ ከቀናት በኋላ ፒዮንግያንግ ለመጀመሪያ ጊዜ የኮቪድ ወረርሽኝ እየተዋጋች መሆኑን አስታውቃለች።
የህክምና ባለማያዎች ቫይረሱ ውስን የህክምና መሳሪያ አቅርቦት እና የቫይረሱ ስርጭት ለመግታት ክትባት መርሃ ግብር ባልነበራት ሀገር የወረርሽኙ መዛመት የከፋ ሊሆን እንደሚችል ስጋታቸውን ሰንዝረዋል ። በሰሜን ኮርያ 392,920 ሰዎች የትኩሳት ምልክት እንደታየባቸው ሲገለፅ ስምንት ሰዎች መሞታቸውን የሀገሪቱ የዜና ወኪል ዘግቧል።
የቫይረሱ ምልክት ከታየባቸው ሰዎች መካከል ለምን ያህሉ የኮቪድ ምርመራ እንደተደረገ አልተዘገበም። ሰሜን ኮሪያ የኮቪድ ክትባቶች፣ የፀረ-ቫይረስ ህክምና መድሃኒቶች ወይም የጅምላ የመመርመር አቅም የላትም። የኪም ጆንግ ኡን አስተዳደር ከጥቂት ቀናት በፊት ሀገሪቱ ከኮሮና ቫይረስ ነፃ መሆኗን አጥብቆ መናገሩ ይታወሳል።
@Addis_Reporter