የአማራ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ውስጥ በሚኖሩ ንጹሃን አማራዎች ላይ በደረሰው ጭፍጨፋ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለጹ።
አሸባሪው የሸኔ ቡድን ዛሬም ሰላምን በሚሻው ንጹሃን ሕዝባችን ላይ የሞት ጽዋን የሚያዘንብ የጥፋት መልአክ ሁኗል ያሉት አቶ ግዛቸው ከማንኛውም የሰው ዘር ጋር በሰላም መኖርን፣ ሠርቶ መበልጸግንና አግኝቶ መደሰትን ብቻ የሚሻው የአማራ ሕዝብም ሆነ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ወገኖች ሰላምን በማይሹ የሀገርና የሕዝብ ጠላቶች እንዲህ የመጠቃታቸው ብቸኛው ግብ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ለማንበርከክ አልመው መሆኑን ገልጸዋል።
ጠላቶቻችን በውስጥ አጀንዳ ተሸካሚዎቻቸውም ሆኑ በውጭ የእጅ አዙርና የውክልና ጦርነት ፈጻሚዎቻቸው ለሚያደርሱብን ጥቃት ምንም ምክንያት ወይም ምንም አይነት ስም ይስጡት ዋነኛ ዒላማው አማራን ከሌሎች ብሔሮች ለይቶ በማጥቃት ኢትዮጵያውያንን አንድ በአንድ ነጥሎ የመብላት ስልታዊ መንገድ እንደሆነም አስረድተዋል።
በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ውስጥ በሚኖሩ ንጹሃን አማራዎች ላይ በደረሰው ጭፍጨፋ ለመላው ሕዝብ መጽናናትን የተመኙት ቢሮ ኃላፊው ዛሬም ሆነ ነገ የዚህ ችግር ብቸኛው መፍትሔ የሕዝባዊ አንድነት ጠላት፣ በጋራ ሠርቶ የማደግ ደመኛ እንዲሁም ፀረ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት የሆኑ ሁሉንም ኃይላት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንደ ሕዝብ በአንድነት ታግሎ ማሸነፍ ሲቻል ብቻ መሆኑን አሳስበዋል።
በሕዝባቸው ላይ በደረሰው መከራ የተሰማቸውን መሪር ሀዘን ገልጸው ለመላው ሕዝባቸው ልባዊ መጽናናትን የተመኙት አቶ ግዛቸው ይህን መሰል ጥቃቶችን በመፈጸም መሪር ሀዘን ላይ የሚጥሉንን ጠላቶቻችንን ታግሎ ለማሸነፍና ለዚህ ጉዳይ ከሥሩ መፍትሔ ለመፈለግ ደግሞ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድ ድምጽ ይህን ድርጊት በመቃወም የመፍትሔው አካል ሊሆን ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
@Addis_Reporter