የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተግባራዊ መሆን ጀመረ!
የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሸከርካሪዎችን ብቻ ተጠቃሚ የሚያደርገው የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ከዛሬ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ከ160 ሺሕ በላይ ተሽከርካሪዎች ላይ ተግባራዊ መሆን መጀመሩን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሸከርካሪዎች የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ ለመሆን አስፈላጊ መረጃዎችን በመስጠት በኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከላት በኩል ምዝገባ ማድረጋቸውን ሚኒስቴሩ አስታውሷል።
የብሔራዊ የታለመለከት የነዳጅ ድጎማን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ በኢትዮ ቴሌኮም በኩል መተግበሪያ በልፅጎ አስተማማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።
በዚህም መሠረት በቴሌ ብር በኩል አገልግሎቱን ለማግኘት የተመዘገቡ ከ160 ሺሕ በላይ ተሸከርካሪዎች ከዛሬ ጀምሮ መተግበሪያውን በመጠቀም ይስተናገዳሉ ተብሏል።
የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ዓመታዊ የነዳጅ ፍጆታ ተቀራራቢ የሊትር መጠን ግምት በጥናት መለየቱና እያንዳንዱ ተሸከርካሪ የሚጠቀመውን የነዳጅ መጠን ያገናዘበ ስሌት በመቀመጡ ተሽከርካሪዎቹ ያለብክነት የታለመ የነዳጅ ድጎማን ጥቅም ላይ እንዲያውሉ የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።
በዚህም መሰረት
- ባለሦስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) በቀን 7 ሊትር
- መለስተኛ የከተማ ታክሲ (ላዳ) በቀን 25 ሊትር
- ሚኒባስ ታክሲ በቀን 65 ሊትር
- መለስተኛ አውቶብስ በቀን 94 ሊትር
- የከተማ አውቶብስ በቀን 102 ሊትር
- የሕዝብ አውቶብስ በቀን 25 ሊትር
- ሀገር አቋራጭ አውቶብስ በቀን 65 ሊትር ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ሚኒስቴሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።
@Addis_News