Addis Admass


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


የአዲስ አድማስ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
=====
አዲስ አድማስ https://bit.ly/2V1zyZQ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2V0I6jx
ትዊተር↠ https://bit.ly/33fDhaP
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/2JgeCvG
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3q2hXiv
የእርስዎና የቤተሰብዎ

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


ልጆቻችንን እንዴት በበይነመረብ (Internet) ከሚፈጸም ትንኮሳ መከላከል እንችላለን?


የሳይበር ትንኮሳ (cyber_bulling) ስልክንና ኮምፒውተርን የመሳሰሉ የዲጂታል መሳሪያዎችን በመጠቀም ሆን ተብሎ በተደጋጋሚ በማህበራዊ ሚዲያዎች፣ በበይነ-መረብ፣ በአጭር የጽሁፍ መልዕክትና በጌሞች አማካኝነት የሚፈጸም የሳይበር ጥቃት ነው።

ወንጀሉ የሌሎችን ስም በክፉ በማንሳት፣ አካላዊ ማስፈራራት በማድረግ፣ ሃሰተኛ ወሬዎችን በማሰራጨትና የአንድን ሰው ምስል ኦንላይን በመለጠፍ ይፈጸማል። የሳይበር ትንኮሳ በታዳጊ ልጆችና በጉርምስና ዕድሜ ላይ ባሉ ወጣቶች በስፋት የተለመደ ሲሆን፤ የፒው የጥናት ማዕከል ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመለክተው፤ ከግማሽ በላይ የሚሆኑ ታዳጊዎች በኦንላይን ለሚፈጸም ትንኮሳ ተጋላጭ ናቸው።

በመሆኑም ልጆቻችንን በበይነመረብ ከሚደርስባቸው ትንኮሳዎች ለመከላከል የሚከተሉትን አማራጮች መጠቀም ይገባናል፦

የልጆቻችንን አካውንት ደህንነት በየጊዜው መፈተሽና የይለፍ-ቃሎቻቸውን ለሌሎች እንዳይሰጡ ማስተማር፤

የልጆቻችንን የዩቲዩብ፣ የጌምና ሌሎች ሳይቶች ደህንነት የሚያረጋግጡ ቅንብሮችን(setting) ማስተካከል፤

የልጆቻችንን የባህሪይ ለውጦች በየጊዜዉ መከታተል፤ የእርምት እርምጃ መውሰድ፤

ልጆቻችን የሚጠቀሟቸውን የማህበራዊ ሚዲያ፣ ኢ-ሜይልና የጌም ማቅረቢያ ገጾችን መፈተሽ፤


(INSA)


የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል የብራንድ አምባሳደር ሄኖክ ስዩም ምን አለ?

"ዛሬ የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል (Gullele Botanic Garden) የብራንድ አምባሳደርነት ሹመቴን በይፋ ተቀብያለሁ። ይፋ በተደረገበት ወቅት ሀገር ውስጥ ስላልነበርኩ ዛሬ በማዕከሉ በተዘጋጀ ሥነ ሥርዓት የአደራ ሹመቴን ተቀብያለሁ። አንድ የ Zeno አባባል አለ። "The goal of life is living in agreement with nature.” የሚል። ሌላ ግብ ለሌለኝ ለእኔ እንዲህ ያለው አደራ ድካም ብቻ አይደለም፣ ሽልማትም ነውና ስለሁሉም አመሰግናለሁ።"


የመገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት የሚዲያ ባለሙያዎችን የመመዝገብም ሆነ
የሙያ ማረጋገጫ የመስጠት ተግባርና ኃላፊነት አልተሰጠውም ተባለ


የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት፣ ለጋዜጠኞች የሙያ ማረጋገጫ ለመስጠትና የጋዜጠኞች ምዝገባ ለማከናወን ውይይትና እንቅስቃሴ መጀመሩን ተከትሎ፤ የተለያዩ የሚዲያ ተቋማት፣ ጋዜጠኞችና የሙያ ማህበራት ጉዳዩን በተመለከተ የሕጋዊነት ጥያቄና ስጋቶቻቸውን በማቅረብ ላይ መሆናቸውን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን አስታውቋል።

ባለሥልጣኑ ባወጣው መግለጫ፤ የመገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ጋዜጠኞችን ወይም የሚዲያ ባለሙያዎችን የመመዝገብም ሆነ የሙያ ማረጋገጫ የመስጠት ተግባርና ኃላፊነት በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 አልተሰጠውም ብሏል።

በመሆኑም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን፣ ለዚህ የምክር ቤቱ ተግባር እውቅና እንደማይሰጥ አስታውቋል፡፡


በወንጀል ተጠርጠረው የታሰሩ ግለሰቦችን ለማስፈታት
50ሺ ብር ጉቦ የሰጠ እጅ ክፍንጅ ተያዘ


የካቲት 19 ቀን 2017 ዓ፣ም ከምሽቱ 3፡00 ላይ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 አስተዳደር አካባቢ አሽከርካሪውን ጨምሮ አራት ወንጀል ፈፃሚዎች የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 1-62976 ኦ/ሮ ተሽከርካሪን በመጠቀም ግምቱ 149 ሺ ብር የሚወጣ አልትራ 23 ሞባይል ቀምተው ቢያመልጡም፣ ፖሊስ ባደረገው ክትትል ወንጀል ፈፃሚዎቹ በቁጥጥር ስር ያውላቸዋል፡፡


ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹንና የተሰረቀውን ንብረት የሚገዛን አንድን ግለሰብ ይዞ ምርመራውን በቀጠለበት ሁኔታ የምርመራ ሂደቱን ለማደናቀፍ እንዲሁም የፍትህ ስርዓቱን ለማዛባት ለጉዳዩ መርማሪ 50 ሺ ብር ጉቦ ሲሰጥ መርማሪ ፖሊሱ በሰጠው መረጃ እጅ ከፍንጅ ተይዟል።


ግለሰቡ ጃንክ በሚል ቅፅል ስም በደላላነት እንደሚታወቅና ከዚህ በተጨማሪ የተሰረቁ እቃዎችን የሚገዛ መሆኑን ፖሊስ ባደረገው ምርመራ ማረጋገጡን ጠቁሞ፣ የተሰጣቸውን ኃላፊነት ጠንቅቀው የሚያውቁ የፖሊስ አመራርና አባላትን ለማፍራት ተቋሙ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።


ለምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢና ሁለት አባላት
እጩዎችን እንዲጠቁም ለህብረተሰቡ ጥሪ ቀረበ


ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢና ሁለት አባላት እጩዎችን ከነገ ጀምሮ እንዲጠቁም የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስራ አመራር ቦርድ አባላት መልማይ ኮሚቴ ለህብረተሰቡ ጥሪ አቀረበ።

የእጩዎች ጥቆማ መስጫ ጊዜ ከነገ ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 21 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚቆይም ኮሚቴው አስታውቋል፡፡

ባለፈው ሳምንት መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ.ም. ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ ስምንት አባላትን የያዘ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አባላት ዕጩ መልማይ ኮሚቴ መሰየማቸው ይታወሳል፡፡

ኮሚቴው ከተቋቋመ አንስቶ የዕጩ ምልመላ ሥራውን ለመምራት የሚያስችሉ የውስጥ አሠራር መመሪያ ማጽደቅና የመመልመያ የጊዜ ሰሌዳ ማዘጋጀት የመሳሰሉ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን የኮሚቴው ሰብሳቢ ቀሲስ ታጋይ ታደለ ተናግረዋል።

ቀሲስ ታጋይ እንደገለጹት፤ እነዚህን የምርጫ ቦርድ አመራሮች ለመተካት ሂደት የተጀመረው የሥራ ዘመናቸው የማጠናቀቂያ ጊዜ በመቃረቡ ነው። ዕጩ ጥቆማ የሚደረግባቸው የቦርድ አባላት፤ ምክትል ሰብሳቢው አቶ ውብሸት አየለ እንዲሁም ዶ/ር አበራ ደገፉና ብዙወርቅ ከተተ ናቸው።


10 ሰላማዊ ሰዎች በታጠቁ ኃይሎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን፣ ጃርዳጋ ጃርቴ ወረዳ ውስጥ 10 ሰላማዊ ሰዎች በታጠቁ ኃይሎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ።

በወረዳው ሀሮ ሃቡ በተባለች ቦታ እሑድ ዕለት ምሽት አንድ ሰዓት ተኩል ገደማ ታጣቂዎቹ ሰዎችን በአንድ ቦታ ሰብስበው ጥቃቱን ማድረሳቸውንም አመልክተዋል፡፡ ለጥቃቱም በአካባቢው በፋኖ ስም ተደራጅተው ይንቀሳቀሳሉ ያሏቸውን ኃይሎች ተጠያቂ አድርገዋል።

ዶቼ ቬለ የቀረበውን ክስ አስመልክቶ በቡሬ ዙሪያ ወረዳ ይንቀሳቀሳሉ የተባሉ የፋኖ ኃይሎችን አስተያየት ለማካተት ያደረገው ጥረት እንዳልተሳካለት ያመለከተ ሲሆን፤ የአካባቢውን ባለሥልጣናትም በስልክ ማግኘት አልተቻለም ብሏል።

ከትናንት በስቲያ በደረሰው ጥቃት ሕይወታቸው ያለፈ ወገኖች ስርዓተ ቀብር በትናንትናው ዕለት በጀምላ መፈጸሙን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በጃርዳጋ ጃርቴ ወረዳ በተለያዩ ስሞች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በሚፈጽሙት ጥቃት የሰው ሕይወት ህልፈትን ጨምሮ የንብረት ውድመትም ሲያደርስ ቆይቷል። እንዲያም ሆኖ በ2016 ዓ.ም የታጣቂዎች ጥቃት ቀንሶ እንደነበር ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡


በዘጠኝ ቀናት ከ7 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎች ላይ ድንገተኛ ፍተሻ ተካሄደ

• በአሽከርካሪዎችና ተሽከርካሪዎች ላይ በርካታ ጉድለቶች ተገኝተዋል

በዘጠኝ ቀናት ውስጥ 7 ሺህ 051 ተሽከርካሪዎች ላይ ድንገተኛ ፍተሻ መካሄዱን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ገልጿል።

በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴርና ባለድርሻ አካላት ቅንጅት የተካሄደው የተሽከርካሪ የመንገድ ላይ ክትትልና ድጋፍ አፈጻጸም ተገመግሟል።

22 የተሽከርካሪ ቴክኒክ ምርመራ ተቋማት፣ 31 የከተማ ትራንስፖርት ተርሚናሎች እንዲሁም 9 የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ድንገተኛ ፍተሻ መካሄዱ በግምገማው ተገልጿል።

ለዘጠኝ ቀናት በአዲስ አበባና በሸገር ከተማ በተለያዩ መንገዶች በተካሄደው የመንገድ ላይ ክትትልና ድጋፍም፣ በአሽከርካሪዎችና በተሽከርካሪዎች ላይ በርካታ ጉድለቶች መታየታቸውን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ደኤታ አቶ በርኦ ሀሰን ገልፀዋል።

በተደረገው ክትትልና ድጋፍም የተሽከርካሪ የቴክኒክ ብቃት ሁኔታ ሳያሟሉ ቦሎ ያላቸው ተሽከርካሪዎች መኖራቸው፣ እንደ ሀገር ወጥ የሆነ ታሪፍ ቢኖርም፣ ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ መኖራቸው ከተገኙ ጉድለቶች መካከል ተጠቅሰዋል፡፡

በተጨማሪም ተሽከርካሪው ከመጫን አቅሙ በላይ ትርፍ ጭነት የሚጭኑ አሽከርካሪዎች መኖራቸውና በአንዳንድ አሽከርካሪዎች ተደራራቢ የትራፊክ ቅጣት ያላቸው መሆኑም ተገምግሟል፡፡
(AMN)


የሐረር ከተማ የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ
ፕሮጀክት ግንባታ እየተጓተተ ነው ተባለ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢ እና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ በሐረር ከተማ እየተገነባ ያለው የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ፕሮጀክት አፈጻጸም እየተጓተተ መሆኑን ጠቁሟል፡፡
ቋሚ ኮሚቴው በሐረር ከተማና ዙሪያዋ ሲያካሂድ የነበረውን የመስክ ምልከታ በማጠናቀቅ ለአካባቢው አመራሮች አጠቃላይ ግብረ መልስ ማቅረቡ ተጠቁሟል፡፡
የከተማው የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ፕሮጀክት ግንባታ አፈጻጸም 5 በመቶ ብቻ መሆኑ እጅግ አሳሳቢ ነው ያለው ቋሚ ኮሚቴ፤ ኮንትራክተሩ ያለበትን ችግር ቀርፎ ፕሮጀክቱን በፍጥነት እንዲያንቀሳቅስ አቅጣጫ መስጠቱ ተዘግቧል።
በከተማው የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ስፍራዎች ከከተማው ማስተር ፕላን አንጻር በተገቢው ርቀት መቀመጣቸውን እንዲሁም ሰፊ የአረንጓዴ ልማት ስራዎች መከናወናቸውን ቋሚ ኮሚቴው እንደ ጠንካራ ጎን ማንሳቱ ተጠቁሟል።
የቋሚ ኮሚቴው ቡድን መሪ አቶ ወልደየስ ደበበ፤ የአረንጓዴ ልማት ስራው የሚበረታታ ቢሆንም፣ የተደራጀ የአረንጓዴ አሻራ ማዕከል አለመኖሩን እንዲሁም የከተማው ሜትሮሎጂ ጣቢያ መሳሪያዎች ማርጀታቸውንና ከጥቅም ውጭ የሆኑም እንዳሉ ጠቅሰው፣ በአዲስ መተካት እንደሚያስፈልጋቸው ጠቁመዋል።
የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አሪፍ መሃመድ በበኩላቸው፤ የቆሻሻ አወጋገድን ከምንጩ በመለየት ስርዓቱን ስለ ማዘመንና መልሶ መጠቀም አስፈላጊነት አስረድተዋል።
የክልሉ ውሃና ፍሳሽ ሃላፊ ከኮንትራክተሩ ጋር የተያያዙ ችግሮችን ከሚመለከታቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጋር በመነጋገር ለመፍታት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
(ዜና ፓርላማ)


አቶ ጌታቸው ረዳ ያስተላለፉት መልዕክት


"የሁለት ዓመት የጊዜያዊ መስተዳድር ሀላፊነቴን በይፋ አስረክቤያለሁ። የትግራይ ህዝብ ላሳየኝ ክብርና ድጋፍ ላቅ ያለ ምስጋና አለኝ። ህዝባችን ወደ ተሻለ ሁኔታ እንዲመለስ፣ ሁለንተናዊ ፍላጎቱ እንዲሟላለት የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ። የሰላምና የለውጥ ፍላጎት እንዳይሰናከል ትግላችንን እናጠናክር። ክብረት ይስጥልኝ!"


እኒህ ደሴቶች ሰዎች አይኖሩባቸውም። ፔንግዊን እና ሲል የተባሉ የባሕር እንስሳት መገኛ ናቸው። የአሜሪካ የንግድ ሚኒስቴር፣ ደሴቶቹ ላይ ታሪፍ የተጣለበትን ምክንያት አብራርቷል። ኸርድ ኤንድ ማክዶናልድ ደሴቶች ላይ ታሪፍ የተጣለው ሀገራት በደሴቶቹ በኩል ዕቃ የጫነ መርከብ ይዘው እንዳያልፉ ነው ሲሉ ሚኒስትሩ ሀዋርድ ላትኒክ ተናግረዋል።

ደሴቶቹ ከአውስትራሊያ 4 ሺህ ኪሎሜትር ርቀት ላይ ይገኛሉ። የአውስትራሊያ ባለሥልጣናት ደሴቶቹ ላይ ታሪፍ በመጣሉ መገረማቸውን አልደበቁም። የአውስትራሊያ ንግድ ሚኒስትር ዶን ፋሬል፤ "መቼም ይህ ውሳኔ በስህተት የተላለፈ ነው" ሲሉ ኤቢሲ ኒውስ ለተሰኘው ጣቢያ ተናግረዋል። አክለውም፤ "የችኮላ ሥራ" መሆኑን ያሳያል ብለዋል።

በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር የሆነው ሲቢኤስ የአውስትራሊያ አካል የሆኑት ሰው አልባ ደሴቶች ላይ እንዴት ታሪፍ ሊጣል ቻለ ሲል ጠይቋል። "አንዳንድ ሥፍራዎችን ዝርዝር ውስጥ ካላካተትን አሜሪካ ላይ የበላይነት መቀዳጀት የሚፈልጉ ሀገራት በዚያ በኩል ሊያልፉ ይችላሉ" ሲሉ ላትኒክ ምላሽ ሰጥተዋል።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበርካታ የዓለም ሀገራት ላይ ታሪፍ መጣላቸውን ተከትሎ ባለፈው አርብ የአሜሪካ የአክሲዮን ገበያ ከአውሮፓውያኑ 2020 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ5 በመቶ በላይ አሽቆልቁሏል።

ሀገራት በመርከብ አማካይነት የንግድ ልውውጥ የሚያደርጉ ሲሆን ከአንድ ወደብ ወደ ሌላኛው የሚያደርጉት ጉዞ ትራንስሺፕመንት ይባላል። ፒው ቻሪቴብል የተባለው የሕዝብ ፖሊሲ ተቋም "አንዳንድ የጥፋት ኃይሎች ይህን ሥርዓት ሊበዘብዙት ይችላሉ" ይላል።

መንግሥታዊ ያልሆነው ድርጅት እንደሚለው፤ በመቶ ሚሊዮን ዶላሮች የሚያወጡ ቱና እና ሌሎች ዓሳዎች በሕገ-ወጥ መንገድ ይተላለፋሉ።
ከኸርድ ኤንድ ማክዶናልድ ደሴቶች ወደ አሜሪካ ምን ያህል ምርት እንደሚጓጓዝ የሚታወቅ ነገር የለም።የዓለም ባንክ መረጃ እንደሚያሳየው፤ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ከደሴቶቹ ወደ አሜሪካ የተጋዘው ምርት መጠን አነስተኛ የሚባል ነው። በ2022 አሜሪካ 1.4 ሚሊዮን ዶላር የሚሆን ዋጋ ያለው ሰው አልባ "ማሽን እና የኤሌክትሪክ ዕቃ" ከደሴቶቹ አስጭናለች።

በትራምፕ የታሪፍ መዝገብ ላይ ከተካተቱ ሥፍራዎች መካከል ብሪቲሽ ኢንዲያን የውቅያኖስ ግዛት ይገኝበታል። ይህ ሥፍራ በወታደሮች የተያዘ ሲሆን፤ ለመጎበኘት ፈቃድ ማግኘት ያስፈልጋል።

(ቢቢሲ)


አሜሪካ ሰዎች በማይኖሩባቸው ደሴቶች ሳይቀር ታሪፍ ጥላለች

በመላው የዓለም ሀገራት ላይ ታሪፍ የጣሉት የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ አንድ አስደናቂ ውሳኔ አሳልፈዋል። አሜሪካ ታሪፍ ከጣለችባቸው ሥፍራዎች መካከል ኸርድ ኤንድ ማክዶናልድ ደሴቶች ይገኙበታል።

⬇️⬇️


ዛሬ በብሔራዊ ቴአትር የጽዳት ሥራ ተከናወነ

ብሐራዌ ቴአትር ዛሬ በፌስ ቡክ ገጹ የጽዳት ሥራ መከናወኑን አስመልክቶ ያጋራው መረጃ እንዲህ ይላል፡-

**

በየወሩ መጨረሻ የጽዳት ዘመቻ ማድረግ ባህልና መልካም ልማድ እንዲሆን አካባቢንና ተቋምን ማጽዳት በብሔራዊ ቴአትር ቀጥሏል፡፡

በዚህም መሰረት ዛሬ መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡30 ጀምሮ የጽዳት ሥራ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ሠራተኞች ለ3ኛ ጊዜ ተከናውኗል፡፡

የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም በየወሩ የሚቀጥል የመጀመሪያውን የጽዳት ዘመቻ ያስጀመሩት የቀድሞው ዋና ዳይሬክትር አቶ ማንያዘዋል እንደሻው እንደሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፤ በዕለቱ "እንዲህ ዓይነት ሥራዎች በአስገዳጅ ሁኔታ ሳይሆን እንደ እናንተ ባሉ በጎ ፍቃደኞች፣ለተቋማቸውና ለአካባቢያቸው በሚቆረቆሩ ሰዎች ሲሆን ውጤቱ ያመረ ይሆናል፡፡ በየወሩ መቀጠል አለበት" ማለታቸው የሚታወስ ነው፡፡ ይህ የጽዳት ዘመቻ በየአንዳንዱ ሰራተኛ ባህልና ልማድ እንዲሆን ይጠበቃል፡፡


ጄኔራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንትነትን ሲረከቡ የፈረሙት የትግራይ ክልል አካታች ጊዜያዊ አስተዳደር የተልዕኮ አፈጻጸም የቃል ኪዳን ሰነድ


የትራምፕ የታሪፍ ዛቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል

• በቻይና ላይ ተጨማሪ 50% ታሪፍ ለመጣል ዝተዋል

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተጨማሪ 50% ታሪፍ ቻይና ላይ ለመጣል የዛቱ ሲሆን፤ ቻይና እስከ መጨረሻው ለመታገል ቃል ገብታለች፡፡

ቻይና ይህንን ተጨማሪ የ50% ታሪፍ ዛቻ፣ 'ከስህተት በላይ የሆነ ስህተት' ስትል ነቅፋዋለች፡፡

የቻይና ንግድ ሚኒስቴር የአሜሪካን ውሳኔ ፈጽሞ እንደማይቀበል ያስታወቀ ሲሆን፤ እስከ መጨረሻው ለመዋጋትም ቃል ገብቷል፡፡

ሁሉም የታሪፍ እቅዶች እንዲወገዱና የአሜሪካና ቻይና ልዩነቶች በውይይት እንዲፈቱ ሚኒስቴሩ ጠይቋል።

ባለፈው ሳምንት ትራምፕ ቻይና ላይ ለጣሉት ታሪፍ፣ በምላሹ ቻይና 34% ታሪፍ እንደምትጥል ያስታወቀች ሲሆን፤ ትራምፕም ቻይና የጣለችውን የአጸፋ ታሪፍ እስከ ማክሰኞ ድረስ ካላነሳች 50% ተጨማሪ ታሪፍ እንደሚጥሉ ዝተዋል፡፡

ትራምፕ የጣሉትን ታሪፍ በተመለከተ በአሜሪካ የቻይና ኤምባሲ፤ "የኢኮኖሚ ጭቆና ነው፤መብታችንን ከማስጠበቅ ወደ ኋላ አንልም" ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ትራምፕ በራሳቸው ማህበራዊ ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት፤ "ከቻይና ጋር ስለ ታሪፍ እንድንነጋገር የተያዘው ዕቅድ ተሰርዟል" ብለዋል፡፡


በትላንትናው ዕለት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት በመሆን ለሁለት ዓመታት ያገለገሉትን አቶ ጌታቸው ረዳን በምስጋና ያሰናበቱት ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፤ በዛሬው ዕለት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የፕሬዚዳንትነት ርክክብ ሥነስርዓት መካሄዱን በትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል፡፡

"ባለፈው አንድ ወር ገደማ የኢትዮጵያን ሕገ መንግሥት፣ የፕሪቶሪያን ስምምነትና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡን ምክር በማከል ሰፊ ውይይቶች ሲካሄዱ ቆይተዋል:: የአቶ ጌታቸው የሥልጣን ዘመን በሕጉ መሠረት ሲያበቃ የሚቀሩ ቁልፍ ሥራዎችን የሚያከናውን አካል፣ ጊዜያዊ መንግሥቱ መቀጠለ አለበት የሚል ድምዳሜ ከተያዘ በኋላ፣ ይሄንን ሽግግር ማን መርቶ ከግብ ሊያደርስ ይችላል? የሚሉ ውይይቶችን ስናደርግ ቆይተናል::" ብለዋል፤ጠ/ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፡፡

ዛሬ ስለተከናወነው የስልጣን ርክክብ ሥነስርዓት ሲገልጹም፤ "ዛሬ በይፋና በሰላማዊ መንገድ በአዲስ ባህል የሥልጣን ሽግግሩንና ቅብብሎሹን ለማካሄድ የተዘጋጀ ፕሮግራም አከናውነናል። ጄኔራል ታደሰ ባለፉት ሁለት ዓመታት የአቶ ጌታቸው ምክትል ሆነው ያገለገሉ ሰው ናቸው፡፡ ባለፉት ሁለት ዓመታት የነበሩ ድካሞችንና ጥንካሬዎችን በግልጽ የሚገነዘቡ ሰው ናቸው፡፡ አሁን ትግራይ ውስጥ ያለውን ክፍተት ሞልተው ወደፊት ሊወስዱ ይችላሉ የሚል እምነት በብዙ አካላት የታመነ ነው። የትግራይ ሕዝብ የጠማውን ሰላምና ልማት፣ እንደ ሌሎች ወንድሞቹ ወጥቶ የመግባት መሻት ስናሳካ፣ ለኢትዮጵያም ለአፍሪካም እጅግ ጠቃሚ የሆነ ነገር ሠርቶ ለማለፍ ታሪክ የሰጣቸውን ዕድል እንደሚጠቀሙበት ተስፋ አደርጋለሁ።" ብለዋል፤ጠ/ሚኒስትሩ፡፡


ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ክልል
ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ

"ታሪክ የሰጣቸውን ዕድል እንደሚጠቀሙበት ተስፋ አደርጋለሁ"

ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሆነው የተሾሙ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለት የሥልጣን ርክክብ ሥነስርዓት ተከናውኗል፡፡ ጄኔራል ታደሰ ወረደ ባለፉት ሁለት ዓመታት የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ማገልገላቸው ይታወቃል፡፡

⬇️⬇️








በኮንስትራክሽን ዘርፉ ችግር ፈቺ ጥናቶችን ለማካሄድ
የቲንክ ታንክ ግሩፕ መቋቋም አስፈላጊ ነው ተባለ


የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ዘርፍ የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ችግር ፈቺ ጥናቶችን የሚያካሂድ አሰላሳይ(ቲንክ ታንክ) ግሩፕ መቋቋም አስፈላጊ መሆኑ ተገለጸ።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ፣ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ አሰላሳይ ግሩፕ ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብን ለማዳበር ከከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል።

ቲንክ ታንክ ግሩፑ በኮንስትራክሽን ዘርፉ ችግር ፈቺ ጥናቶችን የሚያደርግና ተጨማሪ እሴቶችን የሚያበረክት የሙያተኞች ስብስብ እንደሆነ ቋሚ ኮሚቴው አስገንዝቧል።

የሚቋቋመው ቲንክ ታንክ ግሩፕ ህጋዊ እውቅና አግኝቶ የተለያዩ ጥናቶችን በማካሄድ በኮንስትራክሽን ዘርፉ ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት ያለመ እንደሆነም ቋሚ ኮሚቴው አስረድቷል።

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ዶ/ር እሸቱ ተመስገን፤ በኮንስትራክሽን ዘርፉ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍና የተሻለ እድገት ማስመዝገብ እንዲቻል የቲንክ ታንክ ግሩፑ መቋቋም አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸዋል። ማቋቋሚያ ረቂቁን የበለጠ ለማዳበር በቀጣይም ከባለድርሻ አካላት ጋር ተመሳሳይ የውይይት መድረኮች እንደሚካሄዱ ዶ/ር እሸቱ አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ ሀብታሙ ጌታቸው በበኩላቸው፤ ቲንክ ታንክ ግሩፑ ውጤት ተኮር ጥናቶችን ማካሄድ እንዲችል አደረጃጀቱ ነጻና ገለልተኛ ሊሆን እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ግሩፑ የተቋቋመበትን ዓላማ በማይጥስ መልኩ የራሱን ገቢ ሊያመነጭ ይገባል ያሉት ተሳታፊዎቹ፤ በአባልነት የሚካተቱ ግለሰቦችም ሙሉ ጊዜያቸውን ለተቋሙ የሚያውሉ መሆን እንዳለባቸው አመላክተዋል።

20 last posts shown.