Al-Afia Schools‘ Community


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Education


We promote quality education that shapes generations

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Education
Statistics
Posts filter






ለአል- አፊያ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ለቤተል ቁ-1 እና 2 ቅርንጫፍ ተማሪዎች በሙሉ

ጉዳዩ:- ሞዴል ፈተና የሚሰጥበት ቀን ስለ ማሳወቅ ይሆናል ::

ውድ ወላጆች ከላይ በርዕሱ እንደተገለፀው የ 8ኛ ክፍል ሚያዝያ 15 እና 16 እንዲሁም የ 6ኛ ክፍል ደግሞ ከሚያዝያ 15-17 የ 2ኛ ዙር በአዲስ አበባ ት/ቢሮ የተዘጋጀ ሞዴል ፈተና ይሠጣል። ስለሆነም ወላጆች ልጆቻችሁን በዚህ በዕረፍት ቀናት ሳይዘናጉ ለሞዴል ፈተና እንዲዘጋጁ አስፈላጊውን ድገፍና ክትትል እንድታደርጉ ለማሳሰብ እንወዳለን ::




ለአል-ዓፊያ ት/ቤት 11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪ ወላጆች

ጉዳዩ፡- የስኮላርሺፕ ትምህርት ይመለከታል

ውድና የተከበራችሁ ወላጆች Icon Scholar Academy  የተባለ ድርጅት በተለያዩ የአውሮፓ፣ የአሜሪካ እና ሌሎች አገሮች ላይ የስኮላርሺፕ ትምህርት ዕድል ያመቻቻል፡፡
በመሆኑም ተቋሙ የት/ቤታችን ተማሪዎች አወዳድሮ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያመቻቸልን ስለሆነ ለወላጆች ዓርብ 04/08/2016 ከጠዋቱ 4፡00 - 5፡00 ገለፃ ይደረጋል፡፡

ወላጆች በተጠቀሰው ሰዓት ት/ቤት ግቢ በመገኘት ተማሪዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ቅድመ መረጃ እንድታገኙ ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡
                   ት/ቤቱ




ለሁሉም አል-አፊያ ት/ቤቶች ወላጆች በሙሉ

ውድ ወላጆች ከ ማክሰኞ ፣ ሚያዝያ ዐ1 - 04/2016 በኢደል- አልፈጥር በዓል ምክንያት ትምህርት የማይኖር መሆኑን እየገለፅን ከሰኞ፣ ሚያዚያ 07/ 2016 ጀምሮ በመደበኛው ፕሮግራም መሠረት ትምህርት የሚጀመር መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን::




Forward from: የአል-ዓፊያ ት/ቤቶች ማህበረሰብ_Al-Afia Community
Dear Parents and Guardians, Greeting and best wishes.

I hope this message finds you well. We will have 1st semester parent teacher conference on Friday, March 01/2024.

As part of our commitment to fostering a strong partnership between our valued parents and schools, we are pleased to announce a series of informative discussions about your students’ academic performance across the semester with teachers and welcoming your comments, suggestions, insights & feedback are crucial in shaping the educational experience of our schools for your child's educational journey.

Wonder Reminding You… Friday, March 01 /2024 Parent Teacher Conference day.

Looking forward to seeing you!

Best Regards,
Mohammed Muktar
Education Manager












Forward from: የአል-ዓፊያ ት/ቤቶች ማህበረሰብ_Al-Afia Community
በአዲስ አበባ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በሰኔ መጀመሪያ ላይ እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ

ይህንንም ተከትሎ በዘንድሮ ዓመት በአዲስ አበባ ለስድስተኛ ክፍል 86 ሺህ 691 ተማሪዎች እንዲሁም ለስምንተኛ ክፍል 88 ሺህ 28 ተማሪዎች በከተማ አቀፍ ፈተናው ይቀመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።  

ተማሪዎች ለፈተናው ብቁ እንዲሆኑ በሥነ-ልቦና የማዘጋጀት፣ ከኩረጃ ነጻ የሆነ አስተሳሰብ እንዲይዙ እና በራስ መተማመን እንዲኖራቸው እየተሰራ መሆኑም ተመላክቷል።

ተማሪዎች በስልክና በመሰል የቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይ የሚያሳልፉትን ጊዜ እንዲቀነሱና ትምህርት ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ወላጆች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ መነገሩን ኢዜአ ዘግቧል።


Forward from: የአል-ዓፊያ ት/ቤቶች ማህበረሰብ_Al-Afia Community
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ ተጀመረ ።

...................................................
የካቲት 7/2016 ዓ.ም (ትሚ) የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2016ዓ/ም የኢትዮጵያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና (12ኛ ክፍል) የተፈታኞች ምዝገባን በሚመለከት ለሚዲያ አካላት ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ የ2016ዓ/ም የኢትዮጵያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ተፈታኞች የመመዝገቢያ መስፈርቱን በማሟላት በተቀመጠው የጊዜ ገድብ መመዝገብ እንዳለባዉ አብራርተዋል፡፡

ም/ዋና ዳይሬክተሩ ምዝገባዉ የሚከናወነዉ በበይነመርብ /Online Registration / ሲሆን ከየካቲት 3 -30/2016 ዓ.ም ይሆናል ብለዋል።

በየደርጃዉ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ትኩርት ማድርግ ያለባቸውን ጉዳዮችም እንደሚከተለው አሳስበዋል።

1. በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መምዘገብ እንዳለባቸው ከየካቲት 3 -30 /2016 ዓ.ም ብቻ

2. ምንም አይነት ስህትት ማለትም የፆታ ߹የስም ስህተት߹የፎቶ ߹የትምህርት መስክ እና የመሳስሉት ችግሮች እንዳይፈጠሩ በትኩርት መስራት መቻል

3. ከየካቲት 30 /2016 ዓ.ም በኃላ የሚመጣ ምዝገባ ተቀባይነት እንደሌለዉ ማወቅ መቻል

4. የመደበኛና የማታ ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወንው በተማሩበት ት/ቤት እንደሚሆን

5. የግል ߹ የርቀት /የበይነ መርብ /ተፈታኞ ምዝገባ በክፍለ ከተማ ߹በወረዳና ትምህርት ፅ/ቤቶች እንደሚከናወን የየትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መረጃ ያመለክታል።


ለአል ዓፊያ ት/ቤት ተማሪዎች እና ወላጆች

12 ኛ ክፍል ዶክመንት ያላሟላችሁ ተማሪዎች እስከ ማክሰኞ የካቲት 5/2016 እንድታሟሉ ከወዲሁ እናሳውቃለን።

የሁለተኛው መንፈቅ ዓመት ትምህርት የካቲት 11/ 2016 ይጀመራል::




Forward from: የአል-ዓፊያ ት/ቤቶች ማህበረሰብ_Al-Afia Community
ለአል-አፈያ የ 6ኛ እና 8ኛ ክፍል ቤተል ቅንጫፍ ተማሪዎች በሙሉ

  የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የዘንድሮ የ 2016 የት/ዘመን የ 6ኛ እና የ 8ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተና የሚዘጋጃው በ6ኛ እና በ 8ኛ ክፍል ትምህርት ብቻ መሆኑን አሳውቆናል ስለዚህ ውድ ወላጀች ልጆቻችሁን ይህንን የዕረፍት ጊዜ በጥናት እንዲያሳልፉ አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ እንድታደርጉላቸው እንጠይቃለን።
ማስታወሻ:- የሚኒስትሪ ፈተና የ 5ኛ እና የ 7ኛ ክፍል ትምህርት አያካትትም::

=> ሚኒስትሪ የሚፈተኑዋቸው የትምህርት አይነቶች :-
6ኛ ክፍል
- አማርኛ
- እንግሊዝኛ
- ሂሳብ
- አካባቢ ሳይንስ
- ግብረ- ገብ
8ኛ ክፍል
- Amharic
-English
- Mathematics
- General science
- Social
- Citizenship


ለአል-አፈያ የ 6ኛ እና 8ኛ ክፍል ቤተል ቅንጫፍ ተማሪዎች በሙሉ

ነገ ማክሰኞ ጥር 28/2016 የት/ዘመን በሚኒስትሪ ፎርም ያልተሟሉ ነገሮች እንዲሁም የስም ፣ የእድሜ ፣ የስፔሊንግ እናም ሌሎች ችግሮች ካሉ ማስተካከያው የመጨረሻ ቀን ስለሆነ ጠዋት 2፡30 ት/ቤት ግቢ እንድትገኙ በጥብቅ እናሳስባለን።
ማስታወሻ:- በዕለቱ ተማሪው/ዋ ሳይመጣ/ ሳትመጣ ቀርቶ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች ቢያጋጥሙ ሀላፊነቱ የሚወስደው ተማሪው ነው።

20 last posts shown.