Forward from: ስለ እውነት
ክፍል 2
5. የልጆችዎን የትምህርት አቀባበል የሚመዝኑባቸው ቀላል ዘዴዎች ይኑርዎት
ወላጆች ልጆቻቸውን በትምህርታቸው ለመርዳት በየዕለቱ ምን ተምረው እንደመጡ መፈተሸና መከታተል እንዲሁም ቀለል ባለ ዘዴ የምዘና ጥያቄ አዘጋጅተው መመዘን ይችላሉ፡፡ በተወሰነ የጊዜ ርቀት ይህን ተግባር በማከናወን ልጆችዎን ከተማሩት ምን ይህል በሚገባ እንደተረዱት መገንዘብ ይቻላል፡፡ ይህ ግን ልጅዎን በሚያሳስብና በሚያስጨንቅ መልኩ መካሄድ የለበትም፡፡ ልጆችዎ እተዝናኑና እየተጫወቱ ሊሰሩ የሚችሉበትን ድባብ መፍጠር ይገባል፡፡ ልጆችን በዚህ መልኩ የተማሩትን በተለያየ ዘዴ እየገመገሙ ማነፅ በልጆቻችን ትምህርት በስፋት ተሳታፊ እንድንሆን፤ ልጆችንም የተማሩትን ትምህርት በጊዜ በሚገባ እንዲከልሱና በጥልቀት እንዲረዱ እንዲሁም በቀላሉ የተማሩትን አስታውሰው በምዘና መለኪያዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ እና በክፍል ውስጥም በንቃት እንዲሳተፉ ጭምር ያበረታታቸዋል፡፡
6. ልጆችዎን በትምህርታዊ ጉዞ ያዝናኑዋቸዋል
“ካሉበት ቦታ መቀየር ከድካም ዕረፍት የመውሰድ ያህል አስደሳች ነው” ይባላል፡፡ እንግዲያው እርስዎ ልጆችዎን ቀኑን ሙሉ ከሚውሉበት ት/ቤት እንዲሁም ከቤትዎ በተወሰነ ጊዜም ቢሆን በማላቀቅ ለምን በሽርሽር አያዝናኗቸውም? ከተለመደ ቦታ መቀየር ለሁሉም ቢሆን ያዝናናል፡፡ በተለይ ደግሞ ትምህርት በመማር ከፍተኛ ውጣ ውረድ በት/ቤትም ሆነ በቤት ለሚጋፈጡ ልጆችዎ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ እዚህ ጋር ግን አንዴ ቆም ብለን ማሰብ የሚገባን አለ እሱም ልጆቻችን በሽርሽር/በጉብኝት ለማዝናናት ከመነሳታችን በፊት የምናዝናናበት/የምናስጎበኝበት ቦታ ለልጆቻችን የአካልም ሆነ የአዕምሮ ጤና እንዲሁም የሥነ ልቦና ደህንነታቸው ብሎም ሞራልና ግብረ-ገብነታቸው ላይ ምንም አይነት ጉዳት የማያስከትል (ዋጋ የማያስከፍለን) ስለመሆኑ ቅድሚያ እርግጠኛ ልንሆን ይገባል፡፡ አለያ ግን አተርፍ ባይ . . . ነው የምንሆነው፡፡
7. ልጆችዎ የተሻለ ውጤት ሲያስመዘግቡ ዕውቅና ሰጥተው ያበረታቱ፤ ይሸልሙ
ልጆችዎን ለሚያስመዘግቧቸው የትምህርት ስኬቶች ዕውቅና ሰጥቶ ማበረታታትና መሸለም የተሻለ እንዲሰሩ በጣም ያግዛቸዋል፡፡ እርስዎ ታዲያ ልጆችዎ የላቀ ውጤት ይዘው ወደ ቤት ሲመጡ በማበረታታትና በሽልማት ሊቀበሏቸው ይገባል፡፡ ይህን ለማድረግ ግን የግድ ከፍተኛ የሆነ ወጪ ማውጣት አይጠበቅም፡፡ አቅም በፈቀደ ከወላጅ ለልጆች የሚደረግ ሽልማት ልጆች ደክመው ያመጡት ውጤት በወላጅ የላቀ ዋጋ እንደሚሰጠው መልዕክት ለማስተላለፍ መሆን ነው የሚገባው፡፡
8.ልጆችዎ እረፍት እንዲኖራቸው ያድርጉ! ለልጆችዎ ሰዓት ይኑርዎት!
ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን ከጥናት ዕረፍት መውሰድ ለልጆች ጠቃሚ ነው፡፡ ይህም ልጆችዎን በትምህርት ለማገዝ የሚረዳ ቀላል መንገድ ነው፡፡ በቤት ውስጥም ቢሆን አንዳንዴ ልጆች ከትምህርት ተለይተው (አቋርጠው) ሊዝናኑ የሚችሉበት ጊዜ ያመቻቹላቸው፡፡ እርስዎም ካለዎት ሰዓት ምርጡን ከልጅዎ ጋር በመሆን ያሳልፉ፡፡ ግን ግን ስንቶቻችን ነን ካለን ሰዓት ምርጡን ነገ እኛን ይተኩናል ብለን ብዙ ከምንደክምላቸው ውድ ልጆቻችን ጋር የምናሳልፈው? ምን ያህል እርስዎ ለልጆችዎ ቅርብ ነዎት? ለልጅዎት ምርጡን ሰዓት ሰጥተው ያገኟቸዋል ወይስ . . . ? እኛ ለልጆቻችን ቅርብ ልንሆን ይገባል፡፡ ይህን የማናደርግ ከሆነ ግን ልጆቻችንን እኛ ሳንሆን የሚያንፃቸው ሌላ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ ኢንተርኔት፣ ፌስቡክ፣ ቲቪ፣ እና የመሳሰሉት፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ነገ የምንመኘውን አይነት ትውልድ ማፍራት ባዶ ተስፋ ሆኖ ይቀራልና ለልጆቻችን ሰዓት መስጠታችን በሚገባ መፈተሽ ለነገ የማይባል ነው፡፡
9.ልጆችዎ በአግባቡ መመገባቸውንና በተገቢው ሰዓት ወደ መኝታቸው መሄዳቸውን ያረጋግጡ!
ት/ቤት እንደ ስያሜው እውቀት የሚቀሰምበት ቦታ ነው፡፡ ትምህርት ለመማር ደግሞ ተማሪ በአካልም ሆነ በአዕምሮ ዝግጁ መሆን አለበት፡፡ ይህ እንዲሆን ደግሞ የምግብ ስርዓትና የመኝታ ሰዓት የተስተካከለ ሊሆን ይገባል፡፡ እንደ ወላጅ ለልጆች አሸክመን ለምንልከው ምግብ ምን ያህል ተገቢውን ጥንቃቄ እናደርጋለን? አንዳንዴ ልጆች እንደማይመቻቸው እየታወቀ የሚታሰርላቸውን ምግብ እንዲጨርሱ በት/ቤት የሚፈጠረው ግብ ግብ ለጉድ ነው፡፡ ወላጆች የልጆቻቸውን ምግብ በዕርግጥ እየተመለከቱት ነውን? የሚል ጥያቄም ያስነሳል፡፡ በተመሳሳይ የልጆች የእንቅልፍ ሰዓትም ከፍተኛ ክትትል ያሻዋል፡፡ ልጆች መተኛት በሚገባቸው ሰዓት ስለመተኛታቸው እንደ ወላጅ ማረጋገጥ ይገባል፡፡ ልጆች ማረፍ በሚገባቸው የመኝታ ሰዓት ተገቢ ባልሆኑ ተግባራት የሚጠመዱ ከሆነ በአካልም ሆነ በአዕምሯቸው ላይ የሚፈጠረው ጫና በትምህርታቸው ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ ነው፡፡
ውድ ወላጅ እንግዲህ ልጆቻችንን በትምህርታቸው ሥኬታማ ማድረግ ከሚቻልባቸው ቀላል ዘዴዎች 9ኙን የጠቆምንበት መልዕክት በዚሁ ተጠናቋል፡፡
እንደ ወላጅ ከጽሑፉ ልጅዎን በትምህርቱ/ቷ ለመርዳት የሚያስችሉ ጠቃሚ ነጥቦች እንዳገኙ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ እባክዎ ልጆችዎን በትምህርታቸው ስኬታማ ይሆኑ ዘንድ ለመርዳት እንደወላጅ ሃላፊነትዎን በአግባቡ ይወጡ የዛሬው መልዕክታችን ነው፡፡ ሰላም!