Amhara Media Corporation


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን


Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter
የመስቀል በዓል በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ - ዳንሻ ከተማ እየተከበረ ነው።
ፎቶ፦ታርቆ ክንዴ


የመስቀል ደመራ በዓል በዋሽንግተን ዲሲ

የመስቀል ደመራ በዓል በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት በደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ተከብሯል።

በበዓሉ ላይ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለን ጨምሮ ሌሎች የክብር እንግዶች እና ምዕመናን ተገኝተዋል።
❝መስቀል የብሩህ ተስፋ፣ የብርሃንና የድል ምልክት ነው ፤ ደመራም የአንድነት እና የሕብረት ተምሳሌት ነው❞ ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)
https://www.amharaweb.com/❝መስቀል-የብሩህ-ተስፋ፣-የብርሃንና-የድ/
ባሕር ዳር: መስከረም 16/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ለመስቀል የደመራ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ርእሰ መሥተዳድሩ ያስተላለፉት መልዕክት ቀጥሎ ቀርቧል። እንኳን ለመስቀል የደመራ በዓል በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ! የመስቀል በዓል ለሀገራችን ሕዝቦች ባህላዊ እሴት በመሆን ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ነው። በዓሉ ከሃይማኖታዊ ተልዕኮው ባሻገር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ባህላዊ ቅርስና ውርስ ነው። መስቀል [...]


የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የአሸናፊነት መንፈስ ከተቀበረበት ወጥቷል፤ ከእንግዲህ እንደ ችቦ እያበራ ይቀጥላል እንጂ ማን ያቆመዋል!
https://www.amharaweb.com/የኢትዮጵያውያን-የአንድነትና-የአሸናፊነ/
የብሔራዊ መረጃና ደሕንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል ተመስገን ጥሩነህ ባሕር ዳር: መስከረም 16/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የብሔራዊ መረጃና ደሕንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል ተመስገን ጥሩነህ ለብርሃነ መስቀሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። የመስቀል በዓል፣ በክፉዎች ምኞትና ጥረት የሚያልቅና የሚያበቃ ነገር እንደሌለ የተማርንበት ነው። መስቀሉን ሰውረው የቀበሩት ሰዎች፣ የመስቀሉ ነገር በእነርሱ አሸናፊነት ያለቀ፣ የተጠናቀቀ መስሏቸው ነበር። ታሪክ ሠሪ ሰውና ታሪካዊ [...]


የመስቀል በዓል በሰላማዊ መንገድ እንዲከበር በቂ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ባሕር ዳር: መስከረም 16/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የመስቀል በዓል አከባበርን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል። በየግንባሩ የሀገርን ሰላም እያስከበረ እና ጠላትን እየመከተ ለሚገኘው የወገን ጦር ሕዝቡ ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ እንዳለበት ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል።

መግለጫውን የሰጡት የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር እንየው ዘውዴ ኮሚሽኑ ኅብረተሰቡን በማቀናጀት በየደረጃው ከሚገኙ የጸጥታ አካላት ጋር በመኾን የክልሉን ሰላም ለማስጠበቅ ሠፊ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።

ረዳት ኮሚሽነሩ እንዳሉት እንደቀድሞው ኹሉ በክልሉ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ኅብረተሰቡ ተገቢውን ሚና መጫወት አለበት።

ኅብረተሰቡ በዓሉን ምክንያት በማድረግ የእሳት አደጋ፣ የገበያ አካባቢ ስርቆትና ሐሰተኛ የብር ኖት ልውውጥ ክስተት ሊያጋጥም ስለሚችል በቂ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ነው ያስገነዘቡት።

ኅብረተሰቡ የስርቆትና የጸጥታ ችግር ሲያጋጥመው በየአካባቢው ለሚገኙ የጸጥታ አካላት ጥቆማ ማድረግ እንዳለበትም አሳስበዋል።

"ሰላምን ለማስከበር ኅብረተሰቡ ዋና ተዋናይ ነው" ያሉት ረዳት ኮሚሽነሩ በተለይ ወጣቶች ተጨባጭ ሥራን እያከናወኑ መኾኑን ጠቁመዋል።

በበዓሉ ወቅት ርችትም ኾነ ሕገወጥ የጥይት ተኩስ መፈጸም በሕግ የሚያስጠይቅ እንደኾነ አሳስበዋል።

ኮሚሽኑ በበዓሉ ወቅት ሊከሰት የሚችለውን የትራፊክ መጨናነቅ ለማስተካከል በቂ ባለሙያዎችን መመደቡንም ዋና ኀላፊው ገልጸዋል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በዓሉ የሰላምና የፍቅር እንዲኾን መልካም ምኞቱን ገልጿል።

ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ

ለሀገር ክብር በትግል እናብር‼


በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የዳንሻ ከተማ አሥተዳደር የሃይማኖት አባቶች እና ምዕመናን የመስቀል በዓል ማክበሪያ ሥፍራን በጋራ አጸዱ።

ሁመራ: መስከረም 16/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የደመራ ሥፍራውን የእስልምና ሃይማኖት፣ የክርስትና ሃይማኖት አባቶች እና የእምነቱ ተከታዮች ናቸው በጋራ ያፀዱት። ሃይማኖት የግል ሀገር የጋራ፣ አብሮነትም በአንድነት የሚያኖረን እሴታችን ነው ብለዋል።

የመስቀል በዓል የሚከበርበትን ሥፍራ እያፀዱ ያገኘናቸው የእስልምና ሃይማኖት አባት ሸህ አሕመድ አወል የክርስትና እና እስልምና ሃይማኖት ተከታዮች በዓላትን በጋራ እንደሚያከብሩ ነው የተናገሩት። በኢድ አል ፈጥር በዓል አብረውን እያፈጠሩ፣ ፆም ሲፈቱ አብረን ስንፈታ ነው የኖርነው ብለዋል። ሁለቱን ሃይማኖቶች ለፖለቲካ መጠቀሚያ ማድረግ አይቻልም፣ መለያየት የማይችሉ ለሀገር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉና እያደረጉ የሚቀጥሉ ሃይማኖቶች ናቸውም ብለዋል። በአንድነት ሀገራችን እናስከብራለን ነው ያሉት።

የሕወሓት የሽብር ቡድን በሃይማኖት እና ዘርን መሠረት አድርጎ ከፍተኛ በደል ሲያደርስ እንደቆየም አስታውሰዋል።

በእስልምና እና በክርስትና ሃይማኖት መካከል ክፍተት እንዲፈጠር ከፍተኛ የኾነ ሤራ ሲሠራ እንደነበርም ገልጸዋል። ሁለቱን ሃይማኖቶች መነጠል ግን እንዳልተቻለ ነው የተናገሩት።

የሁለቱም ሃይማኖት ምዕመናን የአደባባይ በዓላትን በነጻነት እንዳያከብሩ ሲያደርጋቸው እንደነበርም ተናግረዋል።

የሃይማኖት ልዩነት በመካከላችን ሳይኖር የሽብር ቡድኑን በጋራ እንታገላለንም ብለዋል።

ለመላው የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮችም የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። በዓሉ የጋራ በዓላችን ነውም ብለዋል።

መሪጌታ ነጋ ታደሰ የእስልምና እና የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች በአንድነት እንደሚኖሩ ተናግረዋል።

በሰላሙ በደስታው፣ በሃይማኖት በዓላትና በሌሎች ዝግጅቶች በአንድ ላይ እንደሚያከብሩ ገልጸዋል። በአንድነት ሀገራችንን እንጠብቃለንም ነው ያሉት።

ክፉ ነገር አልፎ ሁሉም ሕዝብ በአንድነት በዓሉን እንዲያከብር እንደሚመኙም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ሰላም ኾና የመስቀል በዓል ከዳር እስከ ዳር በደስታ እንዲከበር እንደሚፈልጉም ገልጸዋል። የክርስትና እና የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች አንድነት አሁን የተጀመረ ሳይኾን ከጥንት የነበረ ወደፊትም የሚኖር እንደኾነ ገልጸዋል።

በየሃይማኖታችን ፀሎት እያደረግን ሀገራችን ሰላም እና አሸናፊ እንድትኾን እንሠራለን ብለዋል።

የዳንሻ ከተማ ነዋሪው አቶ ካሳ ጥሩ በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የእስልምና እና የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች በስቃዩም በደስታውም ጊዜ አንድ ናቸው ብለዋል።

ኢትዮጵያ የሁሉም ናት፣ እኩል ሃይማኖት እኩል ሀገር አለችን ነው ያሉት።

አሸባሪው ሕወሓት ሁለቱን ሃይማኖቶች ለማጋጨት ብዙ ጥሮ ነበር ያሉት አቶ ካሳ አንድነታችን እጅግ የጠነከረ እና ሀገራችን በአንድነት የምንጠብቃት ናት ብለዋል። ቤተክርስቲያን ሥንሠራ ገንዘብ አዋጥተው ይሠራሉ፣ እኛም መስጂድ እንሠራለን ይህ ነው መገለጫችን ብለዋል።

ኢትዮጵያ የሁሉም ናት ያሉት አቶ ካሳ የከፋፍለህ ግዛ አካሄድ ለኢትዮጵያ ጠቃሚ እንደማይኾንም ገልጸዋል።

የዳንሻ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ሥልጣን አድማሴ ሁሉቱ ሃይማኖቶች የማይነጣጠሉ ሃይማኖቶች መኾናቸውን ተናግረዋል። "የእገሌ በዓል ነው የሚባል ነገር የለም፣ በአንድነት ያከብሩታል" ነው ያሉት። ማንም ቀስቃሽ ሳይኖራቸው ለማጽዳት መነሳታቸውንም ነው የገለጹት።

ኢትዮጵያን ለማዳን በሚደረገው ትግል የሁለቱም ሃይማኖት አባቶች እና ምዕመናን የማይተካ ሚና እየተወጡ መኾናቸውም ተናግረዋል።

ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ

ለሀገር ክብር በትግል እናብር‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J


በኩር ጋዜጣ – መስከረም 16/2015 ዓ.ም ዕትም
https://www.amharaweb.com/በኩር-ጋዜጣ-መስከረም-16-2015-ዓ-ም-ዕትም/
በኩር ጋዜጣ – መስከረም 16/2015 ዓ.ም ዕትም Download
የደብረማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ለወገን ጦር ለሁለተኛ ጊዜ የእርድ ሰንጋና ደረቅ ምግቦችን ድጋፍ አደረገ።

ሰቆጣ: መስከረም 15/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በድጋፉ ላይ የተገኙት የዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር የሎጀስቲክስ አስተባባሪ አለሙ ተዘራ "ሕዝባችን በማይነጥፈው ደግነቱ ለወገን ጦር ደጀንነቱን እያሳየ ነው" ብለዋል።

ለሁለተኛ ጊዜ በዋግኽምራ ግንባር ለወገን ጦር ድጋፉን ለላከው የደብረማርቆስ ሕዝብም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የደብረማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ሕዝብን ወክለው ለዋግኽምራ ግንባር የወገን ጦር ድጋፉን ያስረከቡት አቶ አስቻለው አዳነ ለሁለተኛ ጊዜ ለወገን ጦር የተበረከተው ድጋፍ 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ወጭ የተደረገበት ነው ብለዋል።

ድጋፉም 43 የእርድ እንስሳት፣ 187 ነጥብ 6 ኩንታል ሬሽን እንደኾነ ነው የተናገሩት።

ለወገን ጦር ያላቸውን ደጀንነትም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

በዋግኽምራ ግንባር ከወገን ጦር ድጋፉን የተረከቡት ሌቴናል ኮሎኔል ታጠቅ ንጉሴ እንደተናገሩት የሕዝቡ ደጀንነት ለሠራዊቱ ብርታቱ ነው ብለዋል።

የሕዝቡን የማይቋረጥ ደጀንነት ያገኘው ሠራዊት ከፍተኛ የሞራል ልዕልና ላይ ነው የሚገኘው ያሉት ሌቴናል ኮሎሌል ታጠቅ የወገን ጦር በሁሉም አቅጣጫ የተከፈተውን ጦርነት በብቃት እየመከተ መኾኑንም ነው የተናገሩት። "ሠራዊታችን ተልዕኮውን በአግባቡ እየተወጣ ነው" ብለዋል።

ሌቴናል ኮሎኔል ታጠቅ ሕዝቡ ለሚያደርገው አለኝታነት እና ደጀንነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ዘጋቢ:- ጋሻው አደመ

ለሀገር ክብር በትግል እናብር!!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

17 last posts shown.