"ጠላትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ለትውልድ የሚተላለፍ ታሪክ መሥራታችንን እንቀጥላለን።" ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በኢፌዴሪ አየር ኃይል የሰራዊት ቤተሰብ ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።
የሰራዊት አባላትና ቤተሰቦቻቸው በጋራ በመሆን የአየር ኃይልን የዝግጁነት አቅምና በተቋሙ ውስጥ እየተሠሩ የሚገኙ መሰረተ ልማቶችን ጎብኝተዋል።
በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የኢፌዲሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ እንደተናገሩት ወታደር የቤተሰብ ድጋፍ ሲኖር ይጀግናል፣ ለድልም ይበቃል፣ ለቀጣይ ግዳጅም መነሳሳትን ይፈጥራል።
አየር ኃይላችንም ላስመዘገበው ውጤታማ የግዳጅ አፈፃፀም ስኬት የእናንተ የቤተሰቦቻችን ድርሻ የላቀ በመሆኑ ልትኮሩም ፤ ልትመሰገኑም ይገባችኋል ብለዋል።
ዋና አዛዡ አክለውም እኛ የአየር ኃይል አባላቶች ጠላትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ለትውልድ የሚተላለፍ ታሪክ መስራታችንን እንቀጥላለን ብለዋል።
በቀጣይም የሰራዊቱንና የቤተሰቦቹን ኑሮ ለመደጎም በትኩረት እንደሚሠራ ዋና አዛዡ ገልጸዋል።
ከሰራዊት ቤተሰቦች መካከል አንዳንዶች በሰጡት አስተያየት የኢትዮጵያን ጠላቶች ድባቅ በመምታት ለሕዝባችን አኩሪ ድል እያበሰረ የሚገኘው አየር ኃይል የእኛ ቤተሰቦች የሚሠሩበት ተቋም በመሆኑ ደስተኞች ነን ብለዋል።
አየር ኃይልን መጎብኘት በመቻላችን ኩራት እንደተሰማቸው የገለፁት ቤተሠቦች ከሰራዊቱ ጎን በመቆም የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል። መረጃው የመከላከያ ሰራዊት ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/