"አሸባሪው ሕወሓት የኢትዮጵያ ጠላት ነው፤ የሽብር ቡድኑን ለመመከት ኢትዮጵያዊ ትብብርን ይጠይቃል" የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ምክትል አሥተዳዳሪ ሙሐመድ ሙሳ
ወልድያ: ነሐሴ 28/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው ሕወሓት በኢትዮጵያ ላይ ሦስተኛ ዙር ግልጽ ወረራ ከፈጸመ ቀናት ተቆጥረዋል። ኋላ ቀር የጦር ስልት የኾነውን ሕዝባዊ ማዕበል እንደ አንድ የጦርነት አማራጭ በመጠቀም ሕጻናትን ሳይቀር ወደ ጦርነት በመማገድ የዓለም አቀፍ ሕግን የጣሰው የሽብር ቡድኑ በወረራቸው አካባቢዎች ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት እየፈጸመ ነው።
አሸባሪው ሕወሓት የከፈተው ጦርነት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የጣሰ እና ኅልውናዋን አደጋ ላይ የጣለ ድርጊት ነው ያሉት የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ምክትል አስተዳዳሪ ሙሐመድ ሙሳ የኅልውና አደጋውን ለመቀልበስ የኹሉንም ኢትዮጵያዊ የጋራ ትብብር ይጠይቃል ብለዋል። በየአውደ ግንባሩ የሀገራቸውን ሉዓላዊነት ለማስከበር ለሚፋለሙት የጥምር ጦር አባላት ያልተቆጠበ ድጋፍ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ምክትል አሥተዳዳሪው አሳስበዋል።
ብሔረሰብ አሥተዳደሩ ለጥምር ጦሩ የሚያደርገውን ሙሉ የደጀንነት ድጋፉን በዘላቂነት ለማስቀጠል እየሠራ መኾኑንም ምክትል አሥተዳዳሪው ተናግረዋል።
"አሸባሪው ሕወሓት የኢትዮጵያ ጠላት ነው፤ ሕወሓትን ለመመከት ኢትዮጵያዊ ትብብርን ይጠይቃል" ያሉት አቶ ሙሐመድ በብሔረሰብ አሥተዳደሩ የሰላም ስጋት የኾነውን ሽብርተኛውን ሸኔ ከመመከት ባለፈ ሕወሓት ወረራ በፈጸመባቸው አካባቢዎች ላለው ጥምር ጦር የስንቅ ድጋፍ እየተደረገ መኾኑንም ገልጸዋል። ለመጀመሪያ ጊዜ ለጥምር ጦሩ ከብሔረሰብ አስተዳደሩ ወረዳዎች የተሰበሰበ ድጋፍ ለሰሜን ወሎ ዞን አስረክበዋል።
ለጥምር ጦሩ የሚያደርጉት የደጀንነት ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለጹት ደግሞ የከሚሴ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ከድጃ ሉሌ ተናግረዋል። ወጣቶች አካባቢያቸውን ተደራጅተው በመጠበቅ እና በደም ልገሳ ከሚያደርጉት ድጋፍ በተጨማሪ እናቶች የምግብ ዝግጅት እያደረጉ መኾናቸውንም ከንቲባዋ ገልጸዋል።
ጠላት ለሦስተኛ ዙር ለወረራ ሰፊ ዝግጅት አድርጎ መምጣቱን የገለጹት የሰሜን ወሎ ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ ጋሻው አስማሜ የሽብር ቡድኑን እንቅስቃሴ ባለበት መግታት ያስፈልጋል ነው ያሉት። በባለፈው ዓመት ወረራ አካባቢው በብዙ መንገድ ተጎድቷል ያሉት አቶ ጋሻው ያለፈው ጥፋት እንዳይደገም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጋራ እንዲቆም ጠይቀዋል።
ለጥምር ጦሩ የሚደረገው ድጋፍ በአንድ ዞን እና በአንድ ከተማ አሥተዳደር ስለማይሸፈን ሁሉም ኢትዮጵያዊ በቻለው ሁሉ ድጋፍ ሊያደርግ ይገባል ተብሏል።
በደቡብ ወሎ ዞን እና በኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር የተጀመረው ድጋፍ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ተገልጿል።
ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው -ከወልድያ
ለሀገር ክብር በትግል እናብር‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J