ውድ ባለአክሲዮኖቻችን
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ታህሳስ 23 ቀን 2017 ዓ.ም በቁጥር ኢካገባ/607/17 በፃፈው ደብዳቤ በካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013 መሰረት በሰነደ ሙዓለ ንዋይ አውጭዎች የተያዙ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ባለቤትነት መዝገቦች በማዕከላዊ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግምጃ ቤት በሚዘጋጅ ባለቤትነት በኤሌክትሮኒክ ዘዴ መተካት ያለበት በመሆኑ እና ሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን በማዕከላዊ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግምጃ ቤት ለመመዝገብ እንዲቻል የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ባለቤቶችን(የባለአክሲዮኖችን) መረጃ ዝግጁ እንድናደርግ ተጠይቀናል፡፡
በመሆኑም እስካሁን ድረስ መረጃዎችን ያላሟላችሁ ባለአክሲዮኖች
- የፋይዳ ተለዋጭ ቁጥርዎን (FAN ወይም FCN)፣
- የብሔራዊ መታወቂያዎን ኮፒ፣
- የመኖሪያ አድራሻ (የአድራሻ ለውጥ አድርገው ከሆነ አዲሱን አድራሻ)፣
- ኢ-ሜል እና ስልክ ቁጥር፣
- እንዲሁም ባለአክሲዮኑ ሕጋዊ ሰውነት ያለው ድርጅት ከሆነ የታክስ መለያ ቁጥር (TIN) እና የወኪሉ ሰው ሙሉ መረጃ የሚያስፈልግ መሆኑን አውቃችሁ በሁሉም የባንካችን ቅርንጫፎች እየቀረባችሁ ለዚህ ዓላማ የተዘጋጀውን ቅፅ እንድትሞሉ ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን ፡፡
አማራ ባንክ
ከባንክ ባሻገር!
የአማራ ባንክ ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች
Website |
Facebook |
Telegram |
Instagram |
Twitter |
LinkedIn |
YouTube |
TikTok#አማራባንክ #AmharaBank