Posts filter


የሰላም ጥሪን የተቀበሉ የታጠቁ አካላት ወደ ሕዝብ እና መንግሥት ተመለሱ።

አማራ ፖሊስ: ጥር 24/2017 ዓ.ም
በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ በሕዝብ እና በመንግሥት በተደጋጋሚ ይቀርብ የነበረውን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ የታጠቁ አካላት በሰላም መግባታቸውን የወረዳው አሥተዳደር አስታውቋል።

በደቡብ ወሎ ዞን በተሁለደሬ ወረዳ 027 ሙጢበልግ እየተባለ በሚጠራው ቀበሌ በተሳሳተ መንገድ ነፍጥ አንግበው የነበሩ አካላት ናቸው የሰላምን መንገድ መርጠው ወደ ሕዝብ እና መንግሥት የተመለሱት።

የታጠቁት አካላት ወደ አካባቢያቸው ሲደርሱ በተሁለደሬ ወረዳ የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የተሁለደሬ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ደመቁ አበበ፣ የመከላከያ ሠራዊት መሪዎች፣ ሌሎች የወረዳው የሥራ ኀላፊዎች፣ የጸጥታ መዋቅር መሪዎች፣ የአካባቢው የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት አቀባበል ስለመደረጉ ከደቡብ ወሎ ዞን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
#አሚኮ


"ማኅበረሰቡ ፍፁም የሰላም አየር አስኪተነፍስ ድረስ ሕግ የማስከበር ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል" የምዕራብ ጎጃም ዞን

አማራ ፖሊስ : ጥር 24/2017 ዓ.ም
የምዕራብ ጎጃም ዞን የሥድስት ወራት የሕግ ማስከበር የሥራ አፈፃፀም ግምገማ እያካሄደ ነው።

በግምገማ መድረኩ ላይ የተገኙት በምዕራብ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፓለቲካ ዘርፍ ኀላፊ ሙላት ጌታቸው በክልሉ ባጋጠመው የሰላም እጦት የክልል እና የፌዴራል የጸጥታ አካላት በከፈሉት መሰዋዕትነት አንፃራዊ ሰላም መገኘቱን ተናግረዋል።

ባለው የሰላም እጦት ማኅበረሰቡ ለከፍተኛ ችግር መጋለጡን አንስተው ማኅበረሰቡ ፍፁም የሰላም አየር አስኪተነፍስ ድረስ ሕግ የማስከበር ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው አቶ ሙላት የገለጹት።

የምዕራብ ጎጃም ዞን ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ሙሉጌታ ዓለም የጸጥታ ችግሩን ለመፍታት የጸጥታ ኀይሉን ማጠናከር ወሳኝ በመኾኑ ባለፉት ሥድስት ወራት የሰላም አስከባሪ እና የሚኒሻ ኀይል በማደራጀት በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ነው ያስገነዘቡት።

#አሚኮ


የአገው ፈረሰኞች በዓል በሰላም ተጠናቋል።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.facebook.com/share/p/1A71wzrLXX/


በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ክልላዊ የ2017 ዓ/ም 6 ወር የእቅድ አፈፃፀም ግምገማና የውይይት መድረክ ተካሄደ።

አማራ ፖሊስ፦ጥር 24/2017 ዓ.ም
ክልሉ ለወራት የሰላም መደፍረስ የነበር ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ ሰላም እየተረጋገጠ የመጣበት ሁኔታ አለ ተብሏል።

በመድረኩ የአማራ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ሀብታሙ ሲሳይ፣ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ም/ኮሚሸን ረዳት ኮሚሸነር እንየው ዘውዴ፣የኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር ም/ከንቲባ ወንድወሰን ልሳነወርቅ፣ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኮ/ር ሳይድ አሊ፣ የፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ኮ/ር ጌታቸው ሙህዬ፣ የሚኒሻ ጽ/ቤት እና የማረሚያ ቤት የስራ ኃላፊዎችና የማኔጅመንት አባላትም ተገኝተዋል ።

በዕቅድ አፈፃፀሙ ላይ በዋናነት በክልሉ ሰላም አለመኖርን ተከትሎ የነበሩ የሰውና የንብረት ውድመቶችን ተመላክቷል።

ለዚህም በሀገር መከላከያና የክልሉ የፀጥታ መዋቅሮች የጋራ ተጋድሎ በክልሉ የተንሰራራውን የጽንፈኛ ቡድን መበተን የተቻለ ሲሆን በቀጣይ ሰላም እንዲፈጠር የበለጠ ርብርብና የህብረተሰብ ድጋፍ ያሸዋል ተብሏል።

በክልሉ መንግስት በኩል ለፀጥታ ሀይሉ የሚያስፈልጉ ሁለንተናዊ ድጋፎች እንደሚደረግም ተገልጿል።

በጀግንነት መጠበቅ በሠባዊነት ማገልገል!


❝ብዝሃ ማንነት ባለበት ሀሳቦችና ልዩነቶች መኖራቸው አይቀሩም ልዩነቶች እና አለመግባባቶች በሰፊ አስተውሎት መፍታት የዘመኑ መጣኝ ገድል ነው።❞
አቶ ቴዎድሮስ እንዳለው የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ።

"አርበኝነታችን ለአሁናዊ ሰላማችን"በሚል መሪ ቃል 85ኛው የአገው ፈረሰኞች ቀን በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን በእንጅባራ ከተማ በድምቀት ተከብሯል።

በዕለቱ የተገኙት የብሄረሰብ አስተዳደሩ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቴዎድሮስ እንዳለው እንደገለፁት አገራችን የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች በጋራ የሚኖሩባት ብዝሃ ቋንቋ እና ብዝሃ ልዩነቶች መናገሻ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ የሚኖሩ የሀሳብ ልዩነቶች የግጭት መንስኤዎች ሊሆኑ አይገባም ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች አንዳችን ለአንዳችን በመደጋገፍ የቆምንባት ታሪካዊት ሀገር ባለቤቶች ነን የፅንፈኝነት እና ጎጠኝነት አስተሳሰብ ሊያጋጨንም ሆነ ሊያለያየን አይገባም።

ሰላም የዋጋ ተመን የማይበጅለት፣የሰው ልጅ መሰረታዊ ፍላጎቱን ተጠቅሞ ለመኖር ዋስትናና ማረጋገጫ ሰነድ ነው።የክልላችን ህዝብ የራሱን እኩይ ተግባር በሚያራምድ የአብራኩ ክፋይ የመከራ ዋጋ እየከፈለ ነው ብለዋል ዋና አስተዳዳሪው።

የእልህ ፖለቲካ ኪሳራው ዘርፈ ብዙ ነውና የህዝባችንን ምሬትና ሰላም ናፋቂነትን ልብ በማለት ወደ አሳደጋችሁ ማህበረሰብ በመቀላቀል የተረጋጋና በልማቱ ተጠቃሚ የሆነ ማህበረሰብ እንዲንፈጥር ለሰላማችን እንትጋ ሲሉ አቶ ቴዎድሮስ እንዳለው ጫካ ለገቡ ታጣቂዎች መልዕክት አስተላልፈዋል።


"ለሰላም መረጋገጥ እና ለማህበረሰብ ደህንነት የማይተጉ እጆች አይኖሩንም።"
ኮሚሽነር ደስየ ደጀን_ የአብክመ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር

አማራ ፖሊስ፦ጥር 23/2017 ዓ.ም
የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ባለፉት 6 ወራት በተከናወኑ የህግ ማስከበር እና ሰላም የማስፈን እንዲሁም በቀጣይ ሰላም በማስፈን ተግባር በሚደረጉ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ግምገማና ምክክር ያደረገ ሲሆን በዚህም የክልሉን ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደስየ ደጀንን ጨምሮ የክልልና የከተማ ፖሊስ አመራሮችና ሌሎች የፀጥታ ዘርፉ አስተባባሪዎች ተገኝተዋል።

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.facebook.com/share/p/19rMnHqojf/


ለሰላም ግንባታ የኅብረተሰቡ ሚና” በሚል መሪ ሃሳብ በደሴ ከተማ በክ/ከተማ ደረጃ የመንግሥት ሰራተኞች የሰላም ዉይይት ተካሄደ።

በደሴ ከተማ አስተዳደር በክ/ከተማ ደረጃ የሚገኙ የመንግሥት ሰራተኞች “ለሰላም ግንባታ የኅብረተሰቡ ሚና” በሚል ሃሳብ የሰላም ዉይይት አካሂደዋል።

ሰላምን ለማፅናት በተለይም የመንግሥት ሰራተኛዉ ማኅብረሰብ ስለ ሰላም ማወቅና የሰላም ግንባታን ባህል ማድረግ መቻል እንዳለበት የተገለፀ ሲሆን የሰላም ባህል በውጫዊ ብዝኃነት ላይ የተመሰረተ ሰብዓዊነትና የአዲስ ሥልጣኔ ፍሬ ተደርጐ ሊታይ የሚገባው ተግባር መሆኑ ተወስቷል።

ደሴ ከተማ የሰላም ተምሳሌትነቷን ለማስጠበቅ፣ ለኑሮ ምቹና ተስማሚ እንድትሆን በማድረግና ከሰላም ሥራዉ ጎን ለጎን መንግሥት ሰራተኛዉ በመደበኛ የሥራ ገበታዉ ላይ በመገኘትና የአገልጋይነት መንፈስን በመላበስ ለኅብረተሰቡ የተቀላጠፈና የላቀ አገልግሎት መሥጠት እንዳለበት ተመላክቷል።

ሰላም የህልውና ጉዳይና የሀገር ዕድገት መሰረት በመሆኑ የመንግሥት ሰራተኞች እውነተኛ ሰላም ወዳድነታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
መረጃ፦የደሴ ከተማ ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ነው።


በእስቴ ወረዳ ሕዝባዊ የሰላም ውይይት ተካሄደ።

በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ በዝጎራ፣ ደንጎልትና መካነ ኢየሱስ ቀበሌ ሕዝባዊ የሰላም ውይይት ተካሂዷል።

በሕዝባዊ ውይይቱ ስለ ሰላም፣ ልማትና መልካም አሥተዳደር በስፋት ተነስቷል። እየገጠመ ያለውን የሰላም ችግር ለመፍታት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።

የእስቴ ወረዳ አሥተዳዳሪ ማንተፋርዶ ሞላ ሰላምን ማምጣት የሚችለው ራሱ ሕዝቡ ነው ብለዋል። ከደቡብ ጎንደር ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ለሰላም ሁላችንም የየድርሻችን እንወጣ ነው ያሉት። ሰላምን እንስበክ ለሰላምም እንሥራ ብለዋል ዋና አሥተዳደሪው በመልዕክታቸው።


የጸጥታ ተቋማት የውይይት መድረክ በደብረ ብርሃን ከተማ እየተካሄደ ነው።

የሰሜን ሸዋ ዞን እና የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር የጸጥታ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች ላይ ትኩረቱን ያደረገ መድረክ በደብረ ብርሃን ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ላይ የተገኙት በቢሮ ኀላፊ ደረጃ የአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ አማካሪ ኮሎኔል ባምላኩ ዓባይ የጸጥታ ኃይሉ የክልሉን ሰላም ለማስፈን በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን እና አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል። ችግሮችን በሰላም ለመፍታት መንግሥት ቁርጠኛ መኾኑንም ተናግረዋል።

ባለፉት የተግባር ሥራዎች ላይ የነበሩ ጥንካሬዎችን እና ክፍተቶችን የመለየት አና የማስተካከል ተግባር ይከወናል ነው ያሉት።

በመድረኩ የሰሜን ሸዋ ዞን ሁሉም የወረዳ፣ የከተማ አሥተዳደሮች እና ከደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ የጸጥታ መዋቅር ኀላፊዎች እና ባለሙያዎች እየተሳተፍ ነው።



10 last posts shown.