💥ታላቅ የምሥራች💥 በመቅደላ ጦርነት በእንግሊዞች ከተወሰዱት ውስጥ "የመቅደላ ጋሻ" (The Shield of Magdala) በመባል የሚታወቀው የንጉሠ ነገሥት የዐጼ ቴዎድሮስ ጋሻ ወደ ሀገሩ ኢትዮጵያ ዐርብ ጥቅምት 22/ 2017 ዓ.ም. ይገባል።
👉 ይኽ ታላቅ ታሪካዊ ቅርስ እንግሊዝ ባለው "አንደርሰን ኤንድ ጋርላንድ" በኩል ጨረታ ላይ ቢወጣው በዐጼ ኃይለ ሥላሴ የልጅ ልጅ በልዑል ኤርምያስ ሣሕለ ሥላሴ ኃይለ ሥላሴ በኩል በተቋቋመው የሮያል ትረስት ተቋም በከፍተኛ ውይይት ወደ ኢትዮጵያ ሊመለስ መኾኑን ዓለም ዐቀፍ ሚዲያዎች እየዘገቡት ነበረ።
👉 ጥረቱ በመሳካቱ የመቅደላ ጋሻ አሁን በሰሜን አሜሪካ በኦሀዮ ቶሌዶ የኪነ ጥበብ መዘክር እጅግ በርካት የውጪ ሀገር ተመራማሪዎች፣ የክብር እንግዶች በተገኙበት ቅዳሜ ጥቅምት 16 በሰሜን አሜሪካ በኦሀዮ ቶሌዶ የኪነ ጥበብ ቤተ መዘክር ከፍተኛ የአቀባበል ሥርዓት ተደርጓል። በዕለቱም በዶክተር አሉላ ፓንክረስት ከመቅደላ በተወሰዱት የኢትዮጵያ ቅርሶች ዙሪያ ጥናታዊ ጽሑፍ የቀረበ ሲኾን እኔም በቦታው በክብር እንግድነት በመገኘት ጋሻው ወደ እናት ሀገሩ ኢትዮጵያ ዐርብ ጥቅምት 22 ከመግባቱ በፊት ለመጎብኘት ችያለኹ። 👉 በዚኹ አጋጣሚ የዐጼ ኃይለ ሥላሴ የልጅ ልጅ ቃለ መጠይቅ ያደረኩ ሲኾን በመቅደላ ጦርነት በ15 ዝኆኖች በ200 በቅሎዎች ከኢትዮጵያ የወጡት ውድ ቅርሶችና የብራና መጻሕፍት ወደ እናት ሀገራቸው እንዲመለሱ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እንደሚያደርጉ ገልጠዋል ሊንኩን https://youtu.be/oSZrLtDqwlw?si=yKDltLnhJbupPJ3w
👉 የአቀባበል ሥርዓት የተደረገበት በቶሌዶ የኪነ ጥበብ ቤተ መዘክር ውስጥ እጅግ ብዙ ቅርሶች የሚጎበኙ ሲሆን በርካታ ጥንታውያት ብራና መጻሕፍት፣ መስቀሎች፣ ቅዱሳት ሥዕላት የሚገኙ ሲኾን ሰፊ ጉብኝት ለ2 ቀናት ለማድረግ ችያለኹ።
👉 የመቅደላ ታሪክን ለማስታወስ ያኽል ዐጤ ቴዎድሮስ ወደ ሺሕ የሚጠጉ በልዩ ልዩ ጌጥ ያጌጡ፤ በልዩ ልዩ ሐረግ የተንቈጠቈጡ የብራና መጻሕፍትን ከመላው ኢትዮጵያ ካሉ ገዳማትና አድባራት አሰብስበው በመቅደላ መድኀኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን አኑረውት ነበር፡፡
👉 የእንግሊዝ ጦር በጄኔራል ናፒየር እየተመራ ድል ካደረገ በኋላ ስለተወሰዱት ቅርሶች ጆሴፍ ፍራንሲስ “Tewodros Prince of Ethiopia” በሚለው ጽሑፉና ተክለ ጻድቅ መኩሪያ በኢትዮጵያ ታሪክ መጽሐፋቸው እንደገለጡት፡-
✍️ “በንጉሣዊ ቤተ መጻሕፍት የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ የሀገሪቱ ጥንታዊ ድርሳናትና የብራና መጻሕፍት፤ ዐሥር አስደናቂ ታቦታት፣ መንበሮች፣ ንዋያተ ቅድሳት፣ ሥዕላት፣ የተለያዩ ውብና ድንቅ የወርቅ ጌጣጌጦች፤ የወርቅ፣ የብር፣ የነሐስ መስቀሎች፣ ለክብረ በዓላት ብቻ የሚወጡ አስደናቂ ቅርጽ ያላቸው መስቀሎች፣ የአቡኑ አክሊልና ታላቅ ማኅተም ተወሰዱ። የተወሰዱት ንብረቶች ቅርሶች በ15 ዝኆኖችና በ200 በቅሎዎች ጭነው ወሰዱ። የማይፈልጉትን ድርሳናትና ቅርሶችን እንዲጠፉ በአምባው በየአግጣጫው ወረወሩት፤ እነዚኽም በ፭ ኪሎ ሜትር ርቀት ሙሉ ተጥለው ይገኙ ነበር፤ የተወሰደው ቅርስ ከብዛቱ የተነሣ ለኹለት ቀናት ለፈጀ ጨረታ አቅርበውት ነበር፤ የእቃው ክምችት ግማሽ ኤከር (4,047 ካሬ ሜትር) ስፋት ያለውን መሬት ሸፍኖት ነበረ።
ዘመቻውን ተከትሎ የመጣው የእንግሊዝ ሙዚየም ባልደረባ የኾነው ሆልምስ ታላቁ ተጫራች ነበር፤ የተወሰዱ ቅርሶች በጊዜው በእንግሊዝ ገንዘብ ሠላሳ ሰባት ሚሊየን ፓውንድ ነበር ወይም አንድ ቢሊየን ብር ይገመታሉ” ይላል ፡፡
👉 ዐምስት መቶውንን ድንቅ የኢትዮጵያውያን የብራና መጻሕፍትን እንግሊዝ ባሉት ቤተ መጻሕፍት ተከፋፍለው እንዲቀመጡ ሲደረጉ፤ የመጻሕፍቱን ዝርዝር እንግሊዛዊዉ ዊሊያም እና ጀርመናዊዉ ዲልማን ጽፈዋቸዋል፡፡ ከአራት ዓመት በኋላ ዐጤ ዮሐንስ ከመቅደላ የተዘረፉትን ቅርሶች ይልቁኑ የጌታችን ኲርዐተ ርዕሱ (ራሱ በዘንግ ሲመታ) የሚያሳየውን እጅግ የሚያስደንቅ ኢትዮጵያዊ ሥዕል እንዲመለስ የእንግሊዟን ንግሥት ቪክቶሪያን ቢጠይቁም እንግሊዞች ግን እንደማይመልሱ በመናገር ከመቅደላ ከወሰዷቸው ዐምስት መቶ የብራና መጻሕፍት ውስጥ መርጠው አንዱን “ክብረ ነገሥትን” ብቻ መልሰውልናል፡፡
👉 ዐጼ ቴዎድሮስ ከእንግሊዞች ጋር ባደረጉት ጦርነት ዐጼ ራሳቸውን በማጥፋታቸው የተበሳጩት አንግሊዞች የንጉሠ ነገሥቱን ሹሩባ (ቁንዳላ) ቆርጠው ከመቅደላ ወስደው በእንግሊዝ አርሚ ሙዚየም ውስጥ ከ 154 ዓመታት በላይ ከቆየ በኋላ የኢትዮጵያውያን ቅርስ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ በመጋቢት 2011 ዓ.ም ወደ ከብሪታኒያ ወደ ኢትዮጵያ መመለሱ ይታወሳል። ጥቀምት 22 ዐርብ ደግሞ ጋሻቸው ይገባልና
"ታጠቅ ብሎ ፈረስ ካሳ ብሎ ስም
ዐርብ ዐርብ ይሸበራል ኢየሩሳሌም"
ተብሎ በተገጠመላቸው ግጥም በማብቃት በሰሜን አሜሪካ በተገኙ ታላላቅ እንግዶች የነበረው ታላቅ የክብር አቀባበል ድንቅ ነበርና ወደ እናት ሀገሩ በዶክተር አሉላ ፓንክረስት ጥቅምት 22 ሲመለስ ደረጃውን የመጠነ ሀገራዊ አቀባበል ለንጉሠ ነገሥቱ ጋሻ እንደሚደረግ አምናለኹ።
መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
#RoyalEthiopiantrust